Administrator

Administrator

  (በር ነኣ አሃ በእድ በጎዳ ነኣ ሀርግያጋ ቤአነ ቤስ) - የወላይትኛ ምሳሌያዊ ንግግር


             በጥንት ጊዜ በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን፣ በአሜሪካው ፕሬዚዳንትና በራሺያው ፕሬዚዳንት ላይ የተቀለደ
አንድ ተረት ቢጤ ዕውነት ነበር፡፡ እነሆ፡-
የሁለቱ አገሮች ፕሬዚዳንቶች፤ ወታደራዊ ኃይላቸውን ያወዳድራሉ፡፡ የእኔ ይበልጥ፣ የእኔ ይበልጥ፣
ይፎካከራሉ። በመጀመሪያ የሩሲያው ፕሬዚዳንት፣ አሜሪካንንና የአሜሪካን ወታደራዊ ኃይል ሊጎበኙ ይሄዳሉ!
ከዚያም አንድ ጉዳይ ያነሳሉ፡፡
“የአንድ አገር ወታደራዊ ኃይል የሚለካው፤ ወታደሩ ለፕሬዚዳንቱ ባለው ታዛዥነት መጠን ነው!”
“እርግጥ ነው!” አሉ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት፡፡
“በል እንግዲያው ወታደሮችህ ምን ያህል ለአንተ ታማኝ እንደሆኑ አሳየኝ?”
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ይዘው፣ ወደ ወታደሮቻቸው ይሄዱና አንዱን ወታደር
ጠርተው፤ ወደ አንድ ገደል አፋፍ ይወስዱትና፤
“በል ወደዚህ አዘቅት ገደል ተወርወር” ይሉታል፡፡
ወታደሩም፤
“አይ አላደርገውም” ይላል፡፡
“ለምን?” ይሉታል፡፡
“ጌታዬ፤ በእኔ ደሞዝ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች” አሉኝ፤ (I have a family to support!) ይላል፡፡
የሩሲያው ፕሬዚዳንት በአሜሪካኑ ወታደር ታዛዥ አለመሆን እየሳቁ፤
“ቆይ የእኔን ወታደር ታማኝነት አሳይሃለሁ!” ይሉና የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ወደ ሩሲያ ይዘውት ይሄዳሉ፡፡
ከዚያም አንዱን ወታደር ጠርተው፤
“ወደዚህ አዘቅት ገደል ተወርወር!” ይሉታል፡፡
ወታደሩም፤
“ታዛዥ ነኝ ጌታዬ!” ብሎ ወደ ገደሉ ይወረወራል፡፡
እንዳጋጣሚ ግን አንድ የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ያርፍና ከሞት ይተርፋል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ወደሳቸው
እንዲመጣና ጥያቄ እንዲያቀርቡለት ይጠይቃሉ፡፡
ወታደሩ ተጠርቶ መጣ!
የአሜሪካው ፕሬዚዳንትም፤
“የእኔ ወታደር ወደ ገደል ተወርወር” ብለው፣ ‹የማስተዳድረው ቤተሰብ አለኝ› አለ፡፡ አንተስ እንዴት ልትወረወር ቻልክ?” አሉና ጠየቁት፡፡
ወታደሩም፤
“I too, have a family to support (እኔም የማስተዳድረው ቤተሰብ ስላለኝ ነው)” አለ፡፡
“እንዴት?” ቢሉት፤
“እኔ አልወረወርም ብል፤ እኔንም ቤተሰቤንም ነው የሚፈጁን!” ሲል መለሰ!
