Administrator

Administrator

Wednesday, 14 October 2020 15:42

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

‹‹የሐሳብ ቀን-ዘሎች››
                                 (አሳዬ ደርቤ)

           በእኔ ዘንድ የእረፍት ትርጉሙ ቁጭ ማለት ሳይሆን ‹‹ሥራ መሥራት›› ነው። ከየትኛውም ነገር በላይ የሚያዝናናኝ ደግሞ የምወደውን ሥራ መሥራት ነው። ስለሆነም ቢሮ ውዬ ስመለስ ቤት ገብቶ ከማረፍ ይልቅ መጻፍ ደስ ያሰኘኛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም፤ በጥሩ እንቅልፍ ካሳለፍኩት ሌሊት ይልቅ ለመንፈሴ የሚጥም ሼጋ ጽሑፍ ስሞነጫጭር ያደርኩበት ሌሊት ማለዳዬን ውብ ያደርገዋል፡፡
ይህ ሁኔታ ግን ኪነ-ጥበባዊ ይዘት ላላቸው ጽሑፎቼ እንጂ ሳልወድ በግዴ ከአክቲቪስት ጎራ ተሰልፌ እዚህ ሶሻል ሚዲያው ላይ የምለጥፋቸውን ጽሑፎች አይመለከትም፡፡ እነሱ ሰላሜን እና ግማሽ ጎፈሬዬን የሚነጥቁኝ ናቸው፡፡ ያም ሆኖ ግን የሆነ ጥቃት ሲፈጸም ‹‹ምን አገባኝ›› ብዬ ከመተኛት ይልቅ ለውጥ አመጣሁም አላመጣሁም ‹‹ያገባኛል›› በሚል ስሜት ማለት ያለብኝን ነገር ማስተጋባት፣ ለመላጣ ጭንቅላቴ ምቾት ይሰጠዋል፡፡ አካበድኩ መሰል! .
በሌላ መልኩ ግን የወቅቱ የፖለቲካ አየር ፌስቡካችንን የኀዘን ድንኳን አድርጎት በመክረሙ የተነሳ እለታዊ አጀንዳዎችን ችላ ብሎ ሌሎች ነገሮችን ሶሻል-ሚዲያው ላይ ለማጋራት ጊዜው ባይፈቅድልንም አልፎ አልፎ ግን ግላዊ ዝንባሌዬን ባለመተዌ ይሄው ሦስተኛ መጽሐፌን ለማሳተም በቃሁ፡፡
መጽሐፉ ‹‹የሐሳብ ቀንዘሎች›› ይሰኛል፡፡ በወሎ አማርኛ ከሐሳብ ዛፍ ላይ የተመለመሉ ቅርንጫፎች እንደማለት…ሽፋኑ ላይ ያለውን ምሥል እንዳሻችሁ ተርጉሙት… የመጽሐፉን ውስጣዊና ውጫዊ ዲዛይን ያቀናበረው ታዋቂው ባለሙያ ሙሉቀን አስራት ሲሆን ለየት ባለ የሕትመት ጥራት ታትሞ ሼልፍ ላይ ውሏል፡፡ ይሄውም መጽሐፍ 275 ገጾች ያሉት ሲሆን በውስጡም ከ25 በላይ ወጎች እና ተረኮች ተካትተውበታል፡፡ በይዘት ረገድ ደግሞ ከሚያስጨንቀው ይልቅ ፈገግ የሚያስብለው ላይ፣ ከዛሬ ይልቅ ትናንት እና ነገ ላይ፣ ከሶሻል ሚዲያው አጀንዳ ይልቅ ምድራዊው ላይ የሚያተኩር ሲሆን ትወዱታላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
.አከፋፋዮቹ ጃዕፋር መጽሐፍት መደብር (ለገሃር) እና ጦቢያ መጽሐፍት መደብር (ካሳንችስ) ሲሆኑ ከነገ ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ በሁሉም መጽሐፍት መደብሮች ታገኙታላችሁ፡፡ በቀጣይ ሳምንት ደግሞ በክልልና በዞን ከተሞች የምናደርስ ሲሆን ባሕር ማዶ ላላችሁ ደግሞ በአድራሻችሁ የምንልክ ይሆናል፡፡ በአንድ ሴሚናር ላይ አነቃቂ ትምህርት የሚሰጠው ኮበሌ፤ ለታዳሚው አንድ ልምምድን ያዝዛል፡፡
“ሁላችሁም እስቲ ቅንጡ መኪና ገዝታችሁ አስቡ!” አላቸው፡፡
ታዳሚው በእዝነ ልቦናው ያሻውን ቅንጡ አውቶሞቢል ሸመተ፡፡
“እስቲ አሁን ደግሞ መኪና ውስጥ ግቡበትና ሞተሩን አሙቁት!” አለና ዙሪያ ገባቸውን ይሰልላቸው ጀመር፡፡
“መኪናውን በፍጥነት ማብረር ጀምሩ! ንዱት በደንብ ንዱት! እጃችሁን በመስኮት አውጥታችሁ፣ ንፋሱ ሁለመናችሁን ሲያረሰርሳችሁ ይሰማችሁ፤ ንዱት፣ ንዱት!” እያለ ትዕዛዙን ቀጠለ፡፡
የሴሚናሩ ታዳሚው በልምምዱ በስሜት ከፍታ ውስጥ ገብቷል፡፡ ሁሉም ያለሙትን ቅንጡ አውቶሞቢል፣ በመረጡት ጎዳና ላይ እያከነፉ ነው፡፡ ልምምዱን አቋርጦ ወጣ፡፡ “ምን ነክቶህ ነው አቋርጠህ የምትወጣው?” ተብሎ በተጠየቀ ጊዜ፤ “አይ እኔ መንጃ ፍቃድ የለኝም!” ሲል አስገራሚ ምላሽ ሰጥቷል ይባላል፡፡
የወጓን ፍሬ ነገር ቀልዱ አስቀድሞ ሹክ ይለናል፡፡ የሴሚናሩ ታዳሚዎች፣ በድሃ ይመሰላሉ፤ መኪናው ደግሞ ገና ያላገኙት ሕልማቸው ወይም ቅቤያቸው ነው፡፡ ድሃ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ፣ የሚለው ሀገርኛ ብሂል፣ በውስጡ ብዙ የሚመነዘር ቁምነገርን አዝሏል፡፡ ድሃ እና ቅቤ፤ ጫፍና ጫፍ የቆሙ፤ የሁለት ዓለም ኹነቶች  ናቸው፡፡ በመካከላቸው ጊዜ የሚባል ህላዌ አለ፡፡ የነጣጠላቸው የጊዜ ድልድይ ሲሰበር፣ ሁሉም ነገር ያከትማል፡፡ ድሃው ለዘመናት የባተተለት ሕልሙ፣ በእጁ ይገባል፡፡ መባተቱ ግን፤ ይለጥቃል፤ መቋጫው አድማስ ነው፡፡ ደግሞ ሌላ ቅቤ ለመጠጣት ይባዝናል፡፡ ሰዶ ማሳደዱ፣ እስከ ዕድሜ ማክተሚያ ድረስ ይዘልቃል፡፡
