Administrator

Administrator

 ሕጻናት ከተወለዱ ከስድስት ወር በሁዋላ ተጨማሪ ምግብ እያገኙ እስከ ሁለት አመት እድሜአቸው ድረስ የጡት ወተት መመገብ ሊቋረጥባቸው አይገባም።
 ሕጻናት ሁሉ በትክክል ጡት ወተት ከተመገቡ በየአመቱ በአለም እስከ 800,000 ልጆችን ሕይወት ማዳን ይቻላል።
 በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚወለዱት ሕጻናት ከ40% በታች የሆኑት ሙሉ በሙሉ የጡት ወተት አግኝተዋል ማለት ይቻላል።
 WHO-
       
 ሕጻናት ከተወለዱ ከስድስት ወር በሁዋላ ተጨማሪ ምግብ እያገኙ እስከ ሁለት አመት እድሜአቸው ድረስ የጡት ወተት መመገብ ሊቋረጥባቸው አይገባም።
ሕጻናት ሁሉ በትክክል ጡት ወተት ከተመገቡ በየአመቱ በአለም እስከ 800,000 ልጆችን ሕይወት ማዳን ይቻላል።
በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚወለዱት ሕጻናት ከ40% በታች የሆኑት ሙሉ በሙሉ የጡት ወተት አግኝተዋል ማለት ይቻላል።
 WHO-
    ጡት ማጥባት ከምንም በላይ ለልጆች ጠቃሚ ነው ቢባልም አንዳንድ ጊዜ ግን ልጆች የሚጎዱበት ምክንያት እንደሚያጋጥም ግልጽ ነው። ይኼውም ከጤና አኩዋያ ሲሆን ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።
ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ ከሚተላለፍባቸው መንገዶች አንዱ ጡት የማጥባት ወቅት ነው። ሌላው ሕመም ደግሞ የሳንባ በሽታ ሲሆን በተለይም በወቅቱ ካልታከመ ይህ ለሕጻኑ ጉዳት ለስከትል ይችላል። የካንሰር ሕመም ገጥሞአት ኬሞራፒ የተባለውን ሕክምና የምትከታተል እናት ልጁዋን ጡት በምታጠባበት ወቅት ለልጁዋ ሕመምን ሊያስከትል ይችላል።
ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ እንደ ኮኬይን ፣ማሪዋና፣ሲጋራ ማጨስና መጠጥ አዘውትራ የምት ጠጣ እናት ልጁዋን በምታጠባበት ወቅት ለልጁ ጎጂ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ መድሀኒቶችን ለምሳሌም ማይግሪን ለተሰኘው ከባድ የራስ ሕመም እና ተመሳሳይ የጤና ችግሮች በሐኪም ትእዛዝ የሚወሰዱ መድሀኒቶችም የጡት ወተቱን ጎጂ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ስለዚህ ምንም አይነት የጤና እና የባህርይ ችግር ቢኖር ጡት ለማጥባት መቻል አለመቻልን ከሕክምና ባለሙያ ጋር መምከር ጠቃሚ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ጎጂ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ እንደ ጉንፋን ወይም የብርድ ሕመም የመሳሰሉት ጡት ከማጥባት የሚያግዱ አይደሉም። የጡት ወተት በእራሱ በሽታን የመከላከል አቅም ስላለው ጡት የሚጠባውን ልጅ ከሕመም ሊከላከልለት ይችላል። አንዳንድ የህክምና ጠበብት ሕጻን ከተወለደ ከ4/ወር ጀምሮ አይረንና ቫይታሚን ዲ የተሰኙትን ንጥረነገሮች በሐኪም ትእዛዝ መስጠት ይችላል። ነገር ግን ለሕጻኑም ሆነ ለእናትየው ይህ ድጋፍ ሰጪ ቋበቅቅቁስቂስቃቋ ከመቼ ጀምሮ እና ምን ያህል መወሰድ እንዳለበት ሐኪምን ማነጋገር ያስፈልጋል።
እናቶች ልጆቻቸውን ለምን ጡት ማጥባት አይፈልጉም?
አንዳንድ እናቶች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ልጆቻቸውን ሲያጠቡ መታየት አይፈልጉም። ምናልባትም የሁዋላቀርነት ምልክት አድርገው ሊወስዱት ይችላሉ።አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የልጁ አባት ወይንም በቤት ውስጥ ልጁን የሚንከባከቡ ቤተሰቦች ጡጦ በማዘጋጀት ሊሰጡት ስለሚ ችሉ ልጁ ተጎጂ አይደለም...እንዲያውም ተጠቃሚ ነው ብለው የሚያስቡ ይኖራሉ። ከዚህ በተጨማሪም ልጆች ከጡት ወተት ይልቅ የተዘጋጀ ወተትን በቀስታ ይመገባሉ። የጡት ወተት ግን በተደጋጋሚ ሊወስዱት የሚችሉት ቀለል ያለ ምግብ ስለሆነ ምናልባትም የሚጠግቡት በተዘጋጀው ወተት ስለሆነ በእርጋታ ይመገባሉ የሚል እሳቤ የሚኖራቸው እናቶች ይኖራሉ።ይህ ግን ተክክል ስላልሆነ የወለዱትን ልጅ ጡት በተገቢው መንገድ ማትባት ጠቃሚነት አለው።
ጡት ለማጥባት አስቸጋሪ ሁኔታዎች
የጡት ጫፍ መቁሰል
ልጅ እንደተወለደ በመጀመሪያው ሳምንት የጡት ጫፍ መቁሰል እንደሚኖር አስቀድሞ ማወቅ ብልህነት ነው። ልጁ በትክክል ጡት መያዙን ማረጋገጥ እና ሲጨርስም ጡቱን ከአፉ ከመጎተት ይልቅ አንድ ጣትን ወደልጁ አፍ በመክተት ጡቱን ከአፉ ለማውጣት በቂ ክፍተት መፍጠር ይጠቅማል።ቁስለቱ ቶሎ የማይድን ከሆነ ጡት ባጠቡ ቁጥር ወተቱን ጨርሶ እንዲጠባ እና ጡቱ እንዳያግት ማድረግ ይጠቅማል። ይህ ካልሆነ ግን ጡቱ በወተት ይሞላል ፣ያብጣል ፣ ሰለሆነም ሕመም ይኖረዋል። ልጅ ከጠባ በሁዋላ ድጋሚ እስኪሰጠው ባለው ጊዜ ጡቱ ደረቅ እንዲሆን ማድረግ ይጠቅማል። ልጁ ደጋግሞ በጠባ ቁጥር በጡት ጫፍ ላይ ያለው ቁስለት እየቀነሰ እንዲያውም እየዳነ ይሄዳል። ስለዚህ የጡት ጫፍ ቆሰለ ተብሎ ልጁ ጡት ከመጥባት መታገድ የለበትም።
ደረቅና የተሰነጣጠቀ የጡት ጫፍ
የጡት ጫፍን ለማጽዳት የሚጠቀሙበት ሳሙና ወይንም የሽቶ መአዛ ያላቸው ቅባቶች እና ሎሽኖች በውስጣቸው አልኮል ስላላቸው ማስወገድ ተገቢ ነው። ከጡት ማጥባት በሁዋላ ንጹህ የሆኑ ጠረን የሌላቸው ቅባቶችን መጠቀም ይጠቅማል። ቅባት ከተቀቡ በሁዋላ ጡት መልሶ ለማጥባት የተቀባውን ቅባት በደንብ ማጠብና ማስወገድ ያስፈልጋል። የጡት መያዣዎ ከጥጥ የተሰራ እንዲሆን ይመከራል።
በቂ የጡት ወተት የለኝም ብሎ መጨነቅ
