የአጥንት ህክምና በኢትዮጵያ
“አብዛኛው በሽተኛ ባህላዊ ሃኪሞችጋ ተውጦ ይቀራል”
በኢትዮጵያ የአጥንት ህክምና ራሱን ችሎ መሰጠት ከጀመረበት እና ሥልጠናውም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዲፓርትመንት ተቋቁሞለት ባለሙያዎችን ማፍራት ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ የህክምናው ፍላጐት እና ህክምናው በሚሰጥባቸው የጤና ተቋማት ላይ የሚፈጠረው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው፡፡ በአንጻሩ የህክምና አሰጣጡ እና በሙያው የሰለጠኑ ባለሙያዎች ቁጥር ከፍላጐቱ ጋር ያለው ልዩነት እጅግም ሲጠብ አይታይም፡፡ ያም ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው በህክምና ዘርፉ የሚያሰለጥኑ ተቋማት እና በሙያው መሰልጠን የሚፈልጉ ተማሪዎች ቁጥር እያደገ መምጣት፣ ህክምናውን የሚያግዙ መሳሪያዎች እና ህክምናውን የሚሰጡ የግል ሆስፒታሎች መፈጠር ለአጥንት ህክምና የተስፋ ጊዜ እየመጣ መሆኑን ያሳያል፡፡
ካንሰር ዝምተኛው ገዳይ በሽታ
በካንሰር ህመም ምክንያት ህይወቱን የሚያጣው ሰው ቁጥር በHIV ከሚሞተው በእጥፍ ይበልጣል
ከቅርብ አመታት በፊት የበለፀጉት አገራት ችግር እንደነበር የምናውቀው የካንሰር በሽታ ዛሬ ዛሬ የደሀ ሀገራትም አሳሳቢ ችግር ሆኗል፡፡ ይኸው በሽታ በዓለም ላይ ካሉትና የሰውን ልጅ ህይወት በማጥፋት ከሚታወቁት ዋና ዋና ገዳይ በሽታዎችም አንዱ ነው፡፡ ዓለም አቀፉ የካንሰር ድርጅት እ.ኤ.አ በ2007 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት መሠረት በዓለም በየዓመቱ 7 ሚሊዮን ህዝብ በካንሰር በሽታ ምክንያት ህይወቱን ያጣል፡፡ ወደ አስራ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋው ደግሞ በየዓመቱ በካንሰር ይያዛል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ችግሩ በዚሁ ባለበት ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ እ.ኤ.አ በ2020 በካንሰር የሚሞተው ህዝብ ቁጥር 10 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን በየዓመቱ በካንሰር የሚያዘው ሰው ቁጥር ደግሞ 16 ሚሊዮን ይደርሳል፡፡
ከድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የተሰጠ ማስተባበያ
“በድሬደዋ የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ብናኝ ለጤና ጠንቅ ሆኗል” በሚል ርዕስ ቅዳሜ ነሐሴ 5 ቀን 2004 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የወጣውን ጽሑፍ በተመለከተ ፋብሪካው የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ድርጅታችን መንግስት ከሚከተለው የተቀናጀ የአረንጓዴ ልማት እድገት አቅጣጫ (Climate Resilient Green Economy Growth) በመነሳት የአካባቢ ብክለት በአየር ንብረት ብሎም በዜጐች ደህንነት ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ተጽእኖ ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ከነዚህ ጥረቶች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ፆምና የጨጓራ ህመም
