Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

Saturday, 27 August 2011 13:35

አበሻው.. ዛሬ ይመረቃል

በፈረንሳዊው ደራሲ ጆን ክሪስቶፍ ሩፊን የተፃፈው |Abyssynia´ የተሰኘ ረዥም ልቦለድ መሃፍ በደራሲና ተርጓሚ አያሌው ምትኩ ..አበሻው.. በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ዛሬ በ3፡30 በሃገር ፍቅር አዳራሽ ይመረቃል፡፡
የመሃፉ ደራሲ ጆን ክሪስቶፍ ሩፊን ወ/ሮ አዜብ ገብረየስ የተባለች ኢትዮጵያዊት አግብቶ ሁለት ልጆችን እንዳፈራ የጠቆመው ተርጓሚው አያሌው ምትኩ፤ በመጪው መስከረም መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ገልል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ ሦስት የሕክምና ኮሌጆች በተለያዩ ዘርፎች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ስመርቃሉ”መሠረት ሜድኮ ባዮሜዲካል ኮሌጅ ተማሪዎቹን ነገ ጧት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ልደት አዳራሽ ያስመርቃል፡፡ ከሦስት መቶ በላይ የሚሆኑት የሜድኮ ተጵራቂዎች በክሊኒካል ነርስነት፣ በፋርማሲ ባለሙያነት፣ በዲግሪና እንዲሁም በዲፕሎማ ለመጨረሻ ጊዜ የተማሩ ናቸው፡፡

ለዕይታ ከበቃ ሁለት ሳምንት የሆነው የትዌንቲ ሴንቸሪ ፎክስ አዲስ ሳይንሳዊ ልቦለድ ፊልም ..ራይዝ ኦፍ ዘ ፕላኔት ኤፕስ.. በሳምንታዊ ገቢ የቦክስ ኦፊስን የገበያ ሰንጠረዥ እየመራ ነው፡፡ በ93 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሠራው ፊልም ባለፉት 15 ቀናት  በዓለም ዙሪያ ያስገኘው ገቢ ከ180 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፡፡ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 3961 ሲኒማዎች በመታየት ላይ ያለው ይኸው ፊልም ላይ ጀምስ ፍራንኮ እና ፍሪዳ ፒኒቶ ይተውናሉ፡፡

እንግሊዛዊቷ የአር ኤንድቢ ፣ ሶልና የካንትሪ ሙዚቃ ስልቶች አርቲስት አዴሌ የቢልቦርድ ምርጥ 10 አልበሞች የደረጃ ሠንጠረዥን በአንደኛነት ከተቆጣጠረች 13 ሳምንት እንደሆናት ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ ለገበያ ከበቃ 24ኛ ሳምንቱን የያዘው የአዴሌ አልበም ቢልቦርድን ለረዥም ሳምንታት በመምራት ከ10 ዓመታት በኋላ አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል፡፡ የአዴሌ 21 የተሰኘው አልበም ሽያጭ 2.9 ሚሊዮን ደርሷል፡፡

Saturday, 27 August 2011 13:20

የዕኩሊሌሊትወግ

አራት ሰዎች ነን፡፡ በአንድ ጓደኛችን ቤት ውስጥ ተቀምጠናል””ጫት እየቃምን፡፡የመሸግነው አውቶቡስ ተራ ሲሆን ጊዜው የረመዳን ጾም ወቅት ስለሆነ ገንዘብ ካለ ሃያ አራት ሰአት ጫት መግዛት የሚቻልበት ሰፈር ነው፡፡ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ላይ ሶስተኛውን ዙር ጫት አንዱ ጓደኛችን ይዞ መጣ፡፡
እንደአጋጣሚ ሆኖ የሚወራው ወሬ ስለሞት ነበር፡፡ ሚስቱን ገሎ እራሱን ስለገደለው ሰው ከተወራ በኋላ ነበር የጨዋታው መንፈስ የተቀየረው፡፡ እሱን ተከትሎ ሌላው ጓደኛችን መጠጥ ቤት በተፈጠረ አምባጓሮ ሲደባደብ በጠርሙስ አናቱን ተበርቅሶ ስለሞተው ኮበሌ አወጋን፡፡ ቢታገስና ባይደባደብ ኖሮ አይሞትም ነበር፤ ብዬ ስከራከር ቢታገስም ባይደባደብም መሞቱ አይቀርም ነበር የሚሉት ሁለቱ ጓደኞቼ እሰጥ አገባ ጀመሩ፡፡ ለግማሽ ሰዓት ያህል ተከራከርን፡፡ ባጭሩ የክርክሩ መንፈስ ሰው እራሱን ለአደጋና ለበሽታ ሳያጋልጥ ከኖረ ረጅም ዕድሜ ይኖረዋል በሚልና የፈለገውን ጥንቃቄ ቢያደርግ ከተጻፈለት ቀን አያመልጥም በሚል ሐሳብ መካከል የተደረገ የሐሳብ ፍጭት ነው፡፡