አንድ ልጅ በቀን በበቂ ሁኔታ ጡት ጠብቶአል ወይንም ተመግቦአል የሚባለው በቀን ከ6 እስከ 8 ዲያፐር ሲቀይር ነው። አንድ ልጅ እስከ 6 ወር ድረስ ካለምንም ተጨመቀሪ ምግብ የጡት ወተት መጥባት አለበት። የእናትየው ሰውነት የልጁን ጡት መጥባት ፍላጎት በየተወሰነው ሰአት ስለሚረዳ ማለትም ጡቱ ወተት ስለሚሞላ ቸል ባለማለት በተገቢው ማጥባት ይገባል። ጡት በተሳበ ቁጥር ወተቱም መመረቱ ይቀጥላል። አንዳንድ ሴቶች ጡታ ቸው በተፈጥሮው ትንሽ ስለሆነ ወተት የለኝም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን የጡት መጠን መተ ለቅ ወይንም ማነስ ወተትን በማምረት በኩል ምንም ልዩነት የለውም። እናቶች ባቅማቸው ጥሩ መመገብ ፣ተገቢ የሆነ እረፍት ማድረግ እና ጡታቸውን በተገቢው እያጸዱ ማድረቅ ልጃቸውን ለማጥባት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል።
ጡትን ማለብና ወተቱን ማስቀመጥ
ጡቱን በእጅ በመጭመቅ ወይንም በማለቢያ በማለብ የጡት ወተት እንዲገኝ ያስችላል። በተ ለይም እናቶች በቶሎ ወደስራ የሚሄዱ ከሆነ የታለበ የጡት ወተት ማግኘት ስላለባቸው በእቃ መመገቡን አስቀድሞ ማለማመድ ያስፈልጋል። የጡት ወተት ከታለበ በሁዋላ እስከሁለት ቀን ድረስ በማቀዝቀዣ ውስጥ በማስቀመጥ መጠቀም ይችላል። የቀዘቀዘውን የጡት ወተት በማይ ክሮዌቭ ማሞቅ ግን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ሊያሳጣ ስለሚችል አይመከርም። የታለበውን የጡት ወተት ለልጁ መስጠት ሲያስፈለግ ከማቀዘቀዣ ውስጥ በማውጣት ትንሽ ማቆየት ወይ ንም የሞቀ ውሀ በሳህን ውስጥ አድርጎ ወተቱን የያዘውን እቃ በሳህኑ ውስጥ ማስቀመጥ ያስፈልጋል።
ጡት በወተት መሞላት
ጡት በወተት ሊሞላ ወይንም ሊወጠር ይችላል። ጡቱ በወተት መሞላቱ ትክክለኛና ተፈጥሮ አዊ ነው። ነገር ግን በጡት ላይ ያሉት የደም ስሮች ሊወጣጠሩና ሊጨናነቁ ይችላሉ።በዚህ ጊዜ ጡት ጠጣር ይሆናል። እንዲሁም በመወጣጠሩ ሕመም ይሰማል። በዚህ ጊዜ በበረዶ በቀዝቃ ዛው ወይንም ሙቅ ሻወር በመውሰድ እንዲላላ ማድረግ ይቻላል።
የጡት ወተት የሚፈስበት መስመሮች
መጠጠር ወይም መታመም
በጡት ውጫዊ አካል ላይ የሚታዩ ቀያይ ወይንም ትኩሳት ያላቸው ነጠብጣቦች የጡት ወተት መፍሰሻው መታመሙን ሊያመላክቱ ይችላሉ። ይህንን አካባቢ በጥንቃቄ መዳሰስ ወይንም ሙቀት እንዲሰማ ጨመቅ ጨመቅ በማድረግ እንዲላላ እና እንዲፍታታ በማድረግ የጠጠረ ውን ነገር እንዲወገድ ማድረግ ይቻላል።
የጡት ኢንፌክሽን
የጡት ኢንፌክሽን ወይንም መመረዝ የሚገጥመው የተሰነጣጠቀው ጡት ከልጁ አፍ ከወጣ በሁዋላ በባክሪያ ሲያዝ ነው።ጡት የመመረዝ ባህርይ ሲያሳይ ትኩሳትና መሰል ስሜቶች ከተስተዋሉ ሐኪምን ማማከር ያስፈልጋል።
ጭንቀት
አንዲት እናት ጭንቀት ካለባት የጡት ወተትዋ ፍሰቱን ሊቀንስ ይችላል። ሰውነት በተፈጥሮው ያመረተውን ወተት ጭንቀት ቢያግደውም ልጁ መጥባት ሲፈልግና እናትየው የልጅዋን ጡት መፈለግ ስታይ ግን ከጭንቀት ስለምትላቀቅ ያን ጊዜ ወተት እንደልብ መፍሰስ ይጀምራል። ስለዚህ የምታጠባ እናት በተቻለ መጠን ዘና ማለት እና መደሰት እንጂ መጨነቅ የለባትም።
እድገቱ ያልተሟላ ሕጻን
አንድ ሕጻን ካለቀኑ ከተወለደና አቅም ከሌለው ጡት መሳብ ሊያቅተው ይችላል። በዚህ ጊዜ የጡት ወተቱን በማለብ በጡጦ ለልጁ ማጠጣት ይገባል።
ባጠቃላይም የተወለደ ልጅን የጡት ወተት መመገብ ተፈጥሮአዊና ጤናማ ተግባር ነው። ነገር ግን ከሐኪም ጋር መመካከር የሚያስፈልግበት አጋጣሚ እንደሚኖር መዘንጋት የለበትም።
ጡት ባልተለመደ ሁኔታ የመቅላት የመቁሰል የመጠንከር እና የመሳሰሉትን ምልክት ካሳየ
ከጡት ውስጥ በጫፉ በኩል ፈሳሽ ወይንም ደም የሚወጣ ከሆነ
ሕጻኑ ክብደቱ እየቀነሰ የሚሄድ ከሆነ ሳይውሉ ሳይድሩ ከሐኪም ጋር መመካከር ያስፈልጋል።  
ምንጭ፡- WebMD, LLC

የኢራን መከላከያ ሚ/ር፤ አለም በትራምፕ አገዛዝ ወደ ጦርነት ልትገባ ትችላለች አሉ
     ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባለፈው ሰኔ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ፕሮግራም ላይ፣ የአንድን ፖሊስ ጠመንጃ በመንጠቅ ትራምፕን ለመግደል ሞክሯል የተባለው እንግሊዛዊ ወጣት የአንድ አመት እስራት እንደተፈረደበት ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡
ማይክል ሳንፎርድ የተባለው የ20 አመት ወጣት፣ ለመርማሪዎች በሰጠው ቃል፤ የሪፐብሊካኑን ዕጩ ዶናልድ ትራምፕን ተኩሶ ለመግደል በማሰብ፣ ከካሊፎርኒያ በመነሳት በወቅቱ ቅስቀሳ ያደርጉበት ወደነበረው ላስቬጋስ ማምራቱን አምኗል፡፡ ወጣቱ በምርጫ ቅስቀሳው ላይ በጥበቃ ስራ ተሰማርቶ የነበረን ፖሊስ ጠመንጃ በመንጠቅ ትራምፕን ተኩሶ ለመግደል የያዘው ዕቅድ ባይሳካለትም፣ የጦር መሳሪያ በመያዝና ስራን በማስተጓጎል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ፣ በላስቬጋስ የፌዴራል ፍርድ ቤት የ1 አመት እስር እንደተጣለበት ዘገባው ጠቁሟል፡፡ ተከሳሹ ሳንፎርድ የአእምሮ ችግር እንዳለበት በመጥቀስ ጠበቆቹ ለፍርድ ቤቱ ያስገቡት የቅጣት ማቅለያ በምርመራ ተጨባጭ ሆኖ መገኘቱ በመረጋገጡ ቅጣቱን እንዳቀለለለትም ታውቋል፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ፣ የኢራን የመከላከያ ሚኒስትር ሁሴን ዴጋን፣ የትራምፕ ስልጣን መያዝ አለማችንን ወደ ጦርነት ሊያስገባት ፣ እስራኤልንም ለጥፋት ሊዳርጋት ይችላል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡ “ትራምፕ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርቶ የኖረ ሰው ነው፤ አማካሪዎቹና ረዳቶቹ በተለይም በባህረ ሰላጤው አገራት ላይ ቀውስ ወደሚፈጥር እንዲሁም እስራኤልን ወደሚያጠፋና አካባቢውን አተራምሶ፣ አዲስ የአለም ጦርነት ወደሚቀሰቅስ አደገኛ አቅጣጫ ሊመሩት ይችላሉ” ብለዋል- ሚኒስትሩ፡፡