ቅቤው ዝና፣ ንዋይ፣ደስታንና ክብርን ሊወክል ይችላል፡፡ የእነዚህ ሁሉ ነዳይ ሰው፣ ድሃ ነው፡፡ ድህነት አንጻራዊ ነው፡፡ ጋሪ ያለው ባጃጅን ይመኛል፤ ባጃጇ በእዝነ ኅሊናው የምትንቆረቆር ቅቤው ልትሆን ትችላለች፡፡ ባጃጇ የምናብ ጠኔውን የምታጠረቃ ቅቤው ነች፡፡ በእርግጥ ያለሙትን ቅቤ ማግኘት ኩነኔ አይደለም፡፡ ጣጣው የሚመጣው፤ ቅቤውን ከቃረሙ በኋላ የሚፈጠረውን የስሜት መዘበራረቅ መሸከም የሚያስችል ጫንቃ ከሌለን ነው፡፡ ለዚህ እኮ ነው፤ ስኬታማ እየሆንን በሄድን ቁጥር፣ የደስታ ምንጮቻችን እየተመናመኑ የሚሄዱት፡፡
ምኞት፣ ጉጉት ወይም እጥረት በራሱ መርገም አይደለም፡፡ አንዳንዴ እንደውም ለመኖራችን ትልቅ ዋስትና ይሆናል፡፡ በማግኘትና በእጦት መካከል የጊዜ ወሰን አለ፡፡ ይህም  ሁልጊዜ እየታደስን እንድኖር የሚረዳን አጋራችን ሊሆን ይችላል። ሁሉ በእጃችን በደጃችን ሲሆን፣ ሌላ የመንፈስ ጦርነት ውስጥ እንገባለን፡፡ ጥበቃ ያከትማል። ነገን ማለም ከንቱ ይሆናል፡፡ ያን ጊዜ መሸሸጊያችን ምን ይሆናል?
እኔ ባቅሜ አርቴፊሻል እጥረት በመፍጠር፤ የሥነልቦና ሚዛኔን ለመጠበቅ እተጋለሁ፡፡ ጎተራዬን ሆን ብዬ በማጉደል፤ በጥበቃ ውስጥ ያለውን ደስታ አጣጥማለሁ። ማለዳ አፌ ላይ የማደርገውን ቁራሽ በመዝለል፣ ምሳዬን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡ ምሳዬ ደርሶ ጎተራዬን ሳደላደል፣ ከወትሮው የተለየ የከፍታ ስሜት ይሰማኛል፡፡ የአእምሮ ምግብ ጥበቃ /ቅቤ/ ነው፡፡ የሚጠበቅውን ነገር በሙሉ ከነጠቅነው፤ ነገር አለሙን ያጨልምብናል፡፡
ለዚህም እኮ ነው፣ ታላቁ እስክንድር፣ የመጨረሻውን ባላንጣ ካሸነፈ በኋላ፣ ቤት ዘግቶ ስቅስቅ ብሎ ያነባው፡፡ “የቀረውን አንድ ባላንጣዬን ድል ነሳሁት፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ጉጉትም ሆነ ምኞት የለኝም፡፡ አንድያ የተስፋ ጥሪቴን ተነጠቁ፡፡” ነበር ያለው፡፡ መንፈሳዊ ክፍታ ውስጥ ካልገባን በስተቀር፣ በዓለም ላይ  የተመኘነው ሁሉ እጃችን ሲገባ፣ እንደ እኛ ብስጩ አይገኝም፡፡
አእምሮ እንዳልተገራ ፈረሰ ነው፡፡ በየደቂቃው እንደ ማእበል ይናጣል፡፡ አንዱን ይዞ ሌላውን ይጥላል፡፡ ጠብ እርግፍ ብሎ ያገኛትን ጉብል ከጎኑ በሻጣት ማግሥት፤ ከነመፈጠሯ የሚረሳት ኮበሌ፤ ጊዜን እጀ ሰባራ ማድረጉ አይቀርም፡፡ ጉብሏን የግሉ ሲያደርጋት፤ በአእምሮው ውስጥ ማርጀት ትጀምራለች፡፡ ጉጉቱን ይነጠቃል። ሁለመናዋን ይለምደዋል፡፡ “ባልተቤትህ ውብ ናት" ሲሉት፤ "ያልተነካ ግልግል ያውቃል፡፡ አሁን ምኗ ነው የሚያምረው?!” ይላል፤ ሌላ በመተካተ ስሜት፡፡
በጊዜ ማእቀፍ ጠብቀን የምንቃርመው ደስታ፣ "ስሄድ አገኘኋት፣ ስመለስ አጣኋት; እንደሚባለው ነው፡፡ እድሜው አፍታ - ጤዛ ይሆናል፡፡ ለዓመታት የዘለቀ የስሜት መቃተታችንን የሚመጥን፤ የሥነልቦና እርካታን አያጎናጽፈንም፡፡ ቆብ ደፍቶ ሰዎቹ ሁሉ በአድናቆት ሲሰግዱለት እያለመ፤ ከኮሌጅ የሚማር ቀለም ቆጣሪ፣ ከቅቤ ነዳይ ጎራ ይመደባል፡፡ የሚማረው ትምህርት፣ ልክ እንደ ታክሲ ወረፋ ይታክተዋል፡፡ ደስታው፣ ቅቤው፣ ምረቃው ነው፡፡ ትልቁ መርዶ፤ ያ ሁሉ ዘመን የቃተተለት ግብ፣ ጠኔ ያጠናገረውን ስሜቱን ማረስረስ አለመቻሉ ነው፡፡
ይኸ ሁሉ መብሰክሰኬ፤ ለውጥን ተጠይፈን፤ ባለንበት እንደ ኩሬ ረግተን እንኑር፤  የሚለውን መፈክር ለማሰማት አይደለም፡፡ ሥነልቦናዊ ቁርኝትን እንበጥሰው፡፡ አእምሮ የለመደውን የስሜት ቀለብ፣ ግልምቢጥ እናድርግበት፡፡ እንቀያይርበት፡፡ ደስታን ከስኬቱ ሳይሆን፣ ከሂደቱ መቃረም ይልመድብን፡፡ ከተራራው ይልቅ ወደ ተራራው በሚያዘልቀን ጎዳና ላይ፣ በምናዘግመው፣ በእያንዳንዱ እርምጃ እንመሰጥ፡፡ ከቅቤ ይልቅ፤ ቅቤውን ለማግኘት በምናፈሳት ጠብታ ላብ፣ ሐሴት እናድርግ፡፡
ባትተን የምናሳካው ግብ፣ የጊዜ ባሪያ እንደሆነ ለማወቅ አስረጂ አያስፈልገንም። ከስኬቱ የምናገኘው የስሜት ከፍታ፣ ጥቂት ተፍገምግሞ፣ መልሶ ወደነበረበት የስሜት እንጦሮጦስ ሲወርድ፤ በተደጋጋሚ ጊዜ ታዝበናል፡፡ ጠቢባን ደስታ ስኬትን እንጂ፤ ስኬት ደስታን አያመጣም ይላሉ። ህልማችንን - ቅቤያችንን፤ የእርካታችን ምንጭ አድርገን መቁጠር ዳፋውን ያከፋብናል፡፡
ቻይናዊያን፤አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር፣ በአንድ እርምጃ ይጀመራል ያሉት ያለነገር አይደለም፡፡ የግባችንን ፍሬ ወይም ቅቤውን የምናጣጥመው፤ ልክ አንድ ሺኛው ኪሎ ሜትር ላይ ስንደርስ መስሎ ከታየን፣ ተላላ እንሆናለን፡፡ እያንዳንዱ እርምጃ በራሱ ፍጻሜ ነው፡፡ ስኬት ነው፡፡ ቅቤ ነው፡፡ የእያንዳንዱ እርምጃ ስኬት ጥምር ውጤት፤ ዐሥር ሺህ ኪሎ ሜትሩን ይፈጥረዋል። ደስታን ከእያንዳንዷ ሽርፍራፊ ቅጽበት ለመቃረም አንሞክር፡፡ ይኽ ዓይነት የልቦና ውቅር፣ ከጊዜ ቀንበር ነጻ ያወጣናል፡፡

