Administrator

Administrator

አንድ ሰባ ሰማኒያ ዘመን የሆናቸው ሽማግሌ፤ ተማሪ ቤት ገብተው ሲማሩ አንድ ተማሪ፤
“አባቴ ፤ ዛሬ ተምረው ከእንግዲህ ወዲህ ሊሾሙበት ነው? ወይስ ሊከብሩበትና ሊታዩበት?” ቢላቸው፤ ሽማግሌው፡-
“ልጄ ልሾምበት፣ ልከብርበትና ልታይበትስ ብዬ አይደለም። ነገር ግን የማይቀረው ሞት ሲመጣ፣ መልአክ-ሞቱ ይዞኝ ወደ ፈጣሪ ሲቀርብ ወዴት አገኘኸው?” ሲለው “ከአትሮኑሱ (መጽሐፍ ማስቀመጫና መግለጫ ገበታ) እግር አገኘሁት” ብሎ እንዲመሰክርልኝ ብዬ ነው” አሉት።
ሽማግሌው “በየትኛውም እድሜ መማር ራሱ ጽድቅ ነው”፤ ነው የሚሉት። እውነት ነው። የድንቁርና ዳር ድንበር በየትኛውም እድሜ አለመማር ነው። መማር ግን ፊደል መፈደል ፣ ቀለም መቅለም ብቻ አይደለም። ከመከራችን መከር፣ ከአሳራችንም ሳር ለማብቀል ይቻላል። ደንቆሮ አእምሮዬን ይዤ ሰማይ ቤት አልገባም። እጌታም ፊት አልቀርብም ያሉት አዛውንት፤ ይህ ገብቷቸዋል። አንድ ጊዜ ደግሞ አንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪ የአክስቱ ልጅ ወደአለችበት ሄዶ አንድ የምስራች ይነግራታል።
“ስሚ ዛሬ ምን ሰማሁ መሰለሽ?”
“ምን ሰማህ?”
“ዘንድሮ ሀሌ ኮሜት የተባለችው ኮከብ፣ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ልትታይ ትችላለች” ሲሉ የጃፓን የስነ-ሊቃውንት ገለጹ አላት። የአክስቱ ልጅ የሳይንስ ተማሪ ናት። ዜናው እጅግ አስደሰታት። ከተቀመጠችበት ተነስታ አቅፋ ሳመችው። ይህ ሁሉ ሲሆን ቁጭ ብላ ከርቀት ታስተውል የነበረችው ታናሽ እህቱ፣ የ12ኛ ክፍል ተማሪ እንዲህ ያስፈነደቃቸው ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉታ ስትሮጥ ትመጣና፤
“ምንድነው እንዲህ ያስደሰታችሁ? እስቲ ለኔም ንገሩኝ?” ብላ ትጠይቃቸዋለች። ታላቅ እህቷ እንዲህ ስትል አስረዳቻት፡-
“ምን መሰለሽ፤ ሃሌ ኮሜት ማለት በ76 ዓመታት አንድ ጊዜ በዓለም ላይ እንደ ፀሀይ ልታበራ የምትችል ብሩህ ኮከብ ናት። ታዲያ ይህቺ ኮሜት እንደ አጋጣሚ ዘንድሮ ኢትዮጵያ ላይ ልትታይ ትችላለች። ብለው ሳይንቲስቶች ገመቱ። የእኛ ትውልድ እድለኛ ትውልድ ነው። ከእንግዲህ እኮ ሃሌ ኮሜት በዓለም ለመታየት ሌላ 76 ዓመት ያስፈልጋታል። የእኔና የአንቺ ትውልድ ደግሞ አያያትም ማለት ነው። ደስ አይልም?”
“ግን ይቺ ኮከብ በመታየቷ ከሌላው ጊዜ ምን የተለየ ነገር ይኑራት?”
“ለውጡማ ምናልባት በዚያ ቀን 24 ሰዓት ሙሉ ብርሃን ይኖረናል። 24 ሰዓት ፀሀይ ይሆናል እንደ ማለት ነው።” እህትየዋም ፊቷን ቅጭም አደረገችና፤
“ወይ መከራ!! 24 ሰዓት ሙሉ ልንማር ነው ማለት ነው?” አለች ምርር ብላ።
ያለንበት ዘመን ትምህርት እንደ ጦር የሚፈራበት ሆኗል።
“በጠቅል ጊዜ ያልተማረ ማዘኑ አይቀርም እያደረ።” እያለ እየዘመረ ያደገ፣ ትንቢቱ ተፈጸመ እንዴ? ይል ይሆናል። ትምህርት በትምህርት ቤት የምናገኘው ብቻ አይደለም። የትምህርት ቤቱም ትምህርት ቢሆን ማጣጣሚያው ኑሮ ነው። የዛሬውን ከመስማት ከማየት እንደምንማር፣ የትላንቱን ከታሪክ መማር አለብን። ለዚህ ደግሞ የማንበብ ባህላችንን ማዳበር ግድ ይለናል። ያየነውን አላየንም፣ የሰማነውን አልሰማንም ያልን እለት ነው የመጨረሻ የድንቁርና ደረጃ። መማር ዘርፈ-ብዙ ነው። “ለምን ሆነ?” ማለት፣ “እንዴት ሆነ?” ማለት መልመድ አለብን። “ብልህ ሰው ትክክለኛ መልስ የሚሰጥ አይደለም። ትክክለኛውን ጥያቄ የሚጠይቅ እንጂ” እንዲሉ ትክክለኛ ጥያቄ መጠየቅ መልመድም አንድ የሚያስፈልገን ትምህርት ነው፤ በስተ እርጅናም ሆነ በወጣትነት።
የእያንዳንዷ ቀን ልምዳችን አስተማሪያችን ናት። ወህኒ ቤት ታስሮ የነበረ አንድ እብድ “ሞኝ ያስራል ብልጥ ይማራል!” ይል ነበር። ትምህርት የትም አለ። ከምንም ነገር መማር ይቻላል። ዋናው ማየት፣ ማስተዋልና ማዳመጥ ነው። ድርቁ ካደረሰብን ጥፋት መማር አለብን። ስለ ድርቁ ከማናገሩ የዘንድሮ ተመራጮችም። እህል አግኝተን ውሃ ማቅረብ ሲያቅተን ከማየትም መማር አለብን። እንደ ኢትዮጵያ ባለች የምርጫ መርህና አተገባበር ገና ጥሬ በሆነባት ሀገር ማሸነፍ ሳይሆን መወዳደር የነገር ሁሉ አሀዱ መሆኑን መማር ያስፈልጋል። የአሁኑ ምርጫ ተመረጥኩም አልተመረጥኩም ለመጪው 5 ዓመት ከዛሬው መዘጋጀት ጀምሬአለሁ ብሎ ማሰብ ብዙ ኪሳራ እንደሌለው መማር ተገቢ ነገር ነው። እጂን አጣጥፎ ከመቀመጥ፤ የተሻለ አወዳደቅን ማየትና መማር ይበጃል። ስርዓት መገንባት ሂደት እንጂ በአንድ ጀምበር ፊርማ “አበጀህ-አበጀሽ” ተባብሎ የሚያበቃ ጉዳይ አይደለም። ለስንት ማህበራዊ ድርና ማግ የተሳሰረን ህዝብ ጉዳይ “እኔ ነኝ መፍትሄህ! ምልክቴ ይሄ ነው! ይሄን እሰራለሁ” የሚለውን ፈሊጥ ለልመና ዜማ ብቻ ከተጠቀምንበት የወረቀት ጨዋታ ነው።
“እምነት ሲታመም ሺ ወረቀት መፈራረም!” እንዲል የሀገራችን ደራሲ።
“ሁሉ ነገር አልቆለታል” የሚል ተስፋ ቆራጭ አካሄድም ጨለምተኛ ነው። አገር ያለ ተስፋ የትም አትደርስም። ተስፋ ደግሞ ባካበትነው ልምድና የችግራችን ጓዳ ሁሉ ለመማር ካለን ዝግጁነት ይመነጫል። ለመማር እልህ እንጂ ቁጣ አያስፈልገንም። ከሰከነ መንፈስ ነው ጠንካራ ጥያቄ የሚወለደው። ጠንካራ ጥያቄ የሚለወጥ መንግስት፣ የሚያስብ ትውልድ ይፈጥራል። በዚህ መንገድ ላይ የሚማር፣ የሚወያይ ዜጋ ለማፍራት እድሉ አለን። በአለው አቅምና የእውቀት ጥሪት የመላወስ ሙከራ ማቆም የለበትም። የጠፋው ጠፍቷል- በቀረው መራመድ ያሻል። አንዲት አሮጊት እንዳሉት ነው፤ ጎረቤታቸውን ሊጠይቋት ጎራ ብለዋል። በጨዋታ መሃል፤
“ምነው መውለዱን አቆምሽ?” ይሏታል።
“ኧረ ምን በወጣኝ ብዙ ወልጃለሁ፤ ከእንግዲህ ንክችም አላደርግም” ትላለች፤ ጎረቤታቸው በምሬት።
አሮጊቷም፡- “አዬ ልጄ ተይ እንዲህ አትማረሪ!”
አሁን ከምትወልጅው ልጅ
ሞኝ ወጥቶለት
ክፉ ወጥቶለት
ሞት ወስዶለት
የሚተርፈው ትንሽ እኮ ነው!!” አሏት።
የተረፈንን የተማረ ሃይል አስተባብረን ለመማር ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል። መልአከ ሞት “ከአትሮኖሱ እግር አገኘሁት” ብሎ እንዲመሰክር እንማር። እስካሁን ከአለመማራችንም ቢሆንም እንማር!!
የወቅቱ ጥቅስ፡- “ሁሉ ነገር አልቆለታል” የሚል ተስፋ ቆራጭ አካሄድም ጨለምተኛ ነው። አገር ያለ ተስፋ የትም አትደርስም።”