* * *
የአንድ ሰው ጥፋት ለቤተሰብና ለዘመድ አዝማድ ከሚተርፍበት ስርዓት ይሰውረን፡፡ ባለፈው ዘመን የመናገር ነፃነት ባልነበረበት ሁኔታ ውስጥ “አፍ-እላፊ” የሚባል ወንጀል ነበር - የአፍ ወለምታ! “ክብረ ነክ ንግግር” ነበር የሚባለው- ከወታደሩ ዘመን በቀደመው የንጉሱ ዘመን! አፍ - እላፊ ባለስልጣንን፣ መሪን፣ ሥርዓትን፣ አስተዳደርን ከመተቸት እስከ አገርን ማንቋሸሽ ድረስ የሚሰፋ ወንጀልን ያካትት ነበር፡፡ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው አነጋገርም ያስቀጣ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡- “ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማርያም ሀቀኛ ኮሚኒስት ናቸው!” እያለ ቀኑን ሙሉ ይለፈልፍ የነበረ ንክ ሰው፣ ታስሮ ነበር! ወንጀሉ፤ “ማንም የሚያውቀውን ሀቅ እየደጋገምክ የምትናገረው ነገር ቢኖርህ ነው!” ተብሎ ነው! “አለፈልሽ ባሮ!” እያለም የባሮን ወንዝ አስመልክቶ መፈክር ያሰማ ሰው፤ ሽሙጥ ነው ተብሎ የታሰረበት አጋጣሚም ነበር!
ዋናው ጉዳይ ሰው ሲታፈን፤ መናገሪያ፣ መተንፈሻ…፣ ዘዴ መሻቱ አይቀሬ ነው የሚለው ዕውነታ ነው!
ያሰበ ጭምር ይቀጣል በሚባልበት ሥርዓት የተናገረ፤ መወንጀሉና መቀጣቱ አይገርምም! ሰብዓዊ መብትና ዲሞክራሲያዊ መብት በማይከበሩበት አገር ምሬቶች ይጠራቀማሉ፡፡ መውጫ ቀዳዳ ይፈልጋሉና ሥርዓት ወዳለው አመፅ አሊያም ወደ ሥርዓተ - አልበኝነት ሊያድጉ ይችላሉ፡፡ የገዢዎችን የመግዛት አቅም ይፈታተናሉ፡፡ ምላሽ የሌላቸው ጥያቄዎች ይበዛሉ!! ዓለም የጋዝ ታንክ ለመሙላት ሲሯሯጥ፣ ደሀ አገሮች ሆዳቸውን ለመሙላት ይፍረመረማሉ። “የምግብ ፍላጎት አለመሟላት ከነፃነት ረሀብ ጋር ከተዳመረ፤ የህዝቦች ህልውና ጥያቄ ውስጥ ይገባል” ይባላል፡፡ የኢኮኖሚ ህመምና የፖለቲካ ህመም ከተደራረቡ፣ ከማስታገሻ ያለፈ በሽታን ይፈጥራሉ!
ፍትሕ-አልባ ሁኔታን ይቀፈቅፋሉ። ሌብነት እንደ ሥራ ይቆጠራል፡፡ አንድ መገንዘብ ያለብን ነገር ግን፤ ሰላም -አልባ ሁኔታ ውስጥ ከገባን የሰረቅነውን የምንበላበት ጊዜም ይጠፋል! ያደለብነው ኪስ ያፈሳል! የገነባነው ቪላ ይፈርሳል! ለሌሎች የቆፈርነው ጉድጓድ፣ የእኛው መቀበሪያ ይሆናል!
 በድሮ ጊዜ አንድ ባለስልጣን እሥር ቤት ሲጎበኙ፣ እስር ቤቱን የማስፋፋት ሰፊ እቅድ መያዙን አስተዳዳሪው ያስረዷቸዋል። ባለስልጣኑም፤ “ጥሩ ሀሳብ ነው፡፡ በደምብ ገንቡና አስፋፉት፡፡ ዞሮ ዞሮ የእኛም የወደፊት ቤታችን ነው!” አሉ ይባላል፡፡
 ያሉት አልቀረም - ገቡበት! ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን፤ በአንድ ተውኔቱ ውስጥ ንጉሡ እሥር ቤት መርቀው ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር፤ “የአባታችን እርስተ - ጉልት የሆነውን ይህንን የሀገር ወህኒ ቤት መርቀን ስንከፍትላችሁ፤ በተለመደው ባህላችሁ እንድትተሳሰሩበት ነው” ይለናል፡፡
ዛሬ፤ ከፊውዶ-ቡርዥዋው ስርዓት ወደ ሶሻሊዝም፤ ከዚያም ወደ ካፒታሊዝም አድገናል እያልን፤
የግሎባላይዜሽን ቅርቃር ውስጥ የገባን ይመስላል፡፡ በጥናት ያልተደገፈ ሥርዓት፣ መላ-አጥ መንገድ ላይ በትኖናል ቢባል ማጋነን አይሆንም!
