Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

አንድ የሕዝብ አስተያየት አሰባሳቢ ባለሙያ እንደተናገረው “የሕዝብ አስተያየቶች ዕጩዎች የሚያዩትንና ሕዝቡ የሚሰማውን ስሜት ማለትም እርካታን፣ ጥላቻን፣ ተስፋ መቁረጥን፣ መተማመንን በሳይሳዊ ዘዴ ያሳያሉ፡፡” ብሏል፡፡  ***እያንዳንዱ የምክር ቤት መቀመጫ የራሱ የሆነ ጂኦግራፊያዊ አካባቢን የሚወክል ሲሆን እያንዳንዱ አባልም ብቸኛው የአካባቢው ተወካይ ሆኖ በብዙ (Plural) ድምጽ የሚመረጥ ነው፡፡ 50ዎቹ ግዛቶች እያንዳንዳቸው ቢያንስ አንድ የምክር ቤት ወንበር ይኖራቸዋል፤ ቀሪው ወንበር በሕዝብ ብዛት መጠን ለየግዛቱ ይመደባል፡፡ለምሳሌ በአላስካ ግዛት የሕዝቡ ብዛት አነስተኛ በመሆኑ በምክር ቤቱ ያለው ተወካይ አንድ ብቻ ነው፡፡ በአንጻሩ የካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ይለው በመሆኑ በምክር ቤት 53 መቀመጫዎች አሉት፡፡ በየአስር ዓመቱ የሚካሄደውን የሕዝብ ቆጠራ ተከትሎ በሚኖረው የሕዝብ ብዛት ለውጥ መነሻነት ለየግዛቱ የተመደበው የምክር ቤት ወንበር በድጋሚ ይሰላል፡፡

አብሮ ሲወጣ አይታይም ወይም አንድም ሰው ዘመድ መጥቶ ሲወስደው አይታይም፡፡ እኔ እደተረዳሁት አሜሪካ ሁለተኛ አገራችሁ ናት›› አለችኝ፡፡  ይኸኛው ግን የእኔም ጥያቄ ነበር፡፡ ዋሽንግተን ኢትዮጵያ ሆናብኛለች፡፡ ከኢትዮጵያ ሳልወጣ የናፈቀችኝ አሜሪካ አሁንም እንደናፈቀችኝ ነው፡፡ አገር ማለት ሕዝብ ነው፤ ዋሽንግተን ደግሞ ኢትዮጵያዊ ይበዛል በአማርኛ እያሰበ፣ በአማርኛ እያወራ፣ በአማርኛ የሚኖር ሕዝብ ነው ያለው፡፡ ታዲያ እንዴት አትናፍቀኝ!  ‹‹እናንተ አገር ትምሕርት እና ሥራ የለም?›› ወተወተችኝ ‹‹አለ ግን እዚህ የተሻለ ትምሕርት እና የተሻለ ሥራ ስለሚያገኙ ነው፤ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩም በርካታ ናቸው›› አልኳት፡፡ ‹‹ይሄ ሁሉ ሰው እዚህ መጥቶ እናንተ አገር ታዲያ ምን ሰው ቀራችሁ?›› አለችኝ፡፡ ‹‹እሱን እንኳን ተይው›› አልኩ በሆዴ፡፡ ‹‹እዚህ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሠርተው ራሳቸውንም አገራቸው ያለውን ቤተሰባቸውንም ይረዳሉ፤ ይህን ለማድረግ ደግሞ የተሻለ ገንዘብ ስለሚያገኙ እዚህ መሥራትን ይመርጣሉ አልኳት፡፡›› በተቻለኝ መጠን ስለሁኔታው ላስረዳት ሞከርኩ፡፡

ለምን ቢባል? ገዢው ፓርቲ ብቻ አይደለም ወደኋላ የሚንሸራተተው። ዜጎችም ይንሸራተታሉ። ኢህአዴግንስ ወቀስን። ግን፤ ምሁራንና ዜጎች ወይም ኢህአዴግን የሚቃወሙ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞችስ? በሂደት ነፃነት እንዲስፋፋና ወደ አሜሪካው አይነት የፖለቲካ ሁኔታ እንድንጓዝ ይመኛሉ? ወይስ በኢህአዴግ ቦታ ሁልጊዜ 99.9% የሚያሸንፍ ሌላ ገናና ፓርቲ ተተክቶ ማየት ነው የሚፈልጉት? ሁሉም ሰው ተቃውሞውንና ድጋፉን በነፃነት የሚገልፅበት ስርዓት እንዲስፋፋ ነው የሚያልሙት? ወይስ፤ ኢህአዴግን ተክተው የነሱ ሃሳብ ብቻ እየተስተጋባ የሌሎች ሰዎች ሃሳብ እንዲታፈን ነው? በአጭሩ የትኛው ይማርካቸዋል - የአሜሪካ ወግ ወይስ የቻይና ወግ?የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲህ የኋሊት መንሸራተቱ አያሳዝንም? ከተጨባጩ ሁኔታ ይልቅ ይበልጥ አሳዛኝ የሚሆነው ግን፤ ብዙ ኢትዮጵያውያን ለወደፊት ያላቸው ምኞት ያን ያህልም ብሩህ ሳይሆን ሲቀር ነው።

