Administrator

Administrator

Thursday, 05 October 2023 00:00

ሠዓሊ መዝገቡ ተሰማ

በ1972 ዓ,ም አራት ኪሎ በሚገኘው አለ የሥነ ጥበባት ትምህርት ኮሌጅ በዲፕሎማ ተመርቋል።
~በ1975 ዓ,ም በሩሲያ በሌኒን ግራድ ፔኒን የሥነ ጥበብ አካዳሚ ከአለማችን ታላላቅ ሠዓሊያን
ጋር ለ5 አመት ተምሮ በከፍተኛ ማዕረግ በማስተርስ ኦፍ ፋይን አርትስ ተመርቋል።
መዝገቡ ተሰማ ከ 40 አመት በፊት ጀምሮ በቡሩሹ የከተባቸው ሥዕሎቹ የኢትዮጵያን መልክአ ምድራዊ ገፅታዎች የሚያንፀባርቁ ናቸው።ምክንያቱን ሲጠየቅ የሚሰጠው ምላሽ ደግሞ እኔ የምስለው የማውቀውን የሀገሬን ትውፊታዊ አኗኗር ነው የሚል ነው።
~ በ1985 ዓ,ም በብሄራዊ ሙዚየም የመጀመረያውን ~በ1996 ዓ,ም በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ
~በ2004 ዓ,ም በብሄራዊ ሙዚየም "ንግስ" የተሰኘው አውደ ርዕይ እንዲሁም
~በ2008 ዓ,ም "የአዲስ አበባ ልጅ"የተሰኘውን የስዕል አውደ ርዕዩን አሳይቷል።
Sunday, 03 December 2023 18:09

"የህጻናት አስም"

በዶ/ር ንጉሤ ጫኔ : የህጻናት ስፔሻሊስት ሀኪም
- አስም ምንድን ነው?
አስም የመተንፈሻ አካላችን ባእድ በሆኑ የትንፋሽ አለርጅ ቀስቃሽ ኬሚካሎች ተጽእኖ ከሚገባው በላይ በድንገት ለተወሰነ ጊዜ መጥበብ ነው። ይህ የአየር ቧንቧ ጥበት መድሀኒት ሲዎስዱ ወደ ነበረበት በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ነው።
- ምክንያተ መንስኤ
ዋና ምክንያቱ ተፈጥሯዊ ፣ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ በሆኑ ምክንያቶች ይነሳል። የሚፈጠረው መስተጋብር አየር ባንቧን ለዘለቀ ቁስለት/ብግነት በማጋለጥ አለርጅ ቀስቃሽ ሽታዎች ሲኖሩ የአየር ቧንቧ ከልክ ያለፈ ተለዋጭ ጥበት እና የቆሸሸ አየር ከሳንባ በሚፈለገው ልክ አለመውጣት  ሳል እና የመታፈን ምክንያትን ያመጣል። ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ ምክንያቶችን መቀነስ ይቻላል።
- የአስም አይነቶች
1. በተደጋጋሚ የሚነሳ አስም/recurrent asthma/seasonal
ይህ ወቅታዊ ሁኔታዎች የሚያስነሱት አስም ነው። ቀስቃሽ ምክንያቶችን በመቀነስ ድግግሞሹን መቀነስ እና ደረጃውንም መቆጣጠር ይቻላል።
2. ረጅም ጊዜ የቆየ አስም /chronic asthma
ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አስም
- አለርጅ/አስም ቀስቃሾች ምንድን ናቸው?
1. የሲጋራ ፣ የከሰል እና የማገዶ ጭስ
2. የአበባ፣ቆሻሻ፣ የፅዳት መጠበቂያ/ዴቶል/ ፣ የሽቶ እና ላበት ማጥፊያዎች ሽታ
3. ላባ እና ጸጉር ያላቸው የቤት እንስሳት
4. የከብቶች ሽንት እና አዛባ
5. በረሮ የሚረጨው ኬሚካል
6. እርጥበት እና ቅዝቃዜ ያለው ስፍራ
7. የጉንፋን ቫይረስ
8. የኬሚካል ሽታ
9. ጭንቀት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
10. ሻጋታ
11. የጨጓራ አሲድ ቅርሻ/Gastro  esophageal reflux  disease
12. የአፍንጫ አለርጅ እና ሳይነስ ህመም
- ለአስም አጋላጭ ሁኔታዎች
1. የቆዳ አለርጅ/የቆዳ አስም
2. የአፍንጫ እና አይን አለርጅ
3. የምግብ አለርጅ
4. አስም ያለበት እናት ፣ አባት ፣ እህት ወይም ወንድም
5. ከጉንፋን ጋር የማይያየያዝ ሳል
- የህመም ምልክቶች
1. በቅዝቃዜ ወቅት እና ማታ ማታ የሚባባስ ደረቅ ሳል
2. የደረት መጨነቅ/የመታፈን ስሜት
3. የትንፋሽ መፍጠን
4. የድካም ስሜት
5. የሰውነት መዛል እና ላበት
6. ሙዚቃዊ ትንፋሽ
7. ራስ ምታት፣ የትኩረት መቀነስ፣  እና አቅልን መሳት
- አስም አመላካች ነገሮች ምን ናቸዉ
1. በጥርጣሬ የአስም መድኃኒት ሲሰጥ በቶሎ የሚሻል ከሆነ
2. ወላጅ አስም ወይም አለርጅ ካለበት
3.ነባር የትንፋሽ  አለርጅ ካለ
4. ተደጋጋሚ የመተንፈሻ አለርጅ:
- ህጻናት ላይ አስም ይምንለው በአመት ውስጥ ሶስት ጊዜ እና ከዚያ በላይ የሆነ ሀኪም ያረጋገጠው የመተንፈሻ አለርጅ ካለ ነው።
- አስምን በምን እናረገግጣለን
1. የሳንባ ምርመራ:
በጤንነታቸው ወቅት ያላቸው የሳንባ አየር የማስገባት እና የማስወጣት የመጨረሻ  አቅም ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል በህመሙ ምክንያት ቀነሰ የሚለውን በመለካት።
2. የአየር ቧንቧ ለትንፋሽ ቧንቧ አስፊ ህይዎት አድን መድሀኒት ያለውን ፈጣን ምላሽ በማየት።
3. በአለርጅ አምጭ/ቀስቃሽ መድሃኒት አስም የመከሰት እድሉን  መሞከር(ይህ ምርመራ ብዙ አይመከርም)
4. በእስፓርታዊ እንቅስቃሴ ያለውን የተቃጠለ አየር የማስውጣት አቅም በመለካት።
- የአስም ህክምና
1. የአየር ቧንቧን ጥበት የሚያስተካክሉ መድሀኒቶች
2. የአየር ቧንቧ ቁስለትን/ብግነትን የሚቀንስ መድሃኒት
3. አለርጅን የሚቀንስ መድሃኒት
4. አስም ቀስቃሽ የሆነውን ህመም ማከም
5. ቤትን ከአስም ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ነጻ በማድረግ አስም እንዳይነሳ መከላከል
6. በቅዝቃዜ እና ጉንፋን በሚበዛባቸው ወቅቶች የአስም ቅድመ መከላከል መድሃኒት መስጠት
- እንደ መውጫ
የህጻናት የመተንፍሻ ቱቦ በተፈጥሮ  ጠባብ በመሆኑ ምክንያት አስም ጋር የሚመሳሰሉ ብዙ ህመሞች ስላሉ አስም አለ የምንለው በታፈኑ ወቅት በአስም መድሀኒት ያላቸው ለውጥ አመርቂ ከሆነ እና ለአስም ተጋላጭነት  ካላቸው ነው።
እድሜያቸው ከ4 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የሳንባን በአግባቡ መስራት ወይም አለመስራት ለማወቅ ለምርመራ እድሜያቸው ስለማይፈቅድ በብዛት በክትትል ብቻ ነው መለየት የሚቻለው። አካባቢያዊ አስም ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስተካከል አስምን መከላከል ዉጤታማ ነው።
የአዲስ አድማስን  መረጃ ይከታተሉ https://bit.ly/2V1zyZQ
 የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Sunday, 03 December 2023 18:09

