Administrator
ማስጠንቀቂያ! ብሔራዊ ባንክ ሕገ-ወጥ የሐዋላ ድርጅቶችን ስም ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የሌላቸውን እና ሕገ-ወጥ የሐዋላ መረቦችን መጠቀም ለከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ፣ ለባንክ ሒሳብ ዕገዳ እና ለሕግ ተጠያቂነት እንደሚያጋልጥ አሳሰበ። ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ ሲልኩም ሆነ ሲቀበሉ ዜጎች ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ አፅንኦት ሰጥቷል።
ባንኩ ይፋ ካደረጋቸው 17 ፈቃድ የሌላቸው ድርጅቶች መካከል አዱሊስ፣ አማል ኤክስፕረስ፣ ጁባ ኤክስፕረስ፣ ተወከል እና ወርልድ ዳይሬክት ሊንክ ይገኙበታል። ኅብረተሰቡ የገንዘቡን ደኅንነት ለማረጋገጥ ሕጋዊ ወኪሎችን ብቻ እንዲጠቀም እና ከማስተላለፉ በፊት በባንኩ ድረ-ገጽ ማረጋገጫዎችን እንዲያደርግ አሳስቧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ የመባረር ስጋት ተደቅኖባቸዋል
ለሁለት አሥርት ዓመታት ያህል በእስራኤል ያለ ቋሚ ሕጋዊ ፈቃድ ሲኖሩ የቆዩ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ሀገሪቱ በምትወስደው አዲስ የሕግ እርምጃ ምክንያት ከባድ የመባረር ስጋት ገጥሟቸዋል። እንደ አቶ እንዳልካቸው የማኔ እና ዮርዳኖስ ያሉ ስደተኞች ከባድ በደሎችን አልፈው እስራኤል ገብተው ሕይወት መስርተው ልጆቻችውን እያስተማሩ ቢሆንም፣ ባለፈው ታኅሣሥ ወር የእስራኤል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቡድን ከለላ ፈቃድ እንዲሰረዝ መወሰኑ ሕልማቸውን አደጋ ላይ ጥሎታል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ እስራኤል የጥገኝነት ማጽደቅ ምጣኔዋ 0.1 በመቶ ብቻ መሆኑ ስጋቱን አባብሶታል። ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰደው 'HIAS Israel' የተሰኘው ድርጅት፣ እስራኤል ዓለም አቀፍ የከለላ ስምምነቶችን አክብራ ስደተኞችን አደጋ ወደ ሚጠብቃቸው ሀገር እንዳትመልስ በቴል አቪቭ የዞን ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱን ሃራምቤ ሬዲዮ ዘግቧል፡፡
የ75 ዓመቱ የካሜሩን ፓርላማ አባል ከ25 ዓመት ፍቅረኛቸው ጋር ተጋቡ
የካሜሩን አንጋፋ ፖለቲከኛ የሆኑት የ75 ዓመቱ የክብር ፓርላማ አባል ሮጀር ሜሊንጊ ከ25 ዓመት አጋራቸው ፕሪስሲል ጋር በቤተሰብ እና በጓደኞች ታጅበው በሰርግ ተጣመሩ። የሜፉ እና አፋምባ ፓርላማ አባል እንዲሁም የቀድሞ የባጀት ሚኒስትር ዴኤታ ከወጣቷ ባለቤታቸው ጋር አዲስ ምዕራፍ ጀምረዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
ትራምፕ ራሳቸውን “የታላቆች ታላቅ” ብለው ሰየሙ
አነጋጋሪ ጉዳዮችን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በማጋራት የሚታወቁት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ራሳቸውን እስካሁን አሜሪካንን ከመሩ ፕሬዝዳንቶች ሁሉ የላቁ መሆናቸውን ገለጹ።
የመጀመሪያዎቹን ጨምሮ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አሜሪካንን የመሩ የ34 ፕሬዝዳንቶችን ምሥል በመደርደር የተለያዩ ደረጃዎችን የሰጡት ትራምፕ ራሳቸውን “ከሁሉም ያላቁ” አድርገው በማቅረብ መነጋገሪያ ሆነዋል።
በትሩዝ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ታሪክ ራሳቸውን “የታላቆች ታላቅ” በሚለው ደረጃ ላይ በማስቀመጥ ሌሎቹን በተለያዩ ደረጃዎች “ደካማ” እስከሚል ፈርጀው ከእሳቸው ስር አስቀምጠዋቸዋል።
በርካቶቹን የአሜሪካ ቀደምት ፕሬዝዳንቶች ከዝርዝሩ ውስጥ ባለማካተትም ቦታ ነፍገዋቸዋል። ምናልባትም ያልተካተቱት “ደካማ” ከተባሉት በታች ያሏቸውን ሊሆን ይችላል።
ከአውሮፓውያኑ 1789 አሜሪካ 47 ፕሬዝዳንቶች ተፈራርቀው የመሯት ሲሆን፣ በትራምፕ የደረጃ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት ግን 34ቱ ብቻ ናቸው። የዓለማችን የዲሞክራሲ ተምሳሌት የምትባለውን አገር እስካሁን ሴት ፕሬዝዳንት አልመራቻትም።
ትራምፕ ከንጽጽር ያቀረቧቸውን ቀደምት ፕሬዝዳንቶች በስድስት ክፍል የመደቧቸው ሲሆን፣ ራሳቸውን “የታላላቆች ታላቅ”፣ እርሳቸውን የሚከተሉትን ደግሞ “ታላቅ”፣ ከዚያም “ለታላቅነት የቀረቡ”፣ “መካከለኛ”፣ “ከመካከለኛ በታች” እና ደካሞች” ብለዋቸዋል።
“ደካማ” ከሚለው ምድብ ስር ያካተቷቸው ከእሳቸው የቀደሙትን ባራካ ኦባማ እና ጆ ባይደንን እንዲሁም ጂሚ ካርተር፣ ዋረን ሃርዲንግ እና ኡሊሴስ ግራንት ይገኙበታል።
BBC-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
ከስክሪን ቀንሰን መጽሐፍትን እንግለጥ!
