Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

‹‹ጎበዝ ከሆነ የራሱን ሃብት ያፈራል›› ብሏልዝነኛው የሆሊውድ ተዋናይ ጃኪ ቻን ለብቸኛ ልጁ ለጄይስ ቤሳቤስቲን እንደማያወርስ መናገሩን ‹‹ሰለብርቲ ኔትዎርዝ›› ዘገበ፡፡ ከአባቱ ጋር የተቀማጠለ ኑሮ እየመራ የሚገኘው የ30 ዓመቱ ጄይሲ፤ ድምፃዊና ተዋናይ ለመሆን ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም ተብሏል፡፡ ሆኖም አባቱ በህይወት ዘመኑ ያፈራውን 130 ሚ. ዶላር የሚገመት ሃብት ሲሞት መቶ በመቶ ለበጎ አድራጎት እንደሚለግስ ገልጿል፡፡ ሰሞኑን በቤጂንግ የተዘጋጀለትን ልዩ ሽልማት ሲቀበል ንግግር ያደረገው ጃኪ ቻን፤ ለልጁ ቤሳቤስቲን እንደማያወርስ ያስታወቀ ሲሆን ቀደም ሲል ከሃብቱ ግማሹን ለበጎ አድራጎት፣ ግማሹን ደግሞ ለቤተሰቡ ለማውረስ የነበረውን እቅድ መሰረዙን ገልጿል፡፡

ዳንኤል ዴይ ሊውስ በመሪ ተዋናይነት የሚሰራበትና ከሳምንት በኋላ በመላው ዓለም መታየት የሚጀምረውን ‹‹ሊንከን››  ፊልምን ያዘጋጀው ዕውቁ የፊልም ዳይሬክተር ስቲቨን ስፒልበርግ ነው፡፡ ፊልሙ ዶሪስ ኪርኔስ የተባለ ደራሲ ‹‹ቲም ኦፍ ራይቫልስ፡ ዘ ፖለቲካል ጂኒዬስ ኦፍ አብርሃም ሊንከን›› በሚል ከፃፈው የታሪክ መፅሃፍ በተወሰደ መነሻ ሃሳብ የተሰራ ነው፡፡ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በፊልም ተዋናይነት የዘለቀው የሁለት ጊዜ ኦስካር ተሸላሚው ዳንኤል ዴይ ሊውስ፤ “በህይወት ያለ የፕላኔታችን ምርጥ ተዋናይ” ተብሎ በታይም መፅሄት ተመረጠ፡፡ ተዋናዩ ምንም እንኳን በመስኩ በቆየባቸው ዓመታት ከ20 ያልበለጡ ፊልሞችን ቢሰራም በእነዚሁ ጥቂት ስራዎቹ ከፍተኛ ተሰጥኦውን አስመስክሯል ሲል አድንቆታል - ታይም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን አሜሪካ ባለፈው ሰሞን ለእይታ የበቁ እና ታላላቅ ተዋናዮችን ያሳተፉ ፊልሞች ብዙም ገበያው እንዳልቀናቸው የቦክስኦፊስሞጆ ሪፖርት አመልክቷል፡፡ ለገበያው መቀዛቀዝ በመላው አሜሪካ የተከሰተው የሃሪኬን ሳንዲ የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ቤን አፍሌክ ዲያሬክት ያደረገው “አርጎ” የተሰኘ ፊልም 12.1 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት የሰሜን አሜሪካን ገበያ እንደሚመራ የገለፀው ቦክስ ኦፊስ ሞጆ ፤ ቶም ሃንክስ የተወነበት “ክላውድ አትላስ” 9.6 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት በሁለተኛነት እንደሚከተል አስታውቋል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት በመላው ዓለም በ25 አገራት  ለእይታ የበቃው የጀምስ ቦንድ 23ኛ ፊልም “ስካይ ፎልስ” በ80.6 ሚ. ዶላር የቦክስ ኦፊስን የዓለም የገቢ ደረጃ እንደሚመራ ታውቋል፡፡የሰውነት ክብደታቸውን ለመቀነስ የሚሹ ፊልም አፍቃሪዎች ከሌሎች የፊልም ዘውጐች ይልቅ ድንጋጤና ፍርሃት የሚለቁ ሆረር ፊልሞችን እንዲመለከቱ ጥናቱ መክሯል፡፡

ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን በፊኒክስ፤አሪዞና   ያለፈው ማክሰኞ ለአሜካ ወሳኝ ቀን ነበረች፡፡ እንደሌሎቹ የአሜሪካ ግዛቶች ሁሉ በፊኒክስ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችም ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ላይ ነበር የተከፈቱት፡፡ ቀድመው በሚመሹ ግዛቶች ምርጫው ተጠናቆ የምርጫ ውጤት መገለጽ ሲጀምር የየፓርቲው ደጋፊዎች  በከተማዋ መሀል እንብርት ላይ ወደተዘጋጁት የውጤት መከታተያ ድግሶች ላይ ለመገኘት ዝንጥ እያሉ መጓዝ ጀመሩ፡፡አሪዞና ለረጅም ዘመናት በሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊነቷ ትታወቃለች፡፡ በዘንድሮው ምርጫ ግን በርካታ ወጣቶች አስቀድመው  ድጋፋቸውን ለፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በመስጠታቸው ምርጫውን አጓጊ እንዳደረገው የአሜሪካን ምርጫ የመዘገብ ልምድ ያላቸው ጋዜጠኞች ነግረውኛል፡፡የዴሞክራቲክ ፓርቲ የአሪዞና ጽ/ቤት የምርጫ ውጤት መከታተያ ፕሮግራሙን ያዘጋጀው በሬነሳንስ ሆቴል ሲሆን ሪፐብሊካኑ ደግሞ ከዚሁ ሆቴል ጎን ባለው በሃያት ሆቴል ነበር ያዘጋጀው፡፡

Saturday, 10 November 2012 14:56

የአማኑኤል በሮች

አማኑኤል ከገባሁ ዛሬ ልክ አንድ ወሬ ነው፡፡ ብዙም ያስገረመኝ እብድ አላየሁም፡፡ የተለመዱት አይነት ናቸው፡፡ ትንሽ አረቄው ከፈጠረብኝ አበሳ አገግሜ ግቢውን ስቃኝ አንድ ነገር አየሁ የሚገርም ነገር፡፡ የሆስፒታሉ ክፍሎች የበሮቹ መስታወቶች በሙሉ ረግፈዋል፡፡ በመጀመሪያ የገረመኝ እንዴት ሠው የእብዶች መታከሚያ የሆነ ሆስፒታል ሲሠራ መስታወት እንዲህ ያበዛል? እሱስ ይሁን ግን ማን ሠበራቸው? “ቆይ አሳይሃለሁ” አለኝ Substance 6፡፡ (በአልኮል፣ በሲጋራ፣ በጫት፣ በካናቢስና … በሚያመጧቸው ጣጣዎች እዚህ ሆስፒታል የገቡ ህመምተኞች ወይም “እብዶች” ሁሉ Substance ነው የሚባሉት፡፡ Substance abuse ያደረጉ ለማለት ነው፡፡) አልኮልንም ሆነ ሌላ ሱስ አስያዥ ነገር በወጉ፣ በመጠኑ እና በሥነ-ሥርዓት የሚጠቀሙ Substance Users ሲባሉ እንደኔ አረቄ ካልጠጣ መላ ሠውነቱ የሚንቀጠቀጥ ደግሞ Substance abuser ይባላል፡፡ (አሁን abuse የሆነው ማነው? Substance ወይስ እኔ?!) “ይኼውናልህ ልጁ፡፡” አለኝ Substance 6 አንድ ቀን፡፡ 6 የአልጋ ቁጥሩ ነው፡፡ “የቱ ልጅ?”“ያ የበሮቹን መስታወት የሚሠብረው”“የታለ?” በጉጉት ጠየቅሁኝ፡፡