 በሶማሌ ክልል የእስረኞችን አያያዝ በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል የታየባቸው ቦታዎች ቢኖሩም፤ አሁንም ብዙ ማሻሻያዎች የሚስፈልጋቸው ጉዳዮችና ቦታዎች መኖራቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡
 ኮሚሽኑ መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ ፖሊስ ጣቢያዎች ያደረገውን ፈጣን ክትትል ጨምሮ በተደጋጋሚ ጊዜያት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የፖሊስ ጣቢያዎችንና ማረሚያ ቤቶችን በመጎብኘት፣ የእስረኞችን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ በተመለከተ ክትትል አድርጓል፡፡ ከእስረኞች፣ የፖሊስ መምሪያዎችና የማረሚያ ቤቶች ኃላፊዎች እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የክልሉ የሕግ አስከባሪና የአስተዳደር አካላትም ጋር መወያየቱ ተጠቁሟል፡፡  
በክትትሉ ከተጎበኙት ቦታዎች በተለይም በጅግጅጋ ከተማ ካውንስል ፖሊስ መምሪያ በተለምዶ ሃቫና ተብሎ በሚታወቀው የተጠርጣሪዎች ማቆያና በ04 ቀበሌ አቅራቢያ የሚገኘው የካውንስሉ ማቆያ የተጠርጣሪዎች አያያዝ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡
በእነዚህ እስር ቤቶች ተጠርጣሪዎች ንፅህናቸው ባልተጠበቀና በጣም በተጨናነቁ ክፍሎች ለጤና ጎጂ በሆነ መልኩ እንደሚያዙ፣ ከፍተኛ የምግብ እጥረት መኖሩንና በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ሕጻናት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 172 መሰረት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በዋስ እንዲለቀቁ ቢጠበቅም፤ ከዚህ በተቃራኒ ከ 18 አመት በታች ያሉ ሕጻናት እስረኞች፣ ለአካለ መጠን ከደረሱ ሰዎች ጋር ተቀላቅለው እንደሚያዙ ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡
በተጨማሪም፤ በጅግጅጋ ከተማ 04 ቀበሌ አቅራቢያ በሚገኘው የካውንስሉ ማቆያ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች፤ የቤተሰብ ጉብኝት መከልከል፣ ፍርድ ቤት በጊዜ ያለመቅረብና በተወሰኑ እስረኞች ላይ ድብደባም ጭምር እንደደረሰባቸው ኮሚሽኑ ከታሳሪዎች አሳማኝ ምስክርነት መቀበሉን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በግንባር ካደረገው ውይይት በተጨማሪ ለሚመለከታቸው የከተማውና የክልሉ አስተዳደር አካላት በተጻፈ ደብዳቤ፤ ከላይ የተጠቀሱት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ እንዲታረሙ ምክረ ሃሳቦችን አቅርቦ ነበር። በተለይም የሃቫና ፖሊስ ጣቢያ ካለበት አስቸጋሪ ሁኔታ አንጻር በአፋጣኝ እንደሚዘጋ በተደጋጋሚ ለኮሚሽኑ ቃል የተገባ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ተግባራዊ አለመሆኑን አመልክቷል፡፡
ከሀቫና ፖሊስ ጣቢያ እስረኞችን ወደ ጎዴ ማረሚያ ቤት በመላክ የጣቢያውን መጨናነቅ ለመቀነስ የተሞከረ ቢሆንም፤ ይህ የተደረገው ከእስረኞችና  ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቂ ምክክር ሳይካሄድ መሆኑንና የጎዴ ማረሚያ ቤት በራሱ ከፍተኛ መጨናነቅ ያለበት በመሆኑ ታሳሪዎች ቅሬታቸውን ለኮሚሽኑ ተናግረዋል፡፡ በጎዴ ማረሚያ ቤት 14 ክፍሎች ያሉ ሲሆኑ በጉብኝቱ ወቅት 470 እስረኞች እንደነበሩ ኮሚሽኑ ጠቁሟል።  
በወንጀል ውስጥ ገብተው በመገኘታቸው በፍርድ ቤት እስራት የተፈረደባቸውና ከ50 በላይ  የሆኑ ሕፃናት በጎዴ ማረሚያ ቤት ለአካለ መጠን ከደረሱ እስረኞች ጋር ተቀላቅለው እንደሚገኙ የጠቆመው ኮሚሽኑ፤ ይህም ወጣት አጥፊዎች (ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት) ለአካለ መጠን ከደረሱ እስረኞች ተለይተው መያዝ እንዳለባቸው የሚደነግገውን ህግ የሚጥስ በመሆኑ አፋጣኝ ትኩረትና መፍትሄ የሚሻ መሆኑን አሳስቧል፡፡   
በሌላ በኩል ኮሚሽኑ፣ በክልሉ ውስጥ ተዘዋውሮ ክትትል ባደረገባቸው የፖሊስ መምሪያዎች የሚገኙ ተጠርጣሪዎች አያያዝ ላይ የተደረጉ መሻሻሎች እንዳሉ መመልከቱን ጠቁሞ፤ ቢያንስ በአንድ ጣቢያ በተወሰኑ ታሳሪዎች ላይ ድብደባ ስለመፈጸሙ ቢገለጽም፤ ስልታዊና የተስፋፋ አካላዊ ጥቃት ስለመኖሩ መረጃ አልተገኘም ብሏል፡፡ በተለይ በጅግጅጋ ከተማ በሚገኙት የዞንና የክልል ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ተጨማሪ የማቆያ ቦታዎችን በማዘጋጀትና በእስረኞች ሰብአዊ አያያዝ ረገድ አበረታች እርምጃዎች መታየታቸውን ኢሰመኮ ገልጧል፡፡    
እነዚህ አበረታች እርምጃዎች በሁሉም የእስር ቦታዎች እንዲስፋፉና በተለይም የንጽህና ችግርና የቦታ ጥበት መጨናነቅ ለመቅረፍ፣ የቤተሰብ ጉብኝት መብት በሁሉም ቦታዎች በተሟላ መንገድ ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም ታሳሪዎች ፍርድ ቤት በጊዜው መቅረባቸውንና የጥፋተኛ ፖሊስ አባላትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ ተገቢውን እርምጃዎች ሁሉ መውሰድ ያስፈልጋል ብሏል -ኮሚሽኑ፡፡
በተጨማሪም በጅግጅጋ ካውንስል ፖሊስ መምሪያ ስር የሚገኙ በወንጀል ነክ ጉዳዮች ተሳታፊ ናቸው በሚል ተጠርጥረው የታሰሩ ሕጻናት፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 172 መሰረት በአፋጣኝ በዋስ ሊለቀቁ እንደሚገባ ኢሰመኮ አስታውቋል፡፡
የሶማሌ ክልላዊ መንግስት፣ ሰብአዊ መብቶችን በማክበርና በማስከበር ረገድ በወሰዳቸው እርምጃዎች የታዩ መሻሻሎች የሚያበረታታ መሆኑን የገለጹት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ በተለይ ወንጀል ውስጥ ገብተው የተገኙ ሕፃናት እስር ጉዳይ ልዩ ትኩረትና ፈጣን እርምጃ ያስፈልገዋል ብለዋል።

   የቀብር ስነ ስርአታቸው ዛሬ ይፈፀማል

               የኮሪያ ዘማቾች ማህበርን ላለፉት 10 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩትና በቃኘው ሻለቃ ጦር ወደ ኮሪያ በመዝመት አርበኛ ወታደር ኮሎኔን መለሰ ተሰማ ከዚህም ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
ማህበሩ በትናትናው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገረው ኮሎኔል መለሰ አገራቸው ወደ ኮሪያ ባዘመታቸው ወቅት ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር በመሆን ታሪክ የማይዘነጋው ታላቅ ድል አስመዝግበዋል፡፡ ኮሎኔል መለሰ የኮሪያ ዘማቾች ማህበርን በማጠናከር፣የማህበሩን ህንጻና መዝናኛ ፓርክ ባመረ ሁኔታ እንዲሰራ ከፍተኛ ጥረት ያደርጉና ለኮሪያ ዘማች ልጆችና የልጅ ልጆች በስኮላር ሽፕ የትምህርት ዕድልና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲያገኙ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ ሲያደርጉ መቆየታቸው ተናግሯል፡፡
ኮሎኔል መለሰ በደረሰባቸው ህመም ምክንያት መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን የቀብራቸው ስነ-ስርዓትም በዛሬው ዕለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንዲፈፀም ተገልጿል፡፡

 ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ በአሰቃቂ ሁኔታ በተደጋጋሚ ጥቃት ሲደርስባቸው ቆይቷል። በአጣዬና በሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ ድርጊቶች የተፈፀሙ ሲሆን ሁሉም ዜጎች በሕይወት የመጠበቅ እና በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ ኑሮ የመመስረት እና የመሥራት ሰብዓዊ መብት እንዳላቸው በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የተደነገገ መብት መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ይህ መብት ከምንም ነገር በላይ ሊከበርላቸው የሚገቡ ዜጎች በተደጋጋሚ በተከሰቱት ማንነት ተኮር ጥቃቶች ውድ ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ አካላቸው ሲጎል እና ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ ቆይተዋል። ንፁሃን ላይ የሚደርሰው ማንነት ተኮር ጥቃት መብታቸውን የሚጥስ ብቻ ሳይሆን አሰቃቂ እና ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ የሚፈፀም መሆኑ እጅግ ልብ የሚሰብር እና በሰብዓዊ ፍጡር የሚፈፀም መሆኑን ለማመን የሚያስቸግር አድርጎታል።
በያዝነው ሳምንት መግቢያም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ በቦኔ ቀበሌ በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች ላይ ማንነት ላይ መሰረት ያደረገ ጥቃት ተፈፅሞ ብዙ ንፁሃን ዜጎች መተኪያ የሌለው ሕይወታቸውን እንዲያጡ እና ለትውልዶች ከኖሩበት ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ሆነዋል። ከዚህ ከጥቃት ከተረፉ ዜጎች ቃል ለመረዳት እንደተቻለው ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊት አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አካባቢው እንዲያስተዳድሩ ኃላፊነት ከተሰጣቸው የቀበሌና ወረዳ አስተዳዳሪዎች ማስፈራሪያ ደርሷቸው ነበር። ይህም፣ ጥቃቱ ሆን ተብሎ እና ታቅዶበት ለመፈፀሙ እና እና የአካባቢው ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ተሳትፎ አንዳለበት ማሳያ ነው። እስከአሁን በዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የተፈፀሙ ለከት ያጡ ኢሰብዓዊ የወንጀል ድርጊቶች የተፈፀሙት በታወቁ ውሱን በሆኑ ቦታወች መሆናቸው በክልሉም ሆነ በፌደራል መንግሥት በኩል ችግሩን የሚመጥን ትኩረት ላለማግኘቱ አመላካች ነው።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ በደረሰው ግድያ እና መፈናቀል የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ በጥቃቱ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ እና ለመላው ኢትዮጵያዊያን ልባዊ መፅናናትን ይመኛል። 2 በተደጋጋሚ የተከሰቱት ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንደሀገር እንዳንረጋጋ እና ዜጎች ከፍርሃት ተላቀው የዕለት ተለት ሕይወታቸውን እንዳይመሩ እንቅፋት ከመሆኑም በተጨማሪ ከውጭ ለሚመጣብን ሉዓላዊነታችን እና የሀገር ደህንነታችን ላይ ላነጣጠረ አደጋ ተጋላጭ አድርጎናል።
እነዚህ ጥቃቶች የሚፈጽሙት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉም ሆነ ከመንግሥት በተፃራሪ የቆሙ አካላት በድርጊቱ ማሳካት የሚፈልጉት ዓላማ በሀገራችን ውስጥ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዳይፈጠር እንቅፋት መሆን ሲሆን ከዚህ ከፍ ሲልም የማያባራ የእርስ በርስ ብጥብጥ በማስነሳት ሀገራችን ለማፍረስ ነው። ይህን ዓላማቸውን ለማሳካት በሀገራችን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ማኅበረሰቦች መካከል የእርስ በርስ ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ጥቃቶችን ሆን ተብሎ በተቀነባበረ መንገድ እየፈፀሙ ይገኛሉ። ይህን ዕኩይ የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማሳካት እስከመጨረሻው እስኪሸነፉ ድረስ ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን ግልፅ ሆኗል።
ይህንን እና ሀገራችን ያለችበትህ አጠቃላይ ሁኔታ ከግምት በመክተት የሚከተሉት እርምጃዎች እንዲወሰዱ አጥብቀን እንጠይቃለን።
1. የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት፣ ሰላም እና ደህንነት መጠበቅ የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም በዜጎች ላይ ጥቃት እየተፈፀመባቸው ባሉ አካባቢዎች ያለው የመንግሥት መዋቅር በጥልቅ ተፈትሾ በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎች ላይ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን የእርምት እርምጃ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲወስድ እንጠይቃለን።
2. ጥቃት ለደረሰባቸው ዜጎች መንግሥት ተገቢውን ክትትል፣ ካሳ እና መልሶ ማቋቋሚያ እገዛ በአስቸኳይ እንዲደረግላቸው፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ውስጥ አስፈላጊውን ርብርብ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።
3. ጥቃት በተደጋጋሚ የደረሰባቸውን እና ሊደርስባቸው የሚችል አካባቢዎችን በመለየት በአስቸኳይ በፌደራል መንግሥት የፀጥታ አካላት ቁጥጥር ስር በማድረግ እና በአካባቢው ያሉ ጥቃት ፈፃሚዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ እና በእነዚህ አካባቢዎች አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የደህንነት ዕቅድ እንዲቀረፅ እና በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
4. ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች የፌደራል መንግሥት ከሚሠራዉ የሰላም እና የደህንነት ማስጠበቅ ሥራ በተጨማሪ በአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመተባበር የማኅበረሰብ አቀፍ 3  ሰላም እና ደህንነት ሥራ የሚሠራ ኃይል የማደራጀት፣ የማሠልጠን እና የማስታጠቅ ሥራ እንዲሠራ እንጠይቃለን።
5. የፌደራል መንግሥት የፀጥታ መዋቅር በኃይል እጥረት ምክንያት ማስፈር በማይችልባቸው ቦታዎች ላይ ማኅበረሰቡ እራሱን መከላከል የሚያስችለው አደረጃጀት እና ትጥቅ እንዲኖረው እንዲደረግ፤
የተፈጠሩ ችግሮችን እና አጠቃላይ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት እና ደኅንነት በተመለከተ ኢዜማ በቀጣይ በየደረጃው ካሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተመሳሳይ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በዘላቂነት ማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት የሚያደርግ ይሆናል። ኢዜማ በእነዚህ ውይይቶች ችግሩን በመሰረታዊነት ለመፍታት እንዲቻል ዝርዝር ማብራሪያ የሚጠይቅ ሲሆን በየጊዜው በተፈፀሙት ጥቃቶች ውስጥ አስተዋፅዖ ያደረጉ አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበት ውሳኔ እንዲሰጥም ክትትል ያደርጋል። ለሰላም እና የዜጎች ደህንነት መረጋገጥ ማድረግ የሚችለውንም ኃላፊነትም ይወጣል፡፡
የችግሩን ጥልቀት እና ሊኬድባቸው የሚገባ መንገዶችን የሚያብራራ እና ችግሩን የሚመጥን ግብረመልስ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት፣ ለፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት፣ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አዘጋጅተን የምንልክ መሆኑን እና አፈፃፀሙን የምንከታተል ይሆናል።
በሀገራችን ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቆመው ሁሉም ዜጎች በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በዜግነታቸው በዕኩልነት የታዩበት የፖለቲካ ሥርዓት ሲመሰረት ብቻ እንደሆነ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሀገራችን ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ በመረዳት የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በሙሉ የበለጠ ችግሩን የሚያባብስ እና ወደ እርስ በርስ ግጭት የሚከተን እንዳልሆነ እንድናረጋግጥ እና ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት የሚፈጽሙ ኃይሎች መጠቀሚያ እንዳንሆን የአደራ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

 ከዕለታት አንድ ቀን አንድ የጀልባዎች እሽቅድድም ተካሂዶ ነበር፡፡ ውድድሩ በጀልባዎች የባንዲራ ቀለም ነበር፡፡ በሰባት ቀለማት ተሰይመው ነበር የሚወዳደሩት፡፡
ውድድሩ ተቀለጣጠፈ!
እየተወዳደሩ እየተሸቀዳደሙ - ቀይ ሰማያዊ አረንጓዴ ብርቱካንማ ፣ቡናማ፣ ጉራማይሌ፣ ወይናማ ቀለማት ባንዲራ ይዘው ይሯሯጡ ጀመረ፡፡
በመካከል ከባድ ማዕበል ይነሳል፡፡ ማዕበሉም ጀልባዎቹን ገለባበጣቸው፡፡ ባንዲራ ከባንዲራ ተደበላለቁ፡፡ የት የት እንዳለ አልታወቀም፡፡ ማዕበሉም አላርፍ አለ!
እንዲህ ባንዲራዎቻችን  ተዋህደው አንድ ሲሆኑ ልቦቻችን አንድ ሊሆኑ ያልቻሉበትን ምክንያት ማጣራት መልካም ነው!
አንድነታችን አይቀሬ ነው፤ የምናሸንፈው ለዚሁና ለዚሁ ብቻ ነው! ማዕበል የፈጠረው አንድነት ይሄው ነው፡፡
አንድነታችንን ከፍቅር እንውለደው፡፡ የይስሙላ አንድነት የትም አያደርሰንም፡፡ በእርግብ ላባ፤ በአበባ አልጋ ተኝተን የምናፈራው ምቾትና ህይወት የለም፡፡
ምሁራን ይወያዩ ይግባቡ፤ ቀና ቀናውን ይዩ! አንዘናጋ፡፡ አንዶለል መሰረት ያለው ህይወት ጥርጥር የለውም፡፡ በጥንት ጊዜ የነበረ የግድግዳ ላይ ፅሁፍ፤
“ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፣
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም
ይለናል፡፡
ደግ ነገር የመስራት ዝግጁነት አገርን ከክፋት ከማዳን አንድ ነው። ይሄ ደግሞ ወጣቱን ከማስተባበር፣ ሴቶችን ከማገዝ፣ አረጋውያኑን ከሟቋቋምና ምሁራኑን ከማጠናከር ጋር የተያዘ ነው፡፡ ስለዚህ ሚዲያው፣ ት/ቤቶች፣ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በዚህ መልኩ እጅ ለእጅ መያያዝ አለባቸው!
ማዕበል የፈጠረው አንድነት የምንለው ይሄንኑ ነው!!


