Administrator

Administrator

ከሀገራዊ ለውጡ በፊት እንደ ሀገር መቀጠል የማንችልበት ደረጃ ላይ ስለመድረሳችን ብዙ ምክንያቶችን ማንሳት እንችላለን፡፡ ህዝብን በጸረ ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ ለመምራት የሚደረግ አይን ያወጣ ተጽዕኖ፣ አድርግ ወይም አታድርግ በሚሉ ቃሎች ብቻ የተገደበ እና ህዝብን ለማሸማቀቅ በርካታ ድርጊቶች ሲፈፀሙ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ህዝብን ከፋፍሎ የመግዛት አባዜ የተጸናወተው ጥቂት የህወኃት ቡድኖች፣ በርካቶች ተገፍተው ከሀገር እንዲወጡም ምክንያት ነበሩ፡፡ ለሀገራቸው ፖለቲካ ያገባናል ያሉ የፖለቲካ ሀይሎች ሀሳባቸውን አውጥተው መግለጽ እንዳይችሉ ሲደረግባቸው የነበረው አፈና፣እስር፣ግርፋትና አሰቃቂ ድርጊቶች ለፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ እንደ ምክንያት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የመሰረተ ልማት እጥረት ባልተቀረፈበትና የህዝብ የልማት ጥያቁዎችን መፍታት አዳጋች በሆነባት ሀገር፣ እነዚሁ አጥፊ ቡድኖች በርካታ የህዝብና የመንግስት ተቋማትን በመዝረፍና የዘረፉትን ወደ ውጭ ሀገራት በማሸሽ በህዝብ ላይ ክህደት፣ በሀገር ላይ የኢኮኖሚ ውድቀት አስከትለዋል፡፡
እወክለዋለሁ ላለው የትግራይ ህዝብ በተጨባጭ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት የተሳነው ይህ አጥፊ ቡድን፣ ከሀገራዊ ለውጡ እኩል መራመድ ባለመቻሉና ሲፈፅማቸው የነበሩ ኢ-ዴሞክራሲያዊ አካሄዶች ከህዝብ ፊት መቆም እንዳይችል ስላደረገው፣ ውህደቱን ከመቀላቀል ይልቅ መግፋትን አማራጩ አድርጓል፡፡
ለህገ መንግስታዊ ስርዓት ጠበቃ ነኝ ሲል የነበረው አጥፊው የህወሃት ቡድን፤ የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር ለመነጣጠልና ለህገ መንግስቱ ያለውን ንቀት ያረጋገጠበትን ህገ ወጥ ክልላዊ ምርጫ ሲያደርግና ህጋዊ ያልሆነ መንግስት ሲመሰርት በሆደ ሰፊነት የተመለከተው የፌደራል መንግስት፣ ይህ ቡድን እየተከተለው ያለው ኢ-ህገ መንግስታዊ አካሄድ ከዛሬ ነገ ሊለወጥ ይችላል በሚል ጊዜ ሰጥቶት ቆይቷል፡፡ ዳሩ አምባገነናዊ ባህሪው እያደገ ቢመጣም፡፡
የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ለሀገራዊ ለውጡ በጋራ ለመቆም ፍላጎት ቢኖረውም፣ ጥቂት የህወኃት ቡድን አመራሮች ግን የህዝቡን ፍላጎት ወደ ጎን በመግፋት፣ ህዝቡ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖረው ጭቆና ሲያደርስበት ቆይቷል፡፡
ብልጽግናና የለውጡ መሪዎች ህወኃት ውህደቱን እንዲፈጽምና ለጋራ ሀገራችን በጋራ እንቁም መርህ በተደጋጋሚ ጊዜ የድርጀቱን መሪዎች በማግኘት ሰፊ ጊዜ ተወስዶ ማወያየት ቢቻልም፣ ወትሮውንም ሀገርንና ህዝብን የማገልገል ጽኑ ፍላጎት ሳይሆን በስልጣን የሚገኝ ጥቅምን መሰረት ያደረገ ስለሆነ  ለውህደቱ እምቢታቸውን አሳይተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ተስፋ ያልቆረጡት የለውጡ መሪዎች በህዝብ የሚታወቁም ሆነ የማይታወቁ በርካታ ጥረቶችን በማድረግ የትግራይን ህዝብ ከለውጡ ጋር አብሮ ለማስቀጠል ያላሰለሰ ግፊት ቢደረግም፣ በጸረ ለውጥ ቡድኖች ሰንኮፍነት እንደታሰበው ውህደቱን ለማቀላቀል የተደረገው ጥረት ያለ ውጤት ተጠናቋል፡፡
መቀሌ የመሸገው የጥፋት ቡድኑ፣ ምስኪኑን የትግራይን ህዝብ ጠዋት ማታ፣ የአማራ ክልልና የፌደራል መንግስት ጦርነት በህዝባችን ላይ ሊከፍቱብን ነው በሚል የተሳሳተ መረጃ፣ ህዝቡን በማደናገር እረፍት አሳጥቶት ከርሟል፡፡