ባለፉት 2 አመታት በሶርያና በኢራቅ 50 ሺህ ያህል የአሸባሪው ቡድን አይሲስ ታጣቂዎች መገደላቸውን አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘገበ፡፡
ባለስልጣኑ የተገደሉትን የአይሲስ ታጣቂዎች በተመለከተ “የተገመተው ቁጥር ይህን ያህል መድረሱ አሜሪካና ጥምር ሃይሉ በአሸባሪው ቡድን ላይ የከፈቱት ዘመቻ ምን ያህል ስኬታማ እንደሆነ ያሳያል” ማለታቸውንም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡
 ከሁለት አመታት በፊት በኢራቅና በሶርያ የሚገኙ የአይሲስ ታጣቂዎች ቁጥር ከ20 እስከ 30 ሺህ እንደሚገመት የአሜሪካ የመረጃ ተቋም መግለጹን ያስታወሰው ዘገባው፤ ወታደራዊ ሃላፊው ተገድለዋል ያሏቸው ታጣቂዎች ቁጥር ከዚህ የሚበልጥ መሆኑን አስረድቷል፡፡ በሌላ በኩል አንድ የኩርድ ከፍተኛ የጦር መሪ፣ የታጣቂዎቹ ቁጥር ወደ 200 ሺህ እንደሚጠጋ  መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡

በመላው ዓለም 259 ጋዜጠኞች በእስር ላይ ይገኛሉ
     በተለያዩ የአለማችን አገራት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቁጥር በተገባደደው የፈረንጆች አመት 2016 ላይ  259 መድረሱን ያስታወቀው ሲፒጄ የተባለው አለማቀፍ የፕሬስ ተሟጋች ቡድን፣ የጋዜጠኞችን እስር በማጥናት ይፋ ማድረግ ከጀመረበት ከ1990 ወዲህ ከፍተኛው በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቁጥር መሆኑንም ገልጧል፡፡
ቁጥሩ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ለመድረሱ ምክንያት የሆነው፣ የቱርክ መንግስት ባለፈው ሃምሌ ወር የተቃጣበትን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከትሎ በጋዜጠኞች ላይ የወሰደው ከፍተኛ የእስር እርምጃ መሆኑን የጠቆመው ቡድኑ፤ በተገባደደው የፈረንጆች አመት ከአለም አገራት በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ቱርክ ቀዳሚነቱን መያዟን ጠቅሶ፣ የአገሪቱ መንግስት በአመቱ ከ81 በላይ ጋዜጠኞችን ወህኒ መወርወሩን አስታውቋል፡፡
በአመቱ ከቱርክ ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች የታሰሩባት ሁለተኛዋ የአለማችን አገር ቻይና መሆኗን የጠቆመው የቡድኑ አመታዊ ሪፖርት፤ በአገሪቱ የታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር 38 መድረሱን አመልክቶ፣ ሶስተኛ ደረጃን በያዘቺው ግብጽ ደግሞ 25 ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ጠቅሷል፡፡ በመላው አለም በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቁጥር ከአንድ አመት በፊት ከነበረው 199 ዘንድሮ ወደ 259 ከፍ ማለቱን ሪፖርቱ ገልጾ፣ በእስር ላይ ከሚገኙት ጋዜጠኞች መካከል ሶስት አራተኛ ያህሉ ጸረ-መንግስት ተግባር ፈጽመዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው መሆናቸውንና ከታሰሩት 259 ጋዜጠኞች መካከል 20 ዎቹ ሴቶች እንደሆኑ ጠቁሟል፡፡
በኤርትራ 17፣ በኢትዮጵያ 16 ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙም ቡድኑ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

ጃሜህ በይፋ ያደነቁትን ምርጫ በይፋ ሲክዱት፣ ፓርቲያቸው ለፍ/ ቤት አቤት ብሏል
     ላለፉት 22 አመታት ጋምቢያን አንቀጥቅጠው የገዙት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ያያ ጃሜህ፣ ከሰሞኑ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያልጠበቁት ዱብ እዳ ይዞባቸው መጣ - በተፎካካሪያቸው አዳማ ባሮው የመሸነፋቸውን መርዶ አስደመጣቸው፡፡
የምርጫው ውጤት ይፋ መደረጉን ተከትሎ፣ ከሁለት አስርት አመታት በላይ በስልጣን ላይ የቆዩት ጃሜህ፤ ስልጣን እንደጣመው አፍሪካዊ መሪነታቸው ውጤቱን አልቀበልም ብለው እምቧ ከረዩ ይላሉ ብለው ብዙዎች ጠብቀው ነበር፡፡ ጃሜህ ግን፣ ባልተጠበቀ መልኩ የምርጫውን ውጤት እንደሚቀበሉ ተናገሩና፣ አገራቸውንም ዓለምንም አስገረሙ፡፡
“ምርጫው ፍትሃዊ ነበር!...” ሲሉም በአደባባይ አወጁ፡፡
በምርጫው በለስ ለቀናቸው ተፎካካሪያቸው ኣዳማ ባሮው ስልክ ደውለው፣ “ቀጣዩ የጋምቢያ መሪ በመሆንህ እንኳን ደስ አለህ!... መልካሙ ሁሉ እንዲገጥምህ እመኝልሃለሁ!... “ ሲሉ የደስታ መግለጫ መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉም፣ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ለህዝብ ታዩ፡፡
የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽንም “ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ነበር” ሲል አስታወቀ፡፡
የኋላ ኋላ ግን...
