Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 September 2011 10:09

ሹገር ማሚ.. ፊልም ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(3 votes)

የአንጋፋውን ድምፃዊ ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ ልደት በመጪው ረቡዕ ስምንት ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር የሚዘከር ሲሆን የግብዣ ጥሪ ከሚደርሳቸው እንግዶች ውጭ ያሉት አድናቂዎቹና ሌሎች ተመልካቾች የትያትር ቤቱን የመስቀል የዓውዳመት ዝግጅት ለመታደም የመግቢያ ዋጋ እንደሚከፍሉ ታወቀ፡፡

የከያኒውን ልደት አስመልክቶ ባለቤቱ ወ/ሮ ሮማን በዙ፣ ከትያትር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ እና ከጥላሁን ገሠሠ ሕያው የኪነጥበባት አደራጅ ኮሚቴ አባላት ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ቋሚ ዝግጅት ለማቅረብ የተያዘ በጀት ስለሌለ የዘንድሮውን መታሰቢያ ከትያትር ቤቱ የመስቀል ልዩ ዝግጅት ጋር እንደሚዘክረው አስታውቋል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ    ወ/ሮ ሮማን ብሔራዊ ትያትር የበዓል ዝግጅቱን በክፍያ ከሚያስተናግዳቸው ሌላ የጥላሁንን ልደት ጐን ለጐን እንዲታደሙ 600 ነፃ ትኬት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ ስፍራ አምና የተደረገው የጥላሁን መታሰቢያ ደረጃውን የበጠቀ አልነበረም ተብሎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ወ/ሮ ሮማን ዝግጅቱ ደረጃውን የጠበቀ ነበር፣ ታሪካዊነቱንም የጠበቀ ነው፡፡.. ብለዋል፡፡ ጥላሁንን አስመልክቶ ይዘጋጃል የተባለውን ዶክመንታሪ ፊልም የሚያስተባብሩት የፊልም ባለሙያ ብርሃኑ ሽብሩ ..አሳታሚዎችን ለማወያየት የተደረገው ጥረት ከጥቂቶች በስተቀር አልተሳካም.. ብለዋል፡፡

 

Read 8598 times Last modified on Saturday, 24 September 2011 10:14