Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ሊዮናርዶ ዲካርፒዮ ዘንድሮ ከፍተኛ ገቢ በማስመዝገብ ጆኒ ዲፕ የያዘውን የአንደኝነት ደረጃ መረከቡን ፎርብስ መጽሔት አስታወቀ፡፡በቅርቡ ..ዘ ግሬት ጋትስቢ.. የተባለ ፊልሙን ለዕይታ የሚያበቃው ዲካርፒዮ፡ በከፍተኛ ገቢ መሪነቱን የተቆጣጠረው 77 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማስመዝገብ ነው፡፡

..ካው ቦይስ ኤንድ አልየንስ.. እና ..ዘ ስመርፍስ.. እየተፎካከሩ ናቸው

በሆሊዉድ የሚሠሩ ፊልሞች ከሰሜን አሜሪካ ይልቅ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ከፍተኛ ገቢያቸውን እንደሰበሰቡ ሮይተርስ አስታወቀ፡፡ በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት በመላው ዓለም በሚገኙ 5500 ሲኒማ ቤቶች ለመታየት የበቃው ..ካው ቦይስ ኤንድ አልየንስ.. እንዲሁም በ5300 ሲኒማ ቤቶች የታየው የአኒሜሽን ፊልም ..ዘ ስመርፍስ.. በተቀራራቢ ሳምንታዊ ገቢ የቦክስ ኦፊስ ደረጃን በፉክክር እየመሩ ናቸው፡፡

ሟች፡- እ-ፎ-ይ ተገላልኩ ብሎ ነው የሳቀው ፈረሱ፡፡ የሞት ሎተሪ ወጣለት፤ የሞት ዲቪ. . . ፈነዘጠ፡፡ ከእንግዲህ የኑሮ ውድነት. . . ስቃይ. . . ጦም ማደር ብሎ ነገር እሱንእይመለከተውም፡፡ ፡፡ ፡፡ ከራሚ ይጭነቀው፡፡ ሞት የቀረ መስሎት ተስፋ ቆርጦ ነበር፤ . . .ለካ ይዘገያል እንጃ አይቀርም. . . ከሞት ኤምባሲ ቪዛ ተመታለት፡፡ . . . በሞተ ሀገር ላይ ከመኖር ተገላገለ፤ ሳቀ፡፡

Saturday, 06 August 2011 15:42

የሴቶች ገፅታ

አዲስ የልማት ራዕይ ከአጋሮቹ ከኢንቪዥን ቢዮንድ ቤዚክ ኒድስ አሶሲየሽን ከሴቶችና ህፃናት ልማት ድርጅት እና ከማህበረሰብና አካባቢ ልማት አገልግሎት ከሚባሉ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ..የሴቶች ገፅታ ክፍል 2.. በሚል ርዕስ የተሰጠው የስዕል አውደርዕይ በብሔራዊ ቴአትር አርት ጋለሪ ከነሀሴ 4 - ነሀሴ 8 2003 ለተከታታይ አምስት ቀናት ለህዝብ እይታ ክፍት ይሆናል፡፡ ይህ ክንዋኔ በአዲስ አበባ በሚገኙ አምስት ክፍለ ከተሞች ውስጥ ከሚከናወኑ ተግባራቶች አንዱ ሲሆን  አውደርዕዩ በከተማችን ውስጥ ሴቶች በልማት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያመለክት በመሆኑ ጠቃሚ መልዕክት ማስተላለፊያ መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ህብረተሰቡ በተጓዳኝ በሚቀርቡለት የግጥም ምሽቶች ውይይቶች ወ.ዘ.ተ. እየተዝናና ዕውቀት የሚገበይበትም ይሆናል፡፡

Saturday, 06 August 2011 15:42

የምናብ ውጤት ነው!

ከሦስት አሰርት ዓመታት በፊት የሆነ ነው፡፡ ጉንሳዩሉስ የተባለ ወጣት ቄስ በአሜሪካ ቺካጐ ግዛት የሚታተሙ ጋዜጦች ላይ በቀጣዩ እሁድ በዓይነቱ ለየት ያለ ትምህርት እንደሚሰጥ የሚገል ማስታወቂያ አስነግሮ ነበር፡፡ወጣቱ ቄስ በማስታወቂያው ላይ እንደጠቆመው የሚሰጠው ትምህርት ርዕስ ..አንድ ሚሊዮን ዶላር ቢኖረኝ ምን አደርግበት ነበር..ይላል፡፡ ማስታወቂያው የበርካታ አሜሪካውያንን ቀልብ ትኩረት የሳበ ሲሆን ፊሊፕ ዲ. አርሞር የተባለ ዕውቅ የግዛቷ ባለፀጋ ይገኝበታል፡፡