ለማንኛውም ወደየቤታችን የሚወስዱን መንገዶች ለየቅል እንደሆኑት ሁሉ ወደየአገር ዕድገታችንም የሚወስዱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጐዳናዎች የተለያዩ ናቸው፡፡ ዲሞክራሲዎቻችንም እንደዚያው! ማጠቃለያዎች ሁሉ ያለቀላቸው ናቸው ብሎ መደምደም ደግ አይደለም፡፡ የአፍራሽ አፍራሽ አለው፡፡ ጊዜን ጊዜ ይሽራል፡፡ ለውጥን ለውጥ ያሻሽላል፡፡  “እያንዳንዱ ጅምላ - ድምዳሜ (ማጠቃለያ) ስህተት ነው፡፡ ይሄ የእኔ ድምዳሜም እራሱ” ይለናል ሳሙኤል ጆንሰን (Every generalization is wrong, even this one)  ይሄ እጅግ ጥኑ ትግልና ሐሞት ይፈልጋል፡፡ ጥናቱን ይስጠን ነው እሚባል!! “የናዚን ኃይል የጣለው ልዕለ - ዋጋ ግሽበት ነው! የቆጠበውን ሁሉ አሟጦ መካከለኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ድራሹን ስላጠፋው ነው”የእኔ በምንለውና ቤት በአፈራው መኩራት ያስፈልጋል፡፡ ሀገራዊ ስሜታችን መቀዝቀዝም መሸነፍም የለበትም፡፡ ህንድና ቻይና በዓለም ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ኢኮኖሚ ላይ ናቸው፡፡

በቁጥጥር ሥር በዋሉት ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ምርመራውን እያካሄደ መሆኑም ታውቋል፡፡ ከፍተኛ ገንዘብ ያወጣሉ የተባሉት እነዚህ ንብረቶች በሞያሌ በኩል ወደ ኬኒያ ተወስደው ሊሸጡ በዝግጅት ላይ እንደነበሩና ዕቃዎቹን በሞያሌ በኩል ወደ ኬኒያ የሚያጓጉዙ ተረካቢዎችም እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያካሄደ ሲሆን ከወንጀሉ ጋር ተያያዥነት ያላቸውና ገና ያልተያዙ ሰዎችም እንዳሉበት ታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን፣ ከውሃና ፍሳሽ አገልግሎትና ከኢትዮ ቴሌኮም መ/ቤቶች የተውጣጡ ተወካዮች በፍተሻው ወቅት የተገኙትን ንብረቶቻቸውን እንዲለዩ ተደርጐ ተዘርፈው የተከማቹት ንብረቶች በሁለት ገልባጭ መኪኖች ወደ ፖሊስ መጋዘን እንዲጓጓዙ ተደርጓል፡፡ ዕቃዎቹም በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡

በዚሁ መሠረት የዳሽን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ “ሜቄዶኒያ ሂዩማኒተሪያን አሶሾዬሽን” የሚያበረክተውን ማኅበራዊና ሰብአዊ አስተዋጽኦ በጥልቀት በማጤን ማኅበራዊ ኃላፊነትን በጋራ ለመወጣት በማሰብ የ200,000 ብር ድጋፍ በመስጠቱ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል፡፡ የ“ሜቄዶኒያ ሂዩማኒተሪያን አሶሴሽን” መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም በለጠ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር በበጐ ተግባር እንቅስቃሴው ዙሪያ ቃለ ምልልስ ማድረጉ ይታወሳል፡፡   ድርጅታችሁ ረዳት ለሌላቸው አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን ለሚያደርገው ዕርዳታ ያለንን አድናቆት እንገልጻለን ያለው ዳሽን ባንክ፤ ለዚህ የተቀደሰ ሐሳብና ተነሳሽነት ድጋፍ ለመስጠት የጋራ ርብርብ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን እናምናለን ብሏል፡፡ ዳሽን ባንክ ረዳት የሌላቸውን አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን ከጐዳና እየሰበሰበ ለሚረዳው “ሜቄዶኒያ ሂዩማኒቴሪያን አሶሴሽን” የ200ሺ ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