• በ1997 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፍልስፍና የመጀመሪያ ዲግሪ
    • በ1998/99 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር፤
    • በ2000 መጨረሻ ላይ የአውሮፓ ኢኮኖሚ ኮሚሽን በሚሰጠው የራመስ ምንደስ ስኮላርሺፕ፣ በኖርዌይና ስዊድን በApplied Ethics ልዩ ዘርፍ 2ኛ   ዲግሪ፤
    • በ2005 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፍልስፍና 2ኛ ዲግሪ፤
    • ከወራት በኋላ በሚመረቅበት (አሁን በጥናትና ምርምር ላይ) በፍልስፍና 3ኛ ዲግሪውን እየሰራ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ  (አብን)ን በሊቀ መንበርነት እየመራ ይገኛል፡፡

             ቴዎድሮስ፡- የአማራ ንቅናቄን (አብን) መቼ ነው የተቀላቀልከው?
አቶ በለጠ፡- አብንን ከመሰረቱት ውስጥ አንዱ ነኝ፡፡ በ2010 ዓ.ም የመጀመሪያ ወራት አካባቢ (ለውጡ ከመምጣቱ በፊት) የህቡዕ  እንቅስቃሴ እናድርግ ነበር፡፡ በወቅቱ በፖለቲካው መድረክ ላይ የአማራው ወኪል የፖለቲካ ድርጅት ስላልነበረና በአማራም ሆነ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነው አምባገነናዊ ስርዓት መውደቅ አለበት ብለን ስለምናምን፣ አንዳንድ ጓደኛሞች ተገናኝተን እንነጋገር ነበር፡፡ በወቅቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስለነበረም፣ በግልጽ ተገናኝቶ ሰብሰብ ብሎ ለመወያየት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ስለነበሩ፣ በየካፌው 5/6 ሆነን እየተገናኘን እንነጋገራለን፡፡ የደህንነት ሰዎች ይከታተሉናል፡፡ ቤት ውስጥ እንገናኛለን፡፡ እኔ ቤት ውስጥ 5 ስብሰባዎች አድርገናል፡፡
መጨረሻ ላይ በግልጽ የምንወያይበት ሰፋ ያለ ቦታ ስላልነበረ ማንንም ላለመረበሽ (መንግስትንም  ጭምር) ቦታ ፍለጋ ባህርዳር ጣና ላይ ሔደን ከደሴ፣ከደብረ ታቦር፣ ከባሕርዳር፣ ከአዲስ አበባም ተገናኝተን፤ አብንን የመመስረቻ የምክክር ስብሰባ፣ ጣና ሀይቅ ጀልባ ላይ  ስናደርግ  “የአስቸኴይ ጊዜ አዋጁን ጥሳችኋል” ተብለን ለ2 ሳምንት አስረውናል፡፡ ማሰር ብቻ ሳይሆን ደብድበውናል፡፡ ዶ/ር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ንግግር ሲያደርጉ፣ እዚያው እስር ቤት ሆነን ነው ያዳመጥናቸው፡፡ እንግዲህ ከዚያን ጊዜ ወዲህ በአብን ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊና አሁን ደግሞ ሊቀ መንበር ሆኜ በማገልገል እገኛለሁ፡፡ አብን ሰኔ 2 እና 3 ቀን 2010 ዓ.ም በባህር ዳር ሙሉ ዓለም አዳራሽ በተደረገው ጉባኤ ነው በይፋ የተመሰረተው፡፡ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ የእውቅና ምስክር ወረቀት ያገኘው ደግሞ በታህሳስ /2011 ዓ.ም ነው፡፡
ቴዎድሮስ፡- አብንን በንቅናቄ ቅርፅ ለመመስረት ለምን ፈለጋችሁ? ለምን ፓርቲ አላደረጋችሁትም?
አቶ በለጠ፡- የአማራ ሕዝብ ሁለንተናዊ መገፋት ደርሶበታል ብለን ነው የምናመንው። ላለፉት 30 ዓመታት በርካታ ገጽታዎች ያሉት መገፋት ደርሶበታል፡፡ ወደ ፓርቲ ከመሄዳችን በፊት አጠቃላይ ሕዝባዊ ንቅናቄ መፍጠር ነበረብን፡፡ ህዝቡ በኢትዮጵያዊነት እሳቤ ውስጥ የሚኖር በመሆኑ፣ በአማራነቱ እየደረሰበት ያለውን ጉዳት በአማራነቱ ለመተርጎም ስለተቸገረ፣ እኛ በአማራነቱ መደራጀት አለበት የሚለውን ሀሳብ አነሳን፡፡
ቴዎድሮስ፡- የአማራ ሕዝብ ራሱን እንደ ኢትዮጵያዊ ብቻ ቆጥሮ መቀመጡ ችግር  ነው?
አቶ በለጠ፡- አይደለም፡፡ እንደ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ አምኖ መቀመጡ ጤናማነቱን የሚያሳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ውስጥ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ሆኖ ሰፊ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ ትናንት እኮ አማራው ብቻ ሳይሆን ሌላውም ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ውስጥ ነበረ፡፡ ግን ደግሞ ሌሎች በማንነታቸው ተደራጅተው ፖለቲካውን ሲሰሩ፣ አማራው በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ተሰልፎ በመገኘቱ ከባድ መስዋዕትነት ከፈለ፡፡ በማንነታቸው የተራጁ ሀይሎች የመንግስት ስልጣን ተቆጣጠሩ፡፡ አድራጊ ፈጣሪ ሆኑ፡፡ ይህ ሕዝብ (አማራው) ወኪል አጣ፡፡ ኢትዮጵያዊ ኃይል መንበር ላይ አልመጣም፡፡ ስለዚህ በማንነት የተደራጁ ኃይሎች ስልጣን ሲያገኙ፣ በኢትዮጵያዊነቱ የቆመውን ሕዝብ በአንድም ሆነ በሌላው መንገድ ገፉት፡፡ በማንነቱ ተደራጅቶ፣ግን ደግሞ ኢትዮጵያን እያለመ፣ ትግል ማድረግ አለበት የሚል እንቅስቀሴ አደረግን፡፡ ይህ አጠቃላይ እንቅስቃሴ፣ በንቅናቄ መልክ መካሔድ መቻል ነበረበት፡፡
በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ጉዳዮችንም እንዲገነዘባቸው ማስቻል ነበረብን፡፡ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶችም ጉልህ በሆነ ሁኔታ ህዝቡ ላይ ተፈፅመዋል፡፡ እነዚህን ትርጓሜ ሰጥቷቸው በዚያ ልክ ሰፊ ንቅናቄ ፈጥሮ፣ አንድ ወጥ የሆነ ትግል ማድረጉ አስፈላጊ ስለነበር፣ ከዚያ አጠቃላይ ሁለንተናዊ የሆነ የመገፋት ማዕቀፍ እንዲወጣ ሰፊ ንቅናቄ መፈጠር ነበረበትና፣ ፓርቲ በማደራጀት አስቻይ የሆነ ተጨባጭና ፈጣን  ለውጥ መምጣት ይችላል ብለን አላሰብንም፡፡ የአማራው ሁኔታ ሲታይ እንደ ኢትዮጵያዊነቱ ተጎድቷል፡፡ ከኢትዮጵያዊነቱ እንዲወርድ ሰፊ የሆነ ዘመቻ ሲከፈትበት ቆይቷል፡፡ በግልፅ በአደባባይ ነው የሚነገረው፡፡ በኢትዮጵያዊነቱ ጠንካራ የሆነ አደረጃጀት እንዲፈጠር አይፈቀድለትም ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ብዙ ወንድሞቻችን አማራዎችም፣ ከአማራነት ውጭ ያሉትም፣ በአንድነት ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፈው ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ይህ ዋጋ ግን ወደ መንበር እንዲቀርቡ አላደረጋቸውም፡፡ በኢትዮጵያ አሁናዊ ፖለቲካ፣ መሬት ላይ ያለው የማደራጃ መርሁ፣ የብሔር ፖለቲካ ነው፡፡ የብሔር ፖለቲካ ይዘትና ቅርጽ ኖሮት የሚሰራበት ፖለቲካ ነው፡፡ ይህን ማንም አይክደውም፡፡ መሪ የሆነውም ግለሰብ ለመሪነቱ የሚያበቃው የሆነን የብሔር ድርጅት ወክሎ ነው የሚመጣው። አቶ መለስ ዜናዊም፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝም፣ ዐቢይ አህመድም የብሔር ድርጅት ወክለው ነው የመጡት፤ ስለዚህ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚጋብዘው፣ ማደራጃ መርሁ እንደዚህ ያለውን የብሔር ፖለቲካ ነው፡፡ ይህን ተገነዘብን፡፡ አማራ መደራጀቱ የግድና አስፈላጊ ነበር፡፡ ተደራጅቶ ሰፊ ንቅናቄ መፍጠር ነበረበት፡፡ አብን ተፈጠረ፡፡
ቴዎድሮስ፡- ስለዚህ አብን የተፈጠረው ለአማራው መብትና ጥቅሞች ሲል ብቻ ነው? ኢትዮጵያዊነትንስ የት አስቀመጠው?
አቶ በለጠ፡- የትም አላስቀመጠውም። እንደያዘው ነው፡፡ በአማራነት ስንደራጅ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ገፍተን አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን ከእሳቤያችን አውጥተን አይደለም፡፡ ብንፈልግም አንችልም፡፡ መጨረሻችን ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ በእርግጥም አማራ ጠንካራ ሆኖ ባልተደራጀባቸው ጊዜያት ኢትዮጵያ አጠቃላይ ቁመናዋ ዝቅ ብሎ መታየቱን አይተናል፡፡ አማራ ተጎዳ ማለት ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ተጎዳች ማለት ነው፡፡ ኦሮሞም ተጎዳ ማለት ነው፡፡ ጠንካራ የአማራ አደረጃጀት ከተፈጠረ፣ ምናልባትም ባለመፈጠሩ የመጣውን ጉዳት መቀልበስ የሚችል እድልም ይዞ ይመጣል፣ የሚል እምነት ይዘን ነው እንደ ንቅናቄ ልንፈጠር የቻልነው፡፡
ቴዎድሮስ፡- ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ፣ የብሔር ድርጅቶች እያሸነፉ፤ ሀገራዊ ፓርቲዎች ደግሞ አቅም እያነሳቸው የመጣው የብሔሮቹ ከሀገራዊዎቹ በምን ተሽለው ነው?
አቶ በለጠ፡- የብሔር ፓርቲዎች ተሽለው ነው ማለት አልችልም፡፡ ኢትዮጵያዊ ፓርቲዎችም ሳይሻሉ ቀርተው አይደለም። ወቅቱ ነው ማለት  እችላለሁ፡፡ ለ27 ዓመታት ሀገሪቱን እየመራ የነበረው ህወሃት፣ ቀደም ሲል በብሔር ንቅናቄ የተፈጠረ ድርጅት ነበር፡፡ ትግራይን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ማዕቀፍ ገንጥሎ ራሱን የቻለ ሀገር ለማድረግ የተጠነሰሰ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ 1950ዎቹ፣ 60ዎቹ እና 70ዎቹ በብሔር የተደራጁ ድርጅቶች ተፈጥረዋል፡፡ ዛሬ ላይ በዚህ ሂደት መጥተው ነው ስልጣን የተቆጣጠሩት፡፡
እነዚህ ሰዎች ሲደራጁ የእነሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን ያልተደራጀውና በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር የተሰበሰበውን ኃይል ለመጉዳትም ጭምር እንደነበር ለመገንዘብ ጊዜ ወስዷል፡፡ እነዚህ አናሳ ቡድኖች ስልጣን ከያዙ በኋላ ተቋቁመው መቀጠል የሚችሉት ጠንካራ የሆነ የኢትዮጵያዊነት አደረጃጀት እስካልመጣ ድረስ ብቻ ነበር፡፡ ስለዚህ ህዝቦች እርስ በእርስ እንዲጋጩ እንዳይተማመኑ፣ እንዲጠራጠሩ፣ በታሪክ እንዲጣሉ፣ በምልክቶቻቸው እንዳይስማሙ፣ በታሪክ ውስጥ በምናውቃቸው ታላላቅ ሰዎቻችን ላይ ወጥ የሆነ መረዳት እንዳይኖረን፣ እንድንጣላበቸው የሚያደርጉ ትርክቶች መፍጠር ነበረበት፡፡ ህዝቡ በራሱ ጉዳይ ባተሌ መሆን ነበረበት፡፡ ስለዚህ ይህ ሂደት ጠንካራ የሆነ ኢትዮጵያዊ ኃይል ጉልበት አግኝቶ፣ ወደፊት እንዳይመጣ አንድ ምክንያት ነው ማለት እችላለሁ፡፡
ቴዎድሮስ፡- አብን መጀመሪያ ወደ ፖለቲካው መድረክ ሲመጣ ከአሁን አንፃር ድምፁን ጮክ በማድረግ ነበር፡፡ ይህን እንደ አንድ ፖለቲካዊ ስልት አድርጎ መውሰድ ይቻላል? ወይስ ሌላ ምክንያት አለው?
አቶ በለጠ፡- ልክ ነው፡፡ በወቅቱ አብን ሲመሰረት በጣም ክፍ ያለ ድምጽ ነበረው። ይህን በሁለት መንገድ ማየት ያስፈልጋል፡፡ አንደኛ፤ ይህ ሕዝብ አማራ ተብሎ ተፈርጆ፣ “ነፍጠኛ” እና “ትምህክተኛ” እየተባለ በአደባባይ በመሪዎች ጭምር ይዘልፉት የነበረ ሕዝብ ነው፡፡ አማራን በአደባባይ መዝለፍ አንዳንዴ የስልጣን ማግኛ አቋራጭ መንገድ ነበር፡፡ በዚህ ብቻም አላበቃም። የአማራ ልጆች በአደባባይ ጥያቄ ያነሱ፣ የሞገቱ፣አምባገነኑን ስርዓት የጠየቁ ሁሉ “ቶርች” ተደርገዋል፤ ተሰቃይተዋል፤ ተገድለዋል፤ የጠፉት ጠፍተዋል፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች በአማራው፣ በሌላውም ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ግፍ ሕዝብ ስለሚያውቀው መዘርዘር አያስፈልግም፡፡ ይህ ግፍ  ተጠራቅሞ ህዝቡ ላይ የአዕምሮ ቁስለት (Trauma ) ፈጥሮ ኖሯል ብዬ አምናለሁ። መደረግ የሌለበት ግፍ ተፈፅሞባቸው ከእስር ቤት ሲወጡ፣ ያን ምስክርነት ሲሠጡ ህዝብ ስሜት አለው፡፡ ከፍ ያለ የህዝብ ቁጣ ፈጥሯል፡፡ አብንም ይህ ስሜት የወለደው ነው፡፡ ከሕዝብ የወጣ ድርጅት ነው። ሕዝባዊ ንቅናቄ እየፈጠረ ያለ ድርጅት ስለሆነ፣ የሕዝቡ ህመም የሚሰማው ነው፡፡ ወደ ፖለቲካው መድረክ ስንመጣ፣ እንዲህ ከፍ ያሉ ድምጾች ሲሰሙ፣ ከዚህ አንጻር መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ ውጪ እንደ ስልትም ከታየ በእርግጥም ልክ ነው፡፡ እንደ ስልት መውሰድም አለበት፡፡
በተለይ መጀመሪያ ስንመጣ “በአማራነት መደራጀት አስፈላጊ አይደለም; የሚለው እሳቤ፤ ከአማራ ውጭ ካሉት ብቻ ሳይሆን ከአማራ ልሂቃንም ይሰማ ነበር፡፡ አብዛኛው የአማራ ልሂቅ “የብሔር ፖለቲካ አያስፈልግም፤ በኢትዮጵያዊነት ነው መደራጀት ያለባችሁ” ብሎናል፡፡ የደገፉንም አልጠፉም፡፡ የእኛን አስተሳሰብ ተደራሽ ለማድረግና ንቅናቄው ትኩረት እንዲሰጠው እንደ ስልት ብንጠቀምበትም ትክክል ነበር። በአማራነት መደራጀት አማራጭ መሆኑን እንዲነቃና እንዲያስበው፣ የትኛውንም ስልት መጠቀም ያስፈልገን ነበር፡፡ ይሁንና ምክንያቱም አንድ ሳይሆን የተለያየ ነው። አሁን ላይ በተነሳው ደረጃ ተግዳሮት አለብን ማለት አልችልም፡፡ መጀመሪያ ላይ ግን የአማራው እንደ አማራ መደራጀት፣ ለኢትዮጵያ አንድነት ህልውና ስጋት ነው ብለው ከተቃወሙን ውስጥ ሰፊ የአማራ ልሂቃን ነበሩ፡፡
(ከጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ "ፍልስምና" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ የተቀነጨበ)