- ድምጻዊ ኤልያስ ተባባል

          በ1970ዎቹ አጋማሽ ባሳተመው የመጀመሪያ አልበሙ ነው ከሕዝብ ጋር በስፋት የተዋወቀው፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገው ድምጻዊ ኤልያስ ተባባል፤ ወደ ትውልድ ሀገሩ ከተመለሰ ገና ሁለት ወሩ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ከጉራጌ ተወላጆች ጋር ጥልቅ ወዳጅነትና ትስስር እንዳለው የሚናገረው ድምጻዊው፤ የዘንድሮ የመስቀል በዓልን በወዳጆቹ ግብዣ፣ በጉራጌ ዞን መሠረተ ወገራም ነው ያከበረው፡፡ ባለፈው ቅዳሜ መስከረም 16 ቀን 2013 ጋዜጠኛ ብርሃኑ ሰሙ፣ ድምጻዊ ኤልያስን በመሠረተ ወገራም አግኝቶት አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡ እነሆ፡-


             ከማሲንቆ ጋር የተዋወቅኸው እንዴት ነው?
የልጅነቴን የመጀመሪያ 8 ዓመታት ያሳለፍኩት በትውልድ ሀገሬ ጎንደር ነው። በአዲስ አበባ ጊዮርጊስ አካባቢ ትዳር መሥርታ ትኖር የነበረችው እህቴ፣ ወደዚህ እንደመጣ ምክንያት ሆነችኝ፡፡ ምሽት ላይ በገዳም ሠፈር የማየው ሙዚቃ ቀልቤን እንደሳበው ያስተዋለችው እህቴ፤ ወደ ትውልድ መንደሬ ልትመልሰኝ ሞክራ ነበር። አሻፈረኝ አልኩ፡፡
የራሴን መንገድ ይዤ መጓዝ የጀመርኩትም በዚያ አጋጣሚ ነበር፡፡ ከዚያም የምሽት ሙዚቃ ቤት ተቀጠርኩ፡፡ ድምጻዊያኑ እረፍት ሲያደርጉ ማሲንቋቸውን እያነሳሁ በመነካካት ነው፣ ከመሣሪያው ጋር የተዋወቅሁት፡፡ 12 ዓመት ሲሞላኝ በሙዚቃ ሙያ መሰማራት እንደምችል እርግጠኛ ነበርኩ፡፡   
በማሲንቆ ማንጎራጎር መተዳደሪያህ የሆነው ከመቼ ጀምሮ ነው?
በ1972 ዓ.ም ለአምባሳደር ቴአትር ቤት፣ የባሕል ሙዚቃ ቡድን ለማደራጀት ማስታወቂያ ሲወጣ፣ ተመዝግቤ ውድድሩን አለፍኩ፡፡ በወቅቱ ከተቀጠሩት መካከልም፡- ፀሐዬ ዮሐንስ፣ አበበች ደራራ፣ ንዋይ ደበበ … ይገኙበታል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ቴአትር ቤቱ የፊልም ማዕከል ይሁን ተባለና፣ እኛ ወደ ራስ ቴአትር ተዛወርን፡፡
እስቲ የሲኒማ ራስ ትዝታዎችህን አጫውተኝ---?
እኛ ወደ ቴአትር ቤቱ እንደተዛወርን ከፍተኛ መነቃቃት ተፈጠረ፡፡ በየሳምንቱ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ለሕዝብ የሚቀርብ ‹‹የኪነ ጥበባት ምሽት›› ተጀመረ፡፡ በተለይ የባህል ሙዚቃ ቡድኑ በተመልካች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አገኘ፡፡ በሙዚቃው እኔን ጨምሮ ፀሐዬ ዮሐንስ፣ ንዋይ ደበበ፣ አበበች ደራራ፣ መሐመድ አወል፣ ሻምበል በላይነህ … በቴአትሩም ጥላሁን ጉግሳ፣ ደበሽ ተመስገን፣ እንቁሥላሴ ወርቅአገኘሁ፣ አይናለም ተስፋ … ከሕብረተሰቡ ጋር እንድንተዋወቅ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። ዝግጅቱን ለማየት የሚመጣው ሕዝብ ሰልፍ፣ ከሲኒማ ራስ እስከ ተክለ ሃይማኖት ይደርስ ነበር፡፡   
የመጀመሪያ ካሴትህን ለማውጣት የገጠሙህ ተግዳሮቶች ምን ነበሩ?
በራስ ቴአትር የባህል ሙዚቃ ቡድን ዐባል ሆኜ በመስራት ላይ እያለሁ ነበር ካሴት ለማሳተም እንቅስቃሴ የጀመርኩት፡፡ አሳታሚ ማግኘቱ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ብዙ ቦታ ዞሬ ተስፋ ወደመቁረጡ በደረስኩበት ሰዓት አምባሰል ሙዚቃ ቤት ሄድኩ፡፡ መደብሩ ውስጥ ገብቼ ያገኘሁትን አንድ ወጣት ‹‹የሙዚቃ ቤቱን ባለቤት ፈልጌ ነበር›› ስለው፤ ‹‹እኔ ነኝ ምን ፈልገህ ነው?›› አለኝ፡፡ በወቅቱ አቶ ፍቃዱ ዋሪን አላውቀውም ነበር። ራሱን ካስተዋወቀኝ በኋላ የሄድኩበትን ጉዳይ ነገርኩት፡፡ በዕለቱ እግዚአብሔር ሲረዳኝ ደራሲ ተስፋ ለሜሳ በሙዚቃ ቤቱ ውስጥ ነበር፡፡ ስለ እኔ ማንነትና ሥራዎች በማድነቅ፣ ለአቶ ፍቃዱ ዋሪ ነገረው፡፡  አምባሰል ሙዚቃ ቤትም ካሴቴን ሊያሳትምልኝ ከስምምነት ላይ ደረስን፡፡ ስምምነት ካደረግን ከሦስት ሳምንት በኋላም ካሴቱ በ1976 ዓ.ም ለገበያ ቀረበ፡፡ ሥራው ወዲያው ነበር ተቀባይነት ያገኘው፤ እኔንም ከዘመኑ ዝነኞች አንዱ አደረገኝ፡፡
የአንተ ካሴት በታተመበት ዘመን፣ አምባሰል ሙዚቃ ቤት ከነበረበት ሠፈር በስተጀርባ፣ በቀድሞ ከፍተኛ 7 ቀበሌ 32 (ቁጭራ ሠፈር) እና ቀበሌ 34 (ቀጤማ ተራ) መንደሮች፣ የበርካታ ‹‹አዝማሪ››ዎች መኖሪያና መሰባሰቢያ እንደደነበሩ ይታወቃል፡፡ ስለነዚህ ሰፈሮች የምታውቀው ታሪክ አለ?
