Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 15 October 2011 11:37

ለብልሹ አስተዳደር መፍትሄው ዲሞክራሲያዊ ተቋማትን መርጨት ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጆሮዬ ላይ ኢርፎን ሰክቻለሁ ከሞባይሌ በኤፍ ኤም ሬዲዮ የሚሰራጨውን ዜና ለማዳመጥ፡፡ በከፊል ጆሮዬ ግን የተሳፋሪዎችን ወሬ፣ ሃሜት፣ ምሬት፣ ማዳመጤ አልቀረም፡፡ ይቅርታ ያለሁበትን አልነገርኳችሁም፡፡ ሚኒባስ ውስጥ ነኝ፡፡ አንዳንዴ ግን ምን አስባለሁ መሰላችሁ? ወሬ በሚዲያ ከማዳመጥ ይልቅ ሲያጋጥም እንዲህ Live (በቀጥታ) ሥርጭት መከታተል ይሻላል - ከመንገደኛ፣ ከተሳፋሪ፣ ከዘይትና ስኳር ወረፋ ጠባቂ፣ ወደ አረብ አገር ለመሄድ ሰልፍ ከያዙ እንስቶች፣ ኢህአዴግን ለመደገፍ ከወጡ ሰልፈኞች ወዘተ . . .

ለነገሩ የታክሲው ተሳፋሪዎች ያነሱት ርዕሰ ጉዳዩ እኔንም ይመለከተኛል፡፡ ሰዎቹ የሚያወሩት ወይም የሚያማርሩት ስለ ትራንስፖርት ችግር ነው፡፡ በፊት በፊት የትራንስፖርት ችግር ሲነሳ ቀድመው የሚነሱት የታክሲ ሹፌሮችና ረዳቶች (ወያላዎች) ነበሩ፡፡ አሁን ግን መንግስት ነው፡፡ (በገዛ እጁ ነው ልበል?) 
አንደኛው በደንብ የዘነጠ ጐልማሳ ተሳፋሪ በምሁራዊ የንግግር ቃና፣ መንግስት ያወጣውን የታክሲዎች የስምሪት አሰራር ያብጠለጥላል (ዲሞክራሲ ደስ ሲል አልኩኝ - በልቤ) ችግሩ ግን ምሁራዊ ትችቱና ማብጠልጠሉ ውጤት ተኮር አይደለም፡፡ እኔና እኔን መሰሎች ቢሰሙት ምን ፋይዳ አለው? እንደው ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ ህገመንግስታዊ መብትን ለመተግበር ይጠቅም ይሆናል እንጂ ሌላ የረባ ውጤት እንደማያመጣ እርግጥ ነው፡፡ ለነገሩ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ቅሬታውን ቢነግር ምን እንደሚሉት አሳምሮ ያውቃል፡፡ ድብቅ አጀንዳ አራማጅ ተብሎ ይፈረጃል፡፡ ስለዚህ ታክሲ ላይ ሃሳቡን በነፃነት ቢያንሸራሽር ይቀለዋል፡፡ እናም እስኪበቃው አንሸራሸረ… መንግስት የታክሲዎች ስምሪት ውስጥ እጁን ማስገባት እንዳልነበረበት፣ የነፃ ገበያን አሰራር እየተፃረረ ስለመሆኑ፣ መመሪያዎች በቂ ጥናት ሳይደረግባቸው በይድረስ በይድረስ ተግባራዊ መደረጋቸውን፣ ወዘተ ሰውየው እስኪበቃው ደሰኮረ - በአካባቢው ማን አለ የሚል ስጋት ሳያድርበት (ነፃነት ደስ ሲል አልኩኝ በሆዴ) በአድማጭነት የቆየች ሌላ ተሳፋሪ ፈቃድ መጠየቅ ሳያስፈልጋት የሚኒባሱን መድረክ በፈቃዷ ተረከበች፡፡ የመናገር ረሃብ ያንሰፈሰፋት ትመስላለች፡፡ እየተንቀጠቀጠች ነው የምትናገረው፡፡
