Administrator

Administrator

Wednesday, 25 January 2017 07:44

የፍቅር ጥግ

- የመጀመሪያ ፍቅርን የሚያህል ነገር የለም፡፡
   ኒኮላስ ስፓርክስ
- ፍቅር ቃል የመግባት ጉዳይ አይደለም፤ የማመን ጉዳይ እንጂ፡፡
   አናሚካ ሚሽራ
- የመጀመሪያ ፍቅሬ፡፡ እሱ የመጀመሪያ ተወዳጅ ስህተቴ ነበር፡፡
  ሎውረን ብላክሌይ
- የመጀመሪያ ፍቅር ሁልጊዜ ልዩ ቦታ ይይዛል፡፡
   ሊ ኮኒትዝ
- የመጀመሪያ ፍቅር አደገኛ የሚሆነው የመጨረሻም ጭምር ሲሆን ብቻ ነው፡፡
   ብራኒስላቭ ኑሲክ
- የሴት ልጅ ደስታ የሚጀምረው በመጀመሪያ ፍቅሯ ነው፡፡ ከዚያም ያከትማል፡፡
   ጆርጅ በርናርድ ሾው
- እኛ፤ ይገባናል ብለን የምናስበውን ፍቅር እንቀበላለን፡፡
    ስቲፈን ቸቦስኪ
- አፍቃሪ ልብ ሁልጊዜ ወጣት ነው፡፡
    የግሪኮች አባባል
- ቤተሰብ ከየት ይጀምራል? ጥንስሱ የሚጀምረው ኮቦሌው ከኮረዳዋ ጋር በፍቅር ሲወድቅ ነው፡፡ እስካሁን ሌላ የላቀ አማራጭ አልተገኘም፡፡
    ሰር ዊንስተን ቸርችል
- የ40 ዓመት ጎልማሳ ከ20 ዓመት ኮረዳ ጋር በፍቅር ሲወድቅ፤ እየፈለገ ያለው የእሷን ወጣትነት ሳይሆን የራሱን ነው፡፡
    ሊኖሬ ኮፊ
- ፍቅር እንደ አበባ ነው፤ አንዴ ከቀጠፍከው በኋላ ቀስ እያለ ይጠወልጋል፡፡
    ያልታወቀ ጸሃፊ