As a founding member state of the United Nations and a member of the League of
    Nations, Ethiopia has always been an ardent supporter of multilateralism. It is a
    staunch devotee to the principles enshrined in the United Nations Charter including
    the principle of collective security. Ethiopia is hugely proud of its historic and
    weighty contributions to the UN, especially its peacekeeping operations. It also
    joined the Alliance for Multilateralism with a firm belief that only cooperation can
    help us solve shared challenges.
    Notwithstanding this, Ethiopia has also experienced the consequences of the failure
    of multilateralism to act in the interest of collective security. In late 1935, the
    forces of Fascist Italy invaded Ethiopia – while the pleas of the late Emperor Haile
    Selassie to the League of Nations went largely ignored.
    The Emperor appealed to the international community not to abandon Ethiopia
    while the invading fascist forces were using mustard gas on its people. In his
    impassioned speech to world leaders at the League of Nations in 1936, he
    described how “women, children, cattle, rivers and pastures were drenched with
    this deadly rain”.
    But while Fascist Italy’s devastating invasion was in clear violation of international
    law, Ethiopia’s appeal remained unanswered.
    And now, some 86 years later, history appears to be repeating itself, albeit with a
    different set of circumstances. This points to the same lack of multilateralism and
    absence of awareness of the security challenges Ethiopia and the region face.
    The vital reforms implemented by Prime Minister Abiy Ahmed and his team were
    very much lauded by the international community. They brought real changes on
    the ground for which the Ethiopian prime minister received the Nobel Peace Prize.
    These reforms rescued Ethiopia and its people from the grip of the repressive
    Tigray Peoples’ Liberation Front (TPLF), which had dominated the Ethiopian
    government since the 1990s.
    However, we are now witnessing a U-turn by the international community. Misled
    by orchestrated TPLF misinformation and propaganda, the international
    community tends to put the blame on Prime Minister Abiy’s administration for
    going after this grave threat to Ethiopian and regional security.
    Last November’s brutal attack by TPLF Forces against the Ethiopian National
    Defense Force (ENDF) Northern Command in the Tigray region was quite simply
    a declaration of war. Such an attack against a sovereign country’s national defence
    forces, the ultimate guarantors of a constitution and of any nation, is not something
    a government can ignore easily. Our constitution stipulates “the armed forces shall
    protect the sovereignty of the country” so the government had to take action as part
    of fulfilling its basic constitutional duty, which was regrettably not welcomed by
    some in the international community.
    According to a report by Foreign Policy magazine, in a confidential memo to the
    UN secretary-general, Achim Steiner, Head of the UNDP, wrote that the TPLF’s
    attack would have been “an act of war everywhere in the world, and one that
    typically triggers military response in defense of any nation”. This happened in
    Ethiopia and no one appeared to care about this high crime.
    Days after the Ethiopian government started the law enforcement operation in the
    Tigray region, a TPLF-orchestrated massacre took place in Mai Kadra, which
    claimed the lives of more than 600 Amhara  civilians. Yet, the international
    community largely ignored it and few dared to condemn it. There was silence also
    when Sudanese troops violated Ethiopia’s sovereignty and territorial integrity in
    November 2020. It appears it has become easy these days to table one-sided
    motions at international organizations, mainly at the UN Security Council (UNSC),
    before exhausting all available local mechanisms and platforms for resolving such
    issues. The recent open debate at the UNSC on Ethiopia’s internal affairs typifies
    the lesser attention given to the principle of subsidiarity and exhaustion of local
    remedies as customary international law and established trend in the modus
    operandi of the Security Council.
    Not only this, but the UNSC also discussed the Grand Ethiopian Renaissance Dam
    – a hydroelectric dam that aims to change the lives of tens of millions of poverty-
    stricken Ethiopians who lack basic access to food and millions more living under
    Safety Net programs (including 1.8 million Tigrayans  long before the current
    situation.
    However, thanks to the Ethiopian government’s robust diplomatic efforts and the
    support of some principled partners, the African Union (AU) has stepped in to
    facilitate trilateral negotiations on the dam.
    The international community’s support for the humanitarian situation in Tigray far
    from matches its incessant condemnation. It even fails to acknowledge the
    government’s stepped-up humanitarian response that has reached more than 4.2
    million people to date despite limited resources.
    David Beasley, head of the World Food  Programme  (WFP), has called for scaled-
    up humanitarian support to Tigray, amounting to $107m. However, the
    international community and the UN have not made adequate support. In fact, as
    the UNDP memo points out, their confrontational approach “is likely to be
    counter-productive and will yield no results”.
    Access to the Tigray region has been adequately provided to both international
    humanitarian agencies and the media. Yet some in the international community are
    still calling on the government for unfettered humanitarian access.
    The Ethiopian government has strongly expressed its full commitment to undertake
    an in-depth investigation to get to the bottom of the allegations and bring those
    responsible for any crime to justice. It has also called for a constructive
    engagement from the international community to support its investigation. The
    government welcomes the recent understanding between the National Human
    Rights Commission and the UN Human Rights chief to conduct joint
    investigations. But it appears some actors are still adopting double standards in
    their public opinions on the situation in Ethiopia.
    By contrast, the AU has been quite responsive. The AU Commission heeded Prime
    Minister Abiy’s call to undertake an investigation jointly with the Ethiopian
    Human Rights Commission. This instance shows that our future undeniably lies in
    the “African solutions to African problems” maxim.
    Although the international community is failing it by the day, Ethiopia will neither
    lose trust nor revert in its commitment to global values. As former Ethiopian
    Foreign Minister Gedu Andargachew once said: “Despite its painful experience
    during its membership in the League of Nations, Ethiopia has never lost confidence
    in multilateralism.”
    Therefore, if multilateralism is alive, the international community should provide
    significant support to Ethiopia, whose commitment to this principle has not
    wavered. International actors that consider democracy, peace and security, and
    development as crucial tools of the global order, should in principle be ready for
    constructive engagement and providing much-needed assistance to Ethiopia – a
    country of more than 110 million people in one of the most geopolitically sensitive
    regions of the world.
    Yet, we would be remiss not to commend the most principled positions of some of
    our trusted partners during this critical time.
     (Samia Zekaria Gutu is Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary of the Federal
    Democratic Republic of Ethiopia to the State of Qatar)


