Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

የእኔ ሥራ ሁልጊዜ መሥራት ነው፡፡ ለእኔ የሚገባኝ በመሥራቴ ትምህርት እየተማርኩ እንዳለሁ ነው፡፡ ለሙያው ያደረኩትን አስተዋጽኦ በሚመለከት የሚያውቀው ተመልካቹ ነው፡፡ የሚደርሰኝ አስተያየት ደግሞ አበረታች ነው፡፡ ለእኔ ይሄንን ማግኘቴ በጣም ደስ የሚያሰኘኝ እና ወደ ተሻለ ነገር የሚገፋፋኝ ነው፡፡  እኔ እንደ ባለሞያ ዕድገቱን ሳይ ለምሳሌ ሔሮሺማ ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ነው፣ ተመልካችም ጥሩ አስተያየት ይሰጠናል፡፡ ስለዚህ ሙያው ማደጉን ያሳያል፡፡ በዓለም ላይ የተከሰቱት የእርስ በርስ ጦርነት፣ ድርቅ እና የተፈጥሮ አደጋዎች አሰቃቂ ክስተቶች ናቸው፡፡ በ2004 ዓ.ም ኢትዮጵያ ሁሉም ሰው የሚደሰትባት፣ የሚጠግብባት ፍቅር እና ሠላም የሠፈነባት፤ አንድም ሰው ዳቦ አጥቶ የማይራብባት ኢትዮጵያን እመኛለሁ፡፡
መሠረት መብራቴ ተዋናይ

በ2003 ዓ.ም በቂ በሆነ ሁኔታ ጥበብ አድጓል፡፡ እኔ በግሌ ..አባይ ወይስ ቬጋስን.. ሠጥቻለሁ፡፡ ለእኔ በ2003 ዓ.ም አስቸጋሪ ወቅት የነበረው ..አባይ ወይስ ቬጋስ.. ፊልም ለማሳየት የተፈጠረው የአዳራሽ ግርግር ነበር፡፡
አስደሳቹ ደግሞ መሳካቱ ሲሆን ሌላው ሰባት ወር ደክሜ የሠራሁት ፊልም ከእነላፕቶፔ መሠረቁ አሳዛኙ ነገር ነው፡፡ በአገር ደረጃ አስደሳቹ የአባይ ግድብ መገንባቱ ነው፡፡
በአጭር ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ከምዕራባያውያን ቀድማ ቁጥር አንድ ትባላለች ብዬ አስባለሁ፡፡ መልካም ምኞቴ ይህ ነው፡፡
ቴዎድሮስ ተሾመ
የፊልም ዳሬክተር እና ተዋናይ

Saturday, 10 September 2011 13:45

..ጥበብ በደንብ አድጓል..

በ2003 ዓ.ም ጥበብ በደንብ አድጓል፡፡ በሞያው ስላደረኩት አስተዋጽኦ ከእኔ ይልቅ ሰው ቢናገረው ይሻላል፡፡ በአጠቃላይ  በርካታ ሥራዎች በመሠራታቸው ግን ማደጉን እያየን ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ስኬታማ የሆንበትን ጥሩ የቴሌቪዥን ድራማ ሠርተናል፡፡ እየሠራንም ነው፡፡በዓመቱ አስቸጋሪ የምለው የኑሮ ውድነቱን ነው፡፡ ኢትዮጵያ በ2004 ዓ.ም ሠላም የሠፈነባት፤ ኑሮ ተስተካክሎ ከሠላም ጋር የምናያት ኢትዮጵያ እንድትሆን እመኛለሁ፡፡  
ሙሉአለም ታደሰ
የማስታወቂያ ባለሙያ እና ተዋናይ

ካለፉት ጊዜያት አንፃር 2003 ስገመግመው ሥራዎች በጥራትና በብዛት እየተስፋፉ ነው፡፡ ሕዝቡ ትያትሮችን እየተመለከተ እና እየወደደ  መምጣቱ በጣም የሚያስደስት ነገር ነው፡፡ በእኔ በኩል በ2003 ዓ.ም በድርጅቴ የሠራሁት ..የሚስት ያለህ.. ትያትርን ነው፡፡ ከየካቲት ወር ጀምሮ በብሔራዊ ቲያትር እየታየ ነው፡፡ በፊልም ደረጃ ደግሞ ..ሔሮሺማ.. ላይ ሠርቻለሁ፡፡ ይሄንን በማድረጌ ለጥበቡ እድገት አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ እላለሁ፡፡ በጽሑፍና በትወና የምሳተፍባቸው ሥራዎች ደግሞ በ2004 ይቀጥላሉ፡፡

በ2003 ዓ.ም የሥነጥበብ ሞያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ክብር ያገኘበት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ አንድ የአገር መሪ የኪነጥበብ ሰዎችን ..ችግራችሁ ምንድነው? ችግራችሁን እንፍታ?.. በሚል ያወያዩን ጊዜ ነበር፤ ይሄ ትልቅ ክብር ነው፡፡ ትልቅ ሥራ እንዲሠራ የተዘረጋ ነገር በመሆኑ አንድ ለየት ያለ ክንውን ያደርገዋል፡፡ ሌላው ባሳለፍነው ዓመት በርካታ ትልልቅ ፊልሞች ተሠርተዋል፡፡ ለእኔ ግን በዓመቱ ከተከናወኑ ክንውኖች ዋናውን ቦታ የሚይዘው መንግሥት ለጥበቡ ትኩረት መስጠቱ ነው፡፡ ጥበቡ እንዲያድግ አንድ እርምጃ ተሄዷል ማለት ነው፡፡