Wednesday, 25 January 2017 07:33

ማራኪ አንቀፅ

   ሊብራዎች ብልግና አይወዱም፡፡ ሰው ያፈቅራሉ፡፡ ብዙ ህዝብ ወደተሰበሰበበት መሄድ ግን አይፈቅዱም፡፡ እንደ ሰላም ምልክቷ ጨዋ እርግብ፣ የተጣላ ማስታረቅ ይወዳሉ፤ ክርክር ይሆናቸዋል፡፡ ጥሩ ባህሪ ያላቸው ናቸው እና አስደሳቾች ናቸው፡፡ አንዳንዴ ግን ለንቦጫቸውን የሚጥሉ አኩራፊዎችና ትዕዛዝ የማይቀበሉ ለጋሚዎች ይሆናሉ፡፡ በአንድ በኩል እጅግ በጣም ብልሆች ሲሆኑ በሌላ ጎናቸው ደግሞ እጅግ በጣም ገራገርና የዋሆች እንዲሁም ድልሎች ናቸው፡፡ አነብናቢዎች ቢሆኑም ጥ ሩ አ ድማጮችም ይሆናሉ፡፡ ግራ ተጋቡ እንዴ? ራሳቸውም በራሳቸው እስከሚገረሙ ድረስ ሊብራዎች ጠባያቸው ይዋዥቃል፡፡ ብዙ ሰው ሊብራዎች “ፍቅር ናቸው፤ ውበት ናቸው፣ ጣፋጭ ናቸው፣ ብርሃን ናቸው” ይላል፤ ጥሩ ነው። ግን በወርቅ የፍትህ ሚዛን እንደሚመሰሉም ማስታወስ ይጠቅማል፡፡ ሚዛኑ በቀላሉ ይዋዥቃል። ተስተካክሎ እንደቆመ ረግቶ ላይገኝ ይችላል፡፡ የሚዛን ሁሉ ተግባሩ ተስተካክሎ መቆም ነው፡፡ ተስተካክሎ ለመቆም ምን ይሆናል? ይዋዥቃል፡፡ አንዴ በዚህ፣ አንዴ በዚያ ተስተካክሎ እስከሚቆም ይዋዥቃል፡፡ ስለዚህ ሊብራን “ፍቅር፣ ውበት፣ ጣፋጭና ብርሃን” ሆኖ የሚያገኙት እድሜ ልክዎን ሳይሆን ለግማሹ ጊዜዎ ነው፡፡ በግማሹ አናዳጅ፣ ቁንጥንጥና ግራ የተጋባ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ፡፡ የሊብራ ስሜት እንደሚዛን መዋዠቅ ጠባዩ ነው፡፡ ፍቅር ሰጠት ሲያደርጉት ግን ወዲውኑ ይስተካከላል፡፡ አካላዊ መልካቸውም እንደ ጠባያቸው ይስባል፡፡ ዲምፕል አላቸው፡፡ከዚያ
ይጀምሩ እና ቶሎ በግልጽ ወደማይታየው ውበታቸው ይግቡ፡፡ ዲምፕሉ በጉንጫቸው ላይ ካልታየ በእግራቸው ላይ መገኘቱ አይቀርም፡፡ ዲምፕል ሊብራ ባልሆኑ ሰዎች ላይም የሚገኘው የቬኑስ ተፅዕኖ ካረፈባቸው ነው፡፡ ዲምፕሉን ካገኙ በኋላ ፊታቸውን በአጠቃላይ
ይመልከቱ፣ አስደሳች ውበት ይታይዎታል፡፡ ሲቆጡ እንኳ ገራምነት ይነበብባቸዋል፡፡ ድምጻቸው ጣፋጭና ኮለል፣ እንደሞል ደወል ጥርት ያለ ነው፡፡ ሊብራዎች “ጠላሁህ!፣ ጥርስህን ላረግፍልህ ነው!” ብለው በጥሩ የድምጽ ቃና በግልጽ የሚናገሩ፣ በዓለም ላይ ልዩ የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ከንፈሮቻቸው ውቦችና ጉንጮቻቸውም እንደ ቸኮሌት የሚያጓጉ ናቸው፡፡ ሴቶቹም ወንዶቹም ቆንጆዎች ናቸው፡፡ ኮከባቸው ቬኑስ የውበት ተምሳሌት ናት፡፡ ሊብራ ሴቶች ሱሪ መልበስ ይወዳሉ፡፡ ወንዳ ወንድ ናቸው ማለቴ አይደለም፡፡ የተለየ ለዛ ያላቸው ልስልስና ወላንሳ ሴቶች ናቸው፡፡ ደም ግባታቸው ይማርካል፤ ፈገግታቸው ያቀልጣል፤ ሙሉ በሙሉ ካረፈብዎ ወከክ፣ ትርክክ ነው የሚሉት፡፡ ፀጉራቸው ከርል ነው፤ የታውረስ ተጽእኖ ካላረፈባቸው በስተቀር ወፍራሞች አይደሉም፡፡ ሌላው የሚስብዎ ነገር ደስ የሚል ሳቃቸው ነው፡፡ አንዴ ከሰሙት
አይረሳዎትም፡፡ አሁን ባለ ዲምፕልና ማራኪ ሆኖ መወለድ፣ ፍትሀዊና ተፈቃሪ መሆን፣ አስደሳችና በቀላሉም ተደሳች ሆኖ የመፈጠር ፀጋ መሆኑን ሳይረዱ አልቀሩም፡፡ ጨዋነት እና ብልህነት፣ ግርማ ሞገስ እና ሌሎችን የሚገነዘብ /አንደርስታንድ የሚያደርግ/ ኅሊናም የፈጣሪ ስጦታዎች መሆናቸውን ተገንዝበዋል፡፡ ሊብራ የወርቅ ሚዛኑ ሲስተካከልለት እነዚህን ሁሉ ይጣበሳል፡፡ ይህም ሰማያዊ መልዓከ ምድር ላይ የማግኘት ያህል የሚያስደስት ነገር ነው። ችግሩ ሚዛኑ ሲዋዥቅ ነው፤ ቢሆንም ፍቅር ሰጠት ሲያደርጉ ፈጥኖ ይስተካከልለታል፡፡
 