መረጃ በበዛበት የዲጂታል ዘመን፣ አስተሳሰባችንን ቅርፅ የሚያስይዘው ምንድን ነው?
መጽሐፍት ከወረቀትና ቀለም ባለፈ አዳዲስ ዓለማትን የምንቃኝባቸው፣ የሌሎችን የሕይወት ተሞክሮ የምንኖርባቸው እና ከተለመደው አመለካከታችን ወጥተን ነገሮችን በሰፊው እንድንመለከት የሚያደርጉን ኃይለኛ መነጽሮች ናቸው። አንድን መጽሐፍ አንብበን ስንጨርስ፣ ንባቡን የጀመርንበት ማንነታችን አይሆንም።
አንድ መጽሐፍ አስተሳሰባችንን የሚቀይረው በሚከተሉት መንገዶች ነው፦•
➲ አድማስን ያሰፋል፡ ካለንበት ቦታ ሳንነሳ የዓለምን ጥግ እና የሰዎችን የተለያየ ባህል ያሳየናል።
➲ ጥልቅ እይታን ይፈጥራል፡ አጫጭር መረጃዎችን ላይ ላዩን ከማየት አልፈን፣ ነገሮችን በጥልቀት እንድንመረምር እና ምክንያታዊ እንድንሆን ያግዘናል።
➲ ስሜትን ያዳብራል፡ የሌሎችን ህመም እና ደስታ ተረድተን የተሻለ ሰብዓዊ እንድንሆን ያደርገናል።
እንግዲያውስ፣ የዘወትር ልማዳችንን ቆም አድርገን ከስክሪን ቀንሰን መጽሐፍትን እንግለጥ!
የአዲስ አበባ ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ -
«የአፍሪካ ትልቁ ጠላት ውጫዊ አይደለም፤ የኢትዮጵያም! »
ታዋቂው የኢኮኖሚ ባለሙያ ክቡር ገና በአፍሪካ እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ገጽታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ አነጋጋሪ ጽሑፍ ይፋ አደረጉ። አፍሪካ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣች 60 ዓመታት በላይ ቢቆጠሩም፣ አህጉሪቱ አሁንም ጥሬ ዕቃ ብቻ ወደ ውጭ በመላክ የቴክኖሎጂና የማምረት አቅም ጥገኛ ሆና እንደቀጠለች ባለሙያው አስገንዝበዋል። የበለጸጉ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለራሳቸውስትራቴጂካዊ ጥቅም እንጂ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ሽግግር ተቆርቁረው እንደማይሠሩ የጠቀሱት ክቡር ገና፣ የውጭ ኃይሎችን ብቻ መወንጀል ፋይዳ እንደሌለው አብራርተዋል።
በሀገር ውስጥ ደረጃም የፖለቲካ ሥልጣን ከኢኮኖሚ ቁጥጥርና ከሀብት ማከፋፈል ጋር የተቆራኘ መሆኑ ለዘብተኛ ዕድገት ትልቅ እንቅፋት መሆኑን ጽሑፉ ያሳያል። ባለሥልጣናት የንግድ ፈቃድ፣ መሬት እና የውጭ ምንዛሪ በመቆጣጠር ሀብት የሚያከማቹበት ሥርዓት በመዘርጋቱ፣ ፖለቲካዊ ሥልጣን የሞትና ሽረት ውጊያ ሆኗል። ይህ ሁኔታ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር እንዳይመጣ አድርጓል ያሉት ተንታኙ፣ የማንነት ፖለቲካና የሥልጣን ውዝግብ ተቋማዊ ልምሻን እያስከተለ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ሲዳስሱም፣ አገሪቱ ግዙፍ የተፈጥሮ ሀብትና ወጣት ሕዝብ ባለቤት ስትሆን፣ አብዛኛው የፖለቲካ አቅም በማንነት፣ በታሪክ እና በድንበር ውዝግቦች መባከኑን ጠቁመዋል። ሌሎች ሀገራት በቴክኖሎጂ ልህቀትና በስራ ፈጠራ ሲመሩ፣ እኛ በአስተዳደራዊ ድንበር እና በ ትርክት ላይ መመሰጣችን የትውልዱን ወርቃማ ጊዜ እንዳባከነው ተገልጿል። የፖለቲካ ግጭት ጠማቂዎች ታሪክን እያጣቀሱ ማህበረሰቦችን ሲያቀሳቅሱ፣ የነገው የጋራ ዕጣ ፈንታ ሊታሰብ እንደሚገባ አፅንኦት ተሰጥቷል።
በታሪካቸው ፈጽሞ ጦርነት የማያውቁት አስደናቂ ሀገራት..