"የህጻናት አስም"

በዶ/ር ንጉሤ ጫኔ : የህጻናት ስፔሻሊስት ሀኪም
- አስም ምንድን ነው?
አስም የመተንፈሻ አካላችን ባእድ በሆኑ የትንፋሽ አለርጅ ቀስቃሽ ኬሚካሎች ተጽእኖ ከሚገባው በላይ በድንገት ለተወሰነ ጊዜ መጥበብ ነው። ይህ የአየር ቧንቧ ጥበት መድሀኒት ሲዎስዱ ወደ ነበረበት በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ነው።
- ምክንያተ መንስኤ
ዋና ምክንያቱ ተፈጥሯዊ ፣ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ በሆኑ ምክንያቶች ይነሳል። የሚፈጠረው መስተጋብር አየር ባንቧን ለዘለቀ ቁስለት/ብግነት በማጋለጥ አለርጅ ቀስቃሽ ሽታዎች ሲኖሩ የአየር ቧንቧ ከልክ ያለፈ ተለዋጭ ጥበት እና የቆሸሸ አየር ከሳንባ በሚፈለገው ልክ አለመውጣት  ሳል እና የመታፈን ምክንያትን ያመጣል። ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ ምክንያቶችን መቀነስ ይቻላል።
- የአስም አይነቶች
1. በተደጋጋሚ የሚነሳ አስም/recurrent asthma/seasonal
ይህ ወቅታዊ ሁኔታዎች የሚያስነሱት አስም ነው። ቀስቃሽ ምክንያቶችን በመቀነስ ድግግሞሹን መቀነስ እና ደረጃውንም መቆጣጠር ይቻላል።
2. ረጅም ጊዜ የቆየ አስም /chronic asthma
ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አስም
- አለርጅ/አስም ቀስቃሾች ምንድን ናቸው?
1. የሲጋራ ፣ የከሰል እና የማገዶ ጭስ
2. የአበባ፣ቆሻሻ፣ የፅዳት መጠበቂያ/ዴቶል/ ፣ የሽቶ እና ላበት ማጥፊያዎች ሽታ
3. ላባ እና ጸጉር ያላቸው የቤት እንስሳት
4. የከብቶች ሽንት እና አዛባ
5. በረሮ የሚረጨው ኬሚካል
6. እርጥበት እና ቅዝቃዜ ያለው ስፍራ
7. የጉንፋን ቫይረስ
8. የኬሚካል ሽታ
9. ጭንቀት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
10. ሻጋታ
11. የጨጓራ አሲድ ቅርሻ/Gastro  esophageal reflux  disease
12. የአፍንጫ አለርጅ እና ሳይነስ ህመም
- ለአስም አጋላጭ ሁኔታዎች
1. የቆዳ አለርጅ/የቆዳ አስም
2. የአፍንጫ እና አይን አለርጅ
3. የምግብ አለርጅ
4. አስም ያለበት እናት ፣ አባት ፣ እህት ወይም ወንድም
5. ከጉንፋን ጋር የማይያየያዝ ሳል
- የህመም ምልክቶች
1. በቅዝቃዜ ወቅት እና ማታ ማታ የሚባባስ ደረቅ ሳል
2. የደረት መጨነቅ/የመታፈን ስሜት
3. የትንፋሽ መፍጠን
4. የድካም ስሜት
5. የሰውነት መዛል እና ላበት
6. ሙዚቃዊ ትንፋሽ
7. ራስ ምታት፣ የትኩረት መቀነስ፣  እና አቅልን መሳት
- አስም አመላካች ነገሮች ምን ናቸዉ
1. በጥርጣሬ የአስም መድኃኒት ሲሰጥ በቶሎ የሚሻል ከሆነ
2. ወላጅ አስም ወይም አለርጅ ካለበት
3.ነባር የትንፋሽ  አለርጅ ካለ
4. ተደጋጋሚ የመተንፈሻ አለርጅ:
- ህጻናት ላይ አስም ይምንለው በአመት ውስጥ ሶስት ጊዜ እና ከዚያ በላይ የሆነ ሀኪም ያረጋገጠው የመተንፈሻ አለርጅ ካለ ነው።
- አስምን በምን እናረገግጣለን
1. የሳንባ ምርመራ:
በጤንነታቸው ወቅት ያላቸው የሳንባ አየር የማስገባት እና የማስወጣት የመጨረሻ  አቅም ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል በህመሙ ምክንያት ቀነሰ የሚለውን በመለካት።
2. የአየር ቧንቧ ለትንፋሽ ቧንቧ አስፊ ህይዎት አድን መድሀኒት ያለውን ፈጣን ምላሽ በማየት።
3. በአለርጅ አምጭ/ቀስቃሽ መድሃኒት አስም የመከሰት እድሉን  መሞከር(ይህ ምርመራ ብዙ አይመከርም)
4. በእስፓርታዊ እንቅስቃሴ ያለውን የተቃጠለ አየር የማስውጣት አቅም በመለካት።
- የአስም ህክምና
1. የአየር ቧንቧን ጥበት የሚያስተካክሉ መድሀኒቶች
2. የአየር ቧንቧ ቁስለትን/ብግነትን የሚቀንስ መድሃኒት
3. አለርጅን የሚቀንስ መድሃኒት
4. አስም ቀስቃሽ የሆነውን ህመም ማከም
5. ቤትን ከአስም ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ነጻ በማድረግ አስም እንዳይነሳ መከላከል
6. በቅዝቃዜ እና ጉንፋን በሚበዛባቸው ወቅቶች የአስም ቅድመ መከላከል መድሃኒት መስጠት
- እንደ መውጫ
የህጻናት የመተንፍሻ ቱቦ በተፈጥሮ  ጠባብ በመሆኑ ምክንያት አስም ጋር የሚመሳሰሉ ብዙ ህመሞች ስላሉ አስም አለ የምንለው በታፈኑ ወቅት በአስም መድሀኒት ያላቸው ለውጥ አመርቂ ከሆነ እና ለአስም ተጋላጭነት  ካላቸው ነው።
እድሜያቸው ከ4 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የሳንባን በአግባቡ መስራት ወይም አለመስራት ለማወቅ ለምርመራ እድሜያቸው ስለማይፈቅድ በብዛት በክትትል ብቻ ነው መለየት የሚቻለው። አካባቢያዊ አስም ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስተካከል አስምን መከላከል ዉጤታማ ነው።
የአዲስ አድማስን  መረጃ ይከታተሉ https://bit.ly/2V1zyZQ
 የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

 በቅርቡ በህገመንግሥት መሻሻል፣ በጠ/ሚኒስትሩነ ሥልጣን መገደብ ና ሌሎች ተያያዥ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጥናት አካሂዶ
ውጤቴን ይፋ ያደረገው አፍሮ ባሮሜትር ፣ የኢትዮጵያ ተወካይና ተመራማሪ፣አቶ አቶ ሙሉ ተካ፣ ተቋሙ በሚያካሂዳቸው ጥናቶች፣ በናሙና አመራረጥ ና በጥናት በሥነ ዘዴ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተውናል፡፡ እነሆ፡
          አቶ ሙሉ ተካ ፤በእኢትዮጵያ የአፍሮ ባሮሜት ተወካይና ሚስዝ ማሜ አኩየ፤ የአፍሮባሮሜትር ኮሚኒኬሽን አስተባባሪ