ጃሜህ ነገሩን በጥሞና አጤኑት፡፡ ለቀናት ደጋግመው አሰቡበት፡፡ ጊዜ ወስደው መላልሰው አሰላሰሉት፡፡
በዚህ መሃል፣ የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን፣ የጃሜህን ተሸናፊነት ባይቀይርም፣ በውጤቱ ላይ መጠነኛ የሆነ ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ጃሜህ ይህን ሲሰሙ፣ አሪፍ ማፋረሻ ሰበብ አገኙ፡፡
“እየቀለዳችሁ ነው እንዴ!?... የምን ምርጫ ነው የምታወሩት!?... የምን ስልጣን መልቀቅ ነው!?...” ሲሉ ከአንድ ሳምንት በፊት በይፋ ያመኑትን ውጤት፣ መልሰው በይፋ ካዱ፡፡ ለ22 አመታት የተቀመጡበትን መንበረ ስልጣን፣ አሳልፈው ለማንም እንደማይሰጡትም፣ በመንግስት ቴሌቪዥን መስኮት ከኮስታራ ፊት ጋር ብቅ ብለው አስታወቁ፡፡የምርጫ ውጤቱ አሸናፊነታቸውን ያወጀላቸው ባሮው በበኩላቸው፤ ጃሜህ ውጤቱን ላይቀበሉ ቢችሉም፣ እንዲሰረዝና ሌላ ምርጫ እንዲካሄድ የመጠየቅ ህገ መንግስታዊ ስልጣንም ተቀባይነትም የላቸውም ሲሉ ተናገሩ፡፡
“ወታደሩም ቢሆን ከጎኔ እንደሚቆም ተስፋ አለኝ!...” ሲሉም ስጋት የወለደው አረፍተ ነገር ጣል አደረጉ፡፡
አለም ወደ ጋምቢያ እያየ በሽሙጥ ሳቀ፡፡
አለም ያሽሟጥ እንጂ፣ ጋምቢያና ህዝቦቿ ግን በውጥረት ተያዙ፡፡ ጃሜህ የምርጫውን ውጤት አልቀበልም ማለታቸውን ተከትሎ፣ በአገሪቱ የፖለቲካ ውጥረት ተከሰተ፡፡ ይህ ውጥረት ያሳሰባቸው የምዕራብ አፍሪካ አገራት መሪዎችም፣ ጃሜህን መክረው ዘክረው የምርጫ ውጤቱን እንዲቀበሉ ለማግባባት ባለፈው ማክሰኞ ወደ ጋምቢያ አቀኑ፡፡
ያም ሆኖ ግን ያሰቡት አልሰመረላቸውም፡፡
“ወይ ፍንክች የአባ ቢለዋ ልጅ!...” አሉ ጃሜህ፡፡
ይባስ ብሎም፣ ጃሜህ የሚመሩት የጋምቢያው ገዢ ፓርቲ ኤፒአርሲ፣ ምርጫው ተዓማኒነት የጎደለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ውጤቱ እንዲሰረዝና ሌላ ምርጫ እንዲካሄድ የሚጠይቅ ማመልከቻ አርቅቆ፣ በዚያው ዕለት ለአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስገባ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ አሜሪካና ሌሎች አገራት እንዲሁም ተቋማት፣ ጃሜህን “እባክዎት ይለመኑን!... ስለ ሰላም ብለው ስልጣንዎትን ይልቀቁ” እያሉ በመማጸን ላይ ናቸው፡፡
“ፕሬዚዳንት ጃሜህ ስልጣናቸውን ለአሸናፊው ባሮው ማስረከብ አለባቸው!” ብሏል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት፣ ባለፈው ሰኞ ባወጣው መግለጫ፡፡ የአፍሪካ ህብረትም የጃሜህን እምቢተኝነት፣ “ተቀባይነት የሌለው” ሲል በይፋ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ጋምቢያ አሁንም ውጥረት ውስጥ ናት፡፡ ዜጎቿ ብጥብጥ ይፈጠራል በሚል ስጋት ተውጠዋል፡፡ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ የአገሪቱ ወታደሮችም፣ ከተሸናፊው ፕሬዚዳንት ያያ ጃሜህ የተላለፈላቸውን ቀጭን ትዕዛዝ በመቀበል፣ የመዲናዋን ባንጁ ጎዳናዎች ወርረው በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ የመንግስቱ ታማኝ ወታደሮችም፣ ባለፈው ማክሰኞ በመዲናዋ የሚገኘውን የምርጫ ኮሚሽ ቢሮ በጥብቅ ዙሪያውን ከብበዋል፡፡
የአገሪቱ ጦር ሰራዊት ለሁለት ይከፈላል፣ አገሪቱም ወደ ከፋ ብጥብጥ ልትገባ ትችላለች የሚለው ስጋት አይሏል፡፡ ዘ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው፣ ጃሜህ መሸነፋቸውን በጸጋ የተቀበሉ ሰሞን የአገሪቱ የጦር ሃይል አዛዥ ኡስማን ባጄ ከተመራጩ ኣዳማ ቦሮ ጋር ተገናኝተው፣ ጦሩ ለእሳቸው እንደሚታመን ቃል ገብተውላቸው ነበር፡፡ የኋላ ኋላ ግን፣ ጃሜህ ቃላቸውን አጥፈው ውጤቱን አልቀበልም ማለታቸውን ተከትሎ፣ የጦር አዛዡ ፊታቸውን ወደ ጃሜህ አዙረው ትዕዛዝ መቀበል መጀመራቸውን አስተዛዛቢና አደገኛ አካሄድ ብሎታል- ዘገባው፡፡ ጃሜህ ስልጣናቸውን ለማስረከብ የቀራቸው ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ ብቻ መሆኑን የጠቆመው ቢቢሲ፤ ገዢው ፓርቲ ምርጫው እንዲሰረዝና ሌላ ምርጫ እንዲካሄድ ለፍርድ ቤት ያቀረበው አቤቱታ በአጭር ጊዜ ምላሽ የማግኘት ዕድሉ ጠባብ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በሁለቱ ሃይሎች መካከል ግጭት ሊያስከትል እንደሚችል ዘግቧል፡፡ የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት ክልላዊ ተቋም ኢኮዋስ ከፍተኛ ባለስልጣንም፣ ጃሜህ ስልጣኔን አለቅቅም በሚለው አቋማቸው የሚጸኑ ከሆነ፣ ተቋሙ የውጭ ወታደራዊ ሃይል የማስገባት እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የሆነው ሆኖ...
የአህጉሩ ትንሷ አገር ጋምቢያ፣ ትልቅ ስጋት ውስጥ ወድቃለች፡፡ የጋምቢያና የህዝቧ መጻእይ ዕጣ ፈንታ፣ አሁንም በ51 አመቱ ጃሜህ እና ጃሜህ እጅ ላይ ነው- ይላል ቢቢሲ፡፡

የታዋቂዋ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል ታናሽ ወንድም  ሻምበል ታደሰ ወ/ገብርኤል፤ በ2001 ዓ.ም ‹‹ቃዘኖ›› በሚል ርዕስ ያሳተመውን ታሪክ ቀመስ ልብ ወለድ ‹‹ባላገር ቃዘኖ›› በሚል ርዕስ ወደ ፊልምነት የቀየረው ሲሆን በዋሴ ሪከርድስ አማካኝነት ለተመልካች ቀርቧል፡፡
ሻምበል ታደሰ ከዚህ ቀደም እህቱ አዳነች ወ/ገብርኤል ታሳትመው በነበረው ‹‹ጠብታ›› መፅሄትና አሜሪካ ይታተም በነበረው ‹‹ሳሎን ኢትዮጵያ›› ጋዜጣ ላይ በምክትል ዋና አዘጋጅነት ይሰራ እንደነበር ታውቋል፡፡
ሻምበል ታደሰ ከዚህ ቀደም ‹‹ሰዓትና ዘመን›› የተሰኘ የግጥም መድበል ለንባብ ያበቃ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በባህል ህክምና ዘርፍ በአምስት ፈጠራዎች የባለቤትነት መብትና ፈቃድ አግኝቶ፣ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Sunday, 18 December 2016 00:00

አስገራሚው እውነታዎች

- ዓሳማ በተፈጥሮው ወደ ሰማይ መመልከት አይችልም።
- የሞቀ ውሃ ከቀዝቃዛ ውሃ የበለጠ ይከብዳል።
- 90 በመቶ አደን የምታከናውነው ሴቷ አንበሳ ናት፡፡
- ልባችን በቀን ከ100 ሺሁ በላይ ይመታል፡፡
- ቀጭኔ ጆሮዎቿን በ21 ኡብች ምላሷ ማፅዳት ትችላለች፡፡
- አይጦችና ፈረሶች ማስመለስ አይችሉም፡፡
- ሩሲያ (እ.ኤ.አ) እስከ 2011 ዓ.ም ቢራን እንደ አልኮል መጠጥ አትቆጥረውም ነበር፡፡ ለስላሳ መጠጦች ምድብ ውስጥ ነበር፡፡
- ከውልደት አንስቶ የዓይናችን መጠን ተመሳሳይ ነው፤ አፍንጫችንና ጆሮአችን ግን ፈፅሞ ማደግ አያቆሙም፡፡
- የስፔይን ብሄራዊ መዝሙር ምንም ቃላት የሉትም፡፡
- በመጀመሪያው ካሜራ ፎቶ ለመነሳት አንድ ሰው ሳይነቃነቅ ለ8 ሰዓት መቀመጥ ነበረበት።
- ፈረንሳይኛ ከ600 ዓመታት በላይ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቋንቋ ነበር፡፡
- የግመል ወተት አይነጋም፡፡
- ሰው ከ10 ቀናት በላይ እንቅልፍ ካጣ ይሞታል።
- የሰው ልጆች ከህይወት ዘመናቸው 6 ዓመት ያህሉን የሚያሳልፉት ህልም በማለም ነው፡፡
- ቀጭኔ በቀን ለ2 ሰዓት ብቻ ነው የምትተኛው።
- ድመት በአማካይ ከ10-15 ሰዓታት በቀን ትተኛለች፡፡

ሀሜት በብዙ ተቋማትና አካባቢ ይዘወተራል፡፡ በዋናነት ሰውን መሰረት አድርጎ፣ ያልተጣራን መረጃ እውነት አስመስሎ ስለ ግለሰብ አሉባልታ መንዛት ነው፡፡ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ሃሜት በስራ አካባቢ ከተዘወተረ የስራ ጊዜ ከመሻማቱ በተጨማሪ በሰራተኞች ዘንድ የእርስ በርስ ትስስርን በማላላት፣ ምርታማነትና ውጤታማነትን በእጅጉ ይጎዳል፡፡
ሃሜት ብዙ ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። ሰውን ከሰው አጋጭቷል፡፡ ትዳር በትኗል፡፡ ወንድማዊና የጓደኝነት ፍቅርን አሻክሯል፤ ሌላም ብዙ መከራዎችን ፈጥሯል፡፡ አሉባልተኝነት/ሃሜት፤ ማህበረሰብን ጭምር ይጎዳል፡፡ ድርጊቱን  ፈጻሚዎች ድርሻቸው ይለያያል፡፡ በተለይ በየመስሪያ ቤቱና አካባቢው ቀንደኛ የወሬ አነፍናፊዎችና  ሃሜት በታኞች በልዩ ባህሪያቸው ይታወቃሉ፡፡ የተቋምን ሰራተኞችና ሃላፊዎች ስም በማጥፋት የማይገባ ጥቅምን ለማግኘት የሚጥሩ ቀንደኛ አሉባልተኞች መኖራቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ከዚህ በታች የቀረበው ከአንድ የሃሜት አርበኛ ጋር የተደረገ ምናባዊ ቃለ-ምልልስ ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችሁ፡፡
ጠያቂ፡ ቀንዶ፤ እስቲ ያደግህበትን  አካባቢ አስተዋውቀን?