ከእነ ስማቸው እማማ ጦቢያ፤ የሚባሉ የዱሮ ሴት ወይዘሮ ነበሩ አሉ- ደርባባና ጨዋ!
“ከዚህ ከባሪያ የገላገልከኝ ለታ፣ ወዲያውኑ ብትገድለኝ ግዴለኝም” ይሉ ነበረ ሲፀልዩ፡፡
ባሪያ ያሉት ሄደና ሌላ መንግሥት መጣ!
ይሄኛውንም ማማረር ቀጠሉ፡፡
“ምነው እማማ፤ ከዚህ ከባሪያ ገላግለኝ ሲሉ ነበረ፡፡ ገላገለዎት፡፡ አሁን ደግሞ ምን ሆኑና ያማርራሉ?” ቢባሉ፤
“አሃ! ያኛውኮ ከፋም ለማም የጨዋ ባሪያ ነው! ይሄኛውኮ የረባ ጌታ እንኳ የለውም! ጌታውን ቢያውቅ የማንም መጫወቻ አያደርገንም ነበር!” አሉ ይባላል፡፡
አይ እማማ ጦቢያ፡፡ አሜሪካንን አላወቁ! እንግሊዝን አላወቁ! የረባ ጌታ ማን እንደሆነ አላወቁም! ከፊውዳሊዝም ወደ ካፒታሊዝም መሸጋገር፣ የጌታ አማራጭ የማግኘት ጉዳይ ብቻ ቢሆን እንዴት በታደልን ነበር! ጌቶቻችንን በቅጡ አለማወቅ፣ የነገ ዕቅዳችንን በግልፅ እንዳናይ እንዳደረገን ይኖራል! ከዚህ ያውጣን!!
ለችግሮቻችን ምላሽ ፍለጋ ወደ ሹሞቻችን ማንጋጠጥ፣ ዘላቂና ሁነኛ መፍትሔ አያመጣም! ችግሮቹ የራሳችን የመሆናቸውን ያህል መፍትሔም ከእኛ መፍለቅ ይኖርበታል፡፡ በዲሞክራሲያዊና በፍትሐዊ መንገድ ያላፈራናቸው አለቆች፤ መልካም አስተዳደርን ያጎናፅፉናል ብለን ማሰብ “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ” ነው፡፡
ለዕለት ኑሯችን አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንኳ ሸምተን ማደር እያቃተን፤ ነው፡፡ ያም ሆኖ ስለ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን አሀዞች ማውራት አልገደደንም፡፡
አለቆቻችን መፍትሔ-ሰጪ አካላት መሆን ካቃታቸው መሰንበታቸውን እያወቅን፣ ሁነኛ ምላሽ ካልሰጣችሁን እያልን እነሱን ደጅ እንጠናለን፡፡ እንደ ሲቪልም፣ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲም ዕሳቤያችን ያው ነው! አሌ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የቤት-ጣጣ እያለብን፤ ነቅተን፣ በቅተን፣ ተደራጅተን፣ በአንድነት ፈጥረን የበሰለ መፍትሔ ከውስጣችን ማግኘትን ትተን፣ የሌላ ደጃፍ እናንኳኳለን!
የወላይታው ምሳሌያዊ አነጋገር ግንዛቤ የሚሰጠን እዚህ ላይ ነው፡- “የራሱን ልጅ አስከሬን አዝሎ፣ የታመመውን የሹም ልጅ ለመጠየቅ ይሄዳል!” ይለናል፡፡ ሹሞቹ ጤና መስለውት ነው!

