Administrator

Administrator

በባህር ዳርና በአዲስ አበባ ከ15 ዓመታት በላይ በምሽት ክበቦች ሰርቷል፡፡ “ስያሜ አጣሁላት” በሚለው የመጀመሪያ አልበሙ ከህዝብ ጋር የተዋወቀው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ፤ ሦስተኛ አልበሙን (ስወድላት) ሰሞኑን ለቋል፡፡ በአዲሱ ስራውም ስለ ሃገር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ ታማኝነት፣ ስለ ጎንደር፣ ስለ ወሎና ምንጃር ብዙ አቀንቅኗል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ፤ ከድምፃዊ ማዲንጐ ጋር በአዲሱ አልበሙና በሙያው ዙሪያ ተከታዩን ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡
የመጀመሪያ ስራህ “ስያሜ አጣሁላት” የሚል ነበር፡፡ በሁለተኛው “አይደረግም” ብለህ መጣህ፡፡ አሁን ደግሞ “ስወድላት” እያልክ ነው…
የመጀመሪያው አልበሜ የልጅነት ስራዬ ነው፡፡ ያኔ ጠቆር ያልኩ ነበርኩኝ፤ እንዳሁኑ አልገፈፍኩም ነበር፡፡ አሁን እንደ እባብ ቆዳ ቀይሬያለሁ፡፡ የሆነ ሆኖ “ስያሜ አጣሁላት” በልጅነት እድሜ ከህዝብ ያገናኘኝ ስራ ነው፡፡ ወቅቱ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ነበር፡፡ ታዲያ “ስያሜ  አጣሁላት” እና “አማን ነው ወይ ጎራው” የተሰኙት ሁለት ዘፈኖች በተለየ መልኩ ተወደውልኝ ነበር፡፡ ሁለተኛው ስራዬ የትዝታ ዘፈን ያለበት “አይደረግም” በሚል ስያሜ የወጣው ነው፡፡ አሁን “ስወድላት”ን ይዤ ወደ አድማጭ ቀርቤያለሁ፡፡
በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት “ስያሜ አጣሁላት” እና “አማን ነው ወይ ጎራው” የተወደዱበት ምክንያት ምንድን ነው? ከጦርነቱ ጋር የተገናኘ ሃሳብ ይዘዋል እንዴ?
በተለይ “ስያሜ አጣሁላት” ከኤርትራ ጠብ አጫሪነት ጋር ሳይያያዝ አይቀርም፡፡ እኔ በወቅቱ እንደነገርኩሽ ልጅ ስለነበርኩ ጉዳዩ አይገባኝም ነበር፡፡ ግጥሙን የፃፈው አንጋፋው የሙዚቃ ግጥም ደራሲ ይልማ ገ/አብ ነበር፡፡ ይልምሽ ደግሞ ወቅታዊ ፈጠራዎችን በመስራት አይታማም፡፡ አሁን ነው የሚገባኝ፡፡ እኔ ከሴት ልጅ ፍቅር ጋር ብቻ ነበር አገናኝቼ የዘፈንኩት፡፡ በነገራችን ላይ አሁንም ቢሆን ግጥሙ ከወቅቱ ጦርነት ጋር እንዲሄድ ሆን ተብሎ ይሰራ አይሰራ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ግምቴን ነው የነገርኩሽ፡፡
ሁለተኛው አልበምህ “አይደረግም” የሶስት አራት ድምፃዊያንን ትዝታ አፈራርቀህ የሰራህበት ሲሆን የትዝታው ዘፈን ድምፅህ የተፈተነበትና ወደ አድማጭ በደንብ የቀረብክበት እንደሆነ ይነገራል፡፡ እውነት ነው?
በጣም ትክክል ነው፡፡ እኔም ባለውለታዬ የምለው ዘፈን ትዝታው ነው፡፡ የእኔ የመዝፈን ብቃት ምን ያህል እንደሆነ ለህዝብ ግልፅ ያደረገ ስራ በመሆኑ በሚባለው ነገር መቶ በመቶ እስማማለሁ፡፡
“አይደረግም” ከወጣ ረዘም ያለ ዓመት ሆኖታል… ባልሳሳት ሰባት ዓመት አካባቢ… ለምን እንደዚህ ቆየህ?
ተቃርበሻል! ስምንት ዓመት አልፏል አልበም ሳልሰራ፡፡ በመሃል ግን የተሳኩና የተወደዱ ነጠላ ዜማዎችን ሰርቻለሁ፡፡ ለምሳሌ “የበላይ ዘለቀ”፣ “አንበሳው አገሳ”፣ ለ“አባይ ወይስ ቬጋስ” ፊልም የሰራሁት ማጀቢያ ሙዚቃ “አባይ ወይስ ቬጋስ” ህዝቡ ስምንት ዓመት አልበም አለመስራቴን እንዳያስታውስ አድርገውታል፡፡ ከህዝብ ጆሮ አልጠፋሁም ነበር ማለት ነው፡፡ በዚያ ላይ ኮንሰርቶች እሰራለሁ፤ የሰርግ ስራዎችንም እንደዚሁ፡፡ ይህን ስታይው ስምንት ዓመት ሙሉ የጠፋሁ አይመስልም፡፡ ከዚህ በኋላ ግን እንደዚህ አልጠፋም፤ በየሁለት አመቱ አልበም ይኖረኛል፡፡
አዲሱ አልበምህ በግጥማና ዜማ የነማን አስተዋፅኦ አለበት? ምን ያህል ጊዜስ ወሰደ?
በመጀመሪያ ደረጃ የአልበሙን ስራ ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ የወሰድኩት እኔ ነኝ፡፡
ምን ማለት ነው?   
ይሄ ማለት ግጥምና ዜማ የመምረጡን ስራ ያለምንም ጣልቃ ገብነት የተወጣሁት እኔው ነኝ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ሙዚቃ ውስጥ እንደመሆኔ፣ ግጥምና ዜማን በማስተዋል በኩል ጥሩ ተሰጥኦ አለኝ ብዬ አምናለሁ፡፡ የአልበሙን ግጥምና ዜማ የመረጥኩት ራሴ ነኝ፡፡ ነገር ግን ግጥምና ዜማ እንዲሰሩ ትልልቅ የሚባሉና የካበተ ልምድ ያላቸውን ሰዎች አሳትፌአለሁ፡፡ ይልማ ገ/አብ፣ ጸጋዬ ደቦጭ፣ አበበ ብርሃኔ፣ አማኑኤል ይልማ፣ ታመነ መኮንን፣ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ መኮንን ለማ (ዶክተሬ) እና መሰል ታዋቂዎች ተሳትፈዋል፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት የተለያዩ ግጥምና ዜማዎችን ስሰበስብና ስመርጥ ነው የቆየሁት፡፡ 30 ዘፈኖች መረጥኩና ስቱዲዮ ተቀረፅኩ፤ ከ30ው ግን 14ቱን ነው የመረጥኩት፡፡ 14ቱም ዘፈኖች አንዱ ከአንዱ እንዳይበልጥና በጥሩ ሁኔታ እንዲደመጥ ከፍተኛ ጥንቃቄና ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ እነዚህ ዘፈኖች የቀደመውን (የወርቃማውን ዘመን) የሙዚቃ ደረጃ እንዲይዙ ነው የፈለግሁት፡፡
የወርቃማው ዘመን ድምፃዊያን የሚባሉት እነማን ናቸው? የአሁኑ አልበህም ያስቀመጥከውን ደረጃ አሳክቷል ብለህ ታስባለህ?
ኤፍሬም ታምሩ፣ ንዋይ ደበበ፣ ፀጋዬ እሸቱ፣ አረጋኸኝ ወራሽ ያሉበት ዘመን  ለእኔ ወርቃማውና የምወደው ዘመን ነው፡፡ እኔም ያን ዘመን ሊያስታውሱ የሚችሉ በሳል ዘፈኖችን ከአሁኑ ትውልድም እንዳይርቁ አድርጌ ሰርቻለሁ፡፡ አልበሙ ሰሞኑን ነው የወጣው፤ በእነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ የደረሰኝ የአድማጮች አስተያየትና ምላሽ ያለምኩትን ግብ እንደመታሁ አመላካች ነው ብዬ አምኜያለሁ፡፡
በአንድ ወቅት አልበም ማሳተም ተቀዛቅዞ ነበር፡፡ አሁን አሁን ዘፋኞች ደፈር እያላችሁ የመጣችሁ ትመስላላችሁ?