ቀንዶ፡ አሁን አፍንጫዬን አይተህ የት እንዳደኩ ማወቅ ይሳንሀል፡፡ ለማንኛውም ውልደቴ ድንገቴ ሲሆን እድገቴ ደግሞ አፍንጮ በር ነው፡፡
ጠያቂ፡ የትምህርት ደረጃህስ?
ቀንዶ፡ ለማንበብና መጻፍ እዚሁ አስከ 4ኛ ክፍል በአካል ቀርቤ የተማርኩ ሲሆን በመንፈስ ደግሞ እንጦሮንጦስ ከሚገኝ ተቋም በሃሜት ሶስት ዲግሪዎችን ጭኛለሁ፡፡ ለአሰልጣኝና ወዳጄ ክብር ይግባውና፣ ዛሬ ዋና እንጀራዬ  ሃሜት ነው፡፡   አቤት ደስ ሲል!
ጠያቂ፡ ከሃሜት ሌላ ምን ስራዎችን ትሰራለህ?
ቀንዶ፡ ወይ ነዶ! እኔንና ስራዎቼን አለማወቅህ ይገርመኛል፡፡ ሃሜት ብቻውን አልጫ እኮ ነው የሚሆነው፤ ስለዚህም ሶስቱ ማዎች ማለትም - ማምታታት፤ ማጋጨትና ማለያየት  የኔ ስፔሻላይዜሽን ናቸው፡፡ በዚህ ተግባሬ ከኔ ሊወዳደር የሚችለው አስተማሪዬ ዲያቢሎስ ብቻ ነው። ስማ አንተም ብትሆን አንድ ቀን አይቀርልህም፡፡ አንገራግጭሃለሁ።
ጠያቂ፡ ከምግብና መጠጥ ምን ትወዳለህ?
ቀንዶ፡ የጥያቄህ ቅደም ተከትል በራሱ ትክክል አይደለም፡፡ በኛ ቤት መጀመሪያ መጠጥ፣ ከዚያ ስለ ምግብ ነው መጠየቅ ያለበት፡፡ ልንገርህና እኔ በባዶ ሆዴ በልቼ አላውቅም፡፡ አንዳንዱ በጠዋት ሳይጠጣ ምግብ ሲበላ ሳየው ግርም ይለኛል፤ ያበሽቀኛልም፡፡ ለማንኛውም ነጭ አረቄ ነፍሴ ነው፡፡ ብዙዎች ቀንዶ ብለው የሚጠሩኝ ለዚህ ነው፡፡ ቡና፣ ለስላሳ፣ ውሃ፣ ሻይ የሚባሉትን ዘራቸውን ካየሁ ወይም ወደ ሆዴ ከገቡ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ምነው እቴ አያርግብኝ!
ጠያቂ፡ የሰሞኑ የሃሜት ርእስህ ማነው?
ቀንዶ፡ አንድ ያላለቀ ቻፕተር አለኝ፡፡ ሰሞኑን እሱን ለማጠናቀቅ ሌት ከቀን እየለፋሁ ነው። ሰውየውን በሃሜት ዱላ ብለው ብለው ሊጠፋ አልቻለምና ከሰሞኑ በያዝኩት አዲስ የአሉባልታ ዘመቻ ስልት እከሸክሸዋለሁ፡፡ ስሙን ፈልገህ ከሆነ በዚህ መንገድ ስለማይነገር፣ ዘፋኙ “ሺ ሰማኒያ ጠብቂኝ” እንዳለው በቅርቡ መንገድ ላይ ሳሰጣው ታገኘዋለህ፡፡ ደግሞ ለሃሜት!
ጠያቂ፡ አሉባልታን ለማሰራጨት ምን አይነት ስትራቴጂ ነው የምትጠቀመው?