በዘመኑ በየሆቴልና መዝናኛ ስፍራዎች ምሽት ላይ የሚታዩ በርካታ ማሲንቆ ተጫዋቾች ነበሩ፡፡ እኔ በመርካቶም ሆነ በሌሎች አካባቢ የምሽት ሥራ ላይ ብዙ አልተሳተፍኩም፡፡ ለተወሰኑ ጊዜያት ግን በ‹‹እናት ጓዳ›› ተጫውቻለሁ፡፡ ከመርካቶው ይልቅ በመገናኛ፣ በካሳንችስና በቦሌ (እስራኤል ጋራዥ) አካባቢ የነበረውን እንቅስቃሴ የተሻለ አውቃለሁ፡፡ በዚያ ዘመን ማሲንቆ ተጫዋቾች ተበራክተው ነበር፡፡ ምክንያቶቹ ብዙ ቢሆኑም ለኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምና ለመንግስታቸው ከፍተኛ አድናቆት አለኝ። ዋነኛው ምክንያቴ ከእኛ ሙያ ጋር የሚያያዝ ነው፤ ‹‹አዝማሪ››ዎች ክብርና እውቅና ያገኙበት ዘመን ነበር፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ለዚምቧቡዌና ለናምቢያ ነጻነት የታገሉ ኢትዮጵያዊ መሪ ናቸው፡፡ ዘመኑ አንድነት የሚሰበክበት፣ ኢትዮጵያዊነት የሚኮራበት ነበር፡፡ በዘመኑ ከሚነገሩ መፈክሮች አንዱ ‹‹የብሔረሰቦች እኩልነት በትግላችን ይረጋገጣል!›› የሚል ነበር፡፡ በደርግ ዘመን በዘርህ ምክንያት አትገደልም፡፡ በሕግ ያልተዳኘ ሞት የበዛበት ዘመን ቢሆንም፤ ሟች የሚሞተው ‹‹ፀረ - ኢትዮጵያዊ›› ተብሎ ነው፡፡ ጎሳህንና ዘርህን ጠልቶ ሕይወትህን ሊቀማ ገጀራ የሚያነሳብህ ማንም አልነበረም፡፡ አብዛኛው ሕዝብ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ተመሳሳይ ስሜት ነበረው፡፡ የአንድነት ጉዳይ ለጥያቄ የሚቀርብበት ዘመን አልነበረም፡፡
ካሴትህ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱና ዝነኛ መሆንህ ምን አስገኘልህ?
ከዚያ በኋላ ተጋብዤ የምጫወትባቸው መድረኮች ተበራከቱ፡፡ የ‹‹አደይ አበባ የኪነ ጥበብ መድረክ›› ላይ ከተሳተፉት አንዱ መሆን ችያለሁ፡፡ በበርካታ የዓለም ሀገራት በመዞር የኪነ ጥበብ ዝግጅቱን ባቀረበው ‹‹ሕዝብ ለሕዝብ›› የሙዚቃ ዝግጅት ላይ መሳተፍ በቀላሉ የማይገኝ ትልቅ ዕድል ነበር፡፡ ለአፍሪካ ሙዚቃ ኮሌክሽን በጃፓን ከተመረጡ 4 ሙዚቀኞችና ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች አንዱ ሆኜ፤ የዘፈን ሥራዬ በJVC ካምፓኒ ተቀርጾ ለዓለም ገበያ ቀርቧል፡፡
ከሀገር የወጣህበት ምክንያት ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው ይባላል …
ግንቦት 19 ቀን 1982 ዓ.ም ነው ከሀገር የወጣሁት፡፡ አወጣጤ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ባይሆንም፤ የተከፋሁበት ነገር ስለነበር፤ ላለመመለስ ወስኜ ነው ወደ አሜሪካ የሄድኩት፡፡ አሜሪካ ከሄድኩ በኋላ ሁለት ሲዲ አውጥቻለሁ፡፡ የሚበዛውን ጊዜዬን ያሳለፍኩት ግን ከሙያዬ ውጪ በሆነ ሥራ ላይ ነው፡፡ እኔ በትምህርት ጥግ ድረስ መድረስ ባለመቻሌ፣ ቁጭቴን የተወጣሁት እህት ወንድሞቼን አስተምሮ፣ ለቁም ነገር በማብቃት ነው፡፡ ለ30 ዓመታት ነው በአሜሪካ የቆየሁት፡፡ በቀሪው ዘመኔ፣ በሙዚቃው ዘርፍ የራሴን አስተዋጽኦ የማድረግ ዓላማና እቅድ አለኝ፡፡
የመስቀል በዓልን ከጉራጌ ማህበረሰብ ጋር ስታከብር የመጀመሪያህ ነው?
ከዚህ ማሕበረሰብ ጋር ሰፊ ሊባል የሚችል ትውውቅና ቀረቤታ አለኝ፡፡ በትዳር ለ25 ዓመታት አብራኝ የዘለቀችው ባለቤቴ የዚህ ብሔረሰብ ተወላጅ ናት፡፡
አባቷ አቶ ተክሌ ጉንጆ ከቀድሞ ዘመን የመርካቶ ባለሀብቶች አንዱ ሲሆኑ በስማቸው የሚጠራ ትልቅ ሆቴል ሁሉ ነበራቸው፡፡ በዘንድሮ የመስቀል በዓል ጋብዞኝ ወደ መሠረተ ወገራም ይዞኝ የመጣው ከ35 ዓመት በፊት ጀምሮ የማውቀው አቶ በላይ ካሳ ኢርከታ ነው። ጉራጌዎች እንደ መስቀል በዓላቸው ብዙ የሚስብ ነገር ያላቸው ሕዝቦች ናቸው። የትም ቢሄዱ ኢትዮጵያዊነታቸውን ያስቀድማሉ፡፡
ከየትኛውም ብሔርና ዘር ጋር በጋራ ለመኖርና ለመስራት አይቸገሩም። ለመስቀል በዓል በተገኘሁበት መሠረተ ወገራም ኦሮሞዎች፣ ትግሬዎች፣ አማሮች … ተጋብዘናል፡፡ ጉራጌ ዘር የለውም፣ ዘሩ ሥራ ነው፡፡
ከአዘጋጁ፡- ብርሃኑ ሰሙ የጋዜጣው ነባር ጸሃፊ ሲሆን በኢሜይል አድራሻው፡- This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ማግኘት ይቻላል፡፡