ልክ ነው፤ የአልበም ስራ የተኛበት ጊዜ ነበር፡፡ ይሄ የቅጂ መብት ጉዳይ ዘፋኙንም አሳታሚውንም ተስፋ አስቆርጦት ነበር፡፡ አሁን እነ ሸዋንዳኝ፣ እነ ሚካኤል በላይነህ፣ እነ ታምራት ደስታ፣ እነ አብነትና ሌሎችም ደፍረው አልበም በማውጣታቸው ሌሎቻችንን አበረታተውናል፡፡ አሁን ሰውም ኦሪጂናል አልበም የመግዛት ፍላጎቱ እየጨመረ መምጣቱን ያወቅሁት፣ የእኔ አልበም በወጣ በሶስተኛው ቀን እንኳን በጥሩ ሁኔታ በመሸጥ ላይ መሆኑን ስመለከት ነው፡፡
አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ በትክክል ምን ያህል ጊዜ ፈጀብህ?
ግጥምና ዜማ መምረጥ የጀመርኩት ከስምንት ዓመት በፊት ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ስቱዲዮ መግባትና ስራውን በደንብ መስራት የጀመርኩት ከአምስት ዓመት በፊት ነው፡፡ ያልገባሁበት ያልወጣሁበት ስቱዲዮ የለም፡፡
ለምንድነው በየስቱዲዮው እየገባህ የወጣኸው?
ያሉትን ግጥምና ዜማዎች ይዤ ስራውን እጀምራለሁ፤ ነገር ግን መርካት አልቻልኩም፡፡ አንድ ስራ ይዤ እገባና አያስደስተኝም ትቼ እወጣለሁ፡፡ ይህን ሳደርግ በራሴ የገንዘብ ኪሳራ ነው፤ ዛሬ አንድ ዘፈን ለመስራት ከ20 ሺህ ብር በላይ ይጠይቃል፡፡ ቅንብር 10 ሺህ ብር፣ ግጥምና ዜማ በቀላሉ 10 ሺህ ብር ወጪ ይጠይቃሉ፡፡ ሌሎች ጥቃቅን ወጪዎችን ሳይጨምር ማለት ነው፡፡ ከኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ጋር የዛሬ ስድስት ዓመት ነው የተፈራረምኩት፡፡ ስንፈራረም ግን በራሴ ስራውን አጠናቅቄ ማስተሩን ላስረክበው ተስማምተን ነው፡፡ ይሄ ማለት ዜማ፣ ግጥም ቅንብር… እያንዳንዱ ወጪና ልፋት በእኔ ላይ ነበር፡፡ ታዲያ ከስድስት አመት በፊት የነበረው ዋጋና የአሁኑ ልዩነቱ ሰማይና ምድር ነው፡፡ በዚያ ላይ ስቱዲዮ ገብቼ ጀምሬ የተውኳቸው አሉ፡፡ ያ ኪሳራ በራሴ ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደነገርኩሽ 30 ዘፈን ሰርቼ፣ 14ቱን ብቻ ነው የመረጥኩት፡፡ 16ቱ ቀሩ ማለት ነው፡፡
ታዲያ ምን ያህል ወጪ ወጣበት አዲሱ አልበምህ?
ያለማጋነን ከ500 ሺህ ብር በላይ አውጥቻለሁ፤ ሆኖም ለህዝብ ጆሮ የሚመጥን ስራ እንደሰራሁ ይሰማኛል፡፡ ራሴን በጣም አስደስቶኛልና፡፡
ከአንተና ከእህትህ ትዕግስት አፈወርቅ ሌላም ታናናሽ ድምፃዊ እህትና ወንድሞች አሉህ ይባላል፡፡ እንደነ አምስቱ እርጎዬዎችና እንደነ ጃክሰን ፋሚሊ “የአፈወርቅ ቤተሰቦች” ለመባል እየተቃረባችሁ ነው ወይስ?
እኛ እንኳን የአፈወርቅ ቤተሰቦች ለመባል አልበቃንም፤ ምክንያቱም በሙዚቃው ነጥረን የወጣነው እኔና ትዕግስት ብቻ ነን፡፡ አንድ ወንድሜ ፍላጎት ስላለው በመሞከር ሂደት ላይ ነው፡፡ ካናዳ ነው የሚኖረው፡፡ ጂጂ የምትባለው የታናሼ ታናሽ በጣም የሚገርምና የሚመስጥ ድምፅ አላት፤ ነገር ግን ዘማሪ መሆን ነው የምትፈልገው፡፡ አሁን እንግሊዝ ነው የምትኖረው፤ ስለዚህ የአፈወርቅ ቤተሰቦች ለመባል አልደረሰንም፡፡ እኔና  ትዕግስት ግን ወደፊት አስተዳደጋችንን፣ ባህላችንን የሚያሳይ አንድ ዘፈን የመስራት ሃሳብ አለን፡፡
ብዙ አድናቂዎች እንዳሉህ ይታወቃል፡፡ አንተስ የማን አድናቂ ነህ?
ኢትዮጵያ የቅዱስ ያሬድ አገር ናት፡፡ በቤተክርስቲያን ስትቀርቢ ዜማ ማህሌትና የመሳሰሉት ያስደምሙኛል፡፡ ወደ ዘፈኑ ስትመጪ አገራችን ብዙ አንጋፋና ተሰጥኦ ያላቸው ድምፃዊያንን አፍርታለች፤ ከእነ ጥላሁን ገሰሰ ጀምሮ፡፡ እኔ ሞዴል ብዬ የያዝኩትና ወደ ሙዚቃው እንድገባ የተሳብኩት በኤፍሬም ታምሩ ነው፤ በጣም ነው የምወደው፡፡ ሙሉቀን መለሰን፣ ቴዎድሮስ ታደሰን፣ እነ ጸጋዬ፣ አረጋኸኝ… እንዲሁም ቀደም ሲል ወርቃማው ዘመን ላይ የነበሩ ብዬ የገለፅኩልሽን በሙሉ አደንቃለሁ፡፡ ቀደም ካሉት ፍሬው ኃይሉ የቤተ-ክህነት አይነት ድምፅ ስላለው እወደዋለሁ፡፡ ከወጣቶች ጎሳዬ፣ ብዙአየሁ፣ አብነት፣ ቴዲ አፍሮን አደንቃለሁ፡፡
ግጥምና ዜማ ድርሰት ላይ እንዴት ነህ?
ባለፈው አልበም ላይ “አፋር” የተሰኘውን ዜማ ሰርቻለሁ፡፡ “ማን እንደኔ ንገሪኛ”፣ “አባይ ወይስ ቬጋስ” እና “አንበሳው አገሳ” የኔ ዜማዎች ናቸው፤ ዜማ ላይ ምንም አልልም፡፡ ግጥም ግን ሰርቼ አላውቅም፡፡ በአሁኑ አልበሜ ላይ በዜማም አልተሳተፍኩም፤ ሁሉንም በሌሎች ባለሙያዎች ነው ያሰራሁት፡፡
በአዲሱ አልበምህ እስካሁን ከመጡት አስተያየቶች በጣም ያስደመመህ አለ?
ያው ብዙ አስተያየቶች ይመጣሉ፡፡ በአብዛኛው አድናቆትና ማበረታታት ናቸው፡፡ አንድ ሰው ግን ደውሎ “ለገና ለበግ መግዣ ያስቀመጥኩትን ብር የአንተን ሲዲ እየገዛሁ ለወዳጅ ዘመድ አድዬበታለሁ፤ በጉን አንተ ግዛልኝ” ብሎኛል፡፡ በጣም ገርሞኛል፡፡ አንዳንዴ ሰው ሲወድሽ እንዲህ ሁሉ ያደርጋል፡፡ ሌላው ችሎታህን በአሁኑ አልበም ላይ በአግባቡ ተጠቅመሃል የሚል አበረታች አስተያየት ነው፡፡
ታዲያ ምን አሰብክ… በጉን ትገዛለታለህ?
 እገዛለታለሁ፡፡ ይሄ ሰው እኮ ሲዲውን ሲገዛ ገንዘቤ በተዘዋዋሪ እኔው ኪስ ገብቷል፡፡ ስለዚህ ደስ እያለኝ እገዛለታለሁ፡፡
በመጨረሻስ….
በመጨረሻ እንግዲህ ይሄ አልበም እንዲህ አምሮ እንዲወጣ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉት የግጥምና ዜማ ደራሲዎች አመሰግናለሁ፡፡ የተለያዩ ጉዳዮችን በማስጨረስ ድካሜን ሲያቀልልኝ የነበረው የአቻሬ ጫማ ባለቤት (አቻሬ) ሳላመሰግነው አላልፍም፡፡ አቀናባሪ ሙሉጌታ አባተና ኤልያስ መልካ፣ እህቴ ትዕግስት አፈወርቅን፣ ማርታ ዘለቀን፣ አህመድ ተሾመንና ሌሎችም በመዘንጋት ስማቸውን ያላነሳሁትን ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ የሙዚቃው ኢንዱስትሪ በደከመበት በአሁኑ ወቅት ከጎኔ ሆኖ የክብር ስፖንሰር የሆነኝን ዳሽን ቢራንና የኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤትን አቶ ተሾመ ፀጋዬን እንዲሁም በአስተያየት እየኮተኮተ ያሳደገኝን የኢትዮጵያን ህዝብ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም ብድሩን ይክፈልልኝ እላለሁ፡፡ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን የገናን በዓል በሰላም አሳለፋችሁ፤ መጪው የጥምቀት በዓል የምትደሰቱበት ይሁን እላለሁ፤ አመሰግናለሁ፡፡