በአዲሱ አሰራር ደንበኞች ተጠቀሙም አልተጠቀሙም ይከፍሉት የነበረው ክፍያ የሚቀር ሲሆን ለተቋማት ብቻ ይፈቀድ የነበረው ባለመስመር ሞባይል ለግለሰቦች ተፈቅዷል፡፡ ባለካርድ ሞባይልን ወደ ባለመስመር፣ ባለመስመርን ወደ ባለ ካርድ መቀየርም ተፈቅዷል ያሉት አቶ አብዱራሂም፤ አምስትና ከዚያ በላይ ሠራተኞች ያሏቸው ድርጅቶች ለአገልግሎቱ ከተመዘገቡ (CUG) በተባለ መርሃግብር እርስ በርስ ለሚያደርጉት የሥልክ ጥሪ በደቂቃ 80 ሳንቲም ያህል የነበረው ወደ 30 ሳንቲም ዝቅ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡ በአምስተኛው አይነት አገልግሎት 1174 በወር የከፈለ ደንበኛ፣ 2500 ደቂቃ የድምጽ ጥሪ፣ 350 የጽሑፍ መልእክት እና 50 ሜጋቢት የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛል፡፡

ባለፈው ዓመት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ሕይወት ነክ ካልሆነው የኢንሹራንስ ሥራ 336 ሚ ብር፣ ከሕይወት ኢንሹራንስ ደግሞ 13.53 ሚ ብር በአጠቃላይ 349.53 ሚ ብር የአረቦን ገቢ በማስመዝገብ ከታክስ በፊት 42 ሚ. ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም 10ኛ ዓመት በዓሉን የሚያከብረው ኩባንያው፤ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀለበት ጀምሮ ባለፉት 10 ዓመታት በካፒታል በኢንቨስትመንት፣ በሀብት መጠን፣ በቅርንጫፍ ስርጭት፣ በየዓመቱ በሚያስገባው የአረቦን ገቢና ትርፍ፣ በፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ዕድገት እያስመዘገበ የቆየ ኩባንያ መሆኑን የጠቆመው ኩባንያው፤ የኢንሹራንስ የገበያ ድርሻውን 9.1 በመቶ በማሳደግ የኢንዱስትሪውን የገበያ ድርሻ ከሚመሩት ኩባንያዎች አንዱ መሆኑን ገልጿል፡፡ ኩባንያው በዚሁ በጀት ዓመት ሕይወት ነክ ባልሆነው የኢንሹራንስ ዘርፍ 136.54 ሚ ብር፣ ለሕይወት ኢንሹራንስ ደግሞ 7.1 ሚ ብር በአጠቃላይ 143.67 ሚ ብር ካሣ መክፈሉን አስታውቋል፡፡ ለካሣ ጥያቄ ከተከፈለው ገንዘብ ውስጥ 69.5 በመቶ የሸፈነው ከተሽከርካሪ አደጋ ጋር በተያያዘ ሲሆን፤ ከሕይወት ኢንሹራንስ ደግሞ ለሕክምና ወጪ የተከፈለው ካሣ 82 በመቶ ድርሻ እንደነበራቸው ገልጿል፡፡በአሁኑ ጊዜ የኩባንያው የተጣራ ሀብት 268.7 ሚ. ብር፣ የተከፈለ ካፒታሉ 65 ሚ. ብር ሲሆን የባለአክሲዮኖች ብዛት 866 መድረሱ ታውቋል፡፡