ቀንዶ፡ ከብዙ ሃሜተኞች እኔን ዋናው የሚለየኝ ይህ ነው፡፡ አሉባልታን የማቀርብበት መንገድና የምሰጠውም ትኩረት እንዲሁ እንደነገሩ ሳይሆን ሳይንሳዊ ሊባል በሚችል ስልት ነው፡፡ አቀራረቤ ለሃሜት ቅርጫ በቀረበው ሰው ልክና እኔ ላመጣ ባሰብኩት አላማ ላይ ይወሰናል፡፡ ስለዚህ ለዚህ ግብ ስኬት፣ በሰው ስብጥርና ብዛት እንዲሁም ለሃሜቱ በምሰጠው ጊዜ ጭምር አሉባልታውን በልክ በልኩ እየመተርኩ፣ እንደ የሰዉ አቅም/ማንንት እየመዘንኩ ለተቀባዩ አስኮመኩመዋለሁ፡፡ በአጠቃላይ አሉባልታዬን ለመንዛት አራት ስትራቴጂዎችን እጠቀማለሁ፡- አንዳንዱ ኑሮ አድቅቆታል፤ ለዚህ አይነቱ “ይሄ እከሌ የሚባል ሰውዬ እኮ ጥቅሞቻችንን አላስከብር አለን፣ እሱና ጓደኞቹ ተቋሙን በዝብዘው ጨረሱን፤ እኛን የበዪ ተመልካች አደረጉን” እያልክ እምባ እስኪወርደው ድረስ ብሶቱን እንዳያወራ እያቀባበልክ ትሞዥቀዋለህ፡፡
1. ሌላው ደግሞ የመንደርተኝነት ጥማት አናቱ ላይ የወጣውን የብሄረተኝነት/ጎሳ ጉዳይን መነሻ አድርገህ፣ “ተበድላችኋል፣ እከሌ እኮ እናንተን አላስጠጋ አለ፣ ትምክህት አለበት፣ የራሱን ሰፈር ልጆች እየሰበሰበ ነው” እያልክ በአሉባልታ መዶሻ ወቅረኸው፣ ኡኡ ለማለት ትንሽ ሲዳዳው፣ አንተ ትመርሻለህ፡፡ ቀሪውን አሉባልታ እሱ ያዳርሰዋል።
2. አሉባልታ የሚነዛበት ስፍራን ይመለከታል፡፡ቤተ-እምነት፤ መንገድ ላይ፣ ስራ ቦታ፣ ለቅሶ ቤት፣ ሰርግ ቤት፣ ስብሰባ ቦታ፣ መኪና ውስጥ፣ ምን አለፋህ --- ነፍስህ እስኪጠፋ ድረስ በተገኘው ቦታና ስፍራ ሁሉ ቱማታው አየር ላይ ይውላል፡፡
3. የአሉባልተኝነት ኤቲክስን ስራ ላይ ማዋል፡- “ድንቅ አሉባልተኛ እንቅልፍ አያስተኛ” ይላል፤ እውቁ የአሉባልታ ሊቅ፡፡ አሉባልታን በሆዱ ተሸክሞ መዞር  ክልክል ነው፡፡ በ”ሃሜት ስኩል ኦፍ ቶውት” መሰረት፣ የሃሜተኛነት 10ቱ  ትእዛዛት/ኤቲክስ ቀጥሎ ተዘርዝረዋል፡-
ሃሜተኛን እንደራስህ አርገህ ወደድ---ጓደኛህ ነውና
ሃሜትን ለመበተን ቦታ አትምረጥ-ሁሉም ስፍራዎች ያንተ ናቸውና
ለሁሉም እንደችሎታውና ፍላጎቱ መዝነህ ሹክ በለው--9-0-1 ታክቲክ ተጠቀም፡፡ ሁሌም ከፊት አንተ ብቻ
ይሉኝታ፣ ሀፍረት፤ ህሊና፣ ሞራል፣ መመሪያ፣ ደንብ የሚባሉትን ንቀህ ተዋቸው--ገገማም በላቸው
ሁሌም አዳዲስ ሃሜቶችን ፈብርክ- ድንቅ ችሎታህንም አሳይ--ከሃሜት ጎተራ ወሬ ተዝቆ አያልቅምና
ሃይማኖተኛ፤ ቅን አሳቢ፣ ሰብዓዊ ለመምሰል ጣር---አስመስል ይሳካልህማል
ከአንዳንድ ሃሜት ጠል ሰዎች ተጠንቀቅ--ያጋልጡሃልና
ይሁዳዊነትን አስታውስ---ከሃዲ ሁን፣ ሸምጥጥ
በየጊዜው የአሉባልታ ስኬታማነትህን ለካ--ምዘና እና ግምገማ አድርግ
ለቀጣይ አዲስ ሃሜት ለማቅረብ ተዘጋጅ--እንጀራህ ነውና
እነዚህን ሁሉ ሳልታክት ስራ ላይ ማዋል ተቀዳሚ ተግባሬ ነው፡፡
ጠያቂ፡ የሰዉን የአሉባልታ/ሃሜት አቀባበል እንዴት አገኘኸው?
ቀንዶ፡ አብዛኛው እኮ ምስኪን ነው፡፡ በውሃ /መጠጥ ብቻ ሳይሆን በወሬ ጥማት ተሰቃይቷል። በጣም ያሳዝንሃል፤ ሃሜት ለቀቅ ስታደርግለት፣ ሳያጣጥም ዥው አድርጎ የሚጋተው መአት ነው። ታዲያ እኔን ሲያገኝ አቤት ደስ ሲለው፣ አፉን ከፍቶ ነው የሚሰማው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሃሜት ድርቀት አጋጥሞኝ፣ ዝም ብዬአቸው ሳልፍ፣”ምነው ዛሬ መረጃ የለም፣ ዝም አልከን” ብለው የሃሜት ስሜቴን ይቆሰቁሱብኛል፡፡ ሰዉ እኮ ምስኪን ነው፤ ወሬ እንኳን ሲጠማው አድራሽ የለውም፤ እኔ ብቻ። ለወሬ ያለችውን ስሜት ስለምረዳ፣ ሁሌም ዝግጁ ሆኜ እጠብቃቸዋለሁ፤ እነሱም በተመሳሳይ፡፡ በአጠቃላይ አቀባበላቸው ከሚጠበቀው በላይ ነው። እረክቼባቸዋለሁ፡፡
ጠያቂ፡ እጅግ በጣም የረካህባቸውና ያዘንክባቸው ጊዜዎች ----?
ቀንዶ፡  ስማ እኔ አሉባልታ የምነዛው በአላማ ነው። ውጤት ላይኖረኝ ለሱስ ብቻ ሃሜት አልጀምርም፡፡ ወሬዎችን ስረጭ ከሰዉ ትኩሳት ጋር እያያዝኩ ስለሆነ በአጭር ጊዜ አቀጣጥለዋለሁ። የሚታማው ሰውዬ፣ አገር ሰላም ነው ብሎ ይንከላወሳል፡፡ ምስኪኑ ስሙን በቀናት ውስጥ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች በሚስጥር አድርሼ እበክለዋለሁ፡፡ በዚህ መልኩ ብዙ ግዳይ ጥያለሁ፡፡ በሥራዬም እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡  የማዝነው ደግሞ አሉባልታዬ ሰሚ ካጣና ኪሴ ከተራቆተ ብቻ ነው፡፡ ሁለቱ ከጎደሉ እውነቴን ነው የምልህ፣ የሌለሁ ያህል ይሰማኛል፡፡ ሲዲ ሰርተህ አድማጭ እንደማጣት ማለት ነው፡፡ አይከብድም፡፡ ወዳጄ፤ ከአሉባልታ ሰሚ እጦት ይሰውርህ!
ጠያቂ፡ እስከ ዛሬ ስንት ሰው አምተሃል?
ቀንዶ፡ በለው! ቁጥሩ የትየለሌ ነው፡፡ እንኳን እኔ መዝገብ ቤቴ ዲያቢሎስም አያውቀው፡፡ እዚህ እንኳን ጥቃቅኑን ትቼ ዋና ዋናዎቹን ብቆጥር፣ እኔ አፍ ውስጥ ገብተው የታኘኩት፣ በአመታት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ይመስለኛል፡፡ ለዛውም ንቄ የተውኳቸውን ሳልቆጥር ማለት ነው፡፡ ስንቶቹን ማርኳቸው መሰለህ፤ ለማንኛውም እነዚህን አስኮናኝ በልልኝ፡፡
ጠያቂ፡ “Gossip is created by haters, spread by fools and owned by idiots” የሚለውን አባባል እንዴት ታየዋለህ?
ቀንዶ፡ ለካ ይህም አለ፤ የሚገርም ነው፡፡ ግን ፈረንጅ ስላለው ብቻ መደናገር አያስፈልግም፡፡ ይህ የአንዳንድ ያልገባቸው ወይም ግራ የገባቸውና የውለታቢሶች ወሬ ነው፡፡ ከነዚህ ምን ትጠብቃለህ። ከኛም የባሱ ምላሰኞች ናቸው፡፡ ሰው ተግቶ እንዳያማ ቅንነት የጎደላቸው፣ የስራ ፈቶች አባባል ስለሆነ ከቁብ አልቆጥረውም፡፡ ይልቅስ ኑና ተቀላቀሉን፤  አብረን እንማ፤ ከውጤቱም ተቋደሱ! ብለህ መልእክት ላክባቸው፡፡
ጠያቂ፡ “የሃሜተኛን ምላስ እንደ አለቀ የጫማ ገበር፣ ዘወትር ደጅ ታገኘዋለህ” የሚለውንስ አባባል?