የጨጓራ በሽታ አንድ አይነት ብቻ ባለመሆኑ የትኛው ዓይነት በሽታ እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህም ህመምተኛው ችግሩ ያለበት በምግብ መዋጫ ቱቦው፣ በትንሹ አንጀቱ፣ ወይም በጨጓራው ውስጥ መሆኑን ለመለየት ያስችላል፡፡ ህክምናውም ምርመራ በተደረገለትና ችግሩ ተለይቶ በታወቀ በሽታ ላይ በመሆኑ ውጤታማ ይሆናል፡፡ በግምታዊ ህክምና የሚታዘዙ መድኃኒቶች እጅግ አደገኛ የሆኑ ችግሮችን ያስከትላሉ፡፡ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የፆመ ፍልሰታ፣ በእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ የታላቁ ረመዳን ወር ፆም ከተያዘ ሰንበትበት ብሏል፡፡የሁለቱም እምነት ተከታዮች እንደየእምነታቸው ህግና ትእዛዛት ፆሙን ተያይዘውታል፡፡ በዚህ የፆም ወቅትም ጿሚዎቹ ከምግብና ከመጠጥ (ከውሃ) ታቅበው ረዘም ያለ ሰዓታትን ያሳልፋሉ፡፡ ይህ ሁኔታም የጨጓራ ህመማቸውን የሚያባብስባቸው እንደሆነና ለጨጓራ ህመምም እንደሚዳርጋቸው አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡
በድሬዳዋ የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ብናኝ ለጤና ጠንቅ ሆኗል መንግስት ለህብረተሰቡ ጤና ደንታ ቢስ ሆኗል
የመተንፈሻ አካላት ላይ የሚከሰተው የጤና ችግር ዋንኛው ሲሆን የአይን በሽታ እና ከንፅህና ጉድለት የሚከሰቱ የሆድ በሽታ ችግሮችም ተጠቃሽ ናቸው (የአካባቢው ነዋሪዎች)
ብናኙ ስለአስከተለው የጤና ችግር ሪፖርት ያደረገልን አካል የለም…. (አቶ ያሬድ ታደሰ የፍብሪካው ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ)
በተደጋጋሚ አሳውቀናል፤ በአጭር ጊዜ ካላስተካከሉ ፋብሪካውን እስከ ማስቆም የሚደርስ እርምጃ እንወስዳለን፡፡ (የድሬዳዋ ጤና ቢሮ) “የምንበላውና የምንጠጣው ሲሚንቶ ነው፡፡ ልብስ አጥበን ማድረቅ፣ እህል አስጥተን ማስፈጨት አንችልም፡፡ የቤት ጽዳቱን ጉዳይ ተይው፡፡ በየሰዓቱ ብታፀጂውም ተመልሶ ያው ነው፡፡ ከዚህ የከፋው ደግሞ አዋራው በጤናችን ላይ የሚያስከትለው ችግር ነው፡፡ በዚህ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች በተለይም ህፃናት አብዛኛዎቹ የአይን በሽተኞች ናቸው፡፡
የሆድ ነገር!
በአትክልት የሚሰራ ላዛኛ
1 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
1 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት
1 ራስ ትልቅ ሽንኩርት (ደቆ የተከተፈ)
1 ራስ ነጭ ሽንኩርት (የተፈጨ)
200 ግራም እንጉዳይ (በቀጫጭኑ የተቆረጠ)
2 ካሮት (የተላጠና የተፈቀፈቀ)
1 በአራት ማዕዘን የተቆረጠ ብሪንጃል
15 ግራም በሶብላ (የተከተፈ)
30 ግራም የአትክልት መረቅ
ፍርሀት ይገድላል
እንዲያውም ከሰዎች ይልቅ እንስሳት ናቸው በብዛት በድንጋጤና በፍርሃት የሚሞቱት፡፡ በተለይ ወፍን በመሳሰሉ እንስሳት ላይ አደጋው የከፋ ነው፡፡ ወጥመድ ውስጥ ከሚገቡ ወፎች መካከል 50 በመቶ ያህሉ በድንጋጤ ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ፤ በቅርብ አመታት እንስሳትን ከማደን ይልቅ መጠበቅ እያመዘነ በመምጣቱ በድንጋጤ የመሞታቸው አጋጣሚ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ሰውየው ቤቱ ተቀምጦ ፀጥ ባለ ምሸት ወደ አልጋው ስር እንዳጋጣሚ ሲማትር ሁለት የሚያበሩ አይኖች ከጨለማው ስርቻ ሲያፈጥጡበት ያያል፡፡ ክው ይላል፡፡ የልቡ የምት ፍጥነት ይጨምርበታል፡፡