    ለ27 ዓመታት ያህል ገዢ ኃይል ሆኖ አገሪቷን በተለያየ  መንገድ ጠፍኖ ይዞ የነበረው ህውሐት/ኢህአዴግ፣ እስከ ቅርብ ወራት ድረስ፣ “የትግራይ ክልልን በሕግና በስልጣን የምወክል ፓርቲ ነኝ፤” ይል ነበር። አሁን በተግባር እንደታየውም ፍጻሜያቸው አላማረም። የትግራይ ሕዝብ በሙሉ በምቾት በተድላ፣ በፍሥሐ ፣ የሚኖር አድርጎ የሚቆጥር የህብረተሰብ ክፍል ቀላል አይደለም። ጀነራል ሳሞራ የኑስን የመሳሰሉ የህወሓት ታጋዮች፤ ለፖለቲካ ትርፋቸው ሲሉ፣ “ህወሓት ማለት የትግራይ ሕዝብ ነው፤ የትግራይ ሕዝብም ሕወሓት ነው። ሁለቱም የማይነጣጠሉ ናቸው፤” በሚል፣ህወሓትንና የትግራይ ሕዝብን በአንድ ላይ  በመግመድ፣ በዐደባባይ ደጋግመው ሲገልጹ ተስማምተዋል። ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት (ዓረና) እና የትግራይ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ትዴፓ)፣ እንዲሁም ሌሎች በክልሉና ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ ተወላጆች፣ ህውሓት እና የትግራይ ህዝብ የተለያዩ መሆናቸውን ደጋግመው ለማስረዳት ይጥራሉ። ሁለቱን ነጥሎ ማየት እንደሚገባ ያስረዳል። የህወሓት ነባር አመራሮችም፣ ህውሓት እና መላው የትግራይ ሕዝብ በሙሉ አንድ አለመሆናቸወን፣ አዘውትረው በግልጽ ባይናገሩም፣ በልባቸው እውነቱ እንደማይጠፋቸው መገመት ይቻላል።
ህውሓታውያን (ሁሉም ላይሆኑ ይችላሉ)፣ እንደ አይን ብሌን የሚሳሱለትና በንቃት የሚጠብቁትን ስልጣናቸውን አስጠብቀው ለማስቀጠል፣ የብሔር ቅራኔንና ከፋፋይ ፖለቲካን እንደ ዋነና መሳሪያ አድርገው ላለፉት 29 ዓመታት ተጠቅመውበታል። ለዚህ የፖለቲካ ጨዋታም ፣ በትግራይ  ሕዝብ ስም መነገድ ሁነኛ ስልታቸው ነው። በትግራይ ሕዝብ ስም ካልተጠለሉ በስተቀር ፣ ድብቅና ግልጽ ዓላማቸውን ማስፈጸም እንደማይችሉ ያውቁታል።
ይህን መሰሪ ሐሳባቸውን ጠንቅቀው የተረዱ የትግራይ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ የተባሉትን ሁሉ እንደ ፈጣሪ ቃል አምነው የተቀበሉና የቀድሞ አገዛዝን የሚደግፉ መኖራቸው አይዘነጋም። በብዙ አገራዊ ችግሮች ዝምታን ከመረጡቱ መካከል፣ ሁሉም ባይባሉም የዚህ ማሳያዎች መኖራቸው አይጠረጠርም።
በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ውጥንቅጡ በወጣው ብሔርተኝነት ሳቢያ፣ ችግሩ ስር ሰድዶ መራራ ፍሬው እየታጨደ በመሆኑ ፣ የጎሳው መተላለቅ ጨርሶ ከቁጥጥር ውጪ ከመሆኑ በፊት ፣ በሐቅ ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በርጋታ ማሰብን ይጠይቃል።
ልዩነት በአንድነት
ማንነት ተኮር ግጭትና ጥቃት በልዩ ልዩ ጊዜያት እየተቀሰቀሰና እየተስፋፋ፣ የዜጎቻችንን ሕይወት እየቀጠፈ ነው፤ ቤት ንብረታቸውን እያወደመ ከመኖሪያ ቀዬያቸው እያፈናቀለ ፣ ለተለያየ አካላዊ ጉዳትና ስነ-ልቡናዊ ቀውስ እየዳረጋቸውም ይገኛል። ለችግሩ ሁነኛ እልባት መሻት ግዴታችን ነው። የጉልበቱን መንገድ ትተን፣ በሐሳቦቻችን ፍጭት ብርሃን የጋራ የሆነ ቤታችንን እንገንባ፤ በሀሳብ ባንስማማም እንኳን፣ ልዩነታችን በአንድነታችን ማዕቀፍ ውስጥ እንዲከበር እንግባባ። ከአንድ ማህጸን የወጡ መንትዮች ሳይቀሩ የአስተሳሰብ ልዩነት አላቸው። እንዲህ ከሆነ ዘንድ ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች ባሉባት አገራችን የተለያየ የአስተሳሰብና እምነት መኖሩ የማይቀር ሀቅ ነው። እነኚህ ልዩነቶች ሕብር እስካላቸው ድረስ ፣ በየፊናቸው ለአገር ግንባታ የሚኖራቸው ጠቀሜታ የላቀ ይሆናል። ለዚህም ሐሳብን በሐሳ ነጥሎ ማስረዳት ፣ መወያየት፣ መከራከርና መሟገት ፣ ሁሉንም አመለካከት ለማስተናገድ የሚያስችል ምህዳር መፍጠር አስፈላጊ ነው። የተለየ አመለካከት ለአደባባይ ሲቀርብ “ለምን ተነሳ፣ ለምን ቀረበ?” ብሎ በእልክ መንቀጥቀጥ መሳደብና በሃይል እርምጃዎች ማፈን፣ ትክክለኛና ዘለቄታዊ መፍትሔ የሚያመጣ አይደለም።
ሁለቱ መንገዶች
የብሔር   ወገንተኝነት፣ ሁለት የተለያዩ የተግባር ምላሾችን አነቃቅቷል። አንደኛው በዚያው የብሄርተኝነት አሳቤና አደረጃጀት፣ ሌላውም ብሔርተኛ ተደራጅቶ እንዲታገል ማነሳሳቱ ሲሆን ፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ ሰፋ ባለ ህብረ ብሔራዊ አገራዊ አደረጃጀት ቅርጽ ተደራጅቶ መታገል ነው።
የመጀመሪያው አማራጭ መንገድ፣ ለአገር ሰላምና ለሕዝብ አንድነት ትርጉም ያለው ለውጥ አላመጣም። በተጨባጭ ሲታይ፣ አንዱን የብሔር ፖለቲከኛ ስብስብን (ብሔሩን ሕዝብ በሙሉ የማይወክል) በሌላ መተካት ሆኗል። ይህ ደግሞ አገርንና ሕዝብን በተመሳሳይ የጨቋኝ አዙሪት ውስጥ በማቆየት መበደል ይሆናል። “ተጨቁኗል” ብሎ የታገለለት ብሔር ልዩ ጥቅምና የበላይነት እንዳገኘ በማስመሰል ፤ ጨቁኖኛል ያለውንና ሌሎች ጭቁን የሆኑ ብሔሮችን በአንድነት ጨፍልቆ ወደ መጨቆን ያመራል። ብሔሬ ያለውን ከፍ ለማድረግ መንቀሳቀሱ ተገማች ነው። ሌላውን ሳይበድ እና ሳይጋፋ የራሱን ከፍ ለማድረግ አይችልም። ለፖለቲካ ትክክለኝነት ሲል፣ በቃል ባይገልጸውም በገቢር ግን ይከውነዋል። ሌላኛውም የህብረ ብሔራዊና አንድት አማራጭ የተሞከረበት መንገድ ፣ ከውድቀት አልታደግንም። ሶስተኛ አማራጭ መፈለግ ሳያሻን አይቀርም።
ብዝሃን ቋንቋና ማንነት ባለበት አገር፣ ዜጎች እኩልነት በተግባር መረጋገጥ ካልቻሉ፣ ኢ-እኩልነት መስፈኑ በገሃድ የሚታይ እውነታ ይሆናል። አንዲት ሉአላዊት አገር መጠንከር፣ ማደግና መበልጸግ የምትችለው፣ በዜጎቿ መካከል በተግባር የተረጋገጠ እኩልነት ሲኖር ነው። በትላንቷና በዛሬዋ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በወረቀት ላይ በደማቅ ቀለማት ተጽፎ የሚነበበው የዜጎች እኩልነት ጉዳይ፣ አማካይ ሜዳ ተፈልጎለት የተግባር እውነታና ልምምድ ሆኖ መታየት ይኖርበታል።
(ከጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና “የአገዛዞች ቀይ መስመር” የተቀነበበ)

