7 ዓመቱ ብራድ ፒት ለዘንድሮ ኦስካር ሽልማት በእጩነት ከሚቀርቡ ተዋናዮች ተርታ እንደተመደበ የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ በዋርነር ብሮስ የተሰራውና ለእይታ ከበቃ ሳምንት የሆነው የብራድ ፒት አዲስ ፊልም ..መኒ ቦል.. ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ 20.26 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቶበት ከ..ላዮን ኪንግ.. ቀጥሎ በቦክስ ኦፊስ 2ኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ በፊልም ስራዎች የሚገኝ የገቢ ስኬት ብዙም ኢምፓየር ለተባለ መፅሄት ሰሞኑን የተናገረው ብራድ ፒት፤ ገቢው ጥሩ ፊልም መሠራቱን የሚያረጋግጥ አይደለም ብሏል፡፡