የትግራይ ህዝብ ጦርነት እንዳንገሸገሸው የኢትዮጵያ ህዝብ ከልብ ይረዳዋል፡፡
ጦርነት የመጨረሻ እንጂ የመጀመሪያ አማራጭ እንዳልሆነ ብልጽግና ይገነዘባል፡፡
የመከላከያ ሰራዊቱን ከክልሉ ፈቃድ ውጭ ማደራጀት አትችሉም የሚል አቋም እየተከተለ ያለው ሴረኛውና ጥቂቱ የህወኃት ቡድን፤ የፌደራል መንግስትን ውሳኔዎችና የሚሰጡ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ እንዳይሆኑ ግትር አቋሙን ሲያሳይ ቆይቷል፡፡
ከህዝብ አብራክ ወጥቶ ህዝብንና ሀገርን ከጥቃት እየተከላከለ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊቱን የቆየ ክብርና ዝና ለማጠልሸት ሲሞክር፣ ሆደ ሰፊው ሰራዊት ምላሽ ሳይሰጥ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ለጥፋት ሁሌም የማይተኛው ጥቂት የህወኃት ቡድን አማካኝነት በተሰጠው ትዕዛዝ በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕና ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ላይ ትናንት ሌሊት ጥቃት ከማድረሳቸው ባሻገር ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርገዋል፡፡
ነገሩን በሆደ ሰፊነት ሲመለከተው የቆየው መንግስት እየተፈፀሙ ያሉ ድርጊቶች ገደብ በማለፋቸውና ግልጽ ትንኮሳ በመፈጠሩ ምክንያት ይህንኑ ድርጊት ሊመክት የሚችል አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ተገዷል፡፡ በዚህ መሀል ምንም የማያውቀው የትግራይ ህዝብ ተጎጂ እንዳይሆን አስፈላጊው ጥንቃቄ እየተወሰደ ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ በፊት እንደምናደርገው ሁሉ ብልጽግና ፓርቲ የሀገርና የህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሌት ተቀን የሚሰራና የህዝብንና ሀገርን ሰላም አደጋ ውስጥ ሊከት የሚችል ማናቸውንም ነገሮች ለመታገስ እንደማይችል ታውቆ፣ በተሣሣተ መረጃ ጭቁኑ የትግራይ ህዝብ ላይ ያልተገባ ስጋት በመፍጠር ተጠራጣሪ ለማድረግ የሚደረገውን ተከታታይ ቅስቀሳ የትግራይ ህዝብ ሊያወግዘው የሚገባ መሆኑን በፅኑ በማመን፣ የሚከተሉትን የአብሮነትና የአጋርነት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
1. ለተከበርከው የትግራይ ህዝብ
የትግራይ ህዝብ ከሌሎቹ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ጠንካራ ታሪካዊ አንድነትና ውህደት ያላቸው፣ ባህላዊና ጥንታዊ ሃይማኖታዊ እሴቶችን የሚጋሩ፣ በጋብቻና በደም የተሳሰሩ፣ በፀረ-ጭቆና ትግል ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሆነው፣ በአንድ ጉድጓድ ክቡር መስዋዕትነት እየከፈሉ አሁን ላለንበት የሀገረ መንግስት ምስረታ ጉልህ አሻራ ያሳረፉ ህዝቦች ናቸው፡፡
ሆኖም የሕወሓት አጥፊ ቡድን፣ የሀገርንና የህዝብን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል የሚያደርጉት ሴራ መሆኑን አውቃችሁ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ያላችሁ ወንድማዊና ቤተሰባዊ ግንኙነታችሁ ሳይቋረጥ፣ የትግራይን ህዝብ የሚያለያዩ ሙከራዎችን በፅናት እንድትታገሉ የከበረ ጥሪያችንን እያቀረብን፣ በዚህ አሸባሪ ቡድን ላይ እርምጃ በመውሰድ፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለማስቀጠል በምናደርገው ትግል ውስጥ ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