የኃይሌ ማናስ አካዳሚ ካስፈተናቸው ተማሪዎች መካከል 38ቱ የውጭ የትምህርት እድል አገኙ
አንጋፋው ድምጻዊ መሐሙድ አህመድ የመጨረሻውን አልበሙን ሊያቀርብ ነው
ለስድስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ አርአያ የሆነው የክብር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አህመድ፤ የኪነ ጥበብ ህይወቱ የመጨረሻ ሥራ የሆነውን እና ለትውልድ የሚሻገር አዲስ የሙዚቃ አሻራ ለማስቀመጥ ያዘጋጀውን 26ኛ አልበሙን በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስተዋውቋል። "ለታሪክ" የተሰኘው ይህ አልበም የቀደሙትን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቅርሶችና ወጎች ከአዲሱ ትውልድ ጋር ለማገናኘት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችንና ባህላዊ ቅኝቶችን በማቀናጀት በፍቅር፣ በሀገርና በማህበራዊ እሴቶች ላይ ያተኮሩ አዳዲስና በትዝታ የተቃኙ ዜማዎችን አካትቷል።
አልበሙ በይፋ ከመለቀቁ በፊት በእንቁጣጣሽ ዋዜማ አንድ ነጠላ ዜማ የሚለቀቅ ሲሆን፣ ሙሉው አልበም በመስከረም አጋማሽ በስፖቲፋይ፣ አፕል ሙዚክ፣ ዩቲዩብ እና በሌሎችም ዲጂታል መድረኮች ለአድማጮች ይደርሳል። ይህንን ታሪካዊ ሥራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚያሰራጨው የሙዚቃ ኩባንያ ጋር በአጋርነት የሚያስተባብረው "ይሳቃል ኢንተርቴይመንት" መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ አርቲስቱ አዲሱ ትውልድ የሀገርን ባህልና ቅኝት ሳይለቅ ዘመናዊነትን እንዲቀላቅል ጥሪ አቅርቧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
ሰዓታት የቀሩት "የአድዋ ፋይት ናይት 02" የፊት-ለፊት ፍጥጫ ተካሄደ
በጉጉት የሚጠበቀው እና በMMA፣ Muay Thai እንዲሁም Boxing ዘርፎች የሚካሄደው የETFC 002 – Adwa Fight Night የፊት-ለፊት የፍጥጫና የሚዛን ልኬት መርሃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል። በዝግጅቱ ላይ ተፋላሚ አትሌቶች ፊት-ለፊት በመገናኘትና የሚዛን ልኬታቸውን በማጠናቀቅ ለዋናው የውድድር መድረክ ብቁ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤ ታዋቂ አርቲስቶች፣ ቲክቶከሮች፣ ዩቲዩበሮች እና የኢንዱስትሪው አጋሮች ተገኝተዋል።
በSweat Box እና ETFC ትብብር እንዲሁም በM-Pesa፣ GoFere እና AbbayTV አጋርነት የተዘጋጀው ይህ ግዙፍ የፍልሚያ መድረክ ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል። የፍልሚያው ትኩሳት እጅግ ከፍተኛ በሆነበት በዚህ ወቅት፣ አድናቂዎች ተጋጣሚዎቹን በድርጊት ለማየት በጉጉት እየጠበቁ የሚገኙ ሲሆን ውድድሩ ዛሬ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 10 ሰዓት ጀምሮ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት ይከናወናል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