    (ከተርጓሚ አብርሃም ጎዝጉዜ “የፀሐይ ምልክቶች” የተሰኘ የአስትሮሎጂ መፅሃፍ ላይ የተቀነጨበ፡፡ ተርጓሚው የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳን
   “The True Origin of Oromo and Amhara” የተሰኘ አነጋጋሪ መፅሐፍ “እውነተኛው የኦሮሞና
   የአማራ የዘር ምንጭ” በሚል የተረጎሙ ናቸው፡፡

     የ3000 ዘመን ታሪክ ባለቤት ከሆነችው ኢትዮጵያ አንድ ፍልስፍና ይመዘዛል፡፡ ይኸውም በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ብቅ ያለው የኢትዮጵያ የፍልስፍና አባት ለማለት የምንደፍርለት ዘርዐ ያዕቆብ ነው፡፡ በዓለም ላይ የተከሰቱ ርዕዮተ ዓለሞችን ሁሉ የፍልስፍና ውጥንና ውጤት መሆናቸው እሙን ነው፡፡ የዘርዐ ያዕቆብ ምናብ ብቻ ሳይሆን ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ ጥብቅ ሀሳቦች የተነሱበት እውነት፤ ሐተታ ዘርዐ ያዕቆብ የረቀቁ የበለጸጉና የጠለቁ ትንታኔዎችን በመስጠት ነፍሳችንን ይክሰዋል፡፡ ለፍልስፍና አእማድ የሆነው ዘርዐ ያዕቆብ፤ “ማንነትን በበጎ ነገር ማጠር” በማለት የሚያቀነቅነው አስተሳሰብ ውስጥ የሚበቅሉ የእውነት ምንጮችን እናገኝበታለን፡፡ በዚህም ወደ ታላቁ የጥበብ ምንጭ እንመጥቃለን፤ ውለታውን ለማስታወስ፣ ኢትዮጵያዊነቱን ለመመስከር ዝክረ ዘርዐ ያዕቆብ ተዘጋጅቷል፡፡

ውልደትና እድገት
ዘርዐ ያዕቆብ የክርስትና ስሙ ሲሆን የዓለም ስሙ ወርቄ እንደሆነ በአለቃ ያሬድ ፈንታ “ሐተታ ዘርዐ ያዕቆብ ወልደ ሕይወት” መግቢያ ላይ ተጠቅሷል፡፡ እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘርዐ ያዕቆብ በገጠር ስለመወለዱ ታሪኩን የሚዳስሱ የተለያዩ ጽሑፎች ያስረዳሉ፡፡ ከገበሬ ቤተሰብ መገኘቱን በገዛ አንደበቱ የሚናገረው ዘርዐ ያዕቆብ፤ በ1592 ዓ.ም ወደዚህ አለም መጥቷል፡፡ ይሄ ዘመን ደግሞ የአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት መሆኑ ነው፡፡
እንደ ቅዱስ ያሬድ፣ እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለትምህርት የሰነፈ ባይሆንም የድምጹ ሻካራነትና የተማሪ ቤት ወዳጆቹ ስላቅ፣ ሰዋሰውና ቅኔ ለመማር ፊቱን እንዲያዞር ያስገደደው ሲሆን እግዚአብሔርም ጥበቡን እንደገለፀለትም ደስተኛ እንደሆነ መፅሀፈ ፍልስፍና ላይ ተጠቅሷል፡፡ ለንባብና ለማወቅ ያደረገውን ጥረት ሳንቆጥር፣ ዘርዐ ያዕቆብ 14 ዓመት ከሦስት ወር ለትምህርት በመጠቀም የትምህርትን ህልውና ለማሳየት ጥረት አድርጓል፡፡ ያውም በዚያ ዘመን!!

