Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 October 2011 10:23

ኃይሌ ገሪማ ለጥቁር ፊልም ሰሪዎች ፈር ቀዳጅ ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ኃይሌ ገሪማ በ1970ዎቹ በሎስ አንጀለስ ለጥቁር ፊልም ሰሪዎች  ፈር ቀዳጅ የሆኑ ተግባራትን ካከናወኑ  ባለሙያዎች ተጠቃሽ እንደሆነ ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዘገበ፡፡ በሎስ አንጀለስ ከሚታወቁ ታላላቅ ዳይሬክተሮች ተርታ ሎስአንጀለስ ታይምስ ያሰለፈው ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ፤ በ1993 የሰራውን “ሳንኮፋ” የተባለ ፊልሙን የሚያከፋፍልለት ኩባንያ አጥቶ ራሱ በ35 አገራት ዞሮ ማሳየቱ ተደንቆለታል፡ ኃይሌ ገሪማ “ዘ ኤልኤ ሬበሊዮን” በሚል የሚታወቀውን የፊልም ሰሪዎች እንቅስቃሴ ከመሰረቱ አፍሮ አሜሪካን ተማሪዎች አንዱ ነው፡፡

ዩሲኤልኤ ፊልምና ቴሌቭዥን ድርጅት ለ2 ወራት የሚዘልቅና አዲስ የሲኒማ ጥበብ የፈጠሩ ጥቁር የፊልም ባለሙያዎችን የሚዘክርበት ፌስቲቫል ያዘጋጀ ሲሆን፤ በ1979 እ.ኤ.አ “ቡሽ ማማ” እና “አሽስ ኤንድ ኤምበርስ” በሚል የተሰሩት የኃይሌ ገሪማ ፊልሞች በፌስቲቫሉ እንደሚካተቱ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል በ400 ሚሊዮን ዶላር በጀት ሎስአንጀለስ ውስጥ የሆሊውድ ሙዚዬም ሊገነባ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የግንባታ ስራው የሚጀመረው ሙዚየሙ፤ ግንባታው ሲጠናቀቅ 42 ሚሊዮን የፊልም ፖስተሮችና ከ10 ሚሊዮን በላይ የፊልም ፎቶግራፎች እንደሚቀመጥበት ተግናሯል፡፡

 

Read 4042 times Last modified on Saturday, 08 October 2011 10:26