(በእውቀቱ ስዩም)

በሰላላው መንገድ
የትየለሌ እግር፣ እንደ ሊጥ ባቦካው
ጸአዳ ጣትሽን ፣ጉድፍ እንዳይነካው
ማጡን እየዘለልሽ
ዳጥ ዳጡን እያለፍሽ
ጤዛ የወረረው ዛፍ እየተደገፍሽ
ትንሽ ስትመጭ
ብዙ ስታዘግሚ
ሁለቴ ተራምደሽ፣ አስሬ ስትቆሚ...
ለተደናገረው ፣መንገድ ስትጠቁሚ
የተላከ ሕጻን ፣አስቁመሽ ስትስሚ…

እኔ ስናፍቅሽ
እኔ ስጠብቅሽ
እንደ ጉድ ተውቤ
ላማልልሽ ጥሬ
በጆንትራ ዘይቤ
ጠጉሬን አበጥሬ
ጅማት እያጠበቅሁ፣ጅማት እያላላሁ
የገዛ ከንፈሬን ፣ቀርጥፌ እየበላሁ፡፡
ስጠብቅሽ በጣም
ምስልሽ ነው እንጂ አካልሽ አልመጣም፡፡

ባይኖቼ ስፈልግ
መስኮት እከፍትና
ሌላ ነው የሚያልፈው ፣በሰፊው ጎዳና
ያው ገጣባ አህያ፣ያቻት ድኩም በቅሎ
በግ እየጎተተ፣አለፈ ቆለኛ
ቅርጫት ያጎበጣት ፣ሚስቱን አስከትሎ
ያውና ድሀ አደግ ፣መንገድ ዳር የተኛ
የተጎነጎነ፣የሣር አምባር መስሎ፡፡
ባይኖቼ ሳማትር ፣መስኮት እከፍትና
ሌላ ነው የሚያልፈው፣ በሰፊው ጎዳና፡፡

ሁሉም ተለውጦ
ያ ገጣባ አህያ፣ ጸጉር አቆጥቁጦ
ያች ድኩም በቅሎ ፣ሰጋር ፈረስ ቀድማ
ቆለኛው ሰውየ፣ ሙክት በጉን ሽጦ
ለሚስቱ ነጭ ሻሽ ፣ለሱ ሸራ ጫማ
በትርፉ ሸምቶ
ሁሉም ከሄደበት ፣ቀንቶት ተመልሶ
ሁሉም ከድቀቱ፣ በወግ ተፈውሶ
እኔ ብቻ ቀረሁ፡፡
መንገድሽ ረዝሞ፣ ባሳብ እያሳጠርሁ፡፡
አንቺን እየናፈቅሁ
አንቺን እየጠበቅሁ
ጅማት እያላላሁ፣ ጅማት እያጠበቅሁ፡፡

በደራሲ ቤል ፍቃዱ ተፅፎ የተዘጋጀውና ፕሮዱዩስ የተደረገው “የማይደገም ስጦታ” የተሰኘ ፊልም ባለፈው ሃሙስ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመረቀ፡፡ በያኔት ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ፊልሙ፤ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ድራማ ዘውግ ያለው ሲሆን አንድ ሰው ለፍቅር የሚከፍለውን መስዋእትነት እንደሚያሳይ ደራሲውና አዘጋጁ ቤል ፍቃዱ ተናግሯል፡፡ ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመት ተኩል እንደፈጀ የተነገረለት ፊልሙ፤ ከ350 ሺህ ብር በላይ እንደወጣበትና የ90 ደቂቃ ርዝማኔ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በፊልሙ ላይ መስፍን አስፋው፣ በለጠ አንፃኪያ፣ ብሩክታዊት ፋንታሁን፣ ማርታ አሸናፊ፣ አለማየሁ በዛብህና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡

በአዲስ ዓመት ዋዜማ “አስታራቂ” በሚል ርዕስ አልበም አውጥቶ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው ድምፃዊ አብነት አጐናፍር “አስታራቂ” የተሰኘ ኮንሰርት ዛሬ በጊዮን ሆቴል ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ያቀርባል፡፡ የተለያዩ ድርጅቶች በጋራ ባዘጋጁት በዚህ ኮንሰርት ላይ ሚካኤል በላይነህ ከዘመን ባንድ ጋር የቀድሞ ስራዎቹን ካቀረበ በኋላ ዋናው የኮንሰርቱ አቅራቢ አብነት አጐናፍር በ “ኬር” ባንድ በመታጀብ ተወዳጅ ስራዎቹን እንደሚያቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጊዮን ሆቴል ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሩ የሚከፈት ሲሆን ከ10-12 ሰዓት በዲጄ ሙዚቃ እና በወጣት ድምፃዊያን፣ እንዲሁም በሚካኤል በላይነህ ስራዎች ታዳሚዎች እየተዝናኑ ቆይተው ወደ አብነት ስራዎች ይሸጋገራሉ ተብሏል፡፡ የኮንሰርቱ መግቢያ ለቪአይፒ 650 ብር ሲሆን ሌላው በ400 ብር እንደሚታደም ታውቋል፡፡
በተያያዘ ዜና ወጣቱ ድምፃዊ አቤል መሉጌታ ዛሬ ምሽት በኤግዚቢሽን ማዕከል “ልብ በ40 ዓመት” የተሰኘ ኮንሰርቱን ያቀርባል፡፡
በሀለ ኮሙኒኬሽን ኤንድ ኤቨንትስ ባዘጋጀው በዚህ ኮንሰርት ላይ ድምፃዊ አቤልን “ጊዜ ባንድ” ያጅበዋል የተባለ ሲሆን፤ በዲጄ ኪንግሰትን (ወዝወዝ) ፋታ እየወሰደ ስራዎቹን እስከ ምሽቱ 3፡00 ሰዓት ለታዳሚው እንደሚያቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኤግዚቢሽን ማዕከል በር ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ክፍት የሚሆን ሲሆን መግቢያው አንድ መቶ ብር እንደሆነም ታውቋል፡፡

የወጪ ንግዱ ባለፉት አምስት ወራት መሻሻል እንዳሳየ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በአገሪቱ ያለው የዋጋ ንረት በህዳር ወር ከነበረበት 5.9 በመቶ ጭማሪ በማሳየት፣ በታህሳስ ወር ወደ 7.1 በመቶ ማደጉን ትናንት አስታወቀ፡፡ የንግድ ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የአገሪቱ የወጪ ንግድ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ባለፉት አምስት ወራት በ10.7 በመቶ እድገት ማሳየቱን ከትናንት በስቲያ አስታውቋል፡፡
ሮይተርስ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የዋጋ ንረቱ ጭማሪ ሊያሳይ የቻለው በምግብና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ ከፍ ያለ የዋጋ ጭማሪ በመከሰቱ ሲሆን ስኳር፣ አትክልቶችና ፍራፍሬዎችን የመሳሰሉ ሸቀጦች ዋጋ በህዳር ወር ከነበረበት 4.8 በመቶ፣ በታህሳስ ወር ወደ 6.5 በመቶ ከፍ እንዳለ አስታውቋል፡፡
ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ዋጋ ላይም በተመሳሳይ ወቅት ከ7.1 ወደ 7.8 በመቶ ጭማሪ መታየቱን የጠቆመው ዘገባው፤ በአመቱ የአገሪቱ የዋጋ ንረት 9.1 ደርሶ እንደነበር አስታውሶ፣ ንረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲቀንስ እንደቆየ ገልጿል፡፡
የንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አማከለ ይማም በበኩላቸው፤ አገሪቱ ባለፉት አምስት ወራት ለወጪ ንግድ ካቀረበቻቸው የግብርና፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የማዕድን ምርቶች 1.16 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ለአናዶሉ ኤጀንሲ ገልጸዋል፡፡
ለወጪ ንግዱ ገቢ መሻሻል አስተዋጽዖ ካበረከቱ የኤክስፖርት ምርቶች መካከል የቡና ምርት በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ የገለጸው ዘገባው፣ አገሪቱ በተጠቀሰው ጊዜ 62 ሺህ 560 ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ አቅዳ፣ ከእቅዱ በላይ 64 ሺህ 228 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ ማቅረቧን ጠቁሟል፡፡

ፍርዱ በአፋጣኝ ተግባራዊ እንዲደረግ ተጠይቋል
በሳዑዲ አረቢያ ከሁለት አመታት በፊት አሰሪዋን በመጥረቢያ ደብድባ ገድላለች በሚል ክስ የተመሰረተባት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ፤ በጣይፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ እንደተፈረደባት አረብ ኒውስ ከትናንት በስቲያ ዘገበ፡፡
በደቡባዊ ጣይፍ ግዛት በምትገኘው ሙሳይላት የተባለች መንደር በቤት ሰራተኛነት ስታገለግል የነበረችውና ስሟ ያልተገለጸው ኢትዮጵያዊቷ፣ ፍርዱን በመቃወም ይግባኝ መጠየቋን የጠቆመው ዘገባው፣ የመካ ፖሊስ ቃል አቀባይ በበኩላቸው፤ ግለሰቧ ዝርፊያ ለመፈጸም በማሰብ ወንጀሉን እንደፈጸመች ተናግረዋል፡፡
በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደምትገኝ የተነገረላት ኢትዮጵያዊቷ፤ በስግደት ላይ በነበረችዋ አሰሪዋ ላይ ወንጀሉን ከፈጸመች በኋላ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏንና በወቅቱም በእጇ ላይ 7 ሺህ የሳዑዲ ሪያል (ገንዘብ) መገኘቱን ዘገባው ያስረዳል፡፡
የሟቿ ባለቤት በበኩሉ፤ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደተደሰተ ገልጾ፣ የሞት ፍርዱ በአፋጣኝ ተግባራዊ እንዲደረግ መጠየቁምን አረብ ኒውስ አክሎ ገልጿል፡

መሠረት የበጎ አድራጐት ድርጅት 480 ችግረኛ ቤተሰቦች የገና በዓልን በደስታ እንዲያከብሩ  የዶሮና የእንቁላል ስጦታ ማበርከቱን ገለፀ፡፡
ለእያንዳንዱ ቤተሰብ አንድ ዶሮና ስድስት እንቁላል፣ በአጠቃላይ 480 ዶሮዎችንና 2880 እንቁላሎች የተበረከተ ሲሆን 64ሺ ብር እንደፈጀም ታውቋል፡፡
ለችግረኛ ቤተሰቦች የተበረከተው ስጦታ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  ከ5 ብር ጀምሮ ባደረጉት መዋጮ እንደሆነ መሰረት በጎ አድራጎት አስታውቋል፡፡
ይሄ ድጋፍ የተደረገበትን ዓላማ ያስረዱት የበጎ አድራጎቱ መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት አዛገ፤ “የባህል እሴቶቻችን ተጠብቀው ሁሉም ቤተሰብ ከልጆቹና ከጐረቤቱ ጋር ባህሉን በደስታ እንዲያከብርና ማንም ሰው ደሀ በመሆኑ ምክንያት በአሉን በችግር እንዳያሳልፍ ለማድረግ ነው” ብለዋል፡፡ መስራቿ፤ ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ለረዷቸው የተለያዩ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ለበጐ ፈቃድ አገልጋዮች፣ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
መሠረት የበጐ አድራጐት ድርጅት፤ በድህነት ለሚኖሩ ሴቶችና ህፃናት የተለያዩ ድጋፎችና ዕድሎች በመስጠት በማብቃት የሚተጋ የበጐ አድራጐት ድርጅት ነው፡፡  