ትዳርና ልጅ
አፈንጋጩ ዘርዐ ያዕቆብ ከፍልስፍና ልጆች የሚቃረነው የትዳር ጓደኛ ምርጫው ጋብቻውን አክባሪነቱ ከመረዳት እንጀምርና ከእርሱ እውቀትና ምጥቀት የማትስተካከለዋን የሀብቱ ቤተሰብ ለማግባት ሲጠይቅ፣ ሲደራደር እሺኝታ ሲያገኝ፣ ሚስቱን ለማስደሰት ሲጥር እንመለከታለን፡፡ በእርሱ አንደበት፤ “ይህ መንገድ ወደ አበሳ ይስባልና ሴት የሌለችው ወንድ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንደማይገባው አወቅኩ” ሰዎች ተፈጥሮአቸውን ክደው ሊኖሩ አይገባቸው እያለ ይሞግታል፡፡ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ከሚለው መለኮታዊ ሃሳብ ጋር ስምሙ የሚያደርገው፣ እምነቱን በዘመን ተሻጋሪ ስብከቱ ሲያስጠነቅቅ፡- የባልና ሚስት ድንበርና ክልሉ ፍቅር መሆን እንዳለበትም አጽእኖት ይሰጣል፡፡
መልከ ጥፉ እንደሆነች የሚመሰክርላት ሂሩት፤ ምግባሯን ልባምነቷን መመዘኛ ማድረጉ፣ ጠንካራ የሆነ የፍቅር እምነት እንዳለው ለማሳየት ምስክር ይሆናል፡፡ ከአራት ዓመት በኋላ ልጁ ሀብተ እግዚአብሔርን መውለዱ፣ ዘርዐ ያዕቆብ የቤተሰብ ምጣኔን የያኔ ጀምሮታል ለማለት ያስደፍራል። ከፅሁፍ ስራ ባገኘው ሀብት ቤት ከሰራና የቤት እንስሳ ከገዛ በኋላ መውለዱ ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ወደ ምንኩስናው የሸፈተውን የልጁን ልብ መልሶ፣ የሦሶት ልጆች አያት መሆን መቻሉ ለህጋዊነት የላቀ ዋጋ እንደሚሰጥና እምነቱ እንደሆነ ያረጋግጥልናል።