13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ በዓል "ሰንደቅ ዓላማችን ለሰላማችን፣ለአብሮነታችንና ለሀገራዊ ብልጽግናችን!" በሚል መሪ ቃል ነው የሚከበረው፡፡

  የሮያሊቲ ክፍያን የሚሰበስብ ቴክኖሎጂ ወደ አገር ሊገባ ነው

         የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጂና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ዘርፎች ማህበራት ህብረት ጋር በመተባበር በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በእጅጉ ለተጐዱ 24 የሙዚቃ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ። ህብረቱና የጋራ አስተዳደር ማህበሩ ከትላንት በስቲያ መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በካፒታል ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ድጋፉን ያደረጉት 113 ሙዚቀኞች የተሳተፉበት ተመልካች አልባ (ቨርቹዋል ኮንሰርት) በማድረግ በተገኘው ገቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የሙዚቃ ዘርፉ 365ቱንም ቀናት 24 ሰዓት የሚደመጥና ያለማቋረጥ አገልግሎት የሚሰጥ ዘርፍ ቢሆንም የዘርፉ ባለሙያዎች በመጀመሪያ በ1996 ዓ.ም በኋላም በ2007 ዓ.ም ተሻሽሎ የወጣውን የሙዚቀኞችን መብት በእጅጉ የሚያስጠብቅ አዋጅ ከእውቀት ማነስ ሳይጠቀሙበት መቆየታቸውን የገለፁት የህብረቱና የጋራ አስተዳደር ማህበሩ አመራሮች ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ታግሎ የጋራ አስተዳደር ማህበሩ ከመመስረቱ ከሁለት ወራት በፊት ህይወቱ ቢያልፍ ታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም በኤልያስ የልደት ቀን የሙዚቃ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር በሙዚቃ አመንጪዎች፣ ከዋኞችና የድምጽ ሪከርዲንግ ፕሮዲዩሰሮች በሶስቱ ማህበራት አማካኝነት የኤሊያስ መታሰቢያ ሆኖ መመስረቱን የሙዚቃ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር ፕሬዚዳንት አርቲስት ኃይለሚካኤል ጌትነት (ሃይሌ ሩትስ) ተናግሯል፡፡
ከዛ በኋላ በተደረገ እንቅስቃሴ፣ የሮያሊቲ ክፍያ ቀመር ተሰርቶ ለአዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት መግባቱንና መጽደቁን የገለፀው ሃይሌ ሩትስ ይህንን የሮያሊቲ ክፍያ እውን ለማድረግና ለመሰብሰብ 85 የዓለም አገራት የሚጠቀሙበትን ቴክኖሎጂ ከውጭ ለማስገባት ማህበሩ በሂደት ላይ መሆኑን ገልጿል።
ቴክኖሎጂው በሆቴሎችና በባሮች ውስጥ የሚቀመጥና ሆቴሉ ወይም ባሩ የተጠቀመውን የሙዚቃ መረጃ እየሰበሰበ ወደ ክፍያ ቀመሩ ቋት የሚከትትም ነው ተብሏል፡፡
የአጋራ አስተዳደር ማህበሩና የማህበራት ህብረቱ አመራሮች ሙዚቀኞቹ ዳዊት ይፍሩ፣ ፍቅር አዲስ ነቅአጥበብ፣ ኃይለሚካኤል ጌትነት (ሃይሌ ሩትስ) እና ሄኖክ መሀሪ ጨምረው እንዳብራሩት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዙሪያ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ “ንጋት” የተሰኘውን አልበም ሰርተው ለከተማ አስተዳደሩ ማበርከታቸውንም አስታውቀዋል። ማህበሩን ይበልጥ ለማጠናከርና ሙያተኛውን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የሁሉም ባለሙያ እገዛና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ትክክለኛ ባለሙያ ለሆኑና መስፈርቱን ለሚያሟሉ አባላት በቅርቡ ተሻሽሎ የተሰራውን የአባልነት መታወቂያ ከጥቅምት 15 ጀምሮ መስጠት እንደሚጀምሩ ገልፀዋል፡፡ የሮያሊቲ ክፍያ ህግ በኤሊያስ መልካ ስም ሊሰየም ነው እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያው የሚናፈሰውና አውታር መልቲ ሚዲያን ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበር ጋር እየደባለቁ ማምታታቱ ተገቢና አስፈላጊ አለመሆኑንም ሃይሌ ሩትስ አብራርቷል፡፡
የሙዚቃው ዘርፍ ማለትም በስቱዲዮ ሙዚቃ መቅረጽ፣ ውዝዋዜም ሆነ የትኛውም እንቅስቃሴ ለኮቪድ 19 ተጋላጭ የሚያደርግ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ወደ ሙዚቃ እንቅስቃሴ መግባት አደገኛ ነው ያለው ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ፣ በተመልካች አልባ (ቨርቹዋል ኮንሰርት) እና በመሰል ስራዎች ዘርፉን ለማነቃቃት ሙከራ ይደረጋል ብሏል፡፡

Saturday, 10 October 2020 15:16

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

    ዋርካው ሲታወስ ---
                         [ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ]