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በስነ ፅሁፍና በስዕል ጥበብ ላይ የተሰማሩ ደራሲያንን፣ ሰአሊያንንና  በዘርፉ እየሰለጠኑ የሚገኙ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች የሚያሳትፍ በስነ ፅሁፍ፣ በግጥም እንዲሁም በስዕል ዘርፎች በማወዳደር በመሸለም በተሻለ ስራ እውቅና ሊያገኙ የሚችሉበትን መድረክ ማመቻቸቱን ገለፀ፡፡
በዚሁ በዳሽን አርት አዋርድ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችን ለመዳኘት ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር፣ ከኢትዮጵያ ሰአሊያን ማህበር፣ ከዜማ ብዕር ኢትዮጵያ ሴቶች የስነፅሁፍ ማህበርና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስነ ጥበባት ተመርጠው መሄዳቸውም ተገልጿል፡፡
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ/ማ ስፖርትና ኪነጥበብን በመሳሰሉ ሀገራዊ፣ ማህበራዊ እና ህዝባዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

   በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች ለከንቲባው ጀርባቸውን ሰጥተዋል

   ባለፈው ወር መጨረሻ፡፡ አንድ ተሲያት ላይ ከብሮክሊን ሰማይ ስር ተደጋጋሚ የተኩስ ድምጽ ተሰማ፡፡ የተኩሱን ድምጽ የሰሙት የከተማዋ ፖሊሶች በአፋጣኝ ወደ ስፍራው ሲያመሩ፣ አስደንጋጭ ትእይንት ገጠማቸው፡፡ ራፋኤል ራሞስ እና ዌንጂን ሊዩ የተባሉ ሁለት የፖሊስ ባልደረቦች በጥይት ተመትተው ደማቸውን እያፈሰሱ ጎዳና ዳር ወድቀዋል፡፡ ተኳሹ ኢስማኤል ብሪንስሊ የተባለ ግለሰብ ነበር፡፡ ሰበቡ ደግሞ ንዴት፡፡ብሪንስሊ ከጥቂት ጊዜያት በፊት በፈርጉሰን እና በኒውዮርክ ሲቲ በነጭ ፖሊሶች በተገደሉት ሁለት ጥቁሮች ጉዳይ በንዴት ሲብከነከን ሰንብቷል፡፡ ንዴቱንና ቂሙን መርሳት ያልሆነለት ይሄው ግለሰብ ታዲያ፣ በገና ዋዜማ ጠመንጃውን አንስቶ ወደ ብሮክሊን ለበቀል ተንደረደረ፡፡ በሁለት ፖሊሶች ላይ አነጣጠረ፡፡ ጥይት ቆጠረ፡፡ በስተመጨረሻም በገዛ ጠበንጃው ራሱን አጠፋ፡፡
በግለሰቡ ድርጊትና መንግስት ተገቢውን ፍትህ ለመስጠት አልቻለም በሚል ክፉኛ የተበሳጩት በርካታ የኒውዮርክ ሲቲ ፖሊሶችም ታዲያ፣ ነግ በእኔ ብለው ተቃውሟቸውን በግልጽ አሰምተዋል፡፡ ላለፉት ሁለት ሳምንታት መደበኛ ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን መተዋቸውንም ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡ፖሊሶቹ ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን ማቆማቸውን ተከትሎ በከተማዋ ያለው የወንጀል ቁጥር መላላቱ ተነግሯል፡፡ ወንጀለኞችን በአግባቡ በቁጥጥር ስር በማዋል ከህገወጦች በቅጣት መልክ ሊሰበሰብ የሚገባው ገንዘብ እየተሰበሰበ አይደለም፡፡ ዘ ታይምስ እንዳለው፤ የከተማዋ ፖሊሶች ወንጀለኞችን በአግባቡ በቁጥጥር ውስጥ ለማዋል ተግተው ባለመስራታቸው የወንጀል ክሶች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል፡፡ በቁጥጥር ውስጥ የሚውሉ ወንጀለኞች ቁጥር 66 በመቶ ያህል ቀንሷል፡፡ ባለፈው ሳምንት በከተማዋ ፖሊስ የተያዙ የወንጀል ክሶች 347 ብቻ መሆኑንና፣ ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ይህ ቁጥር ከ4 ሺህ በላይ እንደነበር ዘ ታይምስ ዘግቧል፡፡ ቀረጥና ፓርኪንግን ከመሳሰሉ ነገሮች የሚገኘው የመንግስት ገቢም፣ ስራ በፈቱ ፖሊሶች ሳቢያ በአግባቡ ሊሰበሰብ ባለመቻሉ ከ90 በመቶ በላይ ቀንሷል፡፡ ይህም በከተማዋ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ጫና እየፈጠረ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡የፖሊስ አባላት ስራ መፍታታቸው ምንም እንኳን በከተማዋ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በማበራከት ረገድ ይህ ነው የሚባል ተጽዕኖ ባይፈጥርም፣ በአንድ አካባቢ የዝርፊያ ድርጊቶች ከወትሮው በተለየ ከፍ ማለታቸውን የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ያሳያል፡፡ ባለፈው ሳምንት በተከበረው የፈረንጆች የገና በዓል ዋዜማ ላይ በተከናወነው የሟቹ የስራ ባልደረባቸውን ዌንጃን ሊዩን የቀብር ስነስርዓት ላይ የተገኙት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች የከተማዋ ከንቲባ ቢል ዲ ባላሲዮ ወደ መድረክ ወጥተው የሃዘን መግለጫቸውን ሲያስተላልፉ ጀርባቸውን ሰጥተዋቸው ነበር - ተገቢውን ምላሽ አልሰጡንም በሚል፡፡
የከተማዋ የፖሊስ ኮሚሽነር ቢል ብራተን ባልደረቦቻቸው በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ተቃውሞ እንዳያሰሙ አበክረው ቢያስጠነቅቁም፣ ፖሊሶቹ ግን ማስጠንቀቂያውን ችላ ብለው ተቃውሟቸውን በግልጽ አሳይተዋል፡፡የፖሊስ አባላቱን አቋም በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ሲሆን፣ ለመብታቸው መከበር በጽናት መቆማቸውን ያደነቁ መኖራቸውን ያህል፣ በወጉ ከመንግስት ጋር ተወያይተው መፍትሄ መሻት ሲገባቸው ስራ መፍታታቸውን ክፉኛ የተቹም ብዙዎች ናቸው፡፡
 ይህ ድርጊት ያናደዳቸውና የፖሊሶች እምቢ ባይነት ያበሳጫቸው የከተማዋ ከንቲባም ታዲያ የፖሊስ አባላቱ በዚሁ ድርጊታቸው የሚገፉና የዕለት ተዕለት ስራቸውን በአግባቡ የማያከናውኑ ከሆነ፣ ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ተቆጥሮ በሌሎች እንደሚተኩ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል፡፡