          • ባለፈው ሳምንት በአዲስ አድማስ ላይ በወጣው የዜና ዘገባ፣ የተከበሩ አፈ ጉባኤ አገኘሁ፣ድርጅታችሁ አፍሮባሮሜትር በቅርቡ ይፋ ባደረገው የጥናት ግኝቶች ላይ አስተያየት መስጠታቸው  የሚታወቅ ሲሆን በተለይ “ህገ መንግስቱ ይሻሻል” የሚለውን የጥናት ግኝት በተመለከተ “ጊዜውን ያልጠበቀና ግልፅነት የጎደለው ነው” ሲሉ ተችተውታል፡፡  “አካታችነት የጎደለውም ነው” ብለውታልም፡፡ የእናንተ ምላሽ ምንድ ነው›?
የአፍሮ ባሮሜት የዳሰሳ ጥናት ሽፋን አገር አቀፍ ነው፡፡ የጥናቱ ናሙና cluster, stratified random sampling በተሰኘ ሳይንሳዊ ዜዴ በ3 ቅደም ተከተል ደረጃ በደረጃ የተመረጠ፤ የምልዓተ ህዝቡ አሰፋፈር፤ ብዝሃነት እና ማሕበራዊ ስብጥር የሚያንፀባርቅ አካታችና ወካይ ጥናት መሆኑን ከጥናቱ ናሙና ስርጭት መረዳት ይቻላል፡፡
1ኛ) ኢትዮጵያውን በ11 ክልልሎች እና በ2 አስተዳደሮች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) በገጠርና ከተማ የሚኖሩ በመሆናቸው የጥናቱ ናሙና (sample size) ከምልዓተ ህዝቡ ብዛት ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ (proportional to population size) ተደልድሏል፡፡ መልስ ሰጪዎች ይህንን የሕዝብ አሰፋፈር ከሚያንፀባርቅ ናሙና በተመጣጣኝ ውክልና የተገኙ በመሆናቸው ጥናቱ ቀዳሚ የውክልና መስፈርት ያሟላ ነው፡፡ 67% የሚሆኑ መልስ ሰጪዎች በገጠር፤ 33% ደግሞ በከተማ የሚኖሩ ናቸው፡፡ይህ ስብጥር ከሀገራዊው  መኖርያ ስርጭት ጋር እጅግ የተቀራረበ በመሆኑ ጥናቱ 2ኛው የአካታችነት መስፍርት ያማላ ነው፡፡ ከፆታ ስብጥር ሲመዘን 51% መልስ ሰጪዎች ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 49% ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡
መልስ ሰጪዎች ከሁለም የእድሜ ክልል የተገኙ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ወጣቶች በብዛት የሚኖርባት አገር ናትና በዛው ልክ በጥናቱ ተወክልላል፡፡ 63% እድሜያቸው በ18ና 35 እድሜ ክልል የሚገኑ ወጣቶች መሆናቸውን ልብ ይላል፡፡ 18% እድሜያቸው 36 45፤ 9% ከ45 55፤ ቀሪዎቹ  10% ደግሞ ከ55 በላይ ናቸው፡፡ በጥናቱ የተሳፉ ዜጎች ኃይማኖታዊ እምነት ስብጥር ስንመለት 627% ክርስትያን፡ 369% ሙዝሊም እና 04% እምነት የሌላቸው እንደሆኑ ነግረውናል፡፡
2ኛ) ክመልስ ሰጪዎች ማንነት (identity) ስብጥር አንፃር ሲመዘን ጥናቱ የኢትዮጵያን የቋንቋ እና የባህል ብዝሃነት (linguistic and cultural diversity) የተንፀባረቀበት ነው፡፡ ክጥናቱ ተሳታፊዎች 98.8% የሚሆኑት ከተለያዮ ብሔርና ብሔረሰቦችና የተገኙ ናቸው፡፡ ማንነታቸው በሚመለክት ላቀርብንላቸው ጥያቄ  ከረጅሙ ዝርዝር በከፊል ለመጥቀስ ያክል ራሳቸውን ኦሮሞ፡ አማራ፤ ሱማሊ፤ ትግራዋይ፤ አፋር፤ ሲዳማ፤ ሀረሪ፤ አገው፤ ቅማንት፤ አኝዋክ፤ ዲንቃ፤ ሽናሻ፤ በርታ፡ ወላይታ፤ ጋሞ፤ ጌድዮ፤ ቤንች፤ ደራሼ፤ ዳውሮ፤ ሀመር፤ መንቲ ወዘተርፈ እንደሆኑ ነግረውናል፡፡
 ቀሪዎቹ 12% ደግሞ “እኢትዮጵያዊ ብቻ እንደሆኑና አንዱ ወይም ሌላኛው ማንነት አለን ብለው እንዳማያስቡ ነግረውናል፡፡
በነሲብ (randomly) ተመርጠው በጥናቱ የተሳተፉ መልስ ሰጪዎች ስብጥር የምልዓተ ህዝቡን ማህበራዊ ስብጥር የሚያንፀባርቅ እና ብዝሃነትን የሚያሳይ ሆኖ ሳለ፤ እንዴት “ሁሉንም ብሔሮችና የህብረተሰብ ክፍሎች ያላካተተ ነው” ሊባል ይችላል? መልሱን ለአንባብያን እተዋለሁ፡፡
3ኛ) በዚህ ጥናት በመልስ ሰጪነት የተሳተፉ ዜጎች የትምህርት ዝግጅት ስንመለከት 42% መደበኛ ትምህርት የሌላቸው፡ 5% መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ያላቸው፤ 35% የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ፤ 18% 2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 13% ድህረ 2ኛ ደረጃ ትምህርት የተማሩ ናቸው፡፡ ከዚህ ስብጥር መረዳት የምንችለው ከአጠቃላዮ መልስ ሰጪዎች ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ (87%) የሚሆኑት ተራ ኢትዮጵውን ዜጎች፤ ልሒቃኑ ደግሞ 13% ብቻ መሆናቸውን ነው፡፡ ለዚህ ነው “ሕዝቡ አስተያየቱን ይስጥ!” በሚል መሪ ቃል የሚናክወነው የአፍሮ ባሮሜትር የጥናት ውጤት የብዙኃኑ ድምፅ ነው የሚለው የምንለው፡፡ ነገር ግን ቢዚህ ጥናት የተሳተፉት ልሒቃን ብዛት አናሳ (13%) ሆኖ ሳለ፤ አፍሮ ባሮሜትር “ጥቂት ልሒቃን አነጋጋፍሮ ያቀረበው ሰነድ ነው” ሊባል ይቻላልን? አሁንም መልሱ ለአንባቢያን እተዋለሁ፡፡
•  ምናልባትም “66 በመቶ ኢትዮጵያውያን  የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን መገደብ አለበት” ብለዋል የሚለው የጥናት ውጤትም ከትችትና ከሂስ አያመልጥም የሚል ግምት አለ፡፡
ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ  እንዲህ ያሉ ፖለቲካዊ ጉዳዮች በአገራችን አወዛጋቢ በመሆናቸው ሳይሆን አናቀርም፡፡ በግላችሁ የደረሳችሁ አሰተያየት ወይም ትችት ይኖር ይሆን? በዚህ ዙሪያ--
 የአፍሮ ባሮሜትር ጥናት ይህ ብቻ ሳይሆን ልሒቃኑ በቀጣይ እያከራከቱ የሚገኙ ሌሎች የሕገ መንግስቱን ድንጋጌዎች ያካተተ ጥናት ነው፡፡ በእነዚህ አወዛጋቢ ድንጋጌዎች የተራው ዜጋ አስተሳሰብ ለመለክት የሚደረግ ጥናት ቢተችና ሂስ ቢቀርብበት ባህርያዊ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አፍሮ ባሮሜትር ዜጎች በጥናቱ ላይ እንዲወያዪ ትችትና ሂስ እንዲሰነዝሩ ያበረታታል፡፡ ይህ ጥናት በ2012 ዓም የተከናወነ ሲሆን በዛን ጊዜ ዜጎች በተለይ በማህበራዊ ሜዲያዎች ተወያይተውበታል፤ ተችተውበታል፡፡ በጥናቱ ስነዘዴ ላይ የቀረቡት ትችቶች ማብራርያ በመስጠት አስረደተናል፡፡ ዘንድሮ በተምሳሳይ ርእሶች የተከናወነው ጥናት ላይ ትችቶች እየቀረቡ ነው፡፡ እኛም የጥናቱን ስነዘዴ በማብራራት ላይ ነን፡፡
•  የጥናት ውጤታችሁን በተመለከተ በአጠቃላይ ከህብረተሰቡ ያገኛችሁት ምላሽ ምን ይመስላል?
“ህብረተሰቡ” የሚለው ቃል ጥቅል በመሆኑ ጥያቄውን ለመመለስ እቸገራለሁ፡፡ ነገር ግን የሜዲያ ሞኒቶሪንግ ስራ በመስራት ላይ በመሆናችን ምላሹ ከየትኛው የህብረተሰ ክፍል ነው? ይዙቱ ምንድ ነው? የሚሉትን ለመመለስ ጊዜው ገና ነው፡፡