            ..በርግጥ ሀገራችን ካፈራቻቸው ትላልቅ ምሁራን አንዱ ነው ጋሽ መስፍን። አኔ እስከማውቀው ድረስ በሀገራችን ብዙ ከጋሽ መስፍን ያልተናነሱ ምሁራን አልፈዋል። ግን በዚህ ደረጃ ክብር ሰጥተን የሸኘናቸው ያሉ አይመስለኝም። ፕ/ር መስፍንን ከሌሎች ምሁራን የሚለየው ለባለሙያ ስብሰባ የሚያቀርባቸው ፅሁፎች ወይም በአደባባይ የሚያቀርባቸው ሂሳዊ መጣጥፎች ሁሉ ማጠንጠኛ ኢትዮጵያ መሆኗ እና አለ ለሚላቸው የማህበረሰብ የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ችግሮች መፍትሄ ለማመላከት ኢላማ ያደረጉ በመሆኖቸው ይመስለኛል።
ጋሽ መስፍንን ቀልቡን የሚስበው እና የሚያብሰለስለው የሀገሪቱ ድህነትና ኋላቀርነት፣ የዜጎች ሰብአዊ መብት፣ አገዛዞች በማህበረሰቡ አባላት ነፃነት ላይ በሚያስከትሏቸው ተፅእኖ ዜጎች ሁሌም መንግስትን እንደፈሩና አንገታቸውን አቀርቅረው የሚኖሩበት ሁኔታ ለዘለቄታው በማህበረሰቡ ስነ ልቦና ይበልጡንም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የሚደቅኑት አደጋዎች ናቸው ጋሽ መስፍን ብዕሩን እንዲያነሳ የሚያደርጉት። ጋሽ መስፍን ከሀገሩ ጋር የተወሳሰበ ግንኙነት ነበረው። ሀገሩን ክፉኛ ይወዳል ግን የዛን ያህል ቅጥ የለሽ ድህነት፣ የፍትህ እጦት ፣ የነፃነት ማጣትና በፍርሃት ቆፈን ተይዞ መኖር ሁሌም ያመዋል።
በሀገር ፍቅር በአንድ በኩል፣ የሀገር ዘርፈ ብዙ ውድቀት በሌላ በኩል፣ ነፍሳቸው የምትዋዥቅባቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ እናውቃለን። ብዙዎቹ ይሄን የውስጥ ግጭት ከቤተሰቦቻቸውና የቅርብ ጓደኞቻቸው ጋር ይነጋገሩበት እንደሆነ እንጂ በአደባባይ በግላጭ ከማህበረሰቡ ጋር ለመናገር ይፈራሉ። ይሄን ሁኔታ ለመቀየር ምንም አይነት ጥረት ሳያደርጉ “ጥሩ ኑሮ” ኖረው ያልፋሉ። እዚ ጋ ነው ጋሽ መስፍን በግልፅ ከሌሎች እንደሱ ምሁራን ከሚባሉ የሚለየው።
ለሱ ሀገርን የሚያክልን ጉዳይ የሚመለከት ነገር፣ በሀገርና በህዝብ ሀብት የተማሩ ምሁራን በየጓዳውና በየማህበሩ ለመበላት ሲገናኙ የሚናገሩትና የሚያሙት ጉዳይ ሳይሆን የተበላሸውን ለማስተካከል በግላጭ ከሚመለከተው አካል ስልጣን ከያዘው መንግስት ጋር ሳይቀር ለመነጋገር የሞራል ድፍረቱ ሊኖራቸው ይገባል የሚል ፅኑ እምነት ስለነበረው ፣ ይሄን እምነቱን ደግሞ በተግባር ለማሳየት በመቻሉ ነው እሱን በተለየ ሁኔታ እንድናየውና እንድናከብረው የሚያደርገን።
ጋሽ መስፍን ለሱ ዘመን እኩዮች ብቻ ሳይሆን በእድሜ በብዛት ለሚያንሱትም ቀጣይ ትውልድ ጭምር የሞራል ዕዳ የሚያሸክማቸው በመሆኑ ነው፣ በተለይም በእድሜ ለሚጠጉት በተለያየ ቁሳዊ ፍላጎት ምክንያት የሀገሪቱን መከራ ከዳር ሆነው ለሚመለከቱ፣ የሱ ግልፅነትና ድፍረት የሚጎረብጣቸው።
ከዚህ አንፃር ዛሬ ልንሸኘው የተሰባሰብነው ሰው ቢያንስ ላለፉት 3 እና 4 ትውልዶች የማህበረሰባችን የሞራል ኩራዝ ሆኖ ያገለገለ ትልቅ ሰው ነው። ይሄን ሚናውን የተወጣው በድንገት ሳይሆን አውቆ ነው። እንዲህ አይነት አስቸጋሪ ሚና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ትችትን፣ ስድብን፣ ውግዘትን ሊያስከትል እንደሚችል ብቻ ሳይሆን እንደማይቀርለት አውቆ የገባበት ነው።
በአገዛዝ ስርአቶች ታስሮበታል ፤ በጊዜና በተውሶ እውቀት ልቀናል በሚሉ ወጣት አብዮተኞች ተዘልፎበታል ፤ ከብሄርህ ውጪ ለምን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ትላለህ በሚሉ አዳዲስ የጎሳ ብሄርተኞች ተንጓጦበታል። ሁሉም በሀሳቡ ሊሞግቱት ከፈለጉ ክፍት ነበር። ሀሳብን በሀሳብ መሞገት አቅቷቸው ወደ ስድብና አካኪ ዘራፍ ለሚሄዱ ምንም ፍርሃትም ሆነ ክብር የለውም! በተለይም ለማህበረሰብ የሞራል ልእቀት ሃላፊነት ያለባቸው አካላትና ግለሰቦች፣ ለነዋይና ለስልጣን ሲሉ ሳይወጡ ሲቀሩ ፍፁም ይጠየፋቸዋል።
ጋሽ መስፍን ኢትዮጵያውያንን እንደ ዜጎች ከመመልከት በቀር በተለየ የሚወደው ብሄር አልነበረውም። ለኢትዮጵያውያን ዘርና ሃይማኖት ሳይመርጥ ለተበደሉ ሁሉ በአደባባይ ጥብቅና ቆሟል። ሁሌም ወገንተኝነቱ አቅም ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ነበር። ለዜጎች ሰብአዊና የዴሞክራሲ መብቶች መከበር ከልቡ ታግሏል። እኔ እስከማውቀው ድረስ የኢትዮጵያና የህዝቧን ጥቅም በሚመለከት ማድረግ ያለበትን፣ ማድረግ እያለብኝ ያላደረግኩት አለ ብሎ የሚቆጭበት ምንም ነገር ያለ አይመስለኝም።
አኔን የሚቆጨኝ ብዙ የደከምክለት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ መጨረሻ ሳታይ ብታልፍም ፤ ምኞትህ እውን እንዲሆን ከልብ እንደምንሞክር ቃል እገባልሃለሁ።
ጋሽ መስፍን የኖረው ኑሮና ህይወቱ ለማህበረሰባችን ትቶ የሄደው ትምህርት ካለ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ላመኑበት አላማ በፅናት መቆም ነው፤ ላላፊ ቁስም ሆነ ስልጣን አለማጎብደድ ወይም አለመሸነፍን ነው። ዝም ብሎ ጎርፍ በሚሄድበት መሄድ ሳይሆን በሁለት እግር ቆሞ በራስ ማሰብንና ባመኑበት መግዘፍን ምንም እንኳ ነዋይ ባያስገኝም በማህበረሰብ ዘንድ በጣም የሚያስከብር እሴት መሆኑን ማህበረሰባችን ለዚህ ሰው ከሰጠው ክብር ትረዳላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
በአጠቃላይ የማህበረሰባችን የሞራል ቁመና እጅግ በተዳከመበት በዚህ ወቅት የጠንካራ የሞራል ልእልና አስፈላጊነት ጋሽ መስፍን በህይወቱ ብቻ ሳይሆን በሞቱም በሰጠነው ክብር የሞራል ልእልና ለማህበረሰብ ሰላምና ጤንነት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ትረዳላችሁ ብዬ እገምታለሁ።
ስሞት አታልቅሱ ፣ ስሞት አትቅበሩኝ ፤ ይልቁንስ አስክሬኔንን አቃጥላችሁ አመዱን አዋሽ ውስጥ በትኑት ፤ በህይወቴ ያልገዛሁት መሬት ስሞት እንዲኖረኝ አልፈልግም ብለሃል። ይህ ፍላጎትህ በሞትህ መሳካቱን አላውቅም፤ ነገር ግን በህይወትህ ግን የምትፈልገውንና የምታምንበትን ኖረሃል። ስንቶቻችን ደረታችንን ነፍተን ይሄን እንለዋለን?
መልካም እረፍት ጋሽ መስፍን፤ አንረሳህም!
(ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፤ በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የሽኝት ፕሮግራም ከተናገሩት መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም)


Monday, 12 October 2020 00:00

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

Sunday, 11 October 2020 00:00

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

    ‹‹የሐሳብ ቀን-ዘሎች››
                                 (አሳዬ ደርቤ)