 "ምርጫቸው ሁለት ነው፤ እጃቸውን መስጠት ወይም መደምሰስ"

              የመከላከያ ሰራዊት እስከ ትናንት ድረስ በትግራይ ተንቤን አካባቢ የህወኃት ታጣቂ ቡድንን ለህግ ለማቅረብ የመጨረሻውን እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ አመራር አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል አስታውቀዋል፡፡
ህግ የማስከበርና ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብ ስራችን የጀግኖች የአገር ባለውለታዎች መፍለቂያ በሆነው የተንቤን አካባቢ ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያሉት አቶ ነብዩ፤ በዚህ የህግ ማስከበር እርምጃ በአካባቢው ለሚደርስ ማናቸውም ችግሮች ተጠያቂው የህወሃት ታጣቂዎች ቡድን ይሆናል ብለዋል፡፡
ከመንግስት ወደ ታጣቂነት በድንገት የተቀየረው የህወሃት ቡድን መሪ ዶ/ር ደብረ ፂዮን ገ/ሚካኤል፤ ጦርነቱ አሁንም መቀጠሉንና ሰራዊታቸው ድል እያደረገ መሆኑን ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
"የኤርትራ ወታደር ወደ ትግራይ ገብቶ እየተዋጋና የህዝቡን ንብረት እየዘረፈ ነው" ሲሉ የወነጀሉት ዶ/ር ድብረጽየን፤ በዚህም የተነሳ ትናንት በመቀሌ ከተማም አመፅ መነሳቱን ለሮይተርስ የተናገሩ ሲሆን የፌደራል መንግስት በበኩሉ፤ ግለሰቡ የሚናገሩት ሁሉ ሃሰት ነው ብሏል፡፡  
መከላከያ ህዳር 19 ቀን 2013  መቀሌን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ የህወኃት ታጣቂ ቡድን ወደ ተንቤን ሃገረ ሰላም መሸሹ የተገለፀ ሲሆን በአሁን ወቅት በመከላከያ ሰራዊት ሙሉ ከበባ ውስጥ ይገኛል ተብሏል። ከትላንት በስቲያ ሃገረ ሰላም የገባው የመከላከያ ሰራዊት፤ ሁለቱን ትላልቅ ምሽጎች በዚያው ምሽት ማፍረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በትላንትናው ዕለትም ሦስተኛውን ምሽግ ያፈረሰ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ የቡድኑ ሚሊሻዎችም እጅ መስጠታቸው ታውቋል፡፡  


 በመጪው የፈረንጆች 2021 ዓመት ለዓለማቀፍ ጉብኝት ምቹ ናቸው ከተባሉ  የዓለማችን  21 ከተሞች መካከል የአፍሪካ መዲናዋ  አዲስ አበባ አንዷ ሆና ተመረጠች
 መቀመጫውን በኒውዮርክ ያደረገውና `Conde Nast traveler  የተሰኘውና ትኩረቱ አለማቀፍ ቱሪዝም አተኩሮ መፅሔት ከትናንት በስቲያ ይፋ ባደረገው  የ2021 ምርጥ የአለም የቱሪዝም ተመራጭ 21 ከተሞች የዘረዘረ ሲሆን በዚሁ ዝርዝር አዲስ አበባ ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ ከተሞች ተመራጭ ሆነዋል፡፡ እነሱም የጋናዋ አክራና የአንጎላ ሉዋንዳ ናቸው፡፡
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የዓለማቀፍ  የሰላም ሽልማቶች ማሸነፋቸውን ተከትሎ  የሃገሪቱ የቱሪዝም አቅም በ48.6 በመቶ መጨመሩን ያመለከተው የመፅሄቱ ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ በዩኒስኮ ከተመዘገቡ ዘጠኝ አለማቀፍ ቅርሶች  ይጠቀሳል፡፡
የአንድነት ፓርክ በአዲስ አበባ ተመራጭ የቱሪስቶች መዳረሻ እንደሚሆን በውስጡ የሚጎበኙ ነገሮች በዝርዝር በማስቀመጥ ነው መፅሔቱ ያወሳው፡፡  
በከተማዋ አዲስ የተከፈተው የቢላል ሀበሻ የማህበረሰብ ሙዚየምን ጨምሮ የተለያዩ ሚዚየሞች በአዲስ አበባ ለጉብኝት ተመራጭ እንደሚሆኑ በመፅሔቱ ተመልክቷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድም ምቹ በሆነው አገልግሎቱ ቱሪዝሙን በእጅጉ እንደሚደግፍ ነው በሪፖርቱ የተመለከተው፡፡