በኢኳቶርያል ጊኒ አዘጋጅነት መካሄድ ከጀመረ ሳምንት ባለፈው 8ኛው የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንሺፕ ላይ በሞት ምድብ የሚገኘው የኢትየጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በምድቡ የመጀመርያ ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈቶች ከገጠመው በኋላ ለግማሽ ፍፃሜ ሳይደርስ ቀረ፡፡ ሉሲዎች የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከካሜሮን ጋር መርሃግብሩን ለመፈፀም ያደርጋሉ፡፡ ሉሲዎች ባለፈው ሰኞ ከአይቮሪኮስት አቻቸው ጋር ባደረጉት የምድቡ የመጀመርያ ጨዋታቸው 5ለ0 ሲሸነፉ ከትናንት በስቲያ ሁለተኛ ግጥሚያቸውን ከናይጄርያ ጋር አድርገው 3ለ0 ተረትተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በሁለቱ ጨዋታዎች ያለምንም ነጥብ በ8 የግብ እዳ የምድቡን መጨረሻ ደረጃ በመያዙ የማለፍ ዕድሉ የተከናወነ ይሆናል፡፡

Monday, 05 November 2012 09:07

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ

በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በምድብ 3 ከዛምቢያ፤ ከናይጄርያና ከቡርኪናፋሶ ጋር የተደለደለው ብሄራዊ ቡድን ከፍተኛ ትኩረት አገኘ፡፡ ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ መብቃቷን በርካታ ዘገባዎች በአድናቆት አውስተዋል በምድብ 3 የሚገኙ ተፋላሚዎች ለዋልያዎቹ ከባድ ግምት እንደሰጡም ከድልድሉ በኋላ በተገለፁ አስተያየቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡ ናይጄርያ እና ዛምቢያ ለአፍሪካ ዋንጫው የሚያደርጉትን ዝግጅት ሰሞኑን በዝርዝር ሲያስታውቁ ኢትዮጵያ እና ቡርኪናፋሶ ምን አይነት የዝግጅት መርሃ ግብር እንደያዙ እስከ ትናንት አልታወቀም፡፡ በወጣው የጨዋታ ፕሮግራም መሰረት ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ ሁለቱን ጨዋታዎች በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አምስተኛ ጨዋታ ከዛምቢያ ጋር 2013 በገባ በ21ኛው ቀን እንዲሁም በ14ኛው ጨዋታ ደግሞ 2013 በገባ በ25ኛው ቀን ከቡርኪናፋሶ ጋር በኔልስፑሪት በሚገኘው የሞምቤላ ስታድዬም ታደርጋለች፡፡ የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ደግሞ 2013 በገባ በ29ኛው ቀን ከናይጄርያ ጋር በሩስተንበርግ በሚገኘው የሮያል ባፎኬንግ ስታድዬም ታካሂዳለች፡፡

በአውሮፓ የቅኝ አገዛዝ ታሪክ ውስጥ እንግሊዝ በከፋፍለህ ግዛ፣ ፈረንሳይ ደግሞ በአዋህደህ ወይም አመሳስለህ ግዛ ዘይቤያቸው ይታወቃሉ፡፡ የንጉሰነገስት ዳግማዊ ሊዎፖልዷ ቤልጅየም የቅኝ አገዛዝ ዘይቤ ግን ከእንግሊዝም ሆነ ከፈረንሳይ የአገዛዝ ዘይቤ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ የቤልጅየምን ቅኝ አገዛዝ ዘይቤ የሚገልፀው አስከፊ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ አገዛዝ ብቻ ነው፡፡ የአገዛዙን አስከፊነት ለመግለጽ ግን ቃል ተፈልጐ አይገኝለትም፡፡ እንደደሌሎቹ የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ሁሉ ቤልጅየምም ቅኝ አገዛዟ ለጨለማዋ አህጉር የስልጣኔና የእድገት ብርሀን ለማብራትና ያልሰለጠኑትን አፍሪካውያን ለማሰልጠን ነው ብላ አጥብቃ ትሟገት ነበር፡፡ ለዚህ ሙግቷ ማስረጃ ይሆናት ዘንድም በዋና ከተማዋ በብራሰልስ፣ አሁን የአውሮፓ ህብረት የኮሚሽኑና የካውንስሉ ዋና ጽህፈት ቤቶች አጠገብ በሚገኝ አንድ ትልቅ አደባባይ መናፈሻ ውስጥ አንድ ሀውልት አቁማለች፡፡

Monday, 05 November 2012 08:09

ሳንዲ ማን ናት?