           በእኔ ዘንድ የእረፍት ትርጉሙ ቁጭ ማለት ሳይሆን ‹‹ሥራ መሥራት›› ነው። ከየትኛውም ነገር በላይ የሚያዝናናኝ ደግሞ የምወደውን ሥራ መሥራት ነው። ስለሆነም ቢሮ ውዬ ስመለስ ቤት ገብቶ ከማረፍ ይልቅ መጻፍ ደስ ያሰኘኛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም፤ በጥሩ እንቅልፍ ካሳለፍኩት ሌሊት ይልቅ ለመንፈሴ የሚጥም ሼጋ ጽሑፍ ስሞነጫጭር ያደርኩበት ሌሊት ማለዳዬን ውብ ያደርገዋል፡፡
ይህ ሁኔታ ግን ኪነ-ጥበባዊ ይዘት ላላቸው ጽሑፎቼ እንጂ ሳልወድ በግዴ ከአክቲቪስት ጎራ ተሰልፌ እዚህ ሶሻል ሚዲያው ላይ የምለጥፋቸውን ጽሑፎች አይመለከትም፡፡ እነሱ ሰላሜን እና ግማሽ ጎፈሬዬን የሚነጥቁኝ ናቸው፡፡ ያም ሆኖ ግን የሆነ ጥቃት ሲፈጸም ‹‹ምን አገባኝ›› ብዬ ከመተኛት ይልቅ ለውጥ አመጣሁም አላመጣሁም ‹‹ያገባኛል›› በሚል ስሜት ማለት ያለብኝን ነገር ማስተጋባት፣ ለመላጣ ጭንቅላቴ ምቾት ይሰጠዋል፡፡ አካበድኩ መሰል! .
በሌላ መልኩ ግን የወቅቱ የፖለቲካ አየር ፌስቡካችንን የኀዘን ድንኳን አድርጎት በመክረሙ የተነሳ እለታዊ አጀንዳዎችን ችላ ብሎ ሌሎች ነገሮችን ሶሻል-ሚዲያው ላይ ለማጋራት ጊዜው ባይፈቅድልንም አልፎ አልፎ ግን ግላዊ ዝንባሌዬን ባለመተዌ ይሄው ሦስተኛ መጽሐፌን ለማሳተም በቃሁ፡፡
መጽሐፉ ‹‹የሐሳብ ቀንዘሎች›› ይሰኛል፡፡ በወሎ አማርኛ ከሐሳብ ዛፍ ላይ የተመለመሉ ቅርንጫፎች እንደማለት…ሽፋኑ ላይ ያለውን ምሥል እንዳሻችሁ ተርጉሙት… የመጽሐፉን ውስጣዊና ውጫዊ ዲዛይን ያቀናበረው ታዋቂው ባለሙያ ሙሉቀን አስራት ሲሆን ለየት ባለ የሕትመት ጥራት ታትሞ ሼልፍ ላይ ውሏል፡፡ ይሄውም መጽሐፍ 275 ገጾች ያሉት ሲሆን በውስጡም ከ25 በላይ ወጎች እና ተረኮች ተካትተውበታል፡፡ በይዘት ረገድ ደግሞ ከሚያስጨንቀው ይልቅ ፈገግ የሚያስብለው ላይ፣ ከዛሬ ይልቅ ትናንት እና ነገ ላይ፣ ከሶሻል ሚዲያው አጀንዳ ይልቅ ምድራዊው ላይ የሚያተኩር ሲሆን ትወዱታላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
.አከፋፋዮቹ ጃዕፋር መጽሐፍት መደብር (ለገሃር) እና ጦቢያ መጽሐፍት መደብር (ካሳንችስ) ሲሆኑ ከነገ ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ በሁሉም መጽሐፍት መደብሮች ታገኙታላችሁ፡፡ በቀጣይ ሳምንት ደግሞ በክልልና በዞን ከተሞች የምናደርስ ሲሆን ባሕር ማዶ ላላችሁ ደግሞ በአድራሻችሁ የምንልክ ይሆናል፡፡