Saturday, 27 March 2021 14:04

የግጥም ጥግ

  ምስኪን ሀበሻ፡— አሜን አንድዬ፣ አሜን!
ደህና ሰንብቱልኝማ! የእብዶች ረሀብ

ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የብርሃን ጭላንጭል ሕዝብ በድንገት ሲያይ
ጨለማውን ለምዶ በእንግዳው ብርሃን ተጨንቆ ሲወያይ
‹ውቃቢ› የሚገፋ ይሆናል ዋና ከልካይ ‹አይሆንም ! ይቅር!› ባይ፤
አዲስ ህልም የሚሸሽ ወትሮም ይቸኩላል አጉል ስም ማውጣት ላይ
 . . .
እውቀት የራበችው ዘርዐ ያዕቆብ ለኢትዮጵያ ውብ እብድ ነበረ፤
ያንቀላፋች መንፈስ ተነስታ እንድትቆም በ‹‹እንዴት?›› የቆፈረ፡፡

ዛሬ ልንኮራበት ያኔ ህዝበ ሮሀ የጉድ ዜና አወጀ፤ዠ
ኪነ-ህንፃ እርቦት ንጉስ ድንጋይ ሊወቅር ስለተዘጋጀ፤
‹‹አለቱን ፈልፍለን ቤተ መቅደስ እና´ርገው ኑ እንነሳ›› ባለ
‹‹ቅዱስ ላልይበላል እኩይ ሀሳብ ያዘ - አበደ!›› ተባለ::
           .    .    .
ሩቅ ዘመንም ሳንሄድ እዚህ ሩብ እልፍ አመት የሆነው ቢጠየቅ. . .
ጦቢያ ተከፋፍሎ  በየጎጥ ተቧድኖ  ሹመት ሲነጣጠቅ፤
ኢትዮጵያን ሊያጸና በአንድነት ሊያቆማት ሲነሳ አባ ታጠቅ፤ዠ
ጠላትን ሊመክት ቴክኖሎጂ ጠምቶት ሴባስቶፖል ሊሰራ፤ዠ
መዶሻ ጨብጦ ጋፋት ውሎ ቢያድር ከቀጥቃጮች ጋራ
ጠይባን ማፍቀሩ የጤና እንዳልሆነ
የአጤ ቴዎድሮስ ነገር ‹‹ማበዱ!›› ተወራ፡፡
.   .   .
ሰላሙ ባልጠራ ውጥንቅጥ እንቅጥቅጥ
አንቀጥቅጥ ዙፋኑ ላፍታ ነግሶ የቆየው፤
ዮሐንስ ብርቱ ባዝኗል
ከአሸንክታብ ፡ ድሪ ማተቡ የፀናን
ክቡር ያገር  ወሰን እንደ እብድ የተራበው፡፡
የፀሐይ ገበታን ትዕምርት ማህተም
በአናቱ ተነቅሶሺህ አመታት የቆየው፤
አለት ያንሳፈፉ እንደ ኑግ ለጥልጠው በእብነ አድማስ የሰፉ
ያያት ቅድማያቶቹ ጥበብ አምድ ሳለው፤
የእጹብ ድንቅ ኪን ፀጋ ቱሩፋት ጌጥ ሀውልት
አክሱም ፊቱ ቆሞዞር ብሎ እንዳይቃኘው፤
የውስጥ ትርምሱየሹመት ሁካታው
ሌቱ ያልተገታ የባእዳን ትንኮሳው ከብቦ ሲያሰቃየው
ፊት ፊቱን ሲያማትር የአገር ድንበር ጥሙ እብደቱ ሲያተከነው ፤
የአዕላፍ ጠይባን ቅርሱን
የምድሩን አንጥረኛ የጥበብ ክህሎት
አንገቱን አዙሮ ቀና ብሎ ሳያየው፤
ዋ! ያ ጀግና ቀረ የጦር ዘመን እጣው
ከክቡር አካሉ አንገቱን ቢለየው ፡፡
.ምኒልክ ተነቅፏል ለእድገት የሚበጁ
የጦቢያን ባለ እጆች መርጦ በማክበሩ፤
ስልጣኔ ተርቦ
ስልክና መኪና ወፍጮና ሲኒማ ሲያስመጣ ላገሩ
ዘመኑን ነቃፊ  ሕዝቡን አወገዙ
‹‹ሰይጣን ሥራ መጣ ! ይኼ እብደት ነው!!›› አሉ፡፡. ..