•  በግጭትና ጦርነት ሳቢያ በአንዳንድ ክልሎች ጨርሶ መንቀሳቀስ የማይቻልበት ሁኔታ በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ ባለፉት 2 ዓመታት በትግራይ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ደግሞ በአማራ ክልል ብዙ ቦታዎች፣ በኦሮሚያ እንዲሁ በተወሰኑ ቦታዎች የፀጥታ ችግር ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ የተካሄደ ጥናት አካታች ነው ሊባል ይችላል? ጥናቱ መላ ኢትዮጵያን የሚያካትት ነው ከተባለ ማለቴ ነው?
በቅድሚያ መረጃ ለመሰብሰብ የመስክ ስራ የተክናወነው ከፕሪቶርያ ስምምነት በኃላ ሲሆን በአማራ ክልል ባሁኑ ጊዜ የሚታየው ግጭት ባልነበረበት ጊዜ ነው፡፡
 በመጀመሪያ ደረጃ የናሙና መረጣ (1st stage sample selection ) ጥናቱ የሚከናውንባቸው የቆጠራ ጣቢዎች ክየክልሉ  በነሲብ የተመረጡ ሲሆን በኦሮሚያ የፀጥታ ችግር ባለባቸው የተወሰኑ አከባቢዎች የወደቁ በጣት የሚቆጠሩ የቆጠራ ጣቢያዎች በድጋሚ በrandom drawing ከመተካታቸው በስተቀር ጥናቱ አካታች ስለመሆኑ ከካርታው ከሚታየው የናሙና ክልላዊ ስርጭት መረዳት ይቻላል፡፡  
•  ጥናቱ ሁሉንም ክልሎች ያካተተ እንደኾነ ተጠቅሷል። 2400 መጠይቆች መደረጋቸውም ተነግሯል፡፡  የተወሰዱት ናሙናዎች ከአጠቃላይ የህዝብ ቁጥሩ አንፃር ወካይ ናቸው  ማለት  ይቻላል ?
ለዳሰሳ ጥናቶች የናመኗ መጠን ( sample size) ስንት ይሁን የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በሳይንሱ ተቀባይነት ባገኘ ቀመር ወይም ፎርሙላ እና ቁልፍ ስታቲስቲካዊ መስፈርቶች መሰረት ነው፡፡ ከመስፈርቶቹ አንዱ አስተማማኝ የርቀት መጠን (confidence interval) የሚባለው ነው፡፡ ምልዓተ ህዝቡ (population )  ሲጠና አስተማማኝነቱ መቶ በመቶ ነው፡፡ ነገር ግን ጥናቱ በናሙና የተመሰረተ ነውና 100%  አስተማማኝ  ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ የመጀመርያ ጥያቄ የጥናቱ አስተማማኝነት ስንት ይሁን? 99% 97% ፣ 95%  ወይስ 90 %.? ጊዜና በጀት ታሳቢ በማድረግ፣ አፍሮ ባሮሜትር 95% የአስተማማኝ የርቀት መጠንን ታሳቢ አድርገዋል፡፡ ይሀ ከፍተኛ ከሚባሉት ርቀቶች አንዱ ሲሆን በእንደዚህ ዓይነት ማህበራዊ ጥናቶች ተመራጭ ነው፡፡
የስህተት ወይም የኅዳግ መጠን  (margin of error)  የሚባለው ነው፡፡
ማንኛውም ጥናት በናሙና የተመሰረተ ነው፡፡  ጥናቱ ናሙና እንጂ ምልዓተ ህዝቡን የማያካትት ስለሆነ ለስህተት (sampling error) የተጋለጠ ነው፡፡ ዋናው ቁምነገር ምን ያክል ስህተት እንቀበል የሚለው ነው፡፡ 1%፤ 3%፤5%፤10%. አፍሮ ባሮ ሚትር 2% የስህተት ወይም ኅዳግ መጠን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን የጥናቱን ውጤት ከመተርጎም አንፃር ጠንቃቃ (conservative ) ሊባል የሚችል ግምት ነው፡፡ በዚህ ቀመር መሰረት የጥናቱ መጠን 2400 ይሆናል፡፡ በርግጥ የናመናው መጠን ከፍ ቢል የኅዳግ መጠኑ ስለሚቀንስ የጥናቱ አስተማማኝነት ክፍ ይላል፡፡ ነገር ግን ናሙናውን በጨመርን ቁጥር በጥናቱ አሰተማማኝነትና ትክክለኛነት (precision) የሚያመጣው ለውጥ ከወጪው ጋር ሲነፃፀር ተመጣጣኝ አይደለም፡፡  የናሙናው መጠን በ10 እጥፍ ወደ 24,000 ወይም ወደ 240,000 ከፍ ቢል፣ ከዛን ያክል መልስ ሰጪ መረጃ ለመሰብሰብ ከሚወጣው ወጪ ጋር ሲነፃፀር ተመጣጣኝ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ በተመሳሳይ ርእስ በመንግስታዊው የፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት በ2015 ዓም በተደረገው ሀገራዊ ጥናት ናሙና 1400 ነበር፡፡ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው አሜሪካውያን ብዛት ከ260 ሚልዮን በላይ ቤንም ጋልአፕ (Gallup) እና Pew Research Center የተሰኙ የአሜሪካ የጥናትና ምርምር ድርጅቶች ለሀገራዊ ጥናት የሚውስዱት የናሙና መጠን ከ1000 እስክ 1200 ነው፡፡ እንግዲህ የናሙና መጠን ሲወሰን አጠቃላይ የህዝብ መጠን ሳይሆን እነዛ ስታቲስቲካዊ መስፈቶችን ታሳቢ በማደረግ ነው፡፡
•   በተለይ በእኛ አገር ባለፈው ይፋ ያደረጋችሁት ዓይነት የጥናት ግኝቶች (ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው) ከማወዛገብም አልፈው መንግስት ጥርስ ውስጥ ሊያስገቡ ይችላሉ፡፡ እስካሁን በአጠቃላይ  የገጠሟችሁ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው?
አፍሮ ባሮሜትር በርእሰ ጉዮቹ ላይ ጥናት ሲያደርግ ለ2ኛ ጊዜ ሲሆን የመጀመርያው በ2012  .ዓ.ም የተከናወነ ነው፡፡ በሁለቱም ዙሮች የገጠመን ተጠቃሽ ተግዳሮት የለም፡፡
በነገራችን ላይ በአወዛጋቢ የሕገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ላይ በኢትዮጵያ ጥናት ሲደረግ አፍሮ ባሮሜትር ብቸኛ አይደለም፡፡በ2015.ዓ.ም መንግስታዊው የፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዮት በነዚህ ጉዳዮች ጥናት አከናውኖ አምና ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡
•  የባሮአፍሮሜትር ቀጣይ እቅዶችና ራዕዮች ምንድን ናቸው?
የአፍሮ ባሮሜትር ቀጣይ እቅዶች፣ ጥናት የሚያካሂድባቸውን የአፍሪካ አገሮች ብዛት ከ42 ወደ 53 ከፍ በማደረግ አህጉሪቱን መሉ መሉ ማካተት ሲሆን፤ የተራ አፍሪካያውያን ዜጎች ድምጽ የፖሲና የውሳኔ አሰጣጥ አምድ ማደረግ ነው፡፡
•  አሁን የምትሰሩት ዓይነት ጥናት ብዙ ወጪ ይጠይቃል፡፡ የፋይናንስ ምንጫችሁ ምንድን ነው?
የአፍሮ ባሮሜትር ጥናቶች በበርካታ አለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች የፋይናስ ድጋፍ የሚከናወን ሲሆን፤ ክብዙዎቹ በጥቂቱ ለመጥቀስ ዩኤስኤይድ፤ የስዊድን አለም አቀፍ የልማት ኤጄንሲ፤ ቢል ጌትና ሜለን ፍውንዴሽን፡ የአውሮፓ ሕብረትና አፍሪካዊው ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽኝ ይገኙበታል፡፡
•  ድርጅታችሁ የሚሰራው ዓይነት ጥናት ለአገርና ህዝብ ፋይዳው ምንድን ነው?
የአፍሮባሮሚትር ጥናቶች መንግስት፤ የልማት አጋሮች፡ የሲቪል ማህበራት፤ የፖሊሲ ወትዋቾች እና የተለያዮ ባልደርሻ አካላት የአፍሪካውያንን ዜጎች ፍላገቶችን በፓሊስ ቀረፃ፡ በፕሮግራም እና ፕሮጄክት ዲዛይን ታሳቢ እንዲያደርጉ ጥራቱን የጠበቀ አስተማማኝ መረጃ ያቀርባል፡፡