በዚሁ የ21 ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ከተሞች ዝርዝር ውስጥ ሜክሲኮ፣ ካሊፎርኒያ፣ ኒውዘርላንድ፣ ፣ኪዮቶ፣ኒውዮርክ፣መኖቫ፣ካናዳ፣ ኦስሎ ተካተዋል፡፡

 የቀድሞ  የ”ግንቦት 7” ዋና ፀሃፊ ፖለቲከኛና የነፃነት ታጋይ  አንዳርጋቸው ፅጌ በቅርቡ ለንባብ ካበቁትና  ባለፈው ቅዳሜ በጊዮን ሆቴል ከተመረቀው “የታፋኙ ማስታወሻ” የተሰኘ መፅሃፋቸው ሽያጭ የተገኘውን 100ሺህ ብር ለመከላከያ ሰራዊት ለግሰዋል።
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ድጋፉን ከትናንት በስቲያ ለመከላከያ የውጭ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ብ/ጀነራል ቡልቲ ታደሰ ያስረከቡ ሲሆን ድጋፉ ጉዳት ለደረሰባቸው ወታደሮች ቤተሰብ ይውላል ብለዋል።  በድጋፉ ርክክብ ወቅት ንግግር ያደረጉት አቶ አንዳርጋቸው፤በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ በህወሃት የተፈጸመው አሳዛኝ በደል ታሪክ ይቅር የማይለው መሆኑን ገልፀው በድርጊቱ በእጅጉ ማዘናቸውን ተናግረዋል።
ጥቃቱ በሟችና አካላቸው በጎደለ ቤተሰቦች ላይ ከፍተኛ ችግርና መከራ እንደሚፈጥር ስለሚታወቅ “ከጐናቸው ነን” ለማለት ድጋፉን ማበርከታቸውን  የገለፁት  አቶ አንዳርጋቸው፤ ሌሎችንም ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በ2006 ዓ.ም ከየመን ሰነዓ በህወሃት ደህንነቶች ታፍነው ለ4 ዓመታት በከባድ እስር ላይ የቆዩት የነፃነት ታጋዩ፤ “የታፋኙ ማስታወሻ” የተሰኘው መፅሀፋቸው ከታፈኑበት ጊዜ አንስቶ ከእስር ተፈተው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እስከተገናኙበት ድረስ ያለውን ታሪክ ያስቃኛል፡፡

 የቀድሞ  የ”ግንቦት 7” ዋና ፀሃፊ ፖለቲከኛና የነፃነት ታጋይ  አንዳርጋቸው ፅጌ በቅርቡ ለንባብ ካበቁትና  ባለፈው ቅዳሜ በጊዮን ሆቴል ከተመረቀው “የታፋኙ ማስታወሻ” የተሰኘ መፅሃፋቸው ሽያጭ የተገኘውን 100ሺህ ብር ለመከላከያ ሰራዊት ለግሰዋል።
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ድጋፉን ከትናንት በስቲያ ለመከላከያ የውጭ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ብ/ጀነራል ቡልቲ ታደሰ ያስረከቡ ሲሆን ድጋፉ ጉዳት ለደረሰባቸው ወታደሮች ቤተሰብ ይውላል ብለዋል።  በድጋፉ ርክክብ ወቅት ንግግር ያደረጉት አቶ አንዳርጋቸው፤በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ በህወሃት የተፈጸመው አሳዛኝ በደል ታሪክ ይቅር የማይለው መሆኑን ገልፀው በድርጊቱ በእጅጉ ማዘናቸውን ተናግረዋል።
ጥቃቱ በሟችና አካላቸው በጎደለ ቤተሰቦች ላይ ከፍተኛ ችግርና መከራ እንደሚፈጥር ስለሚታወቅ “ከጐናቸው ነን” ለማለት ድጋፉን ማበርከታቸውን  የገለፁት  አቶ አንዳርጋቸው፤ ሌሎችንም ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በ2006 ዓ.ም ከየመን ሰነዓ በህወሃት ደህንነቶች ታፍነው ለ4 ዓመታት በከባድ እስር ላይ የቆዩት የነፃነት ታጋዩ፤ “የታፋኙ ማስታወሻ” የተሰኘው መፅሀፋቸው ከታፈኑበት ጊዜ አንስቶ ከእስር ተፈተው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እስከተገናኙበት ድረስ ያለውን ታሪክ ያስቃኛል፡፡

 በማይካድራ በንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ ፈፅመው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ወንጀለኞችን መንግስት ተከታትሎ ለህግ እንደሚያቀርብ  ያስታወቀ ሲሆን  በክልሉ በጦርነት ለተጎዱ ዜጎች በረድኤት ድርጅቶች  ድጋፍ እየተደረገ ነው ብሏል።