ፍልስፋና
ዘርዐ ዕቆብ ወደ ፍልስፍና የገባባት ምክንያት ምንም ይሁን ምን ተለምዶአዊ አኗኗሮችን በመገርሰስ፤ ባልዘመነ ዘመን፣ ዘመናዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ ይሰጣል፡፡የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ የተመለከታቸው “ሐተታ ዘርዐ ያዕቆብ” ሆነ “መጽሐፈ ፍልስፋና” ሥለ ፈላስፋው ያለንን ግንዛቤ ከማሳደግና እውቀት ከማዳበር በዘለለ ተቃርኖ የላቸውም፡፡ የዘርዐ ዕቆብ የምርምር ፍልስፋና፤ ወሰን ያልተበጀለትና ሁሉን አቀፍ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ በሁለቱም መጽሐፎች ላይ ፈላስፋው በጥልቀት የተመለከታቸውን የእግዚአብሔር ህላዌነት፣ሥነ ምግባር፣ እውነት፣ በዓለም ላይ ስላሉ ሐይማኖቶች እሰጣ ገባ፣ ፍትህ፣ ስለ መለኮታዊውና ሰዋዊ ህግ፣ ማህበራዊ ኑሮና ዘመናዊነት በተመሳሳይ መልኩ ያቀርባል፡፡ አለቃ ያሬድ ፈንታ ለየት ባለ መልኩ የፈላስፋውን የስነ ፍጥረት ሐተታ፣ ከንባብና ትምህርት ስለሚገኝ ጥቅምና ስለተለያዩ ሕይወታዊ ምክሮች በስፋት ሲዳስስ፤ በአንጻሩ “መጽሐፈ ፍልስፋና” በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ስለተነሱ ጥቄዎች ምላሽ ይሰጣል፡፡ የዘርዐ ዕቆብ የፍልስፋና ጥልቀት፤ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው አጥር ክፋት መሆኑን በማስረዳት ይኮንናል፡፡ ፈላስፋው የእግዚአብሔርን መኖር ቢያረጋግጥም የሁሉንም ሐይማኖት ግን ከመንቀፍ ቦዝኖ አያውቅም። ስለዚህ ሐይማኖት ምንድነው ብለን ለመፈተን ጥልቅ ምርምር ይጠይቀናል፡፡ ሰዎች “ሁሌም በራሴ ልክ ነኝ” ከሚል ትምክህት መውጣት አለባቸው የሚለው በምርምሩ የደረሰበት ጥግ ሲሆን ለእናም የሚበጅ መላ ነው፡፡ የፖስት ሞደርኒዝም አቀንቃኝ የሆነው የመካከለኛው ዘመኑ ዘርዐ ያዕቆብ፤ በ68 ዓመቱ ለዚህ ትውልድ የሚረቡ ሁነኛ ሀሳቦችን በተማሪው ግፊት አንደጻፋቸው ይናገራል፡፡

  በተጠናቀቀው የፈረንጆች አመት 2016፣ በአለማችን የተለያዩ አገራት ከ100 በላይ ጋዜጠኞች መገደላቸውን ያስታወቀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፤ በአመቱ በአማካይ በየአራት ቀኑ አንድ ጋዜጠኛ መገደሉን ገለጸ፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም( ዩኔስኮ) በአለማቀፍ ደረጃ የተሰራን የጥናት ውጤት ጠቅሶ እንዳለው፣ በአመቱ በርካታ ጋዜጠኞች የተገደሉት በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአረብ አገራት ሲሆን በርካታ ግድያዎች የተፈጸሙት በሶርያ፣ ኢራቅና የመን ነው፡፡ ምንም እንኳን የጋዜጠኞች ግድያ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ ቢቀንስም፣ በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው የመብት ጥሰትና ግድያ በአለማቀፍ ደረጃ እየተባባሰ ነው ያለው ተቋሙ፤ መንግስታት የጋዜጠኞችን ግድያዎች እንዲያጣሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በፈረንጆች አመት 2015 በአለማችን የተለያዩ አገራት ስራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ የተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር 115 እንደነበርም ተቋሙ አስታውሷል፡፡