ሴትየዋ እንደ ካድሬ ከመንጣጣቷ በቀር የምትናገረው እንኳ ደርዝ ያለው ነገር ነበር፡፡ የትራንስፖርት ችግሩን ለማቃለል በአዲስ አበባ እንዲሰሩ ተደርገው የነበሩ የኦሮምያ ታርጋ የለጠፉ 3ሺ ሚኒባሶች ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ መደረጉ ልክ አይደለም ባይ ናት - ተሳፋሪዋ፡፡ እነሱም እያሉ እንኳ በሥራ ሰዓት መግቢያና መውጭያ የሚፈጠረውን የትራንስፖርት እጥረትና የተሳፋሪዎች ትንቅንቅ በማንሳት ከዚህ በኋላ ነገሩ እንደሚባባስ በርግጠኝነት ተነበየች፡፡ ለነገሩ ይሄን ለማወቅ ልዩ የትንበያ ችሎታ አያስፈልገውም፡፡ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 3ሺ ሚኒባሶች ሲቀነሱ ትልቅ ክፍተት እንደሚፈጠር ዝም ብሎ ሳያስቡ እንኳን መገመት ይቻላል፡፡ እኔ ይሄንን ዜና አንድ ጋዜጣ ላይ ነው ያነበብኩት - ሰሞኑን፡፡ የቅድሙ በምሁራዊ ቃና የሚናገር ጐልማሳ ያለው ነገር ትዝ አለኝ - በቂ ጥናት ሳይደረግበት የተተገበረ ያለውን ማለቴ ነው፡፡ በእርግጥ እዚህ ኢትዮጵያችን ውስጥ አብዛኞቹ ነገሮች ተግባራዊ የሚደረጉት ያለ በቂ ጥናት ስለሆነ ብዙም ላያስገርም ይችላል፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን የትራንስፖርት ችግሩን ለመቅረፍ 3ሺ የኦሮምያ ታርጋ የለጠፉ ሚኒባሶች አዲስ አበባ ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚል መመሪያ ወጣ፤ ከጥቂት ወራት ትግበራ በኋላ መመሪያው ተቀይሮ ወደ ቀድሞ ምድባችሁ ተመለሱ ተባለ፡፡ ይሄ ምን ይገርማል? ለእኛስ አዲስ ነገር ነው? በፍፁም ስንት መመሪያና ደንብ በስንት አጀብና ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ከወጣና ህይወታችንን ለመመሪያው ለማስገዛት ደፋ ቀና ስንል ከቆየን በኋላ እንደቀልድ “ያ መመሪያ እኮ ፎረሸ” አልተባልንም፡፡ በተደጋጋሚ ተብለናል እንጂ - እስኪታክተን፡፡
የ3ሺ ሚኒባሶቹን ነገር ትንሽ ለየት የሚያደርገው ምን መሰላችሁ? የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ይሄንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እኛን ሊቆጣ መዳዳቱ ነው፡፡ እንዴ በራሱ ጥፋት! የኦሮምያ ሚኒባሶቹ አዲስ አበባ ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ የትራንስፖርት ችግሩን ለመቅረፍ ሲያስብና ሲወስን እኛን (ነዋሪዎቹን) ያማከረ አይመስለኝም፡፡ (“ሚስትህ አረገዘች ወይ ቢሉት ማንን ወንድ ብላ” የሚለው ተረት ለምን ትዝ እንዳለኝ አላውቅም) እሺ እኛን የማማከር ግዴታ የለበትም እንበል፡፡ ስለዚህ ያሰበውንና የወሰነውን በፈቃዱ አደረገ፡፡ አሁን ደግሞ በኦሮምያ ክልል የትራንስፖርት እጥረት