የተባበሩት መንግስታትና የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል አፋጣኝ ሰብአዊ ድጋፍ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ መስማማታቸውን ተከትሎ፣ የረድኤት ድርጅቶች ድጋፍ ማድረግ መጀመራቸውንም ተገልጿል።
ጦርነቱን ሽሽት ወደ ሱዳን የተሰደዱ ከ43 ሺህ በላይ የክልሉ ተወላጆችም ወደ ሃገራቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ የማድረግ ተግባር መከናወን መጀመሩን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሪፖርት አስገንዝቧል። በክልሉ የምግብና የህክምና አገልግሎትን ጨምሮ መንግስት መሰረታዊ የሆኑ የመገናኛ አውታሮችን እየከፈተ መሆኑ የሚበረታታ ነው ያለው ሪፖርቱ፤ የክልሉ ነዋሪዎች ወደ መደበኛ የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው እየተመለሱ መሆኑን የረድኤት ተቋማት አረጋግጠዋል ተብሏል።
በሱዳን በስደተኛ መጠለያ ካምፕ ያሉ የክልሉ ተወላጆች ወደ ነበሩበት ተመልሰው የሚቋቋሙበት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን፣ ነገር ግን በማይካድራው አሰቃቂ የዘር ተኮር ጭፍጨፋ የተሳተፉ አካላት በስደተኛ ካምፑ እንዳሉ ጥቆማዎች በመቅረባቸው መንግስት አጣርቶ ጥፋተኞቹን ለህግ እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡
ስደተኞቹን መልሶ የማቋቋም ተግባሩም በስደተኞቹ ፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ መሆኑን መንግስት ማስታወቁ ተመልክቷል። በትግራይ ለተፈጠረው ሰብአዊ ቀውስና ስደተኞችን መልሶ ለማቋቋም ይውል ዘንድ የአውሮፓ ህብረት 4 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑንም ተመልክቷል፡፡ በትግራይ ከሚከናወነው የሰብአዊ ድጋፍ ጋር በተያያዘ፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በበኩሉ፤ከአለማቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ከ1ሺህ በላይ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን ደህንነት የማሳወቅ ተግባር ማከናወኑን አስታውቋል። ቀድሞ የተጎዱትን በማቋቋም ተግባር ላይ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማህበሩ ጠቁሟል፡፡;የዐቢይን ጭንቅላት  አልቻልነውም” ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም
መንግስት በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ከሚፈልጋቸውና እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ጥሪ ከቀረበላቸው ከፍተኛ የሕወኃት አመራሮች አንዷ የሆኑት የቀድሞ የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ከትላንት በስቲያ እጃቸውን በመስጠት የመጀመሪያዋ አመራር ሆነዋል፡፡ በሽሽት ላይ የሚገኘው የህወኃት ከፍተኛ አመራር #እጅ እንስጥ፤አንስጥ; በሚል ለሁለት ተከፍለዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡  
ወ/ሮ ኬሪያ በቪድዮ በተቀረጹትና በቅርቡ ይለቀቃል በተባለው ቪዲዮ፤ የጠ/ሚኒስትር ዐቢይ መንግስት ህወኃትን በጦርነቱ እንዳሸነፈው በግልጽ አምነዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲናገሩ፤ #የዐቢይን ጭንቅላትና ፍጥነት መቋቋም ስላልቻልን ነው; ብለዋል፡፡