  መኪናዋ ያለ አሽከርካሪ ራሷን ችላ የምትንቀሳቀስ ናት

      ታዋቂው የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ኤርባስ ግሩፕ፣ የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነቺና ያለ አሽከርካሪ ራሷን ችላ የምትንቀሳቀስ በራሪ መኪና እየሰራ መሆኑን አስታውቆ፣ እስከ 2017 መጨረሻ የሙከራ በረራ ለማድረግ ማቀዱን ጠቁሟል፡፡
ኩባንያው ቫሃና የሚል ስያሜ የሰጣትንና አንድ ሰው ብቻ የማሳፈር አቅም እንዳላት የተነገረላትን በራሪ መኪና፣ እስከ አዲሱ የፈረንጆች አመት 2017 መጨረሻ ሰርቶ በማጠናቀቅ፣ የበረራ ሙከራ እንደሚያካሂድ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ኤርባስ በአስር አመታት ጊዜ ውስጥም መሰል መኪናዎችን በብዛት በማምረት ለአለም ገበያ የማቅረብ እቅድ እንዳለው ማስታወቁን የጠቆመው ዘገባው፣ እንዲህ ያሉ በራሪ መኪኖች የትራፊክ መጨናነቅን እንደሚያቃልሉና ለመንገድና ለድልድዮች ግንባታ የሚውለውን በቢሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚያድኑ መግለጹን አስረድቷል፡፡

  የ92 አመቱ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤች ደብሊው ቡሽ ባጋጠማቸው የጤና እክል የህክምና እርዳታ ለማግኘት ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ ሂዩስተን በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ቡሽ ከዚህ ቀደምም ለሁለት ጊዚያት ወደዚህ ሆስፒታል ገብተው የመተንፈሻ አካላት ህክምና እንደተደረገላቸው ያስታወሰው ዘገባው፣ በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና ከቀናት በኋላ ህክምናቸውን ጨርሰው ይወጣሉ ተብሎ ከመጠበቁ ውጪ ወደ ሆስፒታል ያስገባቸው በሽታ ምን እንደሆነ አለመገለጹን አስረድቷል፡፡
አሜሪካን እ.ኤአ. ከ1989 እስከ 1993 ያስተዳደሩት 41ኛው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤች ደብሊው ቡሽ፣ በፓርኪንሰንስ ህመም ሳቢያ ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ አቅቷቸው፣ በሰው ድጋፍና በተሽከርካሪ ወንበር ታግዘው መንቀሳቀስ ከጀመሩ አመታት እንዳለፏቸውም ዘገባው አብራርቷል፡፡
ቡሽ ትናንት በተካሄደው የዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ቀጠሮ ቢይዙም ሆስፒታል በመግባታቸው ሳቢያ በዝግጅቱ ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ተነግሯል፡፡

   20 በመቶ ጃፓናውያን ሰራተኞች ለሞት የሚያሰጋ ስራ ይሰራሉ

       የጃፓን መንግስት ዜጎቹ ከሚገባው በላይ ስራ በመስራት ለአደጋ እንዳይጋለጡ ለማድረግ በማሰብ፣ የትርፍ ስራ ሰዓት ገደብ የሚጥል ህግ ሊያወጣ ማቀዱን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘገበ፡፡
በርካታ የአገሪቱ ዜጎች ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት በማሰብ፣ ከመደበኛው የስራ ሰዓታቸው በተጨማሪ የትርፍ ጊዜ ስራ በመስራት ብዙ ሰዓት ተጠምደው እንደሚውሉና እንደሚያድሩ የጠቆመው ዘገባው፤ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙዎች ለጤና ችግር ብሎም ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ መንግስትን እንዳሳሰበው ገልጧል፡፡
20 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ሰራተኛ ህዝብ ከሚገባው በላይ ስራ በመስራት ለሞት የመጋለጥ አደጋ አንዣቦበታል ያለው ዘገባው፤ አብዛኞቹም በወር ከ80 ሰዓታት በላይ የትርፍ ጊዜ ስራ እንደሚሰሩ ገልጧል፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት በሚልም የአገሪቱ መንግስት ከመጪው ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የትርፍ ሰዓት የስራ ገደብ የሚያስቀምጥ ህግ ለማውጣት መወሰኑን ዘገባው አስረድቷል፡፡