አዲስ ህልም የሚያልም በዘመኑ እብድ ነው
የህልሙ ፍቺ ሰምሮ በእውን እስከሚያየው፤
ያም ባይሆን እስኪሞት ህልሙን ነው እሚኖረው ፡፡
ስለ ረቂቅ ውበት
ከጊዜያቸው ቀድመው ‹‹እብዶች›› የተባሉ
ዘመናት ተሻግረው
በህያው ግብራቸው ገዝፈው ዛሬም አሉ፤
ያገር አድባር ሆነው
የወል ትውልድን ተስፋ እያቀጣጠሉ፡፡

እዛሬም ላይ ሆነን የምንደመመው፤
‹‹ጉድ›› ተብዬዎቹ
አኑረው ባለፉት ዘመን ተሻጋሪ የ‹‹እብደት  ራዕይ›› ነው፡፡

እኛም...
ብርሃን እየናፈቅን ቆመን እየቃዠን በጨለማ የኖርነው፤
ውብ አለም መድረሻ መንገድ የሚያሳዩን እቡዶች ተርበን ነው፡፡

ሀምሌ 2003 ዓ.ም።
የፀሐይ ገበታ

Monday, 29 March 2021 00:00

አብረን እንስከን - 2

ያ! ታላቁ ባለቅኔ ሎሬቱ. . .
ያገር አድባር-የህዝብ ዋርካው «እ…!» እያለ፤
ስለጥበብ፥ ስለ ህዝበ-ዓለም እድሜ ልኩን እንደተብሰለሰለ
ቢቸግረው ”አብረን ዝም እንበል” እንዳለ፤
ከነቁጭቱ - ከነህልሙ እንደዋዛ ከንበል አለ፡፡
ግርምቴ . . .
ተፈጥሮ በነጠላና በህብር በፈጣሪ ጥበብ መዋቀሩን ላስተዋለ
የተነጣጠለ፥ የተቃረነ ቢመስልም
በፈጣሪና በተፈጥሮ ህግጋት ነው’ኮ ተገማምዶ፥ተሳስቦ  በአብሮነት የተሳለ፡፡
የሰው ልጅ ግና…!
«በህግ አምላክ!  . . .   በህገ መንግስት!” »  እየተባባለ
ቁርጥራጭ ብረታ ብረት እየሳለ፤
በሆነ ባልሆነው እርስ በርሱ አንገት ለአንገት ሲቀላላ ስለምን በከንቱ ዋለ?
የኛ ጉዶች፡-
በምላስና-ጠመንጃ እየተቋሰሉ¡
በዛቻ-በፉከራ ተጋግለው ሲገዳደሉ እየዋሉ
በየቤተ-ሃይማኖታቱ ደጃፎች ራሳቸውን ብፁዕ ለማስመሰል እየታገሉ፣
በየሸንጐው -በየፓርላማው እጃቸውን ሰቅለው <ፍትሐዊነት¡ እኩልነት¡> እየተባባሉ፤
በዕውንም ሆነ በህልማቸው ግን
 ለበቀል ለየጣዖታቱ-ለየአድባራቱ ሳይቀር ስለምን ስለት ተሳሳሉ፤
ስንት ሰውስ ሲሰዋ ይበቃ ይሆን? ዕርቅ ለማውረድ-ለአብሮነቱ ተባባሉ፡፡
ጡንቻ ለጡንቻ ተገጫጭተን
ትከሻ ለትከሻ ተለካክተን
በቃላት ድምቀት፥ በዲስኩር ብልጫ ተወናብደን
በባህል፥ በታሪከ ትርክት ተቀራርነን
ከእስራቱ-ግርፋቱ፥ ከደም አዙሪቱ መውጣት ቢያቅተን   
ምነው ለህዝቡ እፎይታ ብንሰክን አብረን።
ወገኖቼ . . .     
በማናውቀው፥ በማያስማማን ሚዛን ተመዛዝነን
በቃላት ጋጋታ በህግ መሰል አንቀጻት ተደናቁረን
መደማመጥ መግባባት ካልቻልን
እባካችሁ ህዝብ አናጫርስ፥ አገር አናፍርስ በደመ-ነብስ ተደናብረን፡፡
ከአልቦ በታች ቁልቁል እንዳይሆን ነጋ’ችን፤
ምናለ  ብንሰክን አብረን    
ህዝብና አገርን ለማዳን ብለን፡፡
ቃል-እምነት-መሀላ በስጋ ተበልጦ ቁልቁል ከምንወድቅ
በምድር በሰደድ፥በሰማይ በሲዖል እሳት ከምንነድ
አይሻልም እንዴ ወገኔ?
አብረን ሰክነን በአገራችን ፍቅርና ሰላምን ብናጸድቅ፡፡
ሁሉም በየጐራው እኔ ነኝ መነሻው፥ አቅኚው ካለ
ያም ይህም እርስ በርሱ ተጧጡዞ ያለልኬት «ገፋኝ-ጨቆንከኝ»  ከተባባለ
በጥላቻ . . . በንቀት አገር ምድሩ ከተበከለ
የሥነ- ሂሊና ሚዛኑ ከተከነበለ
ከዚህ በላይ ውድቀት- ድቀት- ሞትማ የታለ፡፡
ወገኖቼ . . .
ይሻል ይሆናል-ካልን እስቲ በጋራ እንሂድ
ወደ የ…ክልሎቹ አብረን  እንንጐድ…
ህገ መንግስት «ይቀደድ!...አይቀደድ!» ብለን፥ቸኩለን ሳንፈርድ
እባካችሁ! በቅድሚያ፥ የህዝባችንን ዕንባ፥ አብረን እናድርቅ፡፡
ከድምጽ ማጉያና ከእጅ መዳፍ ጭብጨባ እንገለል፡፡
ለአንድ አፍታ እንኳን-ከየአደባባዮቹና  ከየአዳራሾቹ እንነጠል፡፡
እንደጥንቱ በዛፎች ጥላ ስር እንጠለል፡፡
በጋራ ሆነን በየወጋችን-በየባህላችን  አብረን «ሰላም-እርቅ» እንበል፡፡
ከአባይ ማዶ ወደ ቤንሻንጉል-ጉሙዝ ወደ ህዳሴው ግድብ አብረን እንውረድ
እጅ ለእጅ ተያይዘን በፋሲል ግንብ . . .በጣና ዙሪያ እስክስታ እናውርድ፡፡
አብረን እንሂድ ጋምቤላ ከለማለሙ አገር
በባሮ ወንዝ ላይ በፍቅር መርከብ አብረን እንሸርሸር፡፡
ላሊበላ ሂደን «እግዚኦ ማረን» እንበል
የፈጣሪን ቡራኬ መለኮቱን እንቀበል፡፡
ወደጥንታዊቷ አክሱም እንዝለቅ …
ከአዴታቱ እጅ ተቋድሰን አንባሻውን
በበረከቱ እንፈወስ እርስ በእርስ ተመራርቀን፡፡
«ሆ!ያ ማሬዎ! -ማሬዎ!» አብረን እያልን
ቢሾፍቱ-ሆራ አርሰዲ ለእሬቻ እንውረድ
ሀባቦ-መርጋ ጉራቻ … እርቁን በእጃችን ጨብጠን፡፡
ወደ አርባ ምንጭ እንዝለቅ …  
ለህዝብ ክብር፥ ለወገን ፍቅር ብለን፥ ከኒያ ደጋግ ህዝቦች ጋር ሆነን
እርጥብ ሳር ይዘን፥ በመሬት ላይ  እንውደቅ አብረን፡፡
ወደ ቦረና ከአንጋፋዎቹ መገኛ አብረን እንዝለቅ
የገዳ-ዲሞክራሲ ችግኙ በሁሉም ሥፍራ እንዲጸድቅ፤
በአንደበተ ርቱዓኑ፥ በንፁሀኑ አባገዳዎቹ  እንመረቅ፡፡
ወደ ጅማ -ወደ ከፋ ሽምጥ እንጋልብ
ከቡና ረከቦት ዙሪያ እንሰብሰብ!
«አቦል ጀባ!» እየተባባልን እንዋዋብ፡፡
ሐረር ጀጐል፥ ደገሃቡር ሶማሌ፥ ድሬ ሼህ ሁሴን አብረን እንዝለቅ
«አስቶፍሩላህ!...አላሁ አክበር! »  ብለን ከፈጣሪያችን እንታረቅ፡፡
ግርምቴ . . .
እንሂድ አፋር፥ ከቅድመ ዘራችን ከእናታችን ሉሲ አገር
እንድትተርክልን በእሳተ ገሞራ የመኖርን ሚስጥር
ለሚሊዮን አመታት አጽሟ ሳይፈራርስ የመዝለቁን ቀመር፡፡
እኛው በየአምስት አመቱ «ውረድ!...አልወርድም!»  ከምንባባልበት
ለ4 ኪሎው ወንበር ከምንዶልት፥ ከምንፋጅበት
ለህዝባችን፥ ለአገራችን ብለን በቅድሚያ አብረን ብንሰክንለት፡፡
ምናለ ጐበዝ! ለዚህ ምስኪን ህዝብ በቅድሚያ ብናስብለት፤
በሰቀቀን ባይባዝንበት፥ በችጋር- በጠኔ ባይረግፍበት፣፣

ሎሬቱ እንዳለው፡-
« . . . . . . .
ዳግመኛ ሞት ሳንሞት፥ አዲስ ቀን ሳይጨልምብን
ድፍን ደመና ሳይቋጥር፥ክረምት ውርጅት ሳይወርድብን
. . . . . . . ፡፡»
ወገኖቼ . . .
በኮሮና እና በብረት መሃል ተወጥረን
ጦርነቱ ከሚፈጀን፣ በሽታና ረሃቡ ከሚያረግፈን
ምናለ ፉከራው ቀረርቶው ቢቀርብን፡፡
እናም፡-
ለአንድ አፍታ እንኳን «አሐዳዊ!...ፊዴራላዊ» ቃለ ግነቱን ገተን
ህዝባችንን-አገራችንን ብናድን አብረን ሰክነን
ለጊዜው እንኳን ባንስማማም «ሜ. . . ሃቡልቱ ዱቢን » ብለን ተስማምተን፡፡
 አሰፋ ጉያ
መታሰቢያነቱ፡-
የሥነ ጥበብ ፍቅርንና ለህዝብ የመቆርቆርን ቀናኢነት ላወረሰኝ፤
ለጋሽ ለማ፤ የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት፣ ሻምበል ለማ ጉያ ይሁንልኝ፡፡

Page 10 of 529