ተከስቷል የሚል ቅሬታ ደረሰውና የቀድሞ መመሪያውን አጠፈ፡እዚህ ድረስ በእኔ በኩል ባለስልጣን መ/ቤቱ ምንም አላጠፋም፡፡ ጥፋት ሳይፈጽም ቀርቶ ግን አይደለም፡፡ ሌላው የመንግስት መ/ቤት የአሰራር ባህሉ አድርጐ የተካነበትን ያለበቂ ጥናት አዳዲስ መመሪያና ደንብ ማዥጐድጐድ፣ ይሄን መ/ቤት ለብቻው ነጥሎ መውቀስ ትክክል አይደለም ብዬ ስለማምን ነው፡፡ (የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን የእንጀራ ልጅ ነው እንዴ?) ሆኖም ግን ባለስልጣኑ መመሪያው መታጠፉን ሲገልጽ እግረመንገዱን የተናገረው ለትችት የሚያበቃው ነው፡፡ የኦሮምያ ታርጋ የለጠፉ ሚኒባሶች ወደ ቀድሞ ምድባቸው መመለሳቸውን በተመለከተ የተወሰነውን ውሳኔ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ “እናንተ ተቸግራችሁ ለኛ ብቻ ስጡን ማለት አይቻልም” ብሏል - በቁጣ ቅላፄ፡፡ (“ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል” የሚለው ተረት ትዝ አለኝ) እንዴ ማንን ነው የሚገስፀው? እኛን ተጠቃሚዎቹን ከሆነ መቼም አብዷል ማለት ነው፡፡ መቼም እኛ ሚኒባሶቹ እንዲመጡ ጥያቄ አላቀረብንም፡፡ ራሱ አመጣ ራሱ መለሰ፡፡ እና ታዲያ “እናንተ ተቸግራችሁ ለኛ ብቻ ስጡን ማለት አይቻልም” ያለው ማንን ነው? ለማንኛውም አስገራሚ የዓመቱ መግለጫ ብለን እንለፈው፡፡ አሁን ታክሲው ውስጥ የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ - እና ሹፌሩና ረዳቱ፡፡ ከጆሮዬ ላይ የነቀልኩትን ኢርፎን መልሼ ጆሮዬ ላይ ሰካሁት፡፡
በህዝብ ተቃውሞ ከሥልጣን የተወገዱትን “ፍሪኩን” የሊቢያ የቀድሞ መሪ ሙአመር ጋዳፊን የተመለከተ ትንተና እየሰጠ ነበር - ጋዜጠኛው፡፡ ደስ ያለኝ ደግሞ ጋዜጠኛው ሊቢያን እንደ ሰፈሩ፣ ጋዳፊን እንደሰፈር ልጅ ባለ ዓይነት ቅርበት እየጠቀሰ ማውራቱ ነው፡፡ አብዛኞቹ የሬዲዮ ጋዜጠኞች እንዲህ ያለ ድፍረት አላቸው ልበል? ሌላ ጋዜጠኛ ስለ ኦባማ ሲተነትን “አንድ ት/ቤት አንድ መቀመጫ ላይ ለሁለት ተቀምጠን ነው የተማርነው” ማለት ነው የቀረው ሲል አንድ ወዳጄ እንደነገረኝ ትዝ አለኝ፡፡ የጋዜጠኛው አቀራረብ ትኩረት የሚስብ ቢሆንም እኔ ግን በራሴ ሃሳብ ነጐጄአለሁ፡፡
ጋዳፊ ባለፉት የአራት አስርት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው ለአገራቸውና ይወደኛል ለሚሉት ህዝባቸው አንዳችም የረባ ነገር አልሰሩለትም፡፡ እናም አንድ ቀን ከስልጣን በሃይል ያስወግዱኝ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ሳያድርባቸው አልቀረም...ጥርጣሬያቸው ከቀን ወደቀን ግዘፍ እየነሳ ሲመጣባቸው የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ ጀመሩ፡፡
ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካና፣ ከአረብ አገራት በዘመናዊ ከተማ ዲዛይንና እነፃ የተካኑና የተራቀቁ ባለሙያዎችን አስመጡና አማከሩአቸው - ከፓላሳቸው ሥር አዲስ ዘመናዊ ከተማ እንዲቆረቁሩላቸው፡፡ ዕድሜ ለቴክኖሎጂ! የማይቻል ነገር የለም አሏቸው - ባለሙያዎቹ፡፡ “ግን ለእጃችን ብዙ እናስከፍላለን” አሉ የውጭ አገር ባለሙያዎቹ፤ ራሳቸውን ለማዋደድ፡፡
“ጋዳፊ እኮ ነኝ፤ ዝም ብላችሁ ጀምሩ” ተባሉ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ አዲሱ ከተማ ተመሰረተ - ከትሪፖሊ ቤተመንግስት ሥር ማለት ነው፡፡ ስሙንም ጋዳፊ ብለው ሰየሙት - ራሳቸው የሊቢያው የቀድሞ መሪ ሙአመር ጋዳፊ፡፡ ከዚያስ? ከሊቢያ የነዳጅ ጉድጓዶች እየተቀዳ በአዲሱ ከተማ በተቆፈሩ ማጠራቀሚያዎች ይሞላ ብለው አዘዙ፡፡ እንደ ትዕዛዛቸውም ተደረገ፡፡ ለከተማው የጦር ሃይላት አባላት ተመለመለለለት፡፡ ፖሊስና የደህንነት አባላትም ተመደበለት፡፡ አሁን የቀረው ህዝብ ነው፡፡ ጋዳፊ ህዝብም ወደ አዲሱ ከተማ እንዲሰፍር አደረጉ፡፡
ይሄ ሁሉ የሆነው ከ20 ዓመት በፊት ስለነበር ጋዳፊ በራሳቸው ስም የሰየሙትን ከቤተመንግስታቸው ስር የተመሰረተ ከተማ ከነመኖሩም ዘንግተውት ነበር፡፡ መቼ ትዝ አላቸው . . . አትሉኝም? አሁን በቅርቡ . . . የህዝብ አመፁ አይሎ ከትሪፖሊ ቤተመንግስት መውጣታቸው አይቀሬ መሆኑን ሲገነዘቡ ያቺ ጋዳፊ ብለው የሰየሟት ከተማ ትዝ አለቻቸው፡፡ ድምፃቸውን አጥፍተው ለክፉ ጊዜ ብለው ወደቆረቆሯት ከተማ ላፍ አሉ፡፡ ከዚያስ? ከዚያማ የጋዳፊ ከተማ ፕሬዚዳንት ሆነው በተዘጋጀላቸው አዲስ ቤተመንግስት ውስጥ ገቡ፡፡ ከስልጣን ከወረደ በኋላ ድምፁን አጥፍቶ ለበርካታ ጊዜያት ከዓለም ዓይንና ጆሮ በመሰወር የሊቢያው የቀድሞ መሪ ሙአመር ጋዳፊን የሚስተካከል ያለ አይመስለኝም፡፡ የሁለት አገራት መሪ በመሆንም ጋዳፊ አዲስ ሪከርድ አስመዝግበዋል፡፡ ሌላስ? ከምድር በታች የተመሰረተ ከተማና ህዝብም መሪ በመሆን ሌላ ሪከርድ… ቅዠት ከመሰለ ሃሳቤ ያነቃኝ ወይም ያባነነኝ ከጐኔ የቀመጠው አዲስ ተሳፋሪ ሲያስነጥስ ነው፡፡ እግዜር ይስጠው አዲሱ ተሳፋሪ ከሊቢያ ትሪፖሊ ወደ ገዛ አገሬ መለሰኝ፡፡ እናም የበፊቱ ተሳፋሪዎች ሲንጫጩበት የነበረው የትራንስፖርት ችግር ትዝ አለኝ፡፡ በታክሲዎች የቀጣና ስምሪት የተፈጠሩ ችግሮችና ቅሬታዎችንም አስታወስኩ፡፡ ወዲያው ለአንዳንድ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሹ ችግሮቻችን አፋጣኝ የመፍትሄ ፕሮፖዛል ለማርቀቅ ሃሳብ ማውጠንጠን ያዝኩኝ፡፡ ለምሳሌ 