2. ለመላው የትግራይ ምሁራን
ሀገርን በሚፈለገው ደረጃ መለወጥ ካስፈለገ ምሁራን የሚያደርጉት አስተዋጾኦ ከፍ ያለውን ቦታ መያዙ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ግን  በክልሉ የሚገኙ ምሁራንን ለሀገራቸው ሁለንተናዊ አበርክቶ እንዳያደርጉ በጥቅም የተሳሰረው ቡድን እንቅፋት እንደሆነባችሁ መረዳት ተችሏል፡፡ ስለሆነም ምሁራን በነጻነት ተንቀሳቅሰው ያላቸውን አቅምና ዕውቀት ለሀገራችን ህዝቦች እንዲያበረክቱ ካስፈለገ፣ ጨቋኙንና ጸረ ለውጡን የህወኃት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡
ስለሆነም የተከበራችሁ በትግራይ የምትገኙ ምሁራን፣ ሁላችሁም፣ የፌደራል መንግስት በክልሉ እያደረገ ያለው ህገ መንግስቱን የማስከበር ስራ በውጤታማነት ለመፈፀም እንዲቻል የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋልን፡፡
3. ለመላው የትግራይ ወጣቶች
በክልሉ የምትገኙ ወጣቶች ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ መሆን ሳትችሉ ነገር ግን በስማችሁ እየተነገደ ለበርካታ ዓመታት ቆይታችኋል፡፡ ይህንን አይን ያወጣ ዘረፋና ሌብነት በአጥፊ የህወኃት ቡድን አማካኝነት ሲካሄድ እንደነበርም የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡
በስሙ ሲነገድበት ለቆየው የትግራይ ወጣት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይረጋገጥ ዘንድ በዚህ አጥፊ ቡድን ላይ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷልና መላው የትግራይ ወጣቶች፣ በፌደራል መንግስት በኩል እየተወሰደ ያለውን ህግን የማስከበር እርምጃ በመደገፍ ለክልሉና ለሀገር ሰላም አጋር እንድትሆኑ፣ የትግራይ ወጣቶች ከመላው የሀገራችን ወጣቶች ጋር በመሆን የጀመርነውን አገራዊ ለውጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
4. በትግራይ ክልል ለምትገኙ የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች
የትግራይ ክልል የፀጥታ ሀይሎች፣ በሀገሪቱ ከሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመሆን ህዝባዊነታችሁን ጠብቃችሁ ለአንዲት ሉአላዊት አገር መከበርና ቀጣይነት ክቡር መስዋዕትነት በመክፈል ላይ መሆናችሁን ብልጽግና ፓርቲ ከልብ ይገነዘባል፡፡
ምንም እንኳ በክልሉ አምባገነን የሆነው የህወኃት ቡድን፣ በትግራይ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን እንግልትና ስቃይ የታዘባችሁ ቢሆንም ባለው ጸረ-ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ምክንያት ለውጡን ከህዝባችሁ ጋር ሆናችሁ ማጣጣም ሳትችሉ ቀርታችኋል፡፡
ሆኖም ለረዥም ዓመታት የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት በሀላፊነት መንፈስ ወስዳችሁ ስትጠብቁ የቆያችሁ የክልሉ ፖሊስ፣ ልዩ ሀይል አባላትና ሌሎችም፤ በህዝብ ትክሻ ላይ ሆኖ እየቀለደ ባለው ዘራፊና አጥፊ የህወኃት ቡድን ላይ እርምጃ ለመውሰድ እየተደረገ ያለውን ትግል በመቀላቀል ህዝባዊነታችሁን እንድታረጋግጡ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ


ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል። ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው። ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታትና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል።

መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ፣ ጦርነት እንዳይፈጠር የትእግሥቱ ጫፍ ድረስ ታግሷል። ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም።

የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል፣ በየአካባቢው ሊከሠቱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በንቃት እንዲቃኝና ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ።

ህወሓት እናኦነግሸኔን ጨምሮህገወጥ መሳሪያታጥቀውየዜጎችን ህይወትበማጥፋትላይ ያሉቡድኖች በአሸባሪነት
ሊፈረጁእንደሚገባ የህዝብተወካዮችምክርቤትአባላትሃሳብአቀረቡ፡፡እነዚህቡድኖችበአገሪቱህግመሰረት ተጠያቂመሆን  እንዳለባቸውምየም/ቤቱአባላትአሳስበዋል፡፡ምክርቤቱበኦሮሚያክልልበምዕራብወለጋዞንማንነትንመሰረትያደረገውጭፍጨፋላይየተሰማውንሀዘንበመግለፅናየአንድደቂቃ የህሊናፀሎትበማድረግ፣መደበኛውይይቱንሊያደርግቢያስብም፣አባላቱቅድሚያሊሰጥየሚገባውየዜጎችህይወትበመሆኑውይይቱከዚህእንዲጀምር  በሚልበጉዳዩላይበስፋትመወያየቱን  ለማወቅተችሏል፡፡ የምክርቤቱአፈጉባኤውአቶታገሰጫፎ፣ ምክርቤቱአጀንዳውንቀድሞቀርፆየተዘጋጀመሆኑንበመጥቀስ፣ በዜጎችላይየተፈፀመውንጥቃትበሚመለከትትናንትማምሻውንየምክርቤቱአመራርምክክርአድርጎበትአስፈፃሚውአካልማብራሪያ እንዲሰጥበትውሳኔላይመደረሱንጠቁመዋል፡፡ይህንንተከትሎሞበጉዳዩላይየምክርቤቱአባላትሀሳብእንዲሰጡበትየተደረገሲሆንበዚሁ መሰረትም፤ህወሃትእናኦነግሸኔንጨምሮጥቃትየሚፈፅሙህገወጥቡድኖችንበሽብርተኝነትበመፈረጅየማያዳግምእርምጃ  እንዲወሰድባቸውየሚልሀሳብቀርቧል።ም/ቤቱበተለያዩአካባቢዎችየሚፈጸሙጥቃቶችንለማስቆምእየተወሰዱያሉእርምጃዎችበቂአይደሉምብሏል፡፡ምክርቤቱበጉዳዩዙሪያበስፋት   ከተወያየበኋላአስፈፃሚውአካልምክርቤትቀርቦማብራሪያእንዲሰጥ፣ምህረትየሌለውእርምጃ  እንዲወሰድናችግሩ
እንዳይደገምምንመወሰንአለበትበሚለውጉዳይላይየውሳኔሀሳብእንዲቀርብአቅጣጫአሳልፏል።  ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ቤተሰብ ውስጥ ያለ አንድ አስቸጋሪ ልጅ ነበረ፡፡ ይሄ ልጅ ነጋ ጠባ ማልቀስ ነው ሥራው፡፡ ሞገደኛ ነው፡፡
አባት፤ “አንተ ልጅ እረፍ፤ እምቢ ካልክ ዋ! ለጅቡ ነው የምሰጥህ” ይሉታል፡፡
ልጅ ለጥቂት ጊዜ ዝም ይላል፡፡ ሆኖም ብዙ ሳይቆይ እንደገና ማልቀስ ይጀምራል።
“አንተ ልጅ ዛሬ ምን ነክቶሃል ዋ! ለአያ ጅቦ ነው የምሰጥህ፤ አውጥቼ ነው የምወረውርህ” ይሉታል፡፡
አሁንም ልጁ የአያ ጆቦን ድምጽ ሲሰማ፣ ድንግጥ ይልና ድምፁን ያጠፋል፡፡ ሆኖም አመለኛ ልጅ ነውና ከጥቂት ቆይታ በኋላ ማላዘኑን ይቀጥላል፡፡ ስለዚህ አባት ይናደድና ሁለት እጁንና ሁለት እግሩን ጥፍር አድርገው ያስሩታል፡፡ ቆጥ ላይ አውጥተው ያስቀምጡታል፡፡ ይሄኔ ልጁ ዝም ይላል፡፡
እናት መቼም እናት ናትና አንጀቷ ይባባና፤
“ግዴሎትም ይሄ ልጅ አሁን ፀባይ አሳምሯል፤ ልፍታው” ትላለች፡፡
አባት፡- እንደገና ቢያለቅስ ግን ውርድ ከራሴ፤ ልጃችን በጣም ሞገደኛ ሆኗል፡፡”
እናት፡- “ልጅ አይደል፤ በአንዴ አይታረም ቀስ በቀስ ያሻሽላል፡፡ እርሶም ብዙ አይጨክኑበት፡፡”
እውነትም እናት እንዳለችው ልጁ ፀጥ አለ፡፡
