Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 October 2011 10:22

የ ”ዘ ኢትዮጵያን ባንድ” መስራች አረፈ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በስካና ሮክስቴዲ የሙዚቃ ስልቶች የሚታወቀውና በሬጌ ፈር ቀዳጅነት የሚጠቀሰው የ”ዘ ኢትዮጵያን ባንድ” መስራች ሊዮናርድ ዲሎን  በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በአንጎል ካንሰር የሞተው ጃማይካዊው የግጥም ደራሲና ድምፃዊ ዲሎን፤ የሙዚቃ ስልቶችን በአፍሮሴንትሪክ ጭብጥ በመስራት ከጃማይካ ድምፃውያን ቀዳሚው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ባንዱ የተመሰረተበት ዓመት የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ ሃይለስላሴ በጃማይካ ካደረጉት ጉብኝት ጋር  የተገጣጠመ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ ሊዮናርድ ዲሎን በ2009 ያሳተመው አልበም “ኦሪጅናል ሂትሜከርስ ፍሮም ጃማይካ ቮሊውም 1”፤ “ሊዮናርድ ኮመን ዘ ኢትዮጵያን” የመጨረሻ ስራው ሲሆን “ ዘ ኢትዮጵያን ባንድ” ባለፉት 46 ዓመታት  13  አልበሞችን ለገበያ አብቅቷል፡፡

Read 4563 times