ያለምንም ጥርጥር ስኬትንየምንተነፍሰውን ያህልእንፈልገዋለን፡፡ ከተወለድንባት ቅጽበት አንስቶ የበለጠ ለማድረግ፣ የበለጠ ለማግኘት፣ የበለጠ ለመሆን እንሻለን፡፡ ስኬት ወደ ፍጽምና ለመድረስ መትጋት እንደሆነ አዕምሮአዊ ምስል ቢኖረንም እውነታው ግን የበለጠ ተፈጥሮአዊ መሆኑ ነው፡፡ ስኬት በውስጣችን ያለውን ወይም የተቀመጠውን እምቅ ህልም ወይም ሃይል የማውጣት ድፍረት ነው ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ትንፋሽ የመስጠት ዕድል ነው ቢባልም ያስኬዳል፡፡ አብዛኛው ሰውን ግን ይሄን ጉዳይ አይሞክረውም ምክንያቱም አደገኛ መስሎ ስለሚታየው ነው - የተለመደ የአዘቦት ቀን ተግባር አይደለምና፡፡ ከነገሩ ጋር ለተለማመዱ ሰዎች ግን የተለመደ የህይወት ጐዳናቸው ነው፡፡ እነሱ ቤተኛ ናቸው፡፡

ከኤዞፕ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡
አንድ የጫማ ዕደሳ ሥራ ላይ የተሠማራ ጫማ ሰፊ ገበያ አልመጣ ብሎት ይቸገራል፡፡ ስለዚህ ጫማ የማደስ ሥራውን ይተውና ..መድኃኒት አዋቂ ነኝ.. ብሎ የህክምና ሥራ ላይ ይሠማራል፡፡
..ከማናቸውም በመርዝ ከሚመጡ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ  መድኃኒቶች በቅናሽ ዋጋ የሚሰጥ ምርጥ መድኃኒተኛ.. የሚል ሁፍ ይለጥፋል፡፡ (በአዲስ መልክ ሥራ ጀምረናል ከእሱ ይሆን የመጣው?) ሰው እንደ ጉድ ይጎርፍለት ጀመር፡፡ እሱም በየዓይነቱ ቅጠላ ቅጠል እያመጣ እየቀመመ፤
..አንተ ይሄንን ከኑግ ጋር በማንኪያ ጠዋትና ማታ ውሰድ.. ይላል፡፡ ታማሚው ይከፍላል፡፡ አመስግኖ ይሄዳል፡፡
ሌላዋ:- ትመጣለች

ታጋይ- ፈረሱ ራሱ ታጋይ መሆኑ አኩርቶት ሳቀ፡፡ እጅ ከመስጠት መታገል የተሻለ መሆኑን ስለሚያውቅ፡፡ ድንገት ሳያስበው የትግሉ ትርጉም ተገለለት፡፡ ለካ የሚታገለው ኢ-ፍትሐዊነትን ለማጥፋት፣ መልካም የፖለቲካ አስተዳደር ለማምጣት አይደለም፡፡ የሚታገለው የታደሉትን ለማጥፋት ነበር፡፡ ነጻነታቸው ያረጋገጡትን፣ የበለጉትን፣ የሰለጠኑትን ነው የሚታገለው. . . የሚታገለው የተሻለውን ለማምጣት ሳይሆን ለማጥፋት ነው፡፡ የእሱን የበታችነት የሚመሰክረው የነሱ የበላይነት ስለሆነ እነሱን በትግል አጥፍቶ ራሱን ትልቅ ማድረግ. . . ትግል ማለት የተመቻቹትን ማጥፋት መሆኑ ሲገባው አለቀሰ፡፡

የአሜሪካኑ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ መረጃዎችን እየሰበሰበ በማቀበል በዘርፉ የሚደረገውን የምርምር ሥራ እንዲያግዝ ከወራቶች በፊት ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ ልኮት የነበረውን ሮቦት ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲነሳ ማድረጉን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘገበ፡፡ የስነ ፈለክ ተመራማሪዎችን የሚያግዝ ልዩ ሮቦት እንደሆነ የተነገረለት ..ሮቦናውት.. ምድር ላይ ከሚገኘው የመቆጣጠሪያ ማዕከል በተላለፉለት ተእዛዝ መሠረት ሲስተሙ እንዲበራ ከተደረገ በኋላ ስላለበት ሁኔታ አንዳንድ መልእክቶችን እንደላከ የተገለ ሲሆን ነገሩ በሮቦት ቴክኖሎጂው ዘርፍ የታየ ትልቅ ስኬት ነውም ተብሏል፡፡ እንደ ዓይን የሚያገለግሉት እና መረጃዎችን የሚቃርምባቸው ካሜራዎች ያሉት ይህ ጠፈርተኛ ሮቦት ወደ ምድር ከላካቸው መረጃዎች መካከል ደግሞ በህዋ ጣቢያው ላይ የሚገኘውን የአሜሪካን ቤተ-ሙከራ የሚያሳይ ምስል እንደሚገኝበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

የብላክቤሪ ሞባይል ስልክ አምራች ..ሪሰርች ኢን ሞሽን.. (Research in Motion/RIM) በቅርቡ የራሱን የሙዚቃ አቅርቦት ለተጠቃሚዎቹ ማድረስ ሊጀምር እንደሆነ ዴሊሜል አስታወቀ፡፡ ..ብላክቤሪ ሜሴንጀር.. ወይም በአጭሩ “BBM” በመባል የሚታወቀውን የሞባይል ኔትዎርኩን ሲያሻሽል የቆየው ኩባንያው እንደ አፕል እና ጉግል አንድሮይድ (ኦፐሬቴንግ ሲስተም) ካሉ ተቀናቃኞቹ እኩል ለመራመድ የሚያስችሉትን አንዳንድ ማሻሻያዎች በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን አዲስ ለሚጀምረው የሙዚቃ ስትሪሜንግ አገልግሎትም እንደ ሶኒ ሚዩዚክ እና ዋርነር ሚውዚክ ግሩፕ ካሉ ታላላቅ የሙዚቃ እንዱስትሪዎች ጋር ድርድር እያደረገ እንደሆነ ታውቋል፡፡