ለካ ይሄ ሁሉ ሲሆን አያ ጅቦ ጓሮ ሆኖ ያዳምጥ ኑሯል፡፡ ጥቂት ቆይቶ ድምፁ ሁሉ ፀጥ አለ፡፡ አሁን አሁን ልጁን ይወረውሩልኛል እያለ ይጠብቅ የነበረው አያ ጅቦ፣ ጆሮ ቢጥል ምንም ድምጽ ጠፋ፡፡ እናትና አባት ልጁን አስተኝተው የግል ወሬያቸውን ቀጥለዋል፡፡
“ያን ቦታ እንሸጠው ስልሽ… የመሬት ዋጋ አሽቆለቆለ”
እናት፡- “ግዴለም ላመት መጨመሩ አይቀርም፡፡ ዋናው መሬቱ በስማችን ያለ መሆኑ ነው፣ በዚያ ላይ ምንም አንገብጋቢ የኢኮኖሚ ችግር አለመኖሩ ነው፡፡ የመሬት ዋጋው እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይመጣም፡፡”
አባት፡- “ነገሩ እውነትሽን ነው፡፡ የቦታ ሽያጭ በየጊዜው ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አልታየም፡፡ እኔ እንደው ጓጉቼ ነው የተጣደፍኩት”
ይሄንና ሌላም የቤታቸውን ነገር እየተወያዩ ቆይተው ለጥ ብለው ተኙ፡፡
“ይሄኔ አያ ጆቦ ወደ በራፉ ጠጋ ብሎ ኧረ የልጁን ነገር ቶሎ ወስኑልኝና ገላግሉኝ” አለ ይባላል፡፡
*   *   *
በሀገራችን ብዙ ያልተወሰኑና በይደር የቀሩ ጉዳዮች አሉ፡፡ አንድም ቁርጠኛ ወሳኝ አካል ባለመኖሩ፣ አንድም ደግሞ ከስር መሰረት ሲወርዱ ሲዋረዱ የመጡ በመሆናቸው፡፡ ወደ ተወሳሰበ ግጭት ያስገቡም በመሆናቸው ነው፡፡ ለያዥ ለገራዥ የማይመቹ በመሆን ደረጃ ላይ በመድረሳቸው፡፡ ይኸው የኢኮኖሚ ገጽታችን መልክ የሌለው ሁኔታ ውስጥ ገብቷል፡፡
በመሠረቱ ስራዬ ብሎና ይሁነኝ ብሎ የሚያጠና፣ የሚያቅድና የሚተገብር፤ የሚጨነቅና የሚጠበብ አካልና “አባከና” የሚል በሌለበት ንፍቀ ክበብ ውስጥ አገርን ለማልማትና ህዝብ የመታደግ ሂደትን ማጐልበት እጅግ አዳጋች ነው። ፖለቲካዊ ያገባኛል ባይነትና ኢኮኖሚያዊ ይገባኛል ባይነት ተሰናስለው በማይጓዙበት ሁኔታ ውስጥ ሥር የያዘ ለውጥን በአግባቡ ፈር አስይዞ መንቀሳቀስ፣ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአህጉራችንም ካንሰር አከል አባዜ ነው፡፡ ዛሬም ስለ ሙያዊነት፣ ሥነ ምግባራዊነት ማውራት የምንገደደው ወደን አይደለም፡፡ ያልበለፀገ የሰው ኃይል፣ በሌብነት የፈነቀለ ጐደሎ ሥርዓት፣ ስለ ሀገርና ህዝብ ይሄ ነው የሚባል እውቀትም ሆነ ብቃት አሊያም በቂ ትምህርት በሌለው ትውልድ እጅ ላይ የወደቀ ህብረተሰብ ወደፊት እንዳይራመድ አያሌ አሽክላዎች እንደሚደቀኑበት ከቶም አጠያያቂ አይደለም፡፡
ከቀን ቀን እየተሸረሸረ ያለው ሞራል ቁልቁለቱ አሳሳቢ ነው፡፡ የሀገር ፍቅር እየተመናመነ መምጣቱ አስጊ ነው፡፡ እንስራ ሲባል “እንዝረፍ” የሚል አስተሳሰብ ያለው ትውልድ፤ እለት ሰርክ እየቀፈቀፍን፣ ቀቢፀ ተስፋን እንጂ ተስፋን ማለም ጤናማ ራዕይ አይደለም፡፡ ይህ ጥበብ  “decadence” ክፉ አባዜ ነው። ሳይታወቀን እየወረድንበት ያለውን አዘቅት መለስ ብለን የምናይበት አንገት የሚያሳጣ አስደንጋጭ ተዳፋት ነው፡፡
እገሌ ከእገሌ ሳይባል ሁላችንንም ተጠያቂ የሚያደርግ የመሽቆልቆል መርገምት ነው፡፡ “ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ” የሚያሰኝ ሶሽዮ ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ አዝሎ የሚጓዝ ባለቤት አልባ የሚመስል ከባቢ አየር ውስጥ መሆናችን ኤጭ የማይባል ነገር ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ሠላምን ማረጋገጥ የመንግሥትም የህዝብም ግዴታ ነው። “እዚህ ቦታ ግጭት ተጀመረ…እዚህ ቦታ ሽብር ተቀሰቀሰ…” እያልን፣ በዜናና በዜማ የምናልፈው አይደለም፡፡ በድሮው መንግሥት ጊዜ መግለጫው ውስጥ “ዳሩ ሲነካ መሀከሉ ዳር ይሆናል” ይባል ነበር፡፡ ትልቅ እውነት ነው፡፡ በየዳር አገሩ የሚፈጠሩትን ግጭቶች ቸል ማለት ቢያንስ የዋህነት ነው፡፡ የምንመኘው ብልጽግናና