የኢትዮጵያ ቡድን በዓለም ሻምፒዮና ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል
..የደረቀ ቅጠል እሳት ጭረው አትንደድ ቢሉት.......
.6ኛው ቢግ ብራዘርስ አፍሪካ.. በናይጀሪያዊና ዚምባብዌያዊ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር ነገ አመራር ይመርጣል
የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር ነገ ጧት በብሔራዊ ትያትር ስቱዲዮ አዳራሽ የአመራር አባላት እንደሚመርጥ አሳወቀ፡፡ በደራሲ የምወድሽ በቀለ ፕሬዚዳንትነት የሚመራው የአሁኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር ለሁለተኛ ጊዜ መወዳደር እንደሚችልና የተጓደሉ አመራሮችን ለመምረጥም መታቀዱን ከማህበሩ የተገኘው መግለጫ ያስረዳል፡፡ ከምርጫው ሌላ መደበኛ የኪነጥበብ ዝግጅት እንደሚኖርም ማወቅ ተችሏል፡፡
..የተሳሳተ ጥሪ.. እና ..አልሞትም.. ፊልሞች ይመረቃሉ
..ማሕሙድ ጋ ጠብቂኝ.. የተሰኘው ወግ በመጽሐፍ ታተመ
በቀድሞው ..የአዲስ ነገር.. ጋዜጠኛ መሐመድ ሰልማን የቀረቡ ልዩ ልዩ ወጎችና የጉዞ ማስታወሻዎችን የያዘ መጽሐፍ በቀጣዩ ሳምንት ለንባብ ይበቃል፡፡ ..ፒያሳ፣ ማሕሙድ ጋ ጠብቂኝ.. የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ መጽሕፍ በአመዛኙ በቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ቀርበው በስፋት የተነበቡ ወጎችና የጉዞ ማስታወሻዎችን ከአዳዲስ ስራዎች ጋር የያዘ ስብስብ ስራ ሲሆን 200 ገጾች አሉት፡፡
..ሰማያዊ ዐይን.. ትያትር አንደኛ ዓመቱን ነገ ያከብራል
በጋዜጠኛ ተስፋዬ ሽመልስ የተዘጋጀው ..ሰማያዊ ዐይን.. የተሰኘው ትያትር መታየት የጀመረበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ነገ ከሰዓት በኋላ ክብረ በዓል እንደሚኖር አዘጋጁ ለአዲስ አድማስ ገልል፡፡ በቅርቡ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ባዘጋጀው ውድድር ትያትሩ የተሸለመ ሲሆን ክብረ በዓሉ ይህንኑ በማስመልከት ጭምር እንደተዘጋጀ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይኸው ትያትር ካሁን ቀደም በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት እንዲሁም ለሌሎች ተመልካቾች በክፍለ ሀገር የታየ ሲሆን ከነገ ወዲያ ሰኞ ምሽት፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ በክፍያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ይታያል፡፡
ደራሲ መስፍን ኃብተማርያም የህፃናት መሃፍ ታተመ
..መሰረታዊ ሳይንስ.. ለገበያ ቀረበ
ደራሲ እና የወግ ፀሐፊ መስፍን ኃብተማርያም ..ብልጧ ዝንጀሮ.. የሚል አዲስ የሕፃናት መሐፍ ለንባብ አብቅቷል፡፡ በጀርባ በኩል The Rich Man and The Singer የሚል ሌሎች የሕፃናት ታሪኮችን የያዘው መሐፍ ዋጋ 22 ብር ነው፡፡ በአማርኛው 27 በእንግሊዝኛውም የእነዚሁኑ ትርጉም የያዘው መሐፍ በአጠቃላይ 138 ገፆች አሉት፡፡
መስፍን ሃብተማርያም ካሁን ቀደም ..አውድ ዓመት.. እና ..የቡና ቤት ስእሎች.. በሚሉት የወግ መፃሕፍቱና በሌሎቹም ሥራዎቹ ይታወቃል፡፡
በሌላ በኩል ሃና ማንያዘዋልና ኢሳያስ ገብረክርስቶስ ያዘጋጁት ..መሠረታዊ ሳይንስ.. ከ1-4ኛ ክፍል አጋዥ መሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መሐፉ በ27 ብር እየተሸጠ ነው፡፡
ፊፍቲ ሴንት ሃብታምነት ነፃነት ሰጥቶኛል አለ
በሙሉ ስሙ ከርቲስ ጃክሰን ተብሎ የሚጠራው ጥቁር አሜሪካዊው ራፐርና የፊልም ተዋናይ 50 ሴንት፤ ..ሃብታም መሆኔ ነፃነት ሰጥቶኛል.. ሲል ለፋይናሻል ታይምስ መጽሔት ተናገረ፡፡ ..ቺታሪ ቪዥን.. የተባለ የፊልም ኩባንያ በ200 ሚሊዮን ዶላር ያቋቋመው ፊፍቲ ሴንት፤ ሙዚቃውን ወደ ጐን በመተው በፊልም ስራ መጠመዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