Saturday, 02 December 2023 19:50

“የጉንዳን አፈጣጠር…”

 እንዴት ሰነበታችሁሳ!
የሆነ በቅርብ ርቀት የምናውቃቸው ‘እሱና እሷ’ ነበሩላችሁ፡፡ በቃ በፍቅር ‘እፍ’ ብለው ሰውን ሲያስቀኑት ነበር፡፡፡ ታዲያላችሁ… በቀደምለት ‘የማይታረቅ ቅራኔ’ ውስጥ ገብተው “አትድረሽብኝ” “አትድረስብኝ” ተባባሉትና አረፉት፡፡ የዘንድሮ ‘አፍ’ ያስባለ ‘ላቭ’ የአወዳደቁ ፍጥነት አይገርማችሁም! ደግሞ‘ኮ… “የጥንቱ ትዝ አለኝ..” የለ “ያሳለፍነው ዘመን…” የለ… “በጨረታው አልገደድም…” ብቻ!
እኔ የምለው … ዛሬ የተለያዩት ሮሚዮና ጁሉየት ከነገ ወዲያ… ‘ፍሬሽ’ ሮሚዩና ጁሊየት ላይ ተሰክተው ስታዩዋቸው…”መቼ ተቦክቶ መቼ ተጋግሮ ለምሳ ደረሰ!” ያሰኛችኋል፡፡
የምር ግን… ደግ ደጉን አላሳያችሁ ብሎን እንደሁ እንጃ‘ንጂ… በሥራም በሉት፣ በጾታም በሉት ‘ፍቅር’ ወይ ‘ኮማ’ ውስጥ ገብቷል ወይ ትርጉሙ ተለውጧል፡፡ እንዴ… ግርም እኮ ነው የሚለው! ይሄ “ሦስት ብር የነበረው ሀምሳ ሳንቲም!...” የሚሉት ነገር ‘ላቭ’ ውስጥም ገባ እንዴ!
ስሙኝማ… ችግሩ ምን መሰላችሁ… እርስ በእርስ እንዳንተሳሰብ እያደረገን ነው፡፡ ‘ለጋራ ጥቅም’ መባባል እየቀረ ነገርዬው ሁሉ “መጀመሪያ የመቀመጫዬን…” ሆኗል፡፡ እኔ የምለው “ጎረቤትህን እንደራስህ ውደደው…” የሚለው ነገር ትዝታ ሆኖ መቅረቱ ነው!  [እንትና… ስለፍቅር ሲወራ አሁንም ጀኔፌር ሎፔዝ ብቻ ነች ትዝ የምትልህ?]
ተስፋ ቆረጥን መሰለኝ… ‘ፍቅር ድሮ ቀረ’ እየተባባልን ነው፡፡ ለነገሩ ‘ድሮ ያልቀረ’ ምን አለ፡፡ አሀ…. ልክ ነዋ! ዘንድሮ እንደሁ ሁለትና ሶስት ዓመት “ድሮ” እየሆነብን ነው፡፡ በመቶ ብር የገዛናት ጫማ መንጋደድ ሳትጀምር… ‘አመለካከት እያለቀ’ ተቸግረናል፡፡ ደግነቱ እኔና እናንተ… እዚች ‘ዕቃ’ የሌለባት የዓለም ክፍል ስቶር ጠባቂ ሆነን ቀረ‘ንጂ… ለጥቂት ዓመት ወጣ ብለው የሚመለሱት… አለ አይደል… በአራድኛው “ጦጣ” ነው የሚሆኑት [ይኸው “ንክኪ” እንኳን ወደ ‘ተለጣፊ” ተለውጣ… ቂ….ቂ…!] የምር‘ኮ… ግራ ገባን !ድሮ ፋሺኑ የሚለወጠው ወይ ቀሚስ… ወይ የፀጉር አቆራረጥ ነው፡፡
 “አዲስ ፋሺን ቀሚስ መጥቷል…” ይባል ነበር፡፡ ዘንድሮ ልጄ… ሴቱ ሁሉ ሱሪ ለባሽ ስለሆነ ነው መሰለኝ… ፋሺኑ የሚለወጠው… ‘ላንጉዌጁ’ ሆኖብናል፡፡
ሀሳብ አለን… ቴሌቪዥኖች ‘የሳምንቱ አበይት ዜናዎች’ እንደምታቀርቡልን ሁሉ… ‘የሳምንቱ አዳዲስ ቃላት’ የሚል ፕሮግራም ይከፈትልን፡፡ አሀ… አለበለዛ አካሄዳችን የወቅቱን አጣዳፊ ጉዳይ ያላገናዘበና ራዕይ የሌለው ሆኖ ኅብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የጋራ አመለካከት በየደረጃው ለማስረጽ የሚደረገውን ጥረት ለጥገኝነት አስተሳሰብ አጋልጦ ይሰጠዋል፡፡
 [ተናግሬ ልቤ ውልቅ ብሎላችኋል፡፡] ስሙኝማ… የምር ግን ስለዚህ ጉዳይ ብንመክር ጥሩ ነው፡፡ አለበለዛ ነገ በ‘አዲስ ቋንቋ’ ሰላምታ የሚያቀርብልንን ሰው “ኧረ ራስህ ደደብ!” ብለን ልንመልስለት እንችላለና!
እናላችሁ… ስለ ‘ፍቅር’ አልነበር የምናወራው… ነገርዬው ሁሉ ደብልቅለቅ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ የሮሚዮና ጁሊየት ዓይነት ታሪክ እኮ… አይደለም በእውን… በቲያትርም እየቀረ ነው፡፡
የምር ግን… እንትናዬዎችም እኮ ግራ እየተጋቡ ነው፡፡ ወንዱ እንደሁ “ትናንት ምሳ ስበላ ትዝ ብለሽኝ..” “ሌሊት ደስ የሚል ሳቅሽ መጥቶብኝ…” ማለት ትቷል፡፡ ጭራሹን “ከመቼ ወዲህ ነው እስከ አንድ ሰዓት ውጪ የምታመሺው?” “ያን ያህል ጊዜ ስልኩን የያዝሽው ከማን ጋር እያወራሽ ነው፣” ምናምን ማለት ነው የሚቀናው፡፡ ምን መሰላችሁ ነገርዬው ለ‘ማርክ’ አሰጣጥም እየቸገረ ነው፡፡
ማለቴ እንትናዬዎቹም የትኛው ‘ትሩ ላቭ’… የትኛው ‘ንብረት ግዢ’ እንደሆነ ለማወቅ ቸግሯቸዋል፡፡ እንዲያው ዝም ብሎ “የዘንድሮ ሴቶች…” ማለቱ ‘ፌይር አይደለም፡፡ [“እንጀራ በአቋራጭ በምላስ በሰለ” ይሏችኋል ይሄ ነው፡፡]
እኔ የምለው… መቼም ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ… ዘንድሮ’ኮ በምላስ ‘ጠብ’ ማድረግ እየቀረ ነው አሉ፡፡ እነአጅሬዎች መች የዋዛ! ልጄ… ዋናው ‘ተግባር’ ሆኗል፡፡ [‘በጥሬው’ ማለትም ይቻላል!] እንደድሮ… “መኪናዬ ጋራዥ ገብታ….” ምናምን ቢባል መልሱ ምን መሰላችሁ “ውይ … አንድ ብቻ ነው ያለኝ እንዳትለኝ!” (አንዳንዱ’ኮ ‘ከመሸለሉ’ ብዛት… እግሩን እንደ እጁ በመስኮት ሊያወጣብን ምንም አይቀረው ደግነቱ የወንድ እግር ላይ ቼይን ገና አለመጀመሩ) እናችሁ…‘ፍቅር’ በገበያው ዋጋ መባል ከተጀመረ በቃ ነገር ጠፋ ማለት ነው፡፡
 አንዳንዱ ደግሞ አለ፡፡ “ሐሙስ ስደውል የት ነበርሽ?” ሲል “ሺህ ሰማኒያ ያለችው አክስቴ ጋር ሄጄ” ምናምን ሲባል ምን ይላ መሰላች… “አንቺ ስንት  አክስት ነው ያለሽ?... ደግሞ ዘመዶቼ ሁሉ ሰንጋተራ ነው ያሉት  ትይኝ አልነበር!” እኔ የምለው … ይሄ ‘ፍቅር’ ነው… ህዝብና ቤት ቆጠራ? ነገርዬውማ ሀዲዱን መሳት የጀመረው … አለ አይደል…. “እወድሻለሁ…” መባል ቀርቶ “ትመቺኛለሽ” ሲባል ነው፡፡ ‘መውደድ’ ሌላ ‘መመቸት’ ሌላ፡፡ እነእንትና ደግሞ ስለመመቸት ሲያወሩ ትዝ የሚለኝ…ፍራሽ!
ስሙኝማ… ይሄ እንትን ‘ሰፈር’ ያለው መናፈሻ በቃ እንደ ድሮው ላይሆን ነው?  ልጄ… ለስንቱ ውለታ ውሏል መሰላችሁ? ሌሎቹ መናፈሻዎች እንዳሉ ይቆዩልን፡፡ አሀ…. ልክ ነዋ! የምር’ኮ አሪፍ ፍቅር የሚገኘው መናፈሻ ውስጥ ነው፡፡ ‘ገበያ’ ቦታ የለውም፡፡ ልጄ…. ሬስቶራንት ውስጥ ጥንዶች በገቡ ቁጥር “አቤት ጉትቻዋ ደስ ሲል!” “ያውልህ በህልሜ አየሁት ያልኩህ ቀሚስ…” ምናምን መባባል የለ… “ምንድነው አሥሬ የምትዞሪው?”… “እዛ ማዶ ያለውን ሰውዬ የት ነው የምታውቂው?” የለ…. በቃ መናፈሻ ውስጥ ግፋ ቢል ስለተፈጥሮ መመራመር፡፡ ግንዱ ስር የሚርመሰመሱትን ጉንዳኖች እያዩ “የጉንዳን አፈጣጠር ግርም አይልሽም?” ማለት፡፡ አሪፍ አይደል! ሌላ ቦታ ግን “ይሄ ሀብል ደስ አይልም?” ሲል “እገዛልሻለሁ ብለኸኝ አልነበረም!” ማለት ይከተላል፡፡ መናፈሻ ውስጥ ግን “መቼ ነው ጉንዳን የምትገዛልኝ?” አይባል! በየማታው በስልክ መጨቃጨቅ የለ…