የኢቦላ በሽታ ተጠቂዎችን የመፈወስ አቅም ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀውን ብሪንሲዶፎቪር የተባለ መድሃኒት በታማሚዎች ላይ የመሞከር ስራ ላይቤሪያ በሚገኘው የድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን የህክምና ማዕከል ውስጥ መጀመሩ ተዘገበ፡፡በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተዘጋጀው መድሃኒቱ፣ በቫይረሱ በተያዙ ፈቃደኛ ግለሰቦች ላይ እየተሞከረ እንደሚገኝ የዘገበው ቢቢሲ፣ ውጤቱ በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ይታወቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጿል፡፡
ምንም እንኳን ከወራት በፊት ሌሎች መድሃኒቶች ተመርተው በታማሚዎች ላይ ቢሞከሩም፣ አንዳቸውም ፈዋሽነት ሳይኖራቸው እንደቀሩ ዘገባው አስታውሷል፡፡የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ይህንን መድሃኒት በታማሚዎች ላይ ለመሞከር የወሰኑት፣ መድሃኒቱ በቤተ ሙከራዎች ውስጥ በሚገኙ በኢቦላ ቫይረስ የተጠቁ ህዋሳት ላይ ተሞክሮ ውጤታማነቱ በመረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡
መድሃኒቱ በኢቦላ በተጠቁ 100 የአገሪቱ ዜጎች ላይ እየተሞከረ እንደሚገኝና ጎን ለጎንም ሌሎች ምርምሮች መካሄዳቸው እንደሚቀጥል ዘገባው አስታውቋል፡፡