Wednesday, 25 January 2017 07:22

የቢዝነስ ጥግ

 - ሁላችንም በአንድ ላይ ነው የምንሰራው፤ ያ ነው ምስጢሩ፡፡
      ሳም ዋልትን (የዎልማርት መስራች)
- ስኬቴ የሚመነጨው በየቀኑ በእጄ ያለውን ስራ ተግቼ ከመስራት ነው፡፡
     ጆኒ ካርሰን
- ለሰዎች የሚጠቅም ከሆነ፣ ለቢዝነስ ይጠቅማል፡፡
    ሊዎ ቡርኔ
- ሰዎች ሲወዱህ የምትለውን ይሰሙሃል፤ ሲያምኑህ ግን አብረውህ ቢዝነስ ይሰራሉ፡፡
    ዚግ ዚግላር
- ታላላቅ ኩባንያዎች የተገነቡት በታላላቅ ምርቶች ላይ ነው፡፡
    ኢሎን ሙስክ
- ስህተት የማይሰሩት የሚተኙ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡
   ኢንግቫር ካምፓርድ (የIKEA መስራች)
- ስሜ በሌለበት ህንፃ ውስጥ ፈፅሞ ኖሬ አላውቅም፡፡
    ኢቫንካ ትራምፕ
- ከሥራዬ በተባረርኩ በነጋታው አዲስ ኩባንያ ጀመርኩ፡፡
     ማይክል ብሉምበርግ
- ለቢዝነስህ ፍቅር ከሌለህ ልትሸጠው፣ ለሰው ልትሰጠው አሊያም ልትለውጠው ይገባል
- በማትወደው ቢዝነስ ውስጥ መዳከር የለብህም፡፡
      ቶኒ ሮቢንስ
- ራስህን ፈፅሞ እንደ አማካይ ሰው አትቁጠር።
     ጆርጅ ሉካስ
- ቢዝነስ አትገነባም፤ የምትገነባው ሰዎችን ነው፤ ከዚያም ሰዎች ቢዝነሱን ይገነባሉ፡፡
     ዶናልድ ትራምፕ (ቢሊዬነርና የአሜሪካ ፕሬዚዳንት)
- ተግቶ መስራት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በእጅጉ ተግተህ ካልሰራህ የትም አትደርስም
     ጆኢል ስፖልስኪ
- የምትሸጠው የማይጠቅመኝ ከሆነ፣ ለምን በሬን ትቆረቁራለህ፡፡
    ጆርጅ ሉካስ
- ቢዝነስ አትገነባም፤ የምትገነባው ሰዎችን ነው፤ ከዚያም ሰዎች ቢዝነሱን ይገነባሉ፡፡
     ዚግ ዚግላር
- ምርታችንን ሳናሻሽል የምናሳልፈው እያንዳንዱ ቀን የባከነ ቀን ነው፡፡
     ጆኢል ስፖልስኪ
- የምትሸጠው የማይጠቅመኝ ከሆነ፣ ለምን በሬን ትቆረቁራለህ፡፡
    ክሪስ ሙሬይ

Sunday, 22 January 2017 00:00

የፖለቲካ ጥግ

- ሰላም መፍጠር የምትሻ ከሆነ፣ ከወዳጆችህ ጋር ሳይሆን ከጠላቶችህ ጋር ትወያያለህ፡፡
    ሞሼ ዳያን
- እኔ መናገር ስፈልግ ማንም አይሰማኝም፤ እነሱ እንድናገር ሲሹ እኔ የምለው የለኝም፡፡
   ዊንስተን ቸርቺል
- የፖለቲካ ልዩነት ሁልጊዜ ጤናማ ውይይት ይፈጥራል፡፡ ከጊዜ በኋላ ግን ውይይቱ ይበልጥ በጥላቻ የተሞላና አልፎ አልፎም ሁከት ፈጣሪ ይሆናል፡፡
    ማርክ ዩዳል
- ምንም የምትለው ነገር ከሌለህ፣ ዝም በል፡፡
   ማርክ ትዌይን
- እንደ ብልህ አስብ፤ነገር ግን በህዝብ ቋንቋ ተግባባ፡፡
   ዊሊያም በትለር ይትስ
- ዲሞክራሲ ማለት በውይይት የሚመራ መንግስት ነው፡፡ ውጤታማ የሚሆነው ግን ሰዎችን ከንግግር መግታት ከቻልክ ነው፡፡
   ክሌሜንት አትሊ
- ፖለቲካዊ ትክክለኛነት ውይይትን ይገድለዋል፡፡
   ላርስ ቮን ትሪዬር
- ውይይት የዕውቀት ልውውጥ ሲሆን ክርክር የድንቁርና ልውውጥ ነው፡፡
    ሮበርት ኪውይሌ
- በውይይት ላይ የሳይንቲስቱ ዓላማ ማግባባት አይደለም፤ ማብራራት እንጂ፡፡
    ሊዎ ስዚላርድ