የአሜሪካ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻዎች ሰሞኑን በሀይለኛ ዝናብ እና ውሽንፍር ተመተዋል፡፡ ሀሪኬ ሳንዲ የሚል ስያሜ የተሰጣት ውሽንፍር እና ከባድ ዝናብ በማሊዬን የሚቆጠሩ ሰዎችን ያለመብራት አገልግሎት አስቀርታለች፡፡ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ከተዘጉ ውለው አድረዋል፡፡ በኒውዮርክ ት/ቤቶች፣ ሆስፒታሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች የተቋረጡ ሲሆን ከ1888 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውዮርክ ስቶክ ኤክስቼንጅ ለቀናት ተዘግቷል፡፡ ሀሪኬን ሳንዲ በሚቀጥለው ሳምንት የሚካሄደውን የአሜሪካ ምርጫ የምረጡኝ ዘመቻዎች አስተጓጉላለች፡፡ የአሜሪካን የፌደራል የድንገተኛ አደጋ ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ ሚስተር ክሬይ እንደሚሉት፤ ሀሪኬይን ሳንዲ በሚቀጥለው ሳምንት የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ጫና አሳድራለች ይላሉ፡፡ 

በእድሜያቸው ከ40 አመት በሁዋላ በሆኑ ሴቶች የሽንት ፊኛ ሕመም እና የወር አበባ መቋረጥ (Pre Menopause& Menopause) ግንኘነት አላቸውን? ለሚለው ጥያቄ አዎን ... በትክክል ግንኙነት አላቸው ...ይላል Perimenopause symptoms.org የተባለው መረጃ መልስ ሲሰጥ፡፡ ምክንያቱም ይላል መረጃው...የወር አበባ ሊቋረጥ ሲልና ከተቋረጠ በሁዋላ በሴቷ ሰውነት ኢስትሮጂን የተባለው ሆርሞን ወይንም ቅመም መመረቱን ያቆማል፡፡ ኢስትሮጂን በሽንት ፊኛ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎችን የማጠንከር ድርሻ ያለው ሲሆን መመረቱ በሚያቆምበት ጊዜ ግን ዙሪያውን ማለትም በአካባቢው ያሉ ጡንቻዎች መላሸቅ ይጀምራሉ፡፡ መረጃው ከተለያዩ ሰነዶች እና ዶ/ር ወንድወሰን በለጠ የሰጡን ነው፡፡

Monday, 05 November 2012 07:57

ሳንዲ ማን ናት?

የአሜሪካ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻዎች ሰሞኑን በሀይለኛ ዝናብ እና ውሽንፍር ተመተዋል፡፡ ሀሪኬ ሳንዲ የሚል ስያሜ የተሰጣት ውሽንፍር እና ከባድ ዝናብ በማሊዬን የሚቆጠሩ ሰዎችን ያለመብራት አገልግሎት አስቀርታለች፡፡ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ከተዘጉ ውለው አድረዋል፡፡ በኒውዮርክ ት/ቤቶች፣ ሆስፒታሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች የተቋረጡ ሲሆን ከ1888 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውዮርክ ስቶክ ኤክስቼንጅ ለቀናት ተዘግቷል፡፡ ሀሪኬን ሳንዲ በሚቀጥለው ሳምንት የሚካሄደውን የአሜሪካ ምርጫ የምረጡኝ ዘመቻዎች አስተጓጉላለች፡፡ የአሜሪካን የፌደራል የድንገተኛ አደጋ ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ ሚስተር ክሬይ እንደሚሉት፤ ሀሪኬይን ሳንዲ በሚቀጥለው ሳምንት የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ጫና አሳድራለች ይላሉ፡፡

ብዙ ዕውነት ሲቆይ ተረት ይሆናል!
ከዕለታት በአንደኛው የዱሮ ዘመን፤ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አባላት፤ ድርጅታቸውን ይተዉና ወደ መንግሥት ይገባሉ፡፡ በመንግሥት ሥር አንድ አለቃ ተመድቦላቸው እየነቁ፣ እየበቁ፣ እየተደራጁ ኑሮ ይጀምራሉ፡፡
በመካከል አንደኛው ወደ ኪውባ ለከፍተኛ የንቃት ትምህርት ይላካል፡፡ ተምሮ ሲመለስ አንድ አዲስ ክስተት ያጋጥመዋል! የቡድናቸው ኃላፊ ታስሮ ይጠብቀዋል! በጣም ይደነግጥና ለቡድኑ አባላት፤
“ያ ሰብሳቢያችን (በዛሬው ቋንቋ ጠርናፊያችን) የት ሄደ?” ሲል ይጠይቃል፡፡
“ውይ ታሰረኮ!” ይላል አንደኛ የቡድን አባል፡፡