“ለነገሩ አሁን አይደለም  የዐቢይን ጭንቅላት መቋቋም ያልቻልነው” ይላሉ ወ/ሮ ኬሪያ፤ “ ከፓርቲያችን ሲያባርረን….. እያንዳንዷን  አጀንዳ ተንትነን ሳናበቃ…. ሌላ አጀንዳ ያሸክመናል…በዚህም .ግራ ገባን” ሲሉም ያስረዳሉ፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራሯ፡፡ ፓርቲያቸው የተጋረጠበትን ተግዳሮትም ሲቀጥሉ፡-“ራሳችንን በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ማየት ተሳነን፤በፍጥነቱና በሚነካካቸው በርካታ ጉዳዮች ውስጥ አሰረን፤ከፓርቲያችን ኢህአዴግ አንደፋድፎ አባረረን” ሲሉም ጠ/ሚኒስትሩን እንዳልቻሏቸው ጠቅሰዋል፡፡  
በዐቢይ አጀንዳ ሰጪነት ጦርነቱን እናሸንፋለን ብለን ተሸንፈናል ብለዋል-  ወ/ሮ ኬሪያ፡፡ ”የዶ/ር ዐቢይን ፍጥነቱንና ቴክኖሎጂውን መቋቋም አልቻልንም፤በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ እንደተሸነፍን አምነናል”ሲሉም እውነታውን አስረድተዋል፡፡ ወ/ሮ ኬሪያ ያሉት ሁሉ መሬት ላይ የሚታይ ተጨባጭ እውነት ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፤የንግግራቸውን ዓላማ እንደሚጠራጠሩት ግን ይገልጻሉ፤ምክንያታቸውም #ከዚህ ቀደም  ህወሃት ሽንፈትን በግልፅ የማመን ባህል የለውም; የሚል ነው፡፡  


              የአገርን ሉአላዊትና ህግን ለማስከበር ሲሉ የአካል ጉዳት የሚደርስባቸው ጀግኖችን በዘላቂነት የመንከባከብና የጀግና ሰማዕታት ልጆችና ቤተሰቦች ቀሪ ዘመናቸውን ያለ እንግልትና ችግር እንዲገፉ የማገዝ አላማ ያለው ብሔራዊ የጀግኖችና የህፃናት አምባ እውቅናና ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ በአዲስ መልክ ተቋቁሟል፡፡
በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና በዲያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር የተለያዩ በጎ ተግባራትን በሚያከናውነው “የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የተግባር ምክር ቤት CEDA” የተሰኘ ተቋም ትብብር፣ በአዲስ መልክ የተቋቋመውን የብሔራዊ የጀግኖችና የህፃናት አምባ ህጋዊ የምዝገባና የእውቅና የምስክር ወረቀት የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አዳሙ አንለይ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እጅ ተቀብለዋል፡፡
አምባውን በአዲስ መልኩ ለማቋቋም የተካሄደውን እንቅስቃሴ በተመለከተ መረጃ ለመስጠት ባለፈው ሰኞ በጦር ሃይሎች ሆስፒታል በተካሄደው ስነስርዓት ላይ የተቋሙ መስራቾች እንደተናገሩት፣ አምባው በአዲስ መልኩ መቋቋሙ ለአገር ባለውለታ ጀግኖችና ቤተሰቦቻቸው ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
የቀድሞው የጀግኖች አምባ በመፍረሱ ምክንያት ለአገራቸው ሲታገሉ የአካልና የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችና ቤተሰቦቻቸው ለችግር መጋለጣቸውን በወቅቱ የተናገሩት የአምባው ጽህፈት ቤት ሃላፊ ብ/ጄ ካሳዬ ጨመዳ፣ አምባውን በአዲስ መልኩ በማቋቋም፣ የራሱ የሆነ የገቢ ምንጮች እንዲኖሩትና ጀግኖችና የሰማዕታት ልጆችን በቋሚነት ለማገዝ እንዲችል የተጀመረውን ጥረት መደገፍ፣ የሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጎች ታሪካዊ ሀላፊነት በመሆኑ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት የሚኖሩ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የጦር ሀይሎች ሆስፒታል አዛዥ ብ/ጄ ሀይሉ እንዳሻው፣ በቅርቡ በአዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታውጆ መንግስትም የጀግኖችና የህፃናት አምባን ለማቋቋም በእንቅስቃሴ ላይ እንደነበር ጠቁመው፣ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተለይም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ከተቋሙ ጋር በመሆን ድርጅቱን በመመስረታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ለአገር ክብርና ለሉአላዊነት ሲሉ በጦር ሜዳ ጉዳት የሚደርስባቸው ወታደሮችንና  ቤተሰቦችን በዘላቂነት ለማገዝ የሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ፤ ለዓላማው መሳካት መከላከያ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።