እድገት እውን የሚሆነው ቅንነት፣ ታታሪነትና  የመነሳሳት መንፈስ ሲኖር ነው፡፡ ያ በሌለበት ሂደት ውስጥ ያለን ከሆነ ግን “ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” የሚለውን የአበው አባባል እንድናሰላስል እንገደዳለን፡፡በአሜሪካ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ፣ ከሞቀ ቤታቸው እየወጡ፣ ጎዳና አዳሪ የሚሆኑ ዜጎች ቁጥር በየጊዜው እያሻቀበ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ምክንያቱ ደግሞ ከሥራቸው እየተባረሩ፣ ለቤት ኪራይ የሚከፍሉት ገንዘብ በማጣታቸው ነው ተብሏል፡፡
 የ34 ዓመቷ ሜሊሳ ኖርማን፣ ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ከገጠማቸው አሜሪካውያን አንዷ ናት፡፡  ከምትኖርበት ሆስቴል ወጥታ በቶርኩዌይ ዴቮን አቅራቢያ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ድንኳን ተክላ ለመኖር የተገደደችው፣ ለቤት ኪራይ የምትከፍለው ገንዘብ በማጣቷ ነው፡፡
ለአካባቢው አስተዳደር ጎዳና ልትወጣ መሆኑን ማሳወቋን የጠቆመችው ኖርማን፤ ሆኖም የጊዜያዊ መኖሪያ ቤት ፍላጐት በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ሳቢያ፣ ከዓመት በፊት ቤት እንደማታገኝ እንደነገሯት ገልጻለች፡፡  
 “ወደ ሆስቴሉ የገባሁት አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ከመዘጋታቸው በፊት ነበር። ከዚያም በወረርሽኙ ሳቢያ የምሰራበት ማክዶናልድ መዘጋቱን ተከትሎ፣ ሥራዬን በማጣቴ፣ የሆስቴሉን ኪራይ እየከፈልኩ መቀጠል አልቻልኩም፡፡” ትላለች፤ ኖርማን።
በማከልም፤ “በድንኳን ውስጥ መኖር ከጀመርኩ ከሳምንት በላይ ሆኖኛል። አስተዳደሩ በተራ ጠባቂ ዝርዝር ውስጥ መሆኔን ነግሮኛል፤ ግን ቤት ለማግኘት እስከ አንድ ዓመት ድረስ ይወስዳል።; ብላለች፡፡
“ቅዝቃዜው እያየለ መጥቷል፤ እስካሁን የክረምት ድጋፍ አልተደረገልንም፡፡ ለወትሮው የመስክ መኝታ (ስሊፒንግ ባግ) እንደ ግላስቶንበሪ ከመሳሰሉ ፌስቲቫሎች እናገኝ ነበር፤ ዘንድሮ ግን ፌስቲቫሎች በመሰረዛቸው ምንም አላገኘንም፡፡"
"ከ16 ዓመቴ ጀምሮ ከሥራ አልተለየሁም፤ ያልከፈልኩት ግብርም የለም፡፡ ይሄ የሚያሳምም ነገር ነው" ስትልም ኖርማን ተናግራለች - እኒህን ሁሉ ዓመታት ሰርታ ጎዳና መውጣቷ እንደሚያበግናት በመግለጽ።
“ጎዳና ልትወጣ ስትል ለቶርባይ አስተዳደር የምትደውልበት ቁጥር አላቸው፤ ነገር ግን አንድ ሰው ጎዳና መውጣትህን እስኪያረጋግጥልህ ድረስ መደወሉ ለውጥ አያመጣም፤ እናም በዚህ መሃል ያ ሰው ጎዳና  ወጥቶ ያርፈዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ አይገኝም፡፡” በማለትም ታስረዳለች፤ ሜሊሳ ኖርማን፡፡  
የአስተዳደሩ ሃላፊ ክርስቲን ካርተር በበኩላቸው፤ “እንደ አብዛኞቹ የአገሪቱ አካባቢዎች፣ በተባባሰው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ፣ በአማራጭ የመኖሪያ ቤቶች አገልግሎታችን ፍላጎት ረገድ፣ ከፍተኛ መጨመር እያየን ሲሆን ቡድናችን ጊዜያዊ ማረፊያዎችን ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ ለማቅረብ በርትቶ እየሰራ ነው::” ብለዋል::    
የኮቪድ 19 ጦስ ብዙ ነው፡፡ በቫይረሱ መያዝ ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡ ከሥራ ገበታ ያፈናቅላል፡፡ ገቢ አሳጥቶም ተደጓሚ ያደርጋል፡፡ ከሞቀ መኖሪያ ቤት አስወጥቶ፣ ለጎዳና ኑሮም ይዳርጋል፡፡  አያድርስ ነው!


  የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ዋነኛ አጋር እንደሆኑ የሚነገርላቸው አንድ የአገሪቱ ፖለቲከኛ፤ በጸረ-ሙስና ባለሥልጣናት በውስጥ ሱሪያቸው ውስጥ በርካታ የገንዘብ ኖቶች ከተገኘባቸው በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተዘግቧል፡፡  
በመጀመሪያ ላይ 1ሺ 380 ፓውንድ እና 4ሺ 650 ፓውንድ ነው በሴናተር ቺኮ ሮድሪጉ መኖሪያ ቤት ካዝና ውስጥ የተገኘው ተብሏል፤ባለፈው ረቡዕ ፖሊስ በመኖሪያ ቤታቸው ባደረገው ፍተሻ፡፡ በዚህ ብቻ ግን አላበቃም፡፡
ሴናተሩ ወደ መታጠቢያ ክፍል እንዲሄዱ የተጠየቁ ሲሆን በእርምጃቸው ወቅትም በውስጥ ሱሪያቸው ውስጥ ትልቅ ባለ አራት ማዕዘን ቅርጽ፣ የታሰረ ነገር መደበቃቸውን፣ አንድ የፖሊስ ኃላፊ ይደርስበታል፡፡   
“ከውስጥ ሱሪያቸው ከመቀመጫቸው አካባቢም ባጠቃላይ 2ሺ ፓውንድ ተገኝቷል” ይላል፤ የፖሊስ ሪፖርት፡፡
ከዚያም ተጨማሪ ገንዘብ በውስጥ ሱሪያቸው ውስጥ ይኖር እንደሆነ ለሦስተኛ ጊዜ ተጠየቁ፡፡ በጥያቄው የተበሳጩት ሴናተሩ፤ እየተነጫነጩ እጃቸውን ወደ ውስጥ ሱሪያቸው ይልካሉ፡፡ እጃቸው ባዶውን አልተመለሰም፡፡ ሌላ 2ሺ 500 ፓውንድ ጎትቶ አወጣ፡፡ ከዚያ በኋላ በተደረገ ፍተሻም፣ 35 ፓውንድ መገኘቱን ፖሊስ ጠቁሟል። በአሁኑ ሰዓት ሴናተር ቺኮ ሮድሪጉ፣ በቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ ታውቋል፡፡


 የፌስቡኩን መስራች ማርክ ዙከርበርግና የማይክሮሶፍቱን መስራች ቢል ጌትስን ጨምሮ 9 አሜሪካውያን ቢሊየነሮች ባለፈው ሰኞ ብቻ በድምሩ 14 ቢሊዮን ዶላር ያህል ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡
በዕለቱ በአሜሪካ የተለያዩ የአክሲዮን ገበያዎች የዋጋ ቅናሽ መከሰቱን ተከትሎ፣ ቢሊየነሮቹ በድምሩ 14 ቢሊዮን ዶላር መክሰራቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ ማርክ ዙከርበርግ ከፍተኛውን የ2.8 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠመው አመልክቷል፡፡
ቢል ጌትስ ሰኞ ዕለት ሃብቱ በ1.7 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ 115 ቢሊዮን ዶላር ያህል መድረሱን የገለጸው ዘገባው፤ ከአስሩ የአሜሪካ ዋነኛ ባለጸጎች መካከል በዕለቱ የሃብት መጠኑ የጨመረው የአማዞኑ መስራች ጄፍ ቤዞስ ብቻ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

    ቦይንግ 20 በመቶ ሰራተኞቹን እንደሚቀንስ አስታወቀ

          ፌስቡክ፣ ጉግልና ማይክሮሶፍትን ጨምሮ ግዙፍ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በከፋ ድህነት ውስጥ ለሚገኙ አገራት በየአመቱ በግብር መልክ መክፈል የሚገባቸውን 2.8 ቢሊዮን ዶላር በማጭበርበር እንደማይከፍሉ አንድ ጥናት ማረጋገጡን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
አክሽንኤይድ ኢንተርናሽናል የተባለው አለማቀፍ ተቋም የሰራውን ጥናት ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ በየአመቱ እጅግ ከፍተኛ ትርፍ የሚያጋብሱት እነዚህ ግዙፍ ኩባንያዎች፣ ዜጎች በከፋ ድህነት ለሚማቅቁባቸው ድሃ አገራት መክፈል የሚገባቸውን ግብር በአግባቡ እየከፈሉ አይደለም፡፡
እነዚህ ግዙፍ ኩባንያዎች ከድሃ አገራት በየአመቱ የሚያጭበረብሩት ከፍተኛ ገንዘብ ለ850 ሺህ ያህል የአገራቱ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ደመወዝ መሆን የሚችል ነው ያለው ጥናቱ፤ ኩባንያዎቹ ከፍተኛ መጠን ያለው ግብር ካጭበረበሩባቸው አገራት መካከል ህንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ብራዚል፣ ናይጀሪያና ባንግላዴሽ እንደሚገኙበትም አመልክቷል፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ፣ ቦይንግ እስከ መጪው የፈረንጆች አመት 2021 መጨረሻ ድረስ ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ውስጥ 20 በመቶ ያህሉን ወይም 7 ሺህ ገደማ ሰራተኞቹን ከስራ እንደሚቀንስ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በምርቶቹ ደህንነት ጉድለትና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ የከፋ ቀውስ ውስጥ የገባው የአሜሪካው ግዙፍ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ፤ እስካለፈው መስከረም በነበሩት ወራት 466 ሚሊዮን ዶላር መክሰሩንና ከዚህ በፊትም 10 በመቶ ሰራተኞቹን ማሰናበቱንም ዘገባው አመልክቷል፡፡


          ታዋቂው ናይጀሪያዊ ጸሃፌ ተውኔት፣ ገጣሚና ደራሲ ወሌ ሾይንካ፣ የረጅም ልቦለድ መጽሐፍ ለህትመት ካበቃ ከ50 አመታት በኋላ በቅርቡ አዲስ መጽሐፍ ሊያሳትም ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