ይሄኛው “እንደ ቡና ዋጋ…” የሚዋዥቀው ‘ዘመነኛው’ ፍቅር ግን… አለ አይደል…. ሲያምርበትም፣ ሲያስጠላበትም ልክ የለውም፡፡ “በእኔ ፍቅር ልብ ድካም ይዟታል…” የተባለላት በየማታው ስልክ እየደወለች “በቅሎ ቤት ምን የመሰለ ክትፎ ቤት ተከፍቷል መሰለህ…” “ወሎ ሰፈር የበላነውን ቦዘና ሽሮ ብትቀምሰው…” ምናምን ስትል… በቃ የ‘ፍቅር’ ‘ዴፊኒሽን ‘ ተለውጧል ማለት ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ በአፍ ገብቶ ሆድ ላይ የሚያርፍ ፍቅር ‘ኮመን ኮርስ’ የሆነ ይመስላል፡፡
ስሙኝማ… እንዲያው እግረ መንገዴን… ይሄ ወደ ዳር አገር ሲሄዱ … የሚይዘው ‘ፍቅርና ናፍቆት’ አይገርማችሁም? አጅሬ ዲሲ ገብቶ ገና የዋሺንግተን ዘጠኝ ቁጥር አውቶብስ የት እንደሚሄድ ሳያውቅ “የህዝቡ ናፍቆት አላስተኛ አለኝ…” ምናምን ይልላችኋል፡፡
 እዚህ’ኮ የሰፈር ሰው “መቼ ከዚህ ሰፈር በነቀለልን!” እያለ አቤቱታ ሲያቀርብበት የቆየ ነው፡፡ እና… አንዳንድ ‘አርቲስቶችም’ ሆነ ሌሎች… አለ አይደል… ገና ‘መሄዳቸውን’ በቅጡ ሳናውቀው እንኳን የህዝቡ ፍቅር እንቅልፍ ነሳኝ…” ሲሉ በ‘ህግ አምላክ!’ የምንልበት አጥተን እንጂ…ስሙኝማ… መቼም ‘ግሎላይዜሽን’ አይደል ‘‘እነዛኞቹ ስቴጅ ላይ ‘አይ ላቭ ዩ’ ሲሉ የሰሙት… እኛንም “እወዳችኋለሁ” ማለታቸው ክፋት የለውም፡፡ ግን አንዳንዴ… ከእነመፈጠሬም የማታውቀኝ ዘፋኝ ከህዝቡ ቀላቅላህ ‘እንደምትወደን’ ስትናገር… “ከሌሎች ሰዎች ጋር ተምታተንባት ይሆን!” ለማለት ምንም አይቀረን! ልክ ነዋ… ዘንድሮ’ኮ… እንኳን ‘የማታውቀው ድምፃዊ’… የሚያውቁንም የኬክ ቤት ሰራተኞች ‘መውደድ’ ካቆሙ ስንት ጊዜያቸው!
ሀሳብ አለን!... የዘንድሮ ፍቅር መልኩና ‘የቆይታ ጊዜው’ ግራ እየገባን ስለሆነ… የሆነ ግንዛቤ ማዳበሪያ ይዘጋጅልን!! ልጄ… ድሮ እኮ “ሼራተን የሀብታሙ ሰውዬ ነው” ሲባል “እምብዮ… ያንተ ነው!” የሚያስብል ‘ላቭ’ ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን “ሞባይል’ኮ ያዝኩኝ፣” ሲባል “ይሄኔ ተውሰህ ይሆናል!” የሚል ‘ፍቅር’ መጥቷል!
ደህና ሰንብቱልኝማ! ካህሊል ጂብራን “መልዐኩ” በተሰኘው ምሳሌያዊ ጽሑፉ ስለ መልዐክና ስለ አንድ ሽፍታ እንዲህ ይተርካል፡፡
አንድ ጊዜ በልጅነቴ ከተራሮቹ ማዶ ባለው ጫካ ከአንድ ዛፍ ስር የሚኖረውን መልዐክ ልጠይቀው ሄጄ ነበር፡፡ ስለ ሰናይ ምግባር ጠቃሚነት እየተወያየን ሳለን በዚያ አካባቢ የታወቅ ሽፍታ እንደሚያነክስ ሁሉ ሸንክል ሸንክል እያለ ቀጭኗን የእግር መንገድ ይዞ ሽቅብ እኛ ወዳለንበት መጣ፡፡
ዛፉ አጠገብ ሲደርስ ከመልዐኩ ፊት ተንበረከከና፡፡
“መልዐክ ሆይ! ኃጢአቴ እጅግ ከብዶኛልና እባክህ ልናዘዝ፡፡ ሰላምና ምቾትን ላገኘ የምችለው ለአንተ ኃጢአቴን ከተናዘዝኩልህ ብቻ ነው!” አለው፡፡
መልዐኩም፤ “ወዳጄ ሆይ የእኔ ኃጢትምኮ እንዳንተው ኃጢአት እጅግ ከብዶኛል” አለው፡፡
ሽፍታ፡- “እኔኮ ሌባና ቀማኛ ነኝ”፡፡
መልዐክ፡- “እኔም ሌባ ቀማኛ ነኝ”
ሽፍታ፡- “መልዐክ ሆይ፤ እኔ ነብሰ-ገዳይ ነኝ፡፡ የብዙ ንጹሀን ሰዎች ደም በጆሮዬ ይጮሃል” አለው፡፡
መልዐክ፡- “እኔ ራሴም ነብሰ - ገዳይ ነኝ፡፡ የብዙ ንፁሀን ሰዎች ደም በጆሮዬ ይጮሃል፡፡”
ሽፍታ፡- “ግን እኮ መልዐከ ሆይ፤ እኔ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ወንጀሎችን ፈጽሜአለሁ”
መልዐኩም መለሰ፡- “እኔም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወንጀሎችን ፈጽሜአለሁ፡፡
ከዚህ በኋላ ያ ሽፍታ ብድግ አለና መልዐኩን ትኩር ብሎ ያየው ጀመር፡፡ በዐይኖቹ ውስጥ እንግዳ ሁኔታ ይታያል፡፡ ተሰናብቶን ሄደ፡፡ አካሄዱ ፈጣን፣ ደስተኛና ዓለም የቀለለው ሰው ዓይነት ነበር፡፡
ወደ መልዐኩ ዘወር ብሎ፣
“መልዐክ ሆይ ያልፈፀምከውን ወንጀል ፈጽሜአለከሁ ብለህ ስለምን ራስህን ትወነጅላለህ? ይሄ ሰው ከእንግዲህ በጭራሽ ባንተ እንደማያምን አይታይህም?”
መልዐኩም ሲመልስ እንዲህ አለ፡-
“እውነት ነው ወዳጄ፡፡ ያ ሽፍታ ከእንግዲህ በእኔ አያምንም፡፡ ግን እንደዚያ ቅስሙ ተሰብሮ አቀርቅሮ እያነከሰ መጥቶ የነበረ ሰውዬ፣ ቀና ብሎ ሰላምና ምቾት እየተሰማው መሄዱን አላየህም? አየህ ዋናው ነገር ከእንግዲህ በእኔ አለማመኑ ሳይሆን ዛሬ ደስ ብሎ ተመችቶት መሄዱ ነው!”
በዚህ ጊዜ ሽፍታው ከሩቅ ካለው የሸለቆ መኖሪያው ውስጥ ሆኖ ሲዘፍንና ሲያፏጭ ተሰማ፡፡ የድምፁም ገደል-ማሚቶ ሸለቆውን በደስታ ሞላው፡፡
***
አገሩ በደስታ እንዲሞላ የድምፁ ገደል - ማሚቶ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ የሚሞላ ሰው ለመፍጠር ይቻል ዘንድ፣ “በእኔ አመነም አላመነም ቀና ብሎ ይሂድ፣ እሱም ይመቸው” የሚል አስተዋይ መሪ፣ ፓርቲ፣ ድርጅት ፣ ወይም ማኅበር ማግኘት እንዴት ያለ መታደል ነበር? ከቶውንም ያጠፉትን አጥፍቻለሁ፣ የማያውቁትን አላውቅም ብሎ በግልጽ እቅጩን ተናግሮ መናዘዝ፣ ሲልም ንሥሀ መግባት ቢጨመርማ፣ የመፍትሄውን ግማሽ መንገድ መዝለቅ ነበር ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በአብዛኛው ያጣነው ይሄንን በግልጽ ችግርን የማስረዳት ባህል ነው፡፡ ለምሳሌ ደሞዝ ጨምሩልኝ ለማለት አዳም የዛፍ ፍሬ ስለመብላቱ፣ አብሃርም በድንኳን ስለመኖሩ፣ የኢዮብ ትዕግስት አስፈላጊ ስለመሆኑ፣ በላብህ ወዝ ጥረህ ግረህ ብላ ስለሚለው ትዕዛዝ ሁሉ ዘብዘቦ ሲያበቃ፣ የደሞዝን ታሪካዊ አመጣ በመተረክ በረዥሙ አውርቶ ያታክትና በመጨረሻ፣ “በአጭሩ ለማለት የፈለግሁት የሰው ልጅ ደሞዝ ቢጨመርለት ጥሩ ነው” ዓይነት የደሞዝ ጥያቄ ማቅረብ፡፡ ዱሮ በአንድ ቴያትር ላይ “ሶሻሊዝም ስብሰባ ያበዛል፡፡ ካፒታዝም ጭቆናና ብዝበዛ ያበዛል፡፡ ለማንኛውም ኢትዮጵያ ትቅደም፡፡ ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ አይጥፋ፡፡” ሲባል ነበር፡፡ ዛሬም ዘመኑ የስብሰባ ሆኗል እንደ ኅብረ ትርዒት የሚጠብቀው ሰውም አለ፡፡ በመሰረቱ ሀሳብን በግልጽ ማስቀመጥ አስቀድሞ ሀሳብን በራስ ውስጥ ማደራጀትን