ከዕለታት አንድ ቀን ከሞጣ (ጐጃም) ገበያ መልስ ሁለት ሰዎች ይገናኛሉ፡፡ ከሁለቱ አንደኛው “ቀ” ማለት አይችልም፡፡ ስለዚህም በቦታዋ “ፀ” የምትለዋን ፊደል ይተካባታል።
አንደኛው ሰውዬ፡- "እንደምን ውለሀል ወዳጄ?"
ሁለተኛው ሰውዬ፡- "ደህና እግዚአብሔር ይመስገን፤ ከወዴት እየመጣህ ነው?"
አንደኛው -"ከሞፃ"
ሁለተኛ - "ምን ይዘሃል?"
አንደኛው - "ድግፃ" (ከድግጣ ዛፍ የተመለመለ በትር ስለያዘ ነው)
ሁለተኛው - "ሞጣ ምን አለ?"
አንደኛው - "ሞፃ፤ ፆርነት በፆርነት ሆኗል"  
ሁለተኛው - "ታዲያ ምን ተሻለን?"
አንደኛው - "ፀሎት! ሠላም እንዲመጣ መፀለይ እና ፀባይ ማሳመር! ፀጽታ ይመፃ ዘንድ ፀሐይ ጊዜ አምፃልን ብሎ መፀለይ"
ሁለተኛው- "በል ወዳጄ ትንሽ አገልግል ይዣለሁ፤ ምግብ እንብላ" አለውና አንድ ጥላ ቦታ ተቀምጠው፣ አገልግሊቱን ፈታና መብላት ጀመሩ፡፡ እንዳጋጣሚ ወጡ ጨው የለውም ኖሯል፡፡
አንደኛው - "አይ ፀው የለውም፤ ፀው ከየት እናምጣ?" አለና ጠየቀው፡፡
ሁለተኛው ሰው - “አይ እንግዲህ ወዳጄ” “ፀ”ን ምንም ብንወዳት፣ ወጥ ውስጥ አንጨምራትም" አለው ይባላል፡፡
*   *   *
የሼክስፒር ሃምሌት፣ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን እንዳለው፣ እንዲህ ይለናል፡-
“ዛሬ ለወግ ያደረግሽው፣ ወይ ለነገ ይለምድብሻል
ልማድ ፊት እንዳሳዩት ነው ወይ ይጠፋል ወይ ያጠፋል
ከርሞውም የሰለጠነ እንደሁ፣ ተፈጥሮ ይሆናል ይባላል፡፡”
አብዛኛውን ጊዜ የልማድ ተገዢዎች መሆናችን እርግጥ ነው፡፡ አንድም በባህላችን ተጽእኖ፣ አንድም በሰውነት ባህሪያችን ሳቢያ፣ ተቀብለን ያቆየናቸውም ሆኑ እያቆየን ያለናቸው ባህሪያት፤ ውለው አድረው፣ የለት የሰርክ ህልውናችን አንድ አካል ይሆኑና እንደ ተፈጥሯአዊ ጉዳይ አድርገን እንቀበላቸዋለን፡፡
በእድገታችን መሽከርክሪት ላይ የትምህርትን ሚና ቸል ካልን ብዙ ነገር ይጐድልብናል። በተለይ ትምህርትን እንደ ለውጥ ዋና መዘውር አድርገን ካልተገለገልንበት፣ የተመራቂ ቁጥር መጨመር ብቻውን ረብ - ያለው የመሻሻል ምልክት አይሆነንም፡፡ ምክኑስ ቢባል ለዋጭ - ተለዋጭ ሃይል የማፍራት አቅም አላበቃንምና! ከትምህርቱ በተጓዳኝ የጤናን ወሳኝነት አበክረን በተለይ ለወጣቱ ትውልድ ማስጨበጥ ዋና ነገር መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ ተረካቢም ትውልድ የማዘጋጀት ታላቅ ኃላፊነት መወጣት ነው፡፡
የፖለቲካ ፀሐፍት “The new invincible” ይሉናል፡፡ አዲሱ አሸናፊ ማለታቸው ነው፡፡ የአሮጌውን መሞትና አዲሱን የመቀበልን ፀጋ በሙሉ ልብ መጨበጥ፣ አገርን ከመቆርቆዝና ከመንቀዝ (Crises and degeneration) ያድናል፡፡ እንደው በደመነፍሳዊ መንገኝነት (Herdism) የመንጋጋት አካሄድ ጠያቂ - ህብረተሰብ (inquisitive Society) እንዳንፈጥር ይገድበናል፡፡
ደጋግመን ስለ ትምህርት ወሳኝነት የምናነሳው ስንመኝ የኖርነውን ጠያቂ ትውልድ ለማምጣት ሁነኛው መሣሪያ ትምህርት ብቻ በመሆኑ ነው። በጥንቱ አባባል፤ “የኛ መማር መማር መማር አሁንም መማር” ስንል የነበረው ያልተማረ፣ ያልበሰለና በሃሳብ ያልበለፀገ ወጣት፤ ቅኝቱ ውጭ አገር የመሄድ፣ ደጅ ደጁን የማየት፣ ሄዶም የትም የትም እደርሳለሁ ሳይል “ከሀገር መውጣት” በሚል መፈክር ስር ብቻ ታጥሮ፣ የአእምሮ - ዘረፋው አካል (Brain Drain)  የእጅ መስጠቱ ሰለባ (Defeats Mentality) አዙሪት ውስጥ የሚባዝን ይሆናል!
“በመሠረቱ ሌሎችን የማያዳምጥና እኔ ያልኩት ብቻ የሚል ካድሬ ነው” በቀኖና ታጥሮ እውነታውን ብቻ የሚል ደግሞ ዲያቆን ብቻ ነው፡፡” ይለናል የስነ ተውኔቱ ፀሐፊ ፀጋዬ ገብረመድህን፡፡ ሁለቱም ባልተሰናሰለ መንገድ የግትርነት ሠለባ ከሆኑ አደጋ ናቸው ማለት ነው፡፡ አገር፣ አንድ አራሽ፣ አንድ ቀዳሽ፣ አንድ ተኳሽ ሊኖራት ግድ ነው ይሏልና አምራች፣ ውዳሴ - ሰጪና ድንበር - ጠባቂ በሌሉበት፤ ሀገር አለኝ ማለት የዋህነትም መሀይምነትም ነው! አምራቹ የኢኮኖሚ ህልውናችንን ጠባቂ፣ ቀዳሹ የመንፈሳዊ ህልውናችን ረካቢ፣ ወታደሩ ዳር ድንበር አስከባሪ፣ ነውና እኒህ ኃይላት ዛሬም አንድም ሦስትም ናቸው እንላለን፡፡    


 ከአለማችን ህዝብ 10 በመቶው በቫይረሱ እንደተያዘ ይገመታል

           ኮሮና ቫይረስ በወረርሽኝ መልክ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ አገራትና አለማቀፍ ተቋማት ከሚናገሩት በ20 እጥፍ ያህል የሚበልጡ ወይም ከ760 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን አጥቅቷል የሚል ግምት የሰጠው የአለም የጤና ድርጅት፣ በመላው አለም ከአስር ሰዎች አንዱ ወይም ከአጠቃላዩ የአለማችን ህዝብ 10 በመቶ ያህሉ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅቶ ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል፡፡
በአለም የጤና ድርጅት የድንገተኛ ጉዳዮች ሃላፊ ዶ/ር ማይክ ራያንን ጠቅሶ አልጀዚራ እንደዘገበው፣ ድርጅቱ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግና መረጃዎችን በመሰብሰብ ባስቀመጠው ግምት፤ 10 በመቶው የአለማችን ህዝብ በቫይረሱ ሳይጠቃ አይቀርም ብሏል። በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በቀውስ ውስጥ የምትናጠው አለም፣ ወደ ከፋው ምዕራፍ እየገባች ነው ያሉት ዶ/ር ማይክ፤ በደቡብ ምስራቅ እስያ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአውሮፓና ምስራቅ ሜዲትራንያን አካባቢዎች ደግሞ ስርጭቱና የሞት መጠኑ ከፍ ማለቱን ገልጸዋል፡፡
ወርልዶሜትር ድረገጽ ያወጣው መረጃ እንደሚለው፤ ኮሮና ቫይረስ እስካለፈው ሃሙስ አመሻሽ ድረስ በመላው አለም 36.52 ሚሊዮን ያህል ሰዎችን በማጥቃት 1.06 ሚሊዮን ያህሉን ለህልፈተ ህይወት ሲዳርግ፣ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 27.48 ሚሊዮን ያህል ደርሷል፡፡ እስከተጠቀሰው ጊዜ ድረስ አሜሪካ በ7,787,879፣ ህንድ በ6,841,813፣ ብራዚል በ5,002,357፣ ሩስያ በ1,260,112 እንዲሁም ኮሎምቢያ በ877,683 የቫይረሱ ተጠቂዎች እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸውንም መረጃው ያመለከክታል፡፡
ወረርሽኙ እስከተጠቀሰው ጊዜ ድረስ በአፍሪካ አገራት በድምሩ ከ1.54 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ማጥቃቱትና ወደ 38 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ለህልፈተ ህይወት መዳረጉን ኦልአፍሪካን ዶት ኮም የዘገበ ሲሆን፣ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር በአንጻሩ 1.28 ሚሊዮን ያህል መድረሱንም አክሎ ገልጧል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሰሃራ አገራትን ኢኮኖሚ ዕድገት በ3.3 በመቶ ያህል እንደሚቀንሰውና 40 ሚሊዮን ያህል አፍሪካውያንን ወደ ከፋ ድህነት ሊያስገባ እንደሚችልም የአለም ባንክ ባወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከግጭቶችና የተፈጥሮ አደጋዎች ጋር ተዳምሮ፣ በመላው አለም 115 ሚሊዮን ያህል ሰዎችን ወደከፋ ድህነት ያስገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአለም ባንክ ማስታወቁን የዘገበው ቢቢሲ፣ በአለማችን በቀን ከ1.9 ዶላር በታች ገቢ የሚያገኙ ወይም በከፋ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር በመጪው አመት 150 ሚሊዮን ያህል ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጧል፡፡