እስካለፈው ሳምንት በአለማችን ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ በ3ኛ ደረጃ ላይ የነበረው የቴስላ ኩባንያው መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤለን መስክ፣ ባለፈው ሰኞ ተጨማሪ 7.2 ቢሊዮን ዶላር ሃብት ማፍራቱንና አጠቃላይ ሃብቱ ወደ 128 ቢሊዮን ዶላር ማደጉን ተከትሎ፣ በማይክሮሶፍቱ መስራች ቢል ጌትስ ተይዞ የነበረውን የአለማችን 2ኛው ባለጸጋነት ስፍራ መረከቡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የ49 አመቱ አሜሪካዊ ቢሊየነር መስክ የ20 በመቶ ድርሻ የያዘበትና የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች የሆነው ኩባንያው ቴስላ የአክሲዮን ዋጋ ሰኞ ዕለት የ6.5 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱን ተከትሎ፣ 7.2 ቢሊዮን ዶላር ያህል ተጨማሪ ሃብት ማፍራቱን የጠቆመው ዘገባው፤ የኩባንያው ሃብትም 521 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አመልክቷል፡፡ ኤለን መስክ በ2020 የፈረንጆች አመት ብቻ የተጣራ ሃብቱ በ100.3 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን ያስታወሰው ዘገባው፣ ይህ የሃብት ጭማሪ በአለማችን ከፍተኛው መሆኑንና ቢሊየነሩ በአለማችን ባለጸጎች ዝርዝር ውስጥ በአመቱ መጀመሪያ 35ኛ ደረጃ ላይ እንደነበርም አክሎ ገልጧል፡፡
የአማዞኑ መስራች ጄፍ ቤዞስ በ182 ቢሊዮን ዶላር አሁንም የአለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፣ ቢል ጌትስ በ129 ቢሊዮን ዶላር ሶስተኛ፣ የፌስቡኩ መስራች ማርክ ዘከርበርግ በ105 ቢሊዮን ዶላር አራተኛ፣ በርናንድ አርኖልት በ104 ቢሊዮን ዶላር አምስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙም  ጨምሮ ገልጧል፡፡

 ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ15 የአፍሪካ አገራት መንገደኞች ላይ አዲስ የጉዞ ገደብ የጣሉ ሲሆን፣ የአገራቱ መንገደኞች ከቀጣዩ ወር ጀምሮ ወደ አሜሪካ መግባት የሚችሉት አስቀድመው እስከ 15 ሺህ ዶላር በቦንድ መልኩ ካስያዙ ብቻ ነው መባሉ ተዘግቧል፡፡ የትራምፕ አስተዳደር ጊዜያዊ ያለውን የጉዞ ገደብ የጣለባቸው አገራት አንጎላ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ጋምቢያ፣ ጊኒቢሳኡ፣ ላይቤሪያ፣ ሊቢያ፣ ሞሪታኒያ፣ ሱዳን፣ ሳኦ ቶሜና ፕሪንሲፔ፣ ኬፕ ቨርዴ እና ብሩንዲ እንደሆኑ የዘገበው ቢቢሲ፤ በአገራቱ ላይ አዲሱን ገደብ መጣል ያስፈለገው ወደ አሜሪካ ከገቡ የአገራቱ መንገደኞች መካከል ከ10 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ እንደሚቆዩ በመረጋገጡ እንደሆነ አመልክቷል፡፡
የአገራቱ መንገደኞች በቦንድ የሚያስይዙት ገንዘብ ከአሜሪካ ሲወጡ እንደሚመለስላቸው የጠቆመው ዘገባው፤ አዲሱ የጉዞ ገደብ ለ6 ወራት ያህል ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ ከተረጋገጠ ቀጣይ እንዲሆን ይደረጋል መባሉንም አክሎ ገልጧል፡፡