“መኖሬን የማውቀው ሌሎች እንዲኖሩ መርዳት ስችል ነው”
“ዕቅዴ ከአገር ለመውጣት በመሞከር ድንበር ላይ ወይም በረሃ ውስጥ ለመሞት ነበር፡፡ በሱማሌ በኩል በአርትሼክ ወደ የመን ያወጣል ስለተባልኩ፣ በዛው መንገድ ጉዞ ጀመርኩና አርትሼክ ድንበር ላይ በፖሊስ ተያዝኩ፡፡ አንድ አምስት ቀን ያህል ከታሰርኩ በኋላ በሥፍራው የነበረውን የመቶ አለቃ በያዘው ጠመንጃ እንዲገላግለኝ አለበለዚያ ደግሞ ወደምሄድበት እንድሄድ እንዲለቀኝ ጠየኩት፡፡ ምክንያቴን ሲጠይቀኝም እውነቱን ነገርኩት፡፡የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ ከተማ በሆነችውና ከአዲስ አበባ በአንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አዳማ ከተማ ውስጥ HIV ቫይረስ በደማቸው ኖሮ ረዳትና አስታማሚ በማጣት እጅግ የተጐዱ ወገኖችን የሚረዳና የሚንከባከብ ማዕከል መኖሩን ሰማንና ወደ ሥፍራው አመራን፡፡ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ በሰፈረው በዚህ ማዕከል በኤችአይቪ ተይዘው በሌሎች ተጓዳኝ ህመሞች እጅግ የደከሙና ረዳትና አስታማሚ የሌላቸው ህሙማን ተኝተው ያገግሙበታል፡፡ በማዕከሉ የመጠለያ፣ የመኝታ፣ የምግብ፣ የህክምናና የመድሃኒት አቅርቦት ያገኛሉ፡፡
“ማንም ሳይታከም እንዲመለስ አልፈልግም”
በ13ሚ. ብር የተከፈተ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል
አብዛኞቹ ሃብታሞች ስኳርና ደም ግፊት ከጣላቸው በኋላ ይመጣሉ
በእግር መሄድና መስራት ጤነኛነትን አያረጋግጥም
“ማንም ሳይታከም እንዲመለስ አልፈልግም”
በውጭ አገራት የመስራት ዕድሉ እያለዎት እንዴት ወደ አገርዎ ተመለሱ?
ብዙ አገሮች ለመሄድም ሆነ ለመስራት እድሉ ነበረኝ፡፡ ከአረብ አገራት እስከ አውሮፓና አሜሪካም ሔጄም አይቼዋለሁ፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ ውስጥ ሠርቼ ለውጥ አመጣለሁ ብዬ ስላሰብኩ ወደ ሌላ አገር መሄድ አልፈለግሁም፡፡ ሁሌም የምመኘውና የማስበው አገርና ወገንን ማገልገል ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው በ1997 ዓ.ም ወደ አገሬ ተመልሼ የመጣሁት፡፡ እንደመጣሁ ዘንባባ ሆስፒታል ተቀጠርኩ፡፡ በትርፍ ሰአቴ አፍሪካ ክሊኒክ እና ፖሊስ ሆስፒታል እሠራ ነበር፡፡ ፖሊስ ሆስፒታል አሁንም እየሰራሁ ነው፡፡
ለሴቶች - ሰውነት እንዳይላላ አራት መፍትሄዎች
ሆድና ጀርባን፤ ጭንና ዳሌን ለማሳመር -
ሩጫና ቀላል ስፖርቶች
ሰውነት የሚላላው በሁለት ምክንያቶች ነው - አንደኛ፤ በስፖርት እንቅስቃሴ እጥረት ጡንቻዎች ይደክማሉ። ሁለተኛ፤ የሰውነት የስብ መጠን መብዛት ነው። እንደ ሩጫ በመሳሰሉ ስፖርቶች የስብ መጠን ካልተስተካከለ፤ ሺ ጊዜ የጡንቻ ስፖርት መስራት የተሟላ ውጤት አያስገኝም።
ለምሳሌ፤ እጃችንን ወገባችን ላይ አድርገን፤ “በርከክ ብድግ” እያልን ደጋግመን በመሥራት፤ የሆድ ጡንቻዎችችንን ማጠንከር እንችላለን። ነገር ግን፤ ይህን የጡንቻ ስፖርት፤ ከ’ስብ’ ስፖርት ጋር ካላጣመርነው፤ የምንመኘው ሸንቃጣነት ላይ አንደርስም። በቦርጭ የተሸፈነ ጠንካራ የሆድ ጡንቻ ይሆንብናል።