Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 October 2011 10:15

መፃሕፍት ይመረቃሉ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የሬዲዮ ፋና ኦሮምኛ ቋንቋ አገልግሎት ባልደረባ በሆነው ጋዜጠኛ ኪዳኑ ዘለቀ ለንባብ የበቁ ሁለት የኦሮምኛ መፃሕፍት ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ቦሌ በሚገኘው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር አዳራሽ ይመረቃሉ፡፡ በዚሁ ወር ከማተሚያ ቤት የወጡት የጋዜጠኛ ኪዳኑ መፃሕፍት ለመጀመርያ ጊዜ በኦሮምኛ የታተመው “ቆሳ ገገባር” የቀልድ መጽሐፍ እና “ኮቲ ሞኮሚቲ” የግጥም መፃሕፍት መሆናቸውን ምረቃውን ያሰናዳው ሱቢ ፕሮሞሽን ለአዲስ አድማስ በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡

ነጃሺ ማተሚያ ቤት “አን - ነፊስ” የተሰኘ ባለ ሶስት ቋንቋ መዝገበ ቃላት ነገ ከጧቱ 2፡30 በሐገር ፍቅር ትያትር ያስመርቃል፡፡ 880 ገፆች ያሉት መዝገበ ቃላት አረቢኛ -አማርኛ - እንግሊዝኛ ነው፡፡ መጽሐፉ የታተመው አምና ነው፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር የትግራይ ቅርንጫፍ ሰብሳቢ የሆነችው አበባ ግርማይ “ ውስብስብ” የተሰኘ ረዥም  ልቦለዷን ትናንት አስመረቀች፡፡ አዲስ አበባ በሚገኘው አክሱም ሆቴል ምረቃው የተከናወነው መጽሐፍ አምና የታተመና 113 ገፆች ያሉት ሲሆን በ25 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ በሌላም በኩልም ማስክ (The secret lover) ባለፈው ዓመት የታተመ ሲሆን ሰሞኑን ከማተሚያ ቤት ወጥቶ ለንባብ ደርሷል፡፡
መጽሐፉን ያዘጋጁት አቶ መኮንን ከድር ናቸው፡፡ 246 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በ45 ብር ይሸጣል፡፡

 

Read 4012 times Last modified on Saturday, 08 October 2011 10:17