እስካሁን ያለው የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል?
በኛ በኩል የምርጫው ሂደት በተቀመጠለት አቅጣጫ መሠረት እየሄደ ነው፡፡ ቀድመን ስትራቴጂና እቅድ አዘጋጅተናል፡፡ ካለፉት ምርጫዎች በተሻለ ለመንቀሳቀስ ዝግጅት አድርገን ነው እየሰራን ያለነው፡፡ ሃገሪቱን እንደሚመራ ገዢ ፓርቲና ተወዳዳሪ ፓርቲ ሁለት ሚናዎች ነው ያሉት፡፡ በመንግስት በኩል (ሀገሪቱን የሚመራ ፓርቲ እንደመሆኑ) ምርጫውን ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ሠላማዊ በማድረግ ረገድ እየተሠራ ነው፡፡ እንደ ተወዳዳሪ ፓርቲ ደግሞ አሸናፊ ሆነን የምንወጣበትን አጠቃላይ ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡ እንደ ድርጅት፣ በስነምግባር ደንቡና በአጠቃላይ በምርጫ ህጐቹ ሂደት ላይ የአሠልጣኞች ስልጠና በከፍተኛ የአመራር ደረጃ ሰሞኑን ተሰጥቷል፡፡
በየደረጃው ለሌሎችም ስልጠናው ይሰጣል፡፡ ካለፉት ምርጫ ልምዶች ተነስተን 5ኛው ሃገራዊ ምርጫ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ፣ ወሳኙ ህዝብ ስለሆነ የህዝቡን ወሳኝነት ለማረጋገጥ እየተንቀሳቀስን ነው፡፡
ከህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ጋር ተያይዞ ተቃዋሚዎች፤ “ኢህአዴግ የ1ለ5 አደረጃጀቱን ተጠቅሞ አባላቱን አስመርጧል” ሲሉ ይወቅሣሉ፤ በዚህ ላይ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው?
የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫን በተመለከተ አንዳንድ ፓርቲዎች መሠል አስተያየቶችን ሲያቀርቡ ሰምተናል፡፡ አንደኛው ወቀሳቸው፣ የታዛቢዎች ምርጫ የተካሄደው ለኛ ሣይነገረን ኢህአዴግ ብቻ ተነግሮት ነው የሚል ነው፤ ይሄ በጣም መሠረታዊ ስህተት ነው፤ ምክንያቱም ኢህአዴግም እነዚህ ፓርቲዎችም ባሉበት የምርጫ ጊዜ ሠሌዳው ቀርቦ ውይይት አድርገንበታል፡፡ ምርጫ ቦርድ ያወጣው የጊዜ ሠሌዳ ኢህአዴግን ጨምሮ ለእያንዳንዱ ፓርቲ አቅርቧል፡፡ ስለዚህ ታህሣሥ 12  የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች በሚዲያም ቀርበው ታህሣሥ 12 የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ በሚስጥር የተደረገ ነው፤ የሚለው የተሣሣተ ነው፤ በይፋ በደብዳቤም በሚዲያም ተገልጿል፡፡
በእለቱም ኢህአዴግ አባሎቹ እንዳይመረጡ ጥንቃቄ አድርጓል፡፡ አንዳንድ ቦታ እንኳ አባሎቻችን ሲጠቆሙ “እኔ አባል ነኝ፤ አልችልም” ብለው ከምርጫው የወጡበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ ይህ የተቃዋሚዎች ውንጀላ የተለመደ ሂደቱን ከጅምሩ ጥላሸት የመቀባት አካል ነው፡፡ የተመረጡት የህዝብ ታዛቢዎች ገለልተኛ አይደሉም ለማስባል የሚረዳ ተራ የስም ማጥፋት ሂደት ነው፡፡
1ለ5 የሚባለው ለመንግስት የልማት ስራ የተደራጀ ነው እንጂ የፓርቲው አደረጃጀት አይደለም፡፡ የተቃዋሚም የኢህአዴግም አባል የሆነ ሊኖር ይችላል፤ ስለዚህ የ1ለ5 አደረጃጀትን ሂዱና የህዝብ ታዛቢ ምረጡ ቢል ችግር የለውም ማለት ነው፡፡ ኢህአዴግን ምረጡ ወይም ደጋፊ የሆነን ሰው ምረጡ የሚባል ነገር የለም፡፡ ስለዚህ በ1ለ5 አደረጃጀት ላይ ብዥታ ሊኖር አይገባም፤ አደረጃጀቱ የልማት አደረጃጀት ነው፡፡ ይህን አደረጃጀት ሂዳችሁ ታዛቢ ምረጡ ወይም በምርጫው ተሳተፉ ቢል ነውር አይደለም፡፡ ከዚህ አንፃር ህዝቡ ገለልተኛ ናቸው ያላቸውን ታዛቢዎቹን መርጧል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ውንጀላዎች ተቀባይነት የሌላቸው፣ ሂደቱን ጥላሸት ለመቀባት ሆነ ተብሎ የሚደረጉ ናቸው፡፡ የኢህአዴግ አባል ተመርጧል የሚሉ ከሆነና የተመረጠበትን ቦታ ከጠቆሙ እኛም ለማጣራት  ዝግጁ ነን፡፡ ድንገት ሾልኮ የገባ ካለም እንዲወጣ እናደርጋለን፡፡ እስካሁን ግን እንዲህ ያለ ነገር ስለመኖሩ ምንም መረጃ የለንም፡፡ ህዝቡ  ምርጫውን ማካሄዱ መብቱን ማረጋገጫ መንገድ ነው፡፡
የምርጫ ስነ ምግባር ደንቡን ካልፈረሙ ፓርቲዎች ጋር ኢህአዴግ ለመወያየት የማይችልበት መሠረታዊ ምክንያት ምንድን ነው? ደንቡን መፈረምን እንደ ግዴታ ማስቀመጥ የውይይት በርን መዝጋት አይሆንም?  
ደንቡ ሲዘጋጅ ብዙ ሂደት አልፏል፡፡ በወቅቱ የነበሩት ፓርቲዎች በእርጋታ እየተወያዩ ያለፉበት ሂደት ነበር፤ በዚህ ሂደት መድረክ ሶስት ጊዜ ረግጦ ወጥቷል፡፡ መጀመሪያ ሂደቱ ሲጀመር ወደ ውይይቱ ተጋብዞ መጣ፤ ያኔ ከኢህአዴግ ጋር እንጂ ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር መወያየት የለብኝም አለ፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ ብዙ ፓርቲዎች ባሉበት ሃገር፣ የተናጥል ውይይት ከእያንዳንዱ ጋር ማድረግ አይችልም፡፡ መድረክ፤ ሌሎች ፓርቲዎች ተቃዋሚዎች አይደሉም የሚል አመለካከት ስለለው ወጣ፡፡ በሌላ ጊዜም ተጋበዘ፤ ሂደቱን ትቶ ወጣ፡፡ ለ3ኛ ጊዜ 65 ፓርቲዎች ሲወያዩ ገብቶ ሂደቱን ለመበተን ነው ጥረት ያደረገው፤ ግን መጨረሻ ላይ 65 ፓርቲዎቹ ተስማምተው ህግ ሆኖ ወጣ፡፡ ህግ ሆኖ ሲወጣ በህጉ ውስጥ የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ አለ፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ አባል ሆኖ ለመቀጠል የፈለገ ፓርቲ ህጉን መፈረም አለበት፡፡ ይሄ ማለት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው፡፡ ስለዚህ የስነ ምግባር ደንቡ ህግ ሆኖ እንዲወጣ ፓርቲዎቹ በራሳቸው ሊገፉት ይገባል ማለት ነው፡፡ የፊርማ ቅድመ ሁኔታን ኢህአዴግ አላስቀመጠም፤ ራሱ ህጉ ያስቀመጠው ነው፡፡ እያንዳንዱ ፓርቲ በስነምግባር መመራቱን, የፖለቲካ ቁርጠኝነቱን ቀድሞ ማረጋገጥ አለበት ነው የሚለው ህጉ፡፡ ይህን ያረጋገጡ የጋራ ምክር ቤት ውስጥ እየሠሩ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ጋር እነዚህ ፓርቲዎች በፕሮግራም የተለዩ ናቸው፡፡ በምርጫ ሂደቱ ላይ ግን በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለው የበሠለ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ስነ ምግባሩ ያስረናል ብለው ስለሚያስቡና አመፅና ብጥብጥ ለማስነሳት ያግደናል ብለው ስለሚያስቡ ቁርጠኝነት ስላነሣቸው ነው እንጂ ኢህአዴግ በተናጥል አልደራደርም ስላለ አይደለም፡፡ ከዚህ አንፃር ተስማምተን ህግ ሆኖ በወጣ ጉዳይ ላይ lምንድን ነው ተመልሰን ወደ ድርድር የምንገባው? የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ስለዚህ ተመልሰን ወደ ድርድር የምንገባበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ አሁንም ምርጫ ቦርድ በሚጠራቸው ስብሰባዎች ላይ አብረን እንሣተፋለን፤ የጋራ ምክር ቤት ውስጥ ለመግባት ግን ድርድር አያስፈልገውም፤ በስነምግባር ለመገዛት መስማማት ብቻ ነው፡፡ ኢህአዴግ ያለፈባቸውን ሂደቶች ስናይ ሁልጊዜም በድርድር የሚያምን መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
ለምንድን ነው የአለማቀፍ መስፈርቶችን ያሟላ ስነምግባር ተገዥ ሆናችሁ፣ ለፍትሃዊና ሠላማዊ ምርጫ ውድድር ዝግጁ ያልሆናችሁት የሚለውን ጥያቄ ተቃዋሚዎች መመለስ አለባቸው፡፡ በስነምግባር እንመራ የሚል ውይይት ማካሄድ እንዴት ይቻላል፡፡
ደንቡን ያልፈረሙ መድረክን የመሣሠሉ ድርጅቶች ከኢህአዴግ ጋር መወያየት ቢፈልጉ እንዴት ነው የሚስተናገዱት?