ይጠይቃል፡፡ ያ ደግሞ ንባብን የአካባቢ ግንዛቤን፣ አእምሮን ክፍት ማድረግን፣ ለመማር ዝግጁ መሆንን፣ ለማየት፣ ለመስማት፣ለመቅመስ ደግ መሆንን ይጠይቃል፡፡ ሁለት ተሟጋቾች ልቡናቸው ዘግተው፣ ለመነጋገርና ለመለወጥ ዝግጁ ሳይሆኑ “የኔን አቋም ካልተቀበለ ገደል ይግባ!” የሚል ቅድመ ውሳኔ ደንግገው ሲያበቁ እንወያይ ቢሉ የሁለቱም በር ተዘግቷልና ከንቱ ልፊያ ነው የሚሆነው፡፡ እርግጥ ነው እንዳለ መታደል ሆኖ የሚነገረውን የማይሰማ፣ በውሃ ወቀጣ አይነት ድግግሞሽ የሚነተርክ ልፋ ያለው ተናጋሪም ያጋጥማል፡፡ ዶክተርም ፕሮፌሰርም ቢሆን፣ “እወቅ ያለው ባርባ ቀኑ፣ አትወቅ ያለው ባርባ ዘመኑ” እንዲሉ፣ እንዴ የከረቸመበትን አእምሮ በግድ እንክፈተው ቢባል አጉል ድካም ነው፡፡ አንዳንዱ ተወያይ የጀመረበት ርእስ እስኪጠፋው ድረስ ሲዘበዝብ ውሎ፣መማር! ይሰኛል፡፡ “ሳያስቡ የጀመሩት ቀረርቶ ለመመለስ ያስቸግራል” እንደሚባለው ተረት መሆኑ ነው፡፡በሀገራችን በየዘመኑ የታዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ማህበራትና ታዋቂ ግለሰቦች በመጨረሻ ወድቀው ተንኮታኩተው የፀፀትና የንስሀ ዘመን እስኪደርሱ ድረስ በአንድ ዓይነት የትግል ሀዲድ ላይ ሲጓዙ መታየታቸው እጅግ አስደናቂና አሳዛኝ ነው- ትራጆ ኮሜዲ!፡፡ የአብዛኞቹ ጉዞ “ከማይረባ ጓደኛ የረባ ባለጋራ ይሻላል” የሚለውን ተረት ያላገናዘበ ነው፡፡ አንዳንዶቹ በሌላው መቃብር ላይ አብበናል ለምልመናል ሲሉ ቆይተው የባሰ ጥፋት የባሰ መከፋፈል፣ የባሰ መጠፋፋት ላይ የሚገኙ ይሆናሉ፡፡ መሪ ተዋናዩም ባላንጣውም፣ አስተኔ - ባህርያቱም በጅምላ የሚሞቱበት እጅግ የአሳዛኝ ትራጀዲ ቴያትር ይመስላል፡፡
ቃል የገቡት ሳይፈፀም የተመኙት እግቡ ቀርቶ እውገቡ ሳይደርስ ተሸመድምደው ጭራሽ እነሱንም ሀገርንም ህዝብንም የከፋ መቀመቅ ውስጥ ለሚከት ውድቀት ይዳርጋል፡፡ “ሞት የሌለበት አገር እሄዳሁ ብሎ ሬሳ ቆጥ ላይ የሚያስቀምጡበት አገር ደረሰ” የሚባልበት ሁኔታ ነው፡፡ እርስ በርስ በእውቅሁሽ ናቅሁሽ መተቻቸት፣ መሸራደድ መናናቅና መጠላለፍ ሥረ-ቢስ አካሄድ ነው፡፡ ማንንም በሁለት እግር ለመቆም አያበቃምና አንድም “ድፍርስ ብጥብጥን ትሰድባለች” እንዲሉ፣ አንዱ ካንዱ ላይሻል ነገር ሲያንጓጥጥና ሲያሽሟጥጥ ቢውልም እያደር መኮስመንን ቢያሳይ እንጂ አንዳችም የጥንካሬ ምልክት አይሆንም፡፡
ጠላትን የማይመጥንና የማይረታ ሙግትና ጩኸት ከንቱ ጉልበት መጨረስ ነው፡፡ ወደ ኋላ ሰብሰብ ብሎ አቅም ገዝቶ ጎልብቶ ወደፊት ለመራመድ መጣር ይሻላል እንጂ በትንሽ በትልቁ ጉዳይ፣ ባልተደራጀ ብቃት፣ እግር በጣለና ቃል እንዳመጣ መናገር እንኳን ወንዝ አስፋልት አያሻግርም፡፡ “ሞኝ ውሻ ነጎድጓድ ላይ ይጮሃል” እንዲል መጽሀፍ፣ ሲበዛ ለውድቀት የሚዳርግ ሲያንስ ደግሞ መሳቂያ የሚያደርግ ተግባር ነው፡፡
ልዩነቶች ምንጊዜም ይኖራሉ፡፡ በመሪና፤ በተመሪ በመንግስትና በተቃዋሚዎች ወዘተ መካከል መጠኑ ይለያይ እንጂ ምን ጊዜም ልዩነት ይኖራል፡፡ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከልም ልዩነት ይኖራል፡፡ ሆኖም መቻቻል መኖር አለበት፡፡ በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ባሉ አባላትም መካከል መቻቻልና መግባባት መኖር አለበት፡፡ በምሁራን መካከል መቻቻል መኖር አለበት፡፡ ማሰብና መተሳሰብ መኖር አለበት፡፡ በጠላትነት ተፈራርጆ፣ ጆሮን ከፍቶ ልብን ዘግቶ፣ ባንድ መታደግ ምንም ፍሬ አያፈራም፡፡ “ከተስማሙ አንድ እንጀራ ለዘጠኝ ባልንጀሮች እንደሚበቃ” ሁሉ “በጠብ ጊዜ አስር እንጀራ ለሁለት አይበቃም” የሚለውን ልብ ማለት ያለብን ሰዓት አሁን ነው፡፡ ባልታዛር ግራሺያን የተባለው ፀሐፊ “ሞኝ ከጓደኞቹ ከሚማረው ይልቅ ብልህ ከጠላቶቹ የሚማረው ይበልጣል” ያለውንም አለመርሳት ነው፡፡ የሕብረት ባንክ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዮ ክብረ በዓል ከሕዳር 11 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው። የዚሁ በዓል አካል የሆነው የእውቅናና የድጋፍ መርሀ-ግብርም ተከናውኗል፡፡ባንኩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢነት እናበዋና ስራ አስፈጻሚነት ያገለገሉ እንዲሁም አሁን በማገልገል ላይ ያሉ አመራሮች ከእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እጅ እውቅና እና ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ከ24 አመት እና ከዚያ በላይ በባንኩ ያገለገሉ ሰራተኞች ከባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሳምራዊት ጌታመሳይ እጅእውቅናና ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ ለ10 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለእያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዮን ብር በድምሩ 15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ድጋፍ የተደረገላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል፣ አወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት፣ እዝነት የአካል ጉዳተኛ ህጻናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ፣ ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ ዕድር፣ ባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት፣ በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ፣ ሳሉ መረዳዳት የዐይነ ስዉራንና አካል ጉዳተኞች ማኅበር፣ የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማኅበር እና ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማኅበር ናቸው፡፡