ቀንዶ፡ አባባሉ በኛ ቋንቋ ስለተነገረ ብቻ ዝም ብዬ ልቀበለው አልችልም፡፡ እስቲ ልጠይቅህ- ለመሆኑ የኛ ጫማ ገበር አለው? ታዲያ በሌለን ነገር ልንተርት ስለማንችል፣ ይህችም የነጮቹ ተረት መሆኗን አትጠራጠር፡፡ የሚገርምህ ግን ተረቱ ትንሽም ቢሆን እውነት አለው፡፡ ይህም ምላስ ሶስት ተግባራት አሉት---ምግብን ማላወስ፤ማጣጣምና ማውራት ናቸው፡፡ ምላስ የሚበላውና የሚጠጣው ሲያጣ፣ ወና አፍ ውስጥ ከመደበቅ ብቅ ብሎ ለወሬ ደጅ መገኘቱ ሃላፊነትን በብቃት ከመወጣት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ተገቢ አይደለም ትላለህ፡፡ እንዴታ! ብራቮ ምላሴ!
ጠያቂ፡  የወደፊት አላማህ ምንድነው?
ቀንዶ፡ ሃሜት ውስጤ ነው፡፡ ከአሉባልታ መለየት አልፈልግም፤ አልችልምም፡፡ በአፌ ሰው ሳልቦጭቅ ከዋልኩ ያመኛል፡፡  ብቻ ምን አለፋህ ---- ሃሜት ከደሜ ተዋህዷል፡፡ ስለዚህ በአሉባልታ ሰደድ እያጨዱ መከመሬን አጠናክሬ እቀጥላለሁ። በተጨማሪ የእኔን አላማ ለተከተሉና በቀጣይ ለሚተገብሩ ሸሪኮቼ ልምዴን አካፍላለሁ፡፡ ሃሜትን/አሉባልታን፤ ዋና የመረጃ ምንጭ የማድረግ ህልሜ በጥቂት አመታት ውስጥ እውን ይሆናል፡፡
ጠያቂ፡ ማንን ማመስገን ትፈልጋለህ?
ቀንዶ፡  የዘወትር ተባባሪዎቼን ነዋ! ጆሮዋቸውን ቀስረው ላደመጡኝ፤ ሳይመዝኑ አምነው  እንደወረደ ለተቀበሉኝና ወሬዬን ያለምንም ክፍያ ላሰራጩልኝ በሙሉ “ውለታችሁን እሱ ይክፈልልኝ” በልልኝ። ከዚህ ውጪ ለአድናቂዎቼና ደጋፊዎቼ ወይም ለአንድ የቤተሰባቸው አባል በአሉባልታ ግንባታና ስርጭት ዙሪያ አጭር ስልጠና በነፃ ለመስጠት ቃል እገባለሁ። አሉባልታን ሰምቶ ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን የአሉባልታ ፍብረካ ክህሎትን ተምረው ይወጣሉ፡፡ ይህ ከኛ ኮሌጅ ውጪ የትም ስለማይሰጥ፣ ለእነሱም ትልቅ እድል ይመስለኛል፡፡
ጠያቂ፡ ለቃለ-መጠይቁ ፈቃደኛ ሆነህ አብረኸኝ በመቆየትህ አመሰግንሃለሁ ----
ቀንዶ፡ ቀልደኛ ነህ፡፡ ይህቺም ወሬ ሆና ምስጋና! በል ከፊቴ ጥፋ!!!

 የ2017 የጎልደን ግሎብ ሽልማት ዕጩዎች ይፋ ተደረጉ
      ለ2017 የጎልደን ግሎብ ሽልማት በዕጩነት የቀረቡ ፊልሞች፣ የፊልም ተዋንያን፣ ዳይሬክተሮች፣ ፕሮዲዩሰሮች፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና አከፋፋይ ኩባንያዎች ዝርዝር ባለፈው ሰኞ ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ “ላቪንግ” በተሰኘው ፊልም ላይ በመሪ ተዋናይነት የሰራቺው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የፊልም ተዋናይት ሩት ነጋ፣ በምርጥ ሴት የድራማ ፊልም ተዋናይ ዘርፍ ለሽልማት ታጭታለች፡፡
ኢትዮ-አይሪሽ ዜግነት ያላት ሩት፣ በጄፍ ኒኮላስ ዳይሬክት በተደረገው “ላቪንግ” የተሰኘ የድራማ ዘውግ ያለው የፍቅር ፊልም ላይ ባሳየቺው የትወና ብቃት ለጎልደን ግሎብ የታጨች ስትሆን ለሽልማቱ መታጨቷ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባት  መግለጧን አይሪሽ ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ በዘንድሮው የጎልደን ግሎብ ሽልማት፣ “ላ ላ ላንድ” የተሰኘው ፊልም ምርጥ ዳይሬክተር፣ ምርጥ ወንድ ተዋናይና ምርጥ ሴት ተዋናይን ጨምሮ፣ በተለያዩ ሰባት ዘርፎች ለሽልማት መታጨቱን ያስታወቀው የሆሊውድ ፎሪን ፕሬስ አሶሴሽን፤ “ሙንላይት” በስድስት ዘርፎች፣ “ማንችስተር ባይ ዘ ሲ” በአምስት ዘርፎች መታጨታቸውንም ገልጧል፡፡  
ለ74ኛው የጎልደን ግሎብ ሽልማት በምርጥ ዳይሬክተር ዘርፍ ከታጩት ቶም ፎርድና ኬኔዝ ሎኔርጋን “ጌም ኦፍ ትሮንስ”፣ “ዌስትዎርልድ”፣ “ዘ ናይት ኦፍ” እና “ኢንሴኪዩር” እያንዳንዳቸው 14 ጊዜ በመታጨት ቀዳሚነቱን መያዛቸው የተነገረ ሲሆን  በፊልም አከፋፋይ ኩባንያዎች ዘርፍ “ሰሚት ኢንተርቴንመንት” 10 ጊዜ በመታጨት ቀዳሚነቱን ሲይዝ፣ “ኤ24” 9 ጊዜ፣ “ፓራማውንት ፒክቸርስ” ደግሞ ለ8 ጊዜ በመታጨት ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
በተከታታይ የቴሌቪዥን ፊልሞች ዘርፍ “ዘ ፒዩፕል ቨርሰስ ኦ ጄ ሲምሰን” ለ5 ጊዜ በመታጨት በአንደኛነት ሲቀመጥ፣ “ዘ ናይት ማናጀር” ለ4 ጊዜ፣ “ብላኪሽ” ደግሞ ለ3 ጊዜ በመታጨት ይከተላሉ፡፡ የ2017 የጎልደን ግሎብ ሽልማት ስነስርዓት በመጪው ጥር መጀመሪያ፣ በቤቨርሊ ሂልተን ሆቴል የሚከናወን ሲሆን በኤንቢሲ ቴሌቪዥን በኩል በቀጥታ ለተመልካቾች እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ገጣሚ ደበበ ሰይፉ የሚከተለውን ፅፎ ነበር፡፡ መነሻው ተረት ነበርና አመቻችተን እንደ ተረት ተጠቅመንበታል፡፡
በተረት ላሰላስል
መሬትና ጥንቸል ማኅበር ገቡና
ጽዋ ተጣጡና፤ …
ያጋጣሚ አይደለም፤
የተፈጥሮ ባህል፣ የታሪክ ዘይቤ፣ አለው አንድ ቋንቋ፣
አለው አንድ መላ
አንተና ልደትህን፣ አንተና አገርህን
በማይረግብ ገመድ፣ ባንድ ላይ የቋጨ፣ ከአፀደ ዘመን?