በ2003 ዓ.ም አጣሁት የምለው ነገር የለም፡፡ የማልረሳቸው ክስተቶች ሁለት ነገሮች ናቸው፡፡ አንደኛው ኢዴፓ ለህዝብ ቃል በገባው መሰረት የአመራር ለውጥ አድርጐ ከተለመደው የፖለቲካ አሠራር እራሱን የተለየ ፓርቲ መሆኑን ያረጋገጠበት ነው፡፡ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂደን የቀድሞውን አመራር በአዲስ ተክተናል፡፡ ሁለተኛው በአባይ ግድብ ዙሪያ ያደረኩት ጉብኝት ነው፡፡ የዚህ ታሪክ አካል መሆኔ የማልረሳው ሲሆን ሦስተኛው በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ድርቅ ነው፡፡

Saturday, 10 September 2011 13:04

..መና የቀረ ዓመት - 2003!´

በ2003 ዓ.ም አጣሁት የምለው እርካታንና ነፃነትን ነው፡፡ አንድ ሰው ብቻውን አይደሰትም፤ አካባቢው ከተራበ እሱም አይጠግብም፡፡ ለመብላት ለመተኛት ለመልበስ አይደለም እኔ የምኖረው፡፡ ሌላው ሲደሰት እኔም እደሰታለሁ፤ ሌላው ሲራብ ግን እኔ ብቻዬን የምለውጠው ጉዳይ አይደለም፡፡
2003ን የማልረሳው የችግሩ ማግስት በመሆኑ ነው፡፡ የ2002 ዓ.ም ምርጫ ማለት ነው፡፡ አንድ ፓርቲ ያላገኘውን አገኘሁ፤ ያላሸነፈውን አሸነፍኩ፤ ህዝብ ወደደኝ ማለቱ ለኢትዮጵያ ምንም ፋይዳ የሌለው፣ ለወጣቱም ትምህርት የማይሰጥ ነው፡፡ በእኔ በኩል 2003 ዓ.ም. መና የቀረ አመት እለዋለሁ፡፡

በ2003 ዓ.ም ዲሞክራሲያዊ ስርአትን አጥቻለሁ፡፡ በነፃነት ተደራጅቶ የመንቀሳቀስ መብት ተገድቦ፣ ስልጣን ላይ ያለው አካል ከቀረነው ጋር መነጋገር አለመፈለጉ ይሄ ትልቅ ያጣነው ነገር ነው፡፡ ለዚህ አገር መፍትሄ ሊሆን ይችላል የምለው ውይይት እና መደራደር ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ ለዚህ ፍቃደኛ አለመሆኑ ትልቁ ያጣነው ነገር YmSl¾L””በ2003 ዓ.ም የማልረሳው ክስተት ይሄ የሚሌኒየሙን ግድብ የመስራትን ነገር ነው፡፡ ከሚገባው በላይ ማስጮሁ፤ ህዝቡን በስሜታዊነት አጥሮ በቂ መረጃ ሳይሰጥና ያሉትን አማራጮች ሳያሳይ፣ የምስኪኑን ህዝብ ልቦና ማዋለሉ ለምን እንደሆነ አይገባኝም፡፡

2003 ዓ.ምን ኢህአዴግ ሲገመግመው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማሳካት ወደ ተግባር የተገባበት ሁኔታ የታየበት ነው፡፡ እቅዱ እንዲታወቅና ውይይት እንዲደረግበት በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎችም ለዚህ እቅድ መሳካት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ሠፊ ሥራ የተሠራበት፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እንዲጀመር የተደረገበት ዓመት ነው፡፡ ድርጅታችን ኢህአዴግ የግድቡን ግንባታ ይፋ ካደረገ በኋላ ወጣት ሽማግሌ ሳይል የተነቃቃበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሰፊ የሆነ ግለት፣ የጋራ መግባባት የተፈጠረበት መሆኑን ህዝቡ አሳይቷል፡፡ በራሳችን አቅም ታላቁ ህዳሴ ግድብን ለመስራት ማሰባችን ራሱ ትልቅ መነሳሳት የተፈጠረበት ዓመት መሆኑን ያመለክታል፡፡

በ2003 ዓ.ም አጣሁት የምለው ነገር በግሌ የለም፡፡ በአገር ደረጃ ብዙ ነገሮች የታጡበት አመት ነው፤ የ2003 ብቻ ሳይሆኑ ሲንከባለሉ የመጡ ናቸው፡፡ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ብዙ ሰው የመብላት፣ የመኖር፣ የመልበስ አቅሙን አጥቷል፡፡ በኑሮ ውድነት ምክንያት የተፈጠረው ችግር የማህበራዊ ኢኮኖሚ እጦት የፈጠረው ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ ይሄ መቼም በመንግስት በኩልም ጐልቶ ታይቷል፡፡ መንግሥትም የተከተለው ፖሊሲ ነገሩን አባብሶት ነበር፡፡ የዋጋ ንረቱን ለመከላከል የተወሰደው እርምጃ ዋጋ እንዲንር እቃዎች እንዲጠፉ አድርጓል፡፡ የዲሞክራሲ እጦቱ የቀጠለ ቢሆንም ይሄ ሁኔታ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካም እጦት እየሆነ ነው፡፡ በእርግጥ አምባገነኖች አርባና ሰላሳ አመት ገዝተው የሆኑትን እያየነው ነው፡፡