ታዋቂዋ የሆሊውድ የፊልም ተዋናይት አንጀሊና ጁሊ በ2007 ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ የወሰደቻት ዘሃራ ወላጅ እናት፤ ‹‹በህይወት አለሁ፤አንጀሊና ከልጄ ጋር እንድገናኝ  ትፍቀድልኝ›› በማለት መማፀኗ ተዘግቧል፡፡
አሁን የ12 ዓመት ታዳጊ የሆነችው ዘሃራ ወላጅ እናት፣ ወ/ት ምንትዋብ ዳዊት ሌቢሶ፤ ‹‹እባክሽን አንጀሊና፤ ልጄን እንዳነጋግራት ብቻ ፍቀጅልኝ›› ስትል በተማፅኖ መጠየቋን የእንግሊዙ “ዴይሊ ሜል ኦንላይን” ዘግቧል፡፡
በደቡብ ክልል ሾኔ ከተማ ከወላጅ እናቷ ጋር በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የምትገኘው ወ/ት ምንትዋብ፤  ዘሃራን በ19 ዓመቷ በማታውቀው ሰው ተደፍራ መውለዷን፣ ጠቁማ፤ ከወሊድ በኋላ ለረዥም ጊዜ በመታመሟ በቤተሰቧ ግፊት ልጇን ለአሳዳጊ ድርጅት ለመስጠት መገደዷን ተናግራለች፡፡
‹‹ልጄን ላለፉት 12 አመታት በቀንም በሌት ሆነ ሳስባት የቀረሁበት ጊዜ የለም›› ያለችው ወላጅ እናቷ፤ ‹‹አሁን ግን የልጄን ናፍቆት መቋቋም አልቻልኩም፤ ልጄ ልክ እንደ አሳዳጊዋ  የምትወዳትና የምትሳሳለት ወላጅ እናት እንዳላት እንድታውቅ እፈልጋለሁ›› ብላለች ከዴይሊ ሜል ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ፡፡
አንጀሊና ልጄን በማደጎነት ከወሰደቻት በኋላ ባሉት ጊዜያት ምንም ዓይነት ደብዳቤም ይሁን  መልዕክት አሊያም ገንዘብ ደርሶኝ አያውቅም›› ብላለች፤ የ31 ዓመቷ የዘሀራ ወላጅ እናት
‹‹እንዲያም ሆኖም ዘሃራ ወላጅ እናት እንዳላት እንድታውቅና እንድትጠይቀኝ ብቻ እንጂ ልጅቷን ከአንጀሊና ላይ የመውሰድ ፍላጎት የለኝም›› በማለት አስረድታለች፡፡
እውቋ የሆሊውድ ተዋናይት አንጀሊና ጁሊ፤ በ1997 ዓ.ም ዘሃራን ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ ለማሳደግ ስትወስዳት፣ ወላጆቿን በኤችአይቪ ያጣች ህፃን መሆኗ ተነግሯት እንደነበር ያስታወሰው ዴይሊ ሜል፤ ከ2 ዓመት በኋላ ግን ወላጅ እንዳላት መስማቷን ጠቁሟል፡፡