3ሺ የኦሮምያ ሚኒባሶች ከመዲናዋ ሲወጡ ለሚከሰተው የትራንስፖርት ችግር መንግስት ለምን አዳዲሶቹን ቢሾፍቱ ባሶች በሰፊው አይረጭም? (በነገራችን ላይ እቺን መርጨት የምትል ሃሳብ “ስንዴ መርጨት” ከሚለው የጠ/ሚኒስትሩ አባባል የተወሰደች መሆኑ ይታወቅልኝ) እናም መንግስት ሳይሳሳ ቢሾፍቱ ባሶችን ይርጭልን ይላል ፕሮፖዛሉ፡፡ ዳቦ ቤቶች ግራም አሳንሰዋል በሚል የመዝጋት እርምጃ እየተወሰደ ነው አይደል . . . ይሄ ስህተት ነው፡፡ የዳቦ እጥረትን ከመፍጠር ውጭ መፍትሄ አያመጣም፡፡ የእኔ ፕሮፖዛል መፍትሄው ዳቦ ቤቶችን እንደ ቢሾፍቱ ባሶች ሳይሳሱ በብዛት መርጨት ነው ባይ ነው፡፡ ዳቦ ቤቶቹ ሲበረክቱ ፉክክሩ ስለሚያይል እንኳን ግራሙ ሊቀነስ ቀርቶ እንደውም ከተባለው በላይ ሊጨምር ይችላል፡፡ የመርጨት ምስጢሩ ይሄ ነው! (በርግጥ መጀመሪያ ገበያው ላይ ስንዴ መርጨት ይቀድማል) በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ እርስ በርስ መወጋገዝና መፈራረጅ እየጨመረ መምጣቱን እያየን ነው አይደል? ለዚህ ደሞ መፍትሔው ፍቅርን መርጨት ነው፡፡ ያኔ ሰላም ይወርዳል፡፡
ኢህአዴግን በተደጋጋሚ ለሚያስወቅሰው የብልሹ አስተዳደር ጉዳይም ፕሮፖዛሌ መፍትሄ አለው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ተቋማትን መርጨት ነው ይላል መፍትሄው፡፡ በውጭም በአገር ውስጥም ኢህአዴግ ከሚታማበት ጉዳዮች አንዱ በህገ መንግስቱ የሰፈረውን ዲሞክራሲያዊ መብቶች ያለገደብ አልሰጠም የሚል ነው፡፡ መፍትሄው ቀላል ነው ይላል - አዲሱ ፕሮፖዛሌ፡፡ ነፃ ፕሬስንና የግል ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያን (ሬዲዮና ቲቪ) ሳይሰስቱ መርጨት ዋና መፍትሄው ነው፡፡ እስከዛው ግን በመንግስት እጅ ካለው ቲቪና ሬድዮ ለተቃዋሚዎች የአየር ሰዓት በብዛት መርጨት ጠቃሚ ነው ይላል - የተረቀቀው ፕሮፖዛሌ፡፡ ከ97 የፖለቲካ ቀውስ ወዲህ ገደብ ያበጀለትን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በብዛት መርጨት ኢህአዴግን ከሃሜት ነፃ እንደሚያወጣውም ፕሮፖዛሌ ያትታል፡፡ በቃ ለአብዛኞቹ ችግሮች መፍትሄው ለህዝቡ መብቱንና ነፃነቱን በስፋት መርጨት ብቻ ነው - ሳይሰስቱ፡፡ (መብትና ነፃነት እንደሆነ አያልቅ!) እናም መርጨት . . . መርጨት . . .መርጨት ምንጊዜም መርጨት!!! ምናልባት ይሄ ፕሮፖዛሌ ተግባራዊ ተደርጐ መፍትሄ ካላመጣ በቂ ጥናት አላደረኩበትም ማለት ነውና ከወዲሁ ህዝብንም መንግስንም ይቅርታ እጠይቃለሁ!! እኔም ይቅርታ እንደረጨሁ ይቆጠርልኝ፡፡

Read 3471 times Last modified on Saturday, 15 October 2011 11:56