ከቦታ ከለላ
በደም ቃልኪዳኑ ባንድ ያስተሳሰረ፣ በማይታይ እጆች
ባልተሰማ መሀላ፡፡
… እና፣
መሬትና ጥንቸል ማኅበር ገቡና
ጽዋ ተጣጡና፣ …
መሬት የፈንታዋን ስትከፍል በጽሞና፤ …
እብስ አለች ጥንቸል፣ መክፈል ጠላችና
እና፣
… በስንት ትላንትና፣ ዘንቦ ወይ ፀህይቶ
በቁር ተኮራምቶ፣ በዋዕይ ገርጥቶ
የበቀለ ዛሬ፣
ትውልድም ነውና፣ ያያት የቅድመ - አያት
የእንዝላ የእንጅላት  
የመሰረት ፍሬ፣
በሺ እግሮች ተራምዶ፣ ዛሬን የደረሰ፣ ለእሱ እሱነቱ
በወቅቱ ለወቅቱ
ይኖር ወይ ደካማ፣ የትውልድ እንክርዳድ
አደገኛ አዝመራ ከዚህ ከወጣቱ?
ማነው ይህ መጢቃ፣ የፀደይ ቀን ዘመድ
ወጪቱን እሚሰብር፣ ዕዳውን እሚክድ
ከወገኑ እማይቆም፣ ከወገኑ እማይነድ?
የጫጨ መንፈሱ፣ የሸፈተ አሳቡ፣ የከነፈ ልቡ
ራሱ መነሻው፣ ደሞ ራሱ ግቡ?
እና፤ …
መሬትና ጥንቸል፣ ማኅበር ገቡና፣ ፅዋ ተጣጡና
መሬት የበኩሏን ስትከፍል በጽሞና
እብስ አለች ጥንቸል፣ መክፈል ጠላችና፣ …
ግና ምን ይሆናል?
ብትሮጠው ብትሮጠው፣ ጋራውን ተሻግራ፣
ሜዳውን አቋርጣ
አልቻለችም ከቶ፣ ከዕዳዋ ልትድን፣
ከመሬት አምልጣ፡፡
(1974)
*      *     *
የመሬትን ዕዳ ሳንከፍል አናመልጥም፡፡ መሬት የአገር ነው፡፡ ብዙ ጥንቸሎች ከመሬት ጥቅም አጋብሰዋል። የአገር ዕዳ አለባቸው፡፡ የትም ቢሮጡ አያመልጡም፡፡ አገር በዐይነ ቁራኛ ታያቸዋለች፡፡ እጃቸው ንፁህ አይደለምና ተጠያቂ መሆናቸው አይቀሬ ነው!
ክፈሉ ስንባል የማንከፍለውን ጥዋ አለመጠጣት አስተዋይነት ነው፡፡ አቅም ይፈቅዳል የምንለውን እንጂ ግብረ አበራችንን ዝቅ አድርገን የምንሄደበት መንገድ፣ የኋላ ኋላ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡ “የሸክላ ድስትና የብረት ድስት ወዳጅነት” ከባድ የመንኮታኮት ውጤት እንደሚኖረው ደራሲ ከበደ ሚካኤል ገና በተማሪነት ዕድሜያችን አስገንዝበውናል፡፡ ያም ሆኖ ትንሽ፤ ትልቅ ለመሆን አይጣጣር ማለት አይደለም፡፡ አድጌ እዚህ እደርሳለሁ የማይል፣ የግቤ መጨረሻ ይሄ ነው የማይል፣ ተስፋ መቁረጥ ነው ውጤቱ! ያልነቃ መንፈስ፣ ያልነቃ ድርጅታዊ መሪ፣ ያልነቃ ተቋማዊ አስተዳዳሪ፣ ያልነቃ ዜጋ፤ ለዕድገት ደካማ ጎን ነው! መንቃት ሲባል ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ዕውቀታችንን የማዳበር ጉዳይ ነው፡፡ ሳናውቅ ያወቅን እንዳይመስለን፣ ደግ ሳንሆን ደግ ነን እንዳንል፣ ዲሞክራሲ ሰፈር ሳንደርስ ዲሞክራሲያዊ ነን ብለን ጉራ እንዳንነዛ፣ ከወገናዊነት ሳንላቀቅ ስለ ፍትሐዊ አካሄድ በየደረስንበት እንዳናወጋ፤ ጠቃሚው መላ በንባብ፣ በውይይት፣ በተግባር ልምድ በማበልፀግ፣ ከስህተት በመማር፣ ራሳችንን ማረቅ፣ “ካፈርኩ አይመልሰኝ” ማለትን መተው ነው፡፡
በሀገራችን እጅግ ጠቃሚ ፋይዳ ያለውና ሳናደርገው የቆየን አንድ ታላቅ አላባ (element) መልካም የሰራን ዋጋ የመስጠት፣ የማድነቅ፣ ጮክ ብለን አዎንታዊ ሙገሳን ለማሰማት የመድፈር ባህል፤ አለማዳበራችን ነው፡፡
“ሌላ ባላውቅ የራሴን ዋጋ አቃለሁ” ይላል እያጎ፡፡ ሼክስፒር፣ መሠሪውን እያጎን እንኳ የራስ ዋጋን ስለማወቅ ሰባኪ አድርጎታል፡፡ ምነው ቢሉ፣ ለማንም ቢሆን ለማን፣ የራሱ መለኪያ አለው! የራስን ዋጋ ማወቅ፣ ራስን ከማወቅ የሚመነጭ ነው! ሁኔታውን እንደ መንግስት ስናሰላው፤ ከየት መጣሁ፣ ለምን መጣሁ፣ ወደየት እሄዳለሁ፣ ምን ዕቅድ አቅጃለሁ? በምን እተገብረዋለሁ? በዚህ ዕቅዴ ተግባራዊነት አነማን አጋሮች አሉኝ? ምን ያህልስ ዝግጁ ናቸው? ብሎ መጠየቅ ዓይነተኛ ግንዛቤ መጨበጥን የሚያሳይ ማፀሕያ ነው! ራስን ለመገምገም መነሻው ይሄ ነው፡፡ ማቀድ፣ መተንተን፣ ተግባራዊነቱን መቆጣጠር፣ ፍፃሜውን መከታተልና ውጤቱን መገምገም… የማናቸውንም ስራ ሂደት ፍሬ ነገር መጠቅለያ ነው!
ማናቸውም አዲስ ሹም፤ የራሱን ብቃትና ህልውና ለማረጋገጥ፤ ከሱ ቀደም የነበረውን ሹም ጥፋትና ድክመት በመጥቀስ እወደዳለሁ፣ ክህሎቴንም አረጋግጣለሁ ብሎ ባያስብ መልካም ነው! ይሄ ባህል፣ ማለትም ጥፋትን ሁሉ በቀደሙት ሹማምንት ላይ ማላከክ የቀደሙትን ማውገዝ እጅግ የተሳሳተ መርህ ነው! ህዝብም ይሄን ዘዴ ተረድቶ በመንገኝነት መንገድ ውስጥ ለመጓዝ፣ ለመንገድ መዘጋጀት የለበትም! ይልቁንም ስላለፉት ሹማምንት ውግዘት ከማዳመጥ፣ የራስህን ብቃት አረጋግጥ ማለትን ዋና ጥያቄው ማድረግ አለበት፡፡ መፍጠር ያለብን ጠያቂ ማህበረሰብ (Inquisitive Society) ነው፡፡ ህብረተሰብ፤ ከወጣው መመሪያ፣ አዋጅ፣ መርሀ ግብር ጋር ራሱን አዋህዶ ያይ ዘንድ የማወቅ መብቱን መጠቀም፣ ለምን? እንዴት? ማለት፤ ካልጣመውም እምቢ ማለትን መልመድና መቀበል አለበት፡፡ ግልፅነትና ተጠያቂነት ከዚህ ሂደት የሚመነጩ ናቸው፡፡ የምንሾማቸውን ባለስልጣናት በጥንቃቄና በሚዛናዊ ብስለት መሾም ኋላ ከሚመጣ ስህተትና ፀፀት ያድነናል። ከዚህ ቀደም የፈፀምነው የማመዛዘን፣ ስህተት ኖሮ ከሆነም፣ ከዚያ መማር ተገቢ ነው፡፡ አለበለዚያ ራሷ ሰቅላው ራቀ፣ ራሷ ጋግራው ሊጥ ሆነ… የሚለው ተረት ዕውን ይሆናል፡፡