በተቀመጡ ማዕቀፎች መሠረት ይስተናገዳሉ፡፡ ገለልተኛ የሆነው የምርጫ ቦርድ አለ፡፡ ያልተሟሉ ነገሮች ካሉ ለምርጫ ቦርድ እያቀረቡ ሊፈቱ ይችላሉ፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ በተቋማዊ አሠራር የሚያምን ድርጅት ነው፡፡ የስነምግባር ደንቡ በሌለበትና የጋራ ምክር ቤቶች ባልተቋቋሙበት ሁኔታ ጥያቄው ቢቀርብ ትክክል ነው፡፡ ከእያንዳንዱ ፓርቲ ጋር ኢህአዴግ እየተወያየ ሊሄድ ይችላል፡፡ አሁን ግን የጋራ ማዕቀፍ  በተዘረጋበት ኢህአዴግ እንዴት ብሎ ነው ከ70 ፓርቲዎች ጋር በተናጠል መወያየት የሚችለው? አሁን ተቋዋሚ አሠራር ተዘርግቷል፡፡
ለመወያየት የፈለገ የጋራ ምክር ቤቱ ውስጥ መግባት አለበት፡፡ ችግሮች ሲፈጠሩ ምክር ቤቱ አጣሪ ኮሚቴ አቋቁሞ ያጣራል፤ መፍትሔ እንዲያገኙም ያደርጋል፡፡ ከዚህ ውጪ በተናጠል መወያየት አይቻልም፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች በራሳቸው የሚፈጠረውን ችግር እንኳ ሣይቀር ኢህአዴግ ፈጠረው ነው የሚሉት፡፡
በአመራር እንኳ የተፈጠረባቸውን ችግር በኢህአዴግ የተፈጠረ ጥፋት አድርገው ይወስዱታል፡፡ ስለዚህ ይሄን መፍረድ ያለበት ህዝቡ ነው፡፡ ህዝቡ ሁሉንም ነገር ያያል፡፡ ማን ነው ጥፋተኛ? ኢህአዴግ ነው ለዲሞክራሲያዊ ስርአትና ፍትሃዊ ምርጫ ዝግጅ ያልሆነው ወይስ ሌላው? የሚለውን መፍረድ ያለበት ህዝቡ ነው፡
ኢህአዴግ የገዢነቱን ኃይል ተጠቅሞ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችን ለማፈን ይጥራል የሚሉ ቅሬታዎች ይቀርባሉ፡፡ ኢህአዴግ እንደፓርቲ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ያለው አቋም ምንድን ነው?
ፓርቲያችን ሰላማዊ ሰልፍ ለዜጎች የተሰጠ ህገ መንግስታዊ መብት ነው ብሎ ያምናል፡፡ ይሄ መብት ተግባራዊ የሚሆንባቸው አሰራሮች እንደሚዘረጉ ህገ መንግስቱም አስቀምጧል፡፡ በህገ መንግስቱ ዜጎች በጋራ ሆነው ቅሬታ የማቅረብ፣ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ የማድረግ መብት አላቸው ይላል፡፡ ይሄን መብት ተግባራዊ ለማድረግ አሰራሮች ሊዘረጉ እንደሚችሉ ተቀምጧል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች የህዝቡን ሰላም፣ ክብርና የመሳሰሉ መብቶችን መጣስ እንደሌለባቸው ህገ መንግስቱ አስቀምጧል፡፡
አንድ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ እንደሚጠበቅበትም ተቀምጧል፡፡ የእውቅናውን ጥያቄ የሚያየው አካል የተጠየቀበትን ቦታና ጊዜ ይመለከትና በእውቅና ጥያቄው ላይ ምላሽ ይሰጥበታል፡፡ ቦታ ቀይር ወይም ቀን ቀይር የሚል ምላሽ ይሰጥበታል ማለት ነው፡፡ ዘጠኙ ፓርቲዎች የጠየቁት ቦታ መስቀል አደባባይ ነው፡፡ መስቀል አደባባይ ደግሞ ትልቅ የልማት እንቅስቃሴ እየተደረገበት ያለ ቦታ ነው፡፡ ለ24 ሰዓት ቆመ ማለት ብዙ ነገር ያስተጓጉላል፡፡
 ስለዚህ ቦታው ተገቢ አልነበረም ማለት ነው፡፡ በዚህ የተነሳ የተጠየቀው አካል አልተቀበለውም፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች ዕቅዳቸው ልማትን ማደናቀፍ፣ ህዝብን ወደ አመፅ መንዳት እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ ግን ሰላማዊ ሰልፍ የዜጎች መብት ነው የሚል አቋም አለው፡፡
ኢህአዴግ ለምርጫው ያስቀመጠው ግብ ምንድን ነው? አንዳንድ ወገኖች ሙሉ ለሙሉ አሸናፊ እንዳይሆን ተጠንቅቆ እስከ 15 በመቶ ወንበሮችን ለተቃዋሚዎች ሊለቅ ይችላል የሚል አስተያየት ይሰነዝራሉ?
ኢህአዴግ መንግስት ለመመስረት የሚያስችለውን ወንበር ማግኘት ነው ግቡ፡፡ ይሄ ሲባል ድምፁ እንደ እጩ ቁጥራችንም ይወሰናል በአገሪቱ ባሉ የምርጫ ክልሎች ሁሉ እንወዳደራለን፡፡ በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ለማሸነፍ እንሰራለን ማለት ነው፡፡ ኢህአዴግ ዲሞክራሲን የሚያየው በእውነተኛ ገፅታው ነው፡፡ ዲሞክራሲ በአርቴፊሻል ገፅታ መታየት የለበትም፡፡ ዲሞክራሲ የህዝብ ወሳኝነትን ማረጋገጫ መሳሪያ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ተወዳድረን ህዝቡ የሚመርጠን ከሆነ እሰየው ብለን እንወስዳለን፤ ባይመርጠንም እንቀበላለን፡፡ ከዚህ ውጭ አርቴፊሻል በሆነ መንገድ፣ የህዝብን ውሳኔ ባላከበረ መንገድ የተወሰነ ወንበር እንለቃለን የሚል ሃሳብ የለም፡፡ ወሳኙ ህዝብ ነው፡፡ ምርጫ በውጤት አይመዘንም፤ ዋናው ሂደቱ ነው፡፡ ሂደቱ ማማር አለበት፡፡
በየጊዜው በሚደረጉ ምርጫዎች ላይ የአለማቀፍ ታዛቢዎች ቁጥር እየቀነሰ ሄዶ ዘንድሮ የአውሮፓ ህብረትም ቀርቷል፡፡ አለማቀፍ ታዛቢዎች ከምርጫው ለምን ተገለሉ?
 የኛ ምርጫ ማንም ሊታዘበው የሚችል ምርጫ ነው፡፡ በድብቅ የሚካሄድ ምርጫ ሳይሆን ማንም ሊያየው የሚችል ምርጫ ነው፤ ነገር ግን ምርጫን የአውሮፓ ህብረት ካልታዘበው ችግር ይኖርበታል ብሎ ማሰብ በራሱ የምርጫው ወሳኝ ማን ነው የሚለውን ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ ህብረቱ ምርጫውን ለመታዘብ የበጀት እጥረት አለብኝ የመሳሰሉ ምክንያቶችን ነው ያቀረበው፡፡ ስለዚህ ምርጫውን የአፍሪካ ህብረት ይታዘበዋል፣ ከሃገር ውስጥም የተለያዩ የሲቪል ማህበራት ይታዘቡታል፡፡ ዋናው ወሳኙ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ ይሄ ህዝብ ነው ውሳኔ የሚሰጠውም የሚታዘበውም፡፡
አለማቀፍ ታዛቢዎች የምርጫውን ገለልተኛነት ከማረጋገጥ አንጻር ምንም ዓይነት ሚና አይኖራቸውም እያሉን ነው?
 ሊታዘቡ ይችላሉ ግን ዋናው ሚና የህዝብ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሂደት ከህዝብ ጋር የተገናኘ ነው አለማቀፍ ታዛቢ ተጨማሪ ነው፤ ወሳኝነት የለውም፡፡
ኢህአዴግ በዚህ ምርጫ ሊወዳደረኝ የሚችል ፓርቲ አለ ብሎ ያምናል?
ይሄን ህዝቡ ነው የሚመዝነው፡፡ ቀድመን ባንመዝነው እመርጣለሁ፡፡ ፓርቲዎች ምን እንደሚመስሉ የራሳችን ግምት አለን፡፡ የህዝብን ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችል ሌላ ይህች አገር የጀመረችውን ልማት፣ ዲሞክራሲ በቁርጠኝነት ይዞ ሊሄድ የሚችል ፓርቲ አለ ብለን አናምንም፡፡ በተለያዩ መንገዶች መመዘን እንችላለን፡፡ ከራሳቸው ባህሪ ተነስተን ማለት ነው፡፡
ፓርቲ ማለት የህዝብን ህይወትና ኑሮ ለመቀየር የሚሰራ ፓርቲ ነው፡፡ የትኛው ፓርቲ ነው ህዝቡ ለልማት ሲንቀሳቀስ ከጎኑ ተሰልፎ የሚሳተፈው? የትኛው ፓርቲ ነው ህዝቡ ተግዳሮቶች ሲያጋጥሙት አብሮ እየተንቀሳቀሰ ያለው? የትኛው ፓርቲ ነው ግልፅ የሆነ ሃገር የሚቀይር አማራጭ ፕሮግራም ያለው? የሚለው ስንጠይቅ፣ ሃገርን በዚህ መንገድ ወደፊት የሚያሻግር ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ የለም የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል፡፡ ይሄን ግን ህዝቡ ነው ገምግሞ ሚዛን ላይ ማስቀመጥ ያለበት፡፡ አሁን ቅስቀሳ ባልተጀመረበት ሁኔታ በዚህ ጉዳይ ብዙ አስተያየት መስጠት አይቻልም፤ ግን ህዝብ ይታዘባል፡፡ እናሸንፋለን አናሸንፍም የሚለውም ቅስቀሳ ስለሚሆን የምረጡን ቅስቀሳ ሲካሄድ ብናየው የተሻለ ነው የሚሆነው፡፡
ኢህአዴግ በምርጫ ቦርድ ወይም በምርጫ ሂደቱ ላይ ቅሬታ አለው?
ምርጫ ቦርድ ጋ ቅሬታ የለንም፡፡ ቦርዱ በገለልተኝነት እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡ ስብሰባ ሲጠራን አስተያየት እንሰጣለን፤ እስካሁን ግን ምንም ቅሬታ የለንም፡፡ ሌሎች ፓርቲዎች የሚያቀርቡትም አብዛኛው ቅሬታ ትክክል አይደለም ብለን እናምናለን፡፡
ፓርቲዎቹ ራሳቸው መጨረስ ያለባቸውን የቤት ስራ ሳይሰሩ፣ በቦርዱ ላይ የሚያቀርቡትን አብዛኞቹን ቅሬታዎች ስንገመግም፣ ቦርዱ ገለልተኛ አይደለም የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ የሚያደርጉት ጥረት መሆኑን እንገነዘባለን ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ ለኛ የሚያደላልን ነገር የለም፡፡