Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 15 October 2011 13:02

የአዲስ አበባ ዋንጫ በተመልካች ተሟሙቋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

7 ክለቦች እየተሳተፉበት የሚገኘው የአዲስ አበባ ዋንጫ በተመልካች ብዛት የተሟሟቀ ቢመስልም የቡድኖች አቋም ብዙም እንዳላረካቸው ስፖርት አፍቃሪዎች ገለፁ፡፡ ውድድሩ ዕረቡ እለት ሲጀመር ከምድብ አንድ በመክፈቻው ጨዋታ መብራት ሃይል 3ለ1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ደደቢት ኢትዮያ ቡናን 2ለ1 ረትቶታል፡፡ ሃሙስ እለት መከላከያና ከመድን ተጫውተው ሁለት እኩል ተለያይተዋል ፡፡

የአዲስ አበባ ዋንጫው ዛሬ ሲቀጥል በ8 ሰዓት ደደቢት ከመብራት፣ በ10 ሰዓት ቡና ከባንክ ይጋጠማሉ ጊዮርጊስና መከላከያ ደግሞ ነገ በ10 ሰዓት ይገናኛሉ፡፡ የፊታችን ሰኞ በ9 ሰዓት መብራት ከቡና ፣ ባንክ ከደደቢት ጋር ተገናኝተው የምድብ 1 ጨዋታ ሲጠናቀቅ ማክሰኞ እለት ደግሞ በምድብ 2 መድን ከጊዮርጊስ ጋር ተገናኝተው የምድብ ትንቅንቁ ያበቃል፡፡ በምድብ 1 ባንክ፣ ቡና፣ መብራት፣ደደቢት ሲደለደሉ ጊዮርጊስ፣ መከላካያና መድን በምድብ 2 ይገኛሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዋንጫ ስፖንሰሮች 600ሺ የደገፉ ሲሆን ለሻምፒዮኑ 30 ሺ ብር፤ ለ2ኛ 20ሺ እንዲሁም ለ3ኛ ደረጃ 10ሺ ብር የሚበረከት ይሆናል፡፡ 
ግማሽ ፍፃሜው ሐሙስ ሲቀጥል በ9 ሰዓት የምድብ ሀ 1ኛ ከምድብ ለ 2ተኛ እንዲሁም በ11 ሰዓት የምድብ ሀ 2ተኛ ከምድብ ለ1ኛ ጋር ተገናኝተው ለዋንጫ ያለፉት ክለቦች የሚታወቁ ይሆናል፡፡


 

Read 2900 times Last modified on Saturday, 15 October 2011 13:04