የኖቤል ስነጽሑፍ ሽልማትን በማግኘት የመጀመሪያው አፍሪካዊ የሆነው የ86 አመቱ አንጋፋ ደራሲ ወሌ ሾይንካ፤ በኮሮና ቫይረስ ወቅት ከቤቱ ባለመውጣት ያገኘውን መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ የጻፈውና በቅርቡ ለህትመት ይበቃል የተባለው መጽሐፍ “ክሮኒክልስ ኦፍ ዘ ሃፒየስት ፒዩፕል ኦን አርዝ” የሚል ርዕስ እንዳለውም ዘገባው አመልክቷል፡፡
ከጓደኝነት እስከ ጠላትነት፣ ከእምነት እስከ ክህደት፣ ከተስፈኝነት እስከ ጨለምተኝነት የተለያዩ ለየቅል የሆኑ የህይወት መልኮችን ይዳስሳል የተባለው አዲሱ የሾይንካ መጽሐፍ፤ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ በናይጀሪያ ታትሞ በገበያ ላይ ይውላል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆመው ዘገባው፣ ከወራት በኋላ ደግሞ በውጭ አገራት ታትሞ ለአለማቀፍ ገበያ እንደሚሰራጭ አስታውቋል፡፡
ሾይንካ “ዘ ኢንተርፕሬተርስ” የሚል ርዕስ ያለውን የመጀመሪያውን ተወዳጅ የልቦለድ መጽሐፉን ለአንባብያን ያቀረበው እ.ኤ.አ በ1965 እንደነበር ያወሳው ዘገባው፤ በ1973 ካሳተመው “ሲዝን ኦፍ አኖሚ” የተሰኘ ሁለተኛ ስራው በኋላ ረጅም ልቦለድ አሳትሞ እንደማያውቅም አስታውሷል፡፡
ወሌ ሾይንካ በኮሮና ሳቢያ ለወራት በነበረው የቤት ውስጥ ቆይታው ከአዲሱ የረጅም ልቦለድ መጽሐፉ በተጨማሪ አዲስ ትያትር መጻፉንም የጠቆመው ዘገባው፤ ከዚህ በፊት ለተመልካቾች ያቀረበውን “ዴዝ ኤንድ ዘ ኪንግስ ሆርስማን” የተሰኘውን ትያትሩን በታህሳስ ወር በአዲስ መልክ አዘጋጅቶ በሌጎስ ለእይታ ለማብቃት ማቀዱንም አክሎ ገልጧል፡፡


  በአለማችን በሳምንቱ ከ2 ሚ. በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ተገኝተዋል

            በአለማችን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛው ነው የተባለው ሳምንታዊ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ባለፈው ሳምንት መመዝገቡንና በሳምንቱ በመላው አለም ከ2 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸውን የአለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
በሳምንቱ በመላው አለም ከተመዘገቡት አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች መካከል ወደ ግማሽ የሚጠጉት በአውሮፓ አገራት እንደሚገኙ የዘገበው ቢቢሲ፤ በአውሮፓ አገራት በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በየዕለቱ ለሞት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ መጨመሩንም የአለም የጤና ድርጅትን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ አስነብቧል።
በድርጅቱ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ዳይሬክተር ማይክ ሪያን ባለፈው ሰኞ እንዳሉት፣ ቫይረሱ ከየትኛውም የአለም ክፍል በተለየ ሁኔታ በአውሮፓ አገራት እየተስፋፋ የሚገኝ ሲሆን አውሮፓ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን በሞት ልትነጠቅ ትችላለች፤ የከፋውን ጥፋት ለመቀነስ አገራት ሙሉ ለሙሉ እስከ መዘጋት የሚደርስ ቁርጠኝነት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመላው አውሮፓ የከፋና አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመር ታይቷል ያሉት የአለም የጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ዶ/ር ማርጋሬት ሃሪስ፤ ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በየቀኑ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ሦስተኛ ሲጨምር፣ የሚመዘገበው የሞት መጠን በ40 በመቶ ከፍ ማለቱንም ተናግረዋል።
በአብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ሆስፒታሎች የሚገኙ የጽኑ ህሙማን የህክምና ክፍሎች በቫይረሱ ተጠቂዎች ከአፍ እስከ ገደፋቸው መሙላታቸውን መናገራቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
በአሜሪካ ባለፈው ሳምንት ብቻ ግማሽ ሚሊዮን ያህል አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን የዘገበው ዘ ጋርዲያን በበኩሉ፤ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እስካለፈው ረቡዕ 1.74 ሚሊዮን መድረሱን፣ የሟቾች ቁጥር ወደ 42 ሺህ መጠጋቱን፣ ያገገሙት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ1.42 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ጠቁሟል፡፡ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በታደሙበት የእራት ግብዣ ላይ የተገኘ አንድ እንግዳ በኮሮና ቫይረስ መያዙ መረጋገጡን ተከትሎ፣ ራሳቸውን ማግለላቸውን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

Page 13 of 512