•  ማዕከሉ በ25 ሚ. ብር ወጪ  የማስፋፊያ ስራዎችን ማከናወኑን ገለጸ


33ኛው የገና የንግድ ትርዒት ፣ ባዛርና ፌስቲቫል ከታህሳስ 6 - 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ በዛሬው ዕለት ረፋዱ ላይ  በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት  አዳራሽ  በሰጠው መግለጫ፤ በዚህ  የገና የንግድ ትርዒት፣ ባዛርና ፌስቲቫል ላይ ከ500 እስከ 600 የሚደርሱ አምራቾች የሚሳተፉ ሲሆን፤  15 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውገ ጀማነህ እንደገለጹት፤ በዘንድሮው  የገና የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል ላይ  ድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ፣ ሄለን በርሄና አረጋኸኝ ወራሽ የሙዚቃ ሥራቸውን ያቀርባሉ፡፡

በተያያዘ ዜና፤ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ግቢ በ25 ሚሊየን ብር ወጪ  የማስፋፊያ ስራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ  የተገለፀ ሲሆን፤ በአሁን ሰዓት በአዲስ መልክ በኮንከሪት አስፋልት ተሠርቷል ::  በዚህ የማስፋፊያ ስራው ለገና የንግድ ትርዒት ፣  ባዛርና ፌስቲቫል ተሣታፊዎች አመቺ ሆኖ መታደሱ ብቻ ሳይሆን፣ ተጨማሪ ተሳታፊዎችን ለማስተናገድ ምቹ እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡  

አዘጋጁ ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ፣ ይህንን ተጨማሪ ቦታ የባህል አልባሣትና ጌጣጌጦች ፣  የአነስተኛና መካከለኛ ጀማሪ አምራች ኢንዱስተሪዎች ፣  የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማስተዋወቅ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች በአቅማቸው በአነስተኛ ዋጋ ተከራይተው ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ማስተዋወቅና መሸጥ እንዲችሉ እድል መፍጠሩን አስታውቋል፡፡

የገና የንግድ ትርዒት ፣ ባዛርና ፌስቲቫል  የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ሲሆን፤ ክፍያው የሚከናወነው በቴሌብር እንደሆነም ተነግሯል።

ኢትዮጵያ የሁለት ቅርሶችን ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከዩኔስኮ ተረከበች
ኢትዮጵያ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክና የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተረክባለች፡፡
የቅርሶቹን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ኢትዮጵያ ከዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል የአፍሪካ ቢሮ ሃላፊ ሙሃመድ ጁማ (ዶ/ር) መረከቧን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ በተካሄደው 45ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክና የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ-ምድርን በዓለም ቅርስነት ማስመዝገቧ ይታወሳል፡፡

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Wednesday, 01 November 2023 00:00

>

1, በስኳር በሽታ መያዝን ይከላከላል።
2, የካንሰር ስርጭትን ይከላከላልደ።
3, የሆድ ውስጥ አለሰርን ይከላከላል።
4, በልብ በሽታ መያዝን ይከላከላል።
5, ጉንፍን የጉሮሮ ህመም እና ትኩሳት የመሳሰሉትን ህመሞች የመፈወስ ሀይል አለው።
6, ሰውነታችን በቀላሉ በበሽታዎች እንዳይጠቃ ያግዛል።
7, ለጥርስ ህመም እና ለብሮንካይት ችግር እንደ መፍተሄ ይወሰዳል።
8, የደም ዝውውርን ማስተካከል ይችላል።
9, የኮልሌስትሮል መጠንን ማመጣጠን ይችላል።
10, የሰውነትን ክብደት። የተመጣጠነ እንዲሆን ያደርጋል።
Page 1 of 677