ዲያቆን ዳንኤል የአሜሪካ ቆይታውን አቋርጦ ተመልሷል
የማኅበረ ቅዱሳን ማእከላት የማኅበሩ ሥራ አመራር ጉባኤ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ያስተላለፈውን ከማኅበሩ አባልነት እና አገልግሎት የማገድ ውሳኔ ተቃወሙ፡፡ ከማኅበሩ የሀገር ውስጥ 47 ማእከላት መካከል ከዐሥር ያላነሱት እግዱን በማእከላቸው ተፈፃሚ ለማድረግ እንደሚቸገሩ ለዋናው ማእከል ጽ/ቤት በስልክ እና በደብዳቤ መግለፃቸውን የማኅበሩ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

በሐምሌ 23/2003 ዓ.ም. ዕትም ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ምንነታቸው ያልታወቁ ሳጥኖች በቁፋሮ ተገኙ በሚል የወጣውን ዘገባ ፋብሪካው አስተባበለ፡፡
ፋብሪካው በላከው የማስተባበያ ጽሑፍ፤ ለፋብሪካ ማስፋፊያ ሥራ አጥር ግቢው ውስጥ የነበረን አሮጌ ቤት የማፍረስ ሥራ ከመካሄዱ ውጪ የግንባታ ሥራ እያከናወነ አለመሆኑን ገልጾ ቤቱ ፈርሶ ፍርስራሹ ተጠራርጐ እስኪወገድ ድረስ የተገኙ ሳጥኖች የሉም ብሏል፡፡
ባለፈው አርብ ሐምሌ 22/2003 ዓ.ም. የጋዜጣው ሪፖርተርና ፎቶግራፈር በደረሳቸው ጥቆማ መሠረት ወደፋብሪካው በመሄድ ግቢ ውስጥ ከገቡ በኋላ በፐርሶኔል ኃላፊው እንዲወጡ በመደረጋቸው ከግቢው ውጪ በመሆን በቁፋሮው ተገኙ የተባሉትን ሳጥኖች በምስሉ እንደሚታየው በካሜራ ቀርውታል፡፡

በአሰፋ ጐሳዬ የእውቀትና ትጋት መታሰቢያ ማኅበር የኪነ ጥበብ ምሽት ላይ  የተለያዩ ዜማዎችን በማቅረብ የሚታወቀው ቶማስ አየለ ..ልብ ነው.. የተሰኘ ነጠላ ዜማ አወጣ፡፡ የመጀመሪያው የሆነው ነጠላ ሲዲ የግጥምና ዜማ ደራሲ ራሱ ቶማስ ሲሆን ሙዚቃ ቅንብርና ሚክሲንግ ሮቤል ዳኜ (ኮራ ስቱዲዮ)፣ ቤዝ ሐብታሙ ነጋሽ፣ ከቨር ዲዛይን በቃልዬ ዲጂታል ስቱዲዮ መሠራቱ ታውቋል፡፡ ቶማስ አየለ በሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ ውስጥ በኪነጥበባዊ እንቅስቃሴዎች ሲሳተፍ የቆየ ወጣት አቀንቃኝ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት ለዕይታ የበቃው ..ካፒቴን አሜሪካ፣ ዘ ፈርስት አቬንጀር.. የተባለው ፊልም የሳምንቱን ከፍተኛ ገቢ በማስመዝገብ ቦክስ ኦፊስን እየመራ እንደሆነ ታወቀ፡፡ በካርቱን ኮሚክ መጽሐፍ ..ካፒቴን አሜሪካ.. ላይ ተመስርቶ የተሠራውን ፊልም፤ ጆ ጆንሰን ዲያሬክት ሲያደርገው ክሪስ ኢልንሰና ቶሚሊ ጆንስ በመሪ ተዋናይነት ተሳትፈውበታል፡፡

ባለፈው ሳምንት እሁድ ለንደን በሚገኝ መኖሪያ ቤቷ ሞታ የተገኘችው እንግሊዛዊቷ ድምፃዊት ኤሚ ዋይን ሃውስ አሟሟት ግራ ማጋባቱን የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ አርቲስቷ በህይወት ዘመኗ ያፈራቸውን 10 ሚሊዮን ዶላር ለቤተሰቦች እንዲከፋፈል ተናዛለች፡፡