Administrator

Administrator

   የበጎ አድራጎት ስራ በግለሰቦች መልካም የማድረግ ጽኑ ፍላጎትና ሃሳብ ላይ ተመስርቶ የሚደረግ ተግባር ሲሆን በሃገራችን ረጅም ታሪክ ያለዉና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የማንነት መለያ ዓርማ ሆኖ የሚያገለግል ሃብት ነዉ:: ይህ የበጎ ተግባር ስራ እንደግለሰቡ ወይም ተቋሙ አቅምና አጠቃላይ ይዘት የሚሰጠዉ የድጋፍ አይነት፤ ብዛትና መጠን ይለያያል፡፡ በመሆኑም ከትንሽ እስከ ትልቅ ከግለሰብ እስከ ተቋም በተለያዬ ሁኔታ ዉስጥ ለሚገኙ ድጋፍ ፈላጊዎች የተለያዬ ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል፡፡
ምናልባትም በሃገራችን በግለሰብ ደረጃ የሚደረጉ ድጋፎች በአይነትም በብዛትም በርካታ እንደሆኑ ቢገመትም ተቌማዊ ቅርጽ ያልያዙ ከመሆናቸዉ አንጻር ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ የድጋፉን አይነትና መጠን ለማወቅ ስለማይቻል ይህን ያህል ብሎ በቁጥር ለማስቀመጥ አዳጋች ይሆናል፡፡
ከዚሁ ስራ ጋር በተያያዘ በተለይም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አሁን ባለንበት ዘመን ሰፊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የሚታመን ሆኖ አመሰራረታቸዉን ስንመለከት ቀደም ባለዉ ጊዜ ረሃብና ድርቅ በተከሰተበት ወቅት ነፍስ የማዳን ተልዕኮ ይዘዉ በመንቀሳቀስ በርካታ ህይወት ማትረፍ የቻሉ ሲሆን ከድርቁ በመለስ መልሶ የማቋቋም ስራዎችንና ብሎም ዘላቂ የልማት ግቦችን በማንገብ የልማት ስራዎችን በስፋት ሲያከናዉኑ ቆይተዋል፤ አሁንም እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በሃገራችን ኢትዮጵያ በተለይ በ1965 ዓ.ም በወሎና ትግራይ ደርሶ በነበረዉ ከፍተኛ ድርቅ ቁጥራቸዉ በርከት ያለ መንግሰታዊ ያልሆኑ ዕምነት ተኮር ድርጅቶች የማይናቅ ተሳትፎ ከማድረጋቸዉም በላይ ለአሁኑ በሽህ የሚቆጠር የበጎ አድራጎት ድርጅት መፈጠር ምክንያት ነበሩ ለማለት ያስችላል፡፡ ከአስር አመት በኌላ እንደገና በ 1977 ዓ.ም ድርቁ በተመሳሳይ በወሎና ትግራይ አካባቢ በስፋት በመከሰቱ በወቅቱ እነኚህ ድርጅቶች ሰፊ ድጋፍ በማድረጋቸዉ ምንም እንኳ ብዙ ጉዳት ቢደርስም ችግሩን ለመቆጣጠር ተችሏል፡፡
ከላይ በተገለጸዉ ሁኔታ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሃገራችን ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩ ሲሆን በተለይም ከደርግ ዘመን በኌላ በአዲሱ ህገ መንግስት የመደራጀት መብትን በመጠቀም በርካታ የሃገር ዉስጥና የዉጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት መፈጠር ችለዋል:: ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረዉ እነኚህ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በተለይም ሃገራዊ የልማት ግቦችንና ዕቅዶችን በማገዝ የመንግስትና የህዝብ የልማት አጋር ሆነዉ የወጡበት ሂደት በግልጽ ይታያል:: በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን ከ 3000 የሚልቁ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የሚገኙ ሲሆን በአሰራር ስርዐት በርካታ ችግሮች ቢገጥሟቸዉም ችግሮቻቸውን ተቋቁመዉ በተለያዬ የልማት፤ የእርዳታና መልሶ ማቋቌም ስራ ላይ ተሰማርተዉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በተለይም በአሁኑ ሰአት አጠቃላይ የልማት ዕቅዳቸዉን አገሪቱ ካጸደቀችዉ ሁለተኛዉ የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጋር በማጣጣም፤ የዕቅዱን ተፈጻሚነት በየጊዜዉ ከሚመለከታቸዉ የመንግስት መ/ቤቶች ጋር በቅርበት በመገናኘት በመገምገምና የማስተካከያ እርምጃ በመዉሰድ የልማት አጋርነታቸዉን የበለጠ ያሳዩበት ወቅት ቢሆንም ከሚያከናዉኑት ስራ አንጻር ሲታይ ለህዝብ ግልጽ መሆን ያለባቸዉ በርካታ ጉዳዮች ማለትም ከዉጭ ለጋሽ ድርጅቶች የሚያመጡት ገንዘብ፡ በሴክተሩ ዉስጥ ያለዉ የሰዉ ሃይል፡ እንዲሁም በተጨባጭ ለህዝብ የሚያደርጉትና ያደረጉት የልማት ስራ ጥቅል ይዘት ለማህበረሰቡ በሚፈለገዉ መጠን ታዉቌል ለማለት ያስቸግራል።
አንዳንዴም ከዚህ ባለፈ መልኩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ለህብረተሰቡ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ይልቅ የግለሰብ መጠቀሚያና መክበሪያ ተደርገዉ የመታየታቸዉ ጉዳይ ህዝቡ የተዛባ አመለካከት እንዲይዝ ከማድረጉም ባሻገር የሴክተሩን ገጽታ የሚያበላሽና ጥላሸት የሚቀባ ሆኖ ይታያል፡፡
በዚህ  ጽሁፍ አዘጋጅ - የኢትዮጵያ በጎ አደራጎት ድርጅቶችና ማህበራት መድረክ አመለካከትም በርካታ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት እጅግ ብዙ ዉጤታማ የልማት ስራዎችን የማከናወናቸዉን ያህል የተወሰኑት ደግሞ በጎ ባልሆነ ተግባር ዉስጥ ሲሳተፉ ይስተዋላል፡፡ የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት መድረክም ሴክተሩ፤ በአጠቃላይ ተገዥ የሚሆንበትን የስነ ምግባር ደንብ በማዘጋጀትና በማጽደቅ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን ይህም ጥረት በሴክተሩ ዉስጥ ተጠያቂነትን በማስፈን ግልጽ አሰራር እንዲሰፍን እገዛ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል፡፡ በሌላ ወገን ሌሎች ስራቸዉን በትጋትና በቅንነት የሚያከናዉኑትን በማበረታታት፤ ችግሮቻቸዉ ላይ በመወያየትና መፍትሄ በማፈላለግ የተቀላጠፈ የስራ ማዕቀፍ እንዲፈጠርላቸዉ መድረኩ በትጋት ይሰራል፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በርካታ ስራ ቢሰሩም ድጋፋቸዉ ለህዝብ በቅጡ ያልታወቀ ከመሆኑ አንጻር የተለያዩ የመገናኛ ብዘሁንን በመጠቀም ስራዎቻቸዉን ለህዝብ ማሳወቅ ተገቢ  በመሆኑ ይህንኑ ስራ መስራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም በሃገራችን የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ምን ምን ድጋፍ እንዳደረጉ በተወሰነ መልኩ ከዚህ በታች በተቀመጠዉ ሁኔታ ለመግለጽ ጥረት ተደርጔል፡፡ ከዚህ በላይ በጥቂቱ ለማየት እንደተሞከረዉ በኢትዮጵያ የተለያዬ ይዘት ያላቸዉ በፌደራል ደረጃ ቁጥራቸዉ ከ 3000 የሚልቅ በክልል ደግሞ ከ 1000 የሚበልጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ይገኛሉ፡፡
በእነኚሁ መረጃዎች መሰረት በሃገራችን ያሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚያተኩሩባቸዉ የልማት ስራዎች በቅደም ተከተል የሚከተለዉን ይመስላሉ፤ ጤና፤ የህጻናት ልማት፤ ትምህርት፤ ማህበራዊ ድጋፍ፡ አቅም ግንባታ፤ ገቢ ማስገኛ አካባቢ ጥበቃ እና እርሻ ስራ ይገኙበታል፡፡ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ 2012 በሃገሪቱ በአጠቃላይ 4904 ፕሮጀክቶች የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥም 113 በአዲስ አበባ፤ 856 በኦሮሚያ፤ 621 በደቡብ፤ 610 በአማራ፡ 450 በትግራይ፡ 283 በአፋር፤ 267 በድሬዳዋ፤ 59 በቤንሻንጉል፡ 238 በሃረሪ፤ 237 በሶማሌ፤ እንዲሁም 170 ፕሮጀክቶች በጋምቤላ ክልል ተተግብረዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ዉስጥ ካሉት የጤና ተቌማት ዉስጥ 7% ያህሉ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሙሉ ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በተጨማሪም በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ሪፖርት መሰረት  እ.ኤ.አ በ2011፣ 1626 የጤና ፕሮጀክቶች እንደነበሩ የተጠቆመ ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በኤች አይቪ ኤድስ መቆጣጠርና መከላከል ስራ ላይ ተሰማርተዉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሌላ ሪፖርት እ.ኤ.አ ከ 2004 እስከ 2007 ብር 575 ሚሊዬን ለዉሃ ስራ የዋለ ሲሆን ብር 3 ቢሊዬን ደግሞ በ 336 ፕሮጀክቶች ለእርሻና ተያያዥ ተግባራት ዉሏል፡፡ በተመሳሳይ በሃገሪቱ ካሉ 388 የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት ዉስጥ 74 የሚሆኑት በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሙሉ ድጋፍና ቁጥጥር በስራ ላይ የሚገኙ እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡                                          
በአመታዊ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሪፖርት መሰረት እ.ኤ.አ ከ2009 እስከ 2011 ባሉት ጊዚያት ዉስጥ ብር 544,201,454.98 ለዉሃና ተያያዥ ስራዎች ብቻ ተመድቦ ስራ ላይ ዉሏል፡፡
በኢትዮጵያ ዉስጥ ቁጥራቸዉ ከ54 የሚልቅ ህብረቶችና ጥምረቶች ያሉ ሲሆን ለናሙናነት በክርስቲያን ልማትና ተራድዖ ማህበር ህብረት (ሲሲአርዲኤ) ሪፖርት መሰረት እ.ኤ.አ በ2011 10.8 ቢሊዬን ብር በ 320 አባል ድርጅቶች መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፤ አብዛሃኛዉ ገንዘብም ለምግብ ዋስትና፡ ልህጻናት ድጋፍና ለጤና አገልግሎት ስራ በቅደም ተከተል የዋለ መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ ከአንድ አመት በኃላ በ2012 በተጠናቀረ ሪፖርት ጥቅል ብር 11,841,356,007.87 ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ዉሏል፡፡
በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተገኘ መረጃ መሰረት በ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 2007 ሙሉ አመትና 2008 – 10 ወር ጊዜ ዉስጥ (አንድ አመት ከአስር ወር ዉስጥ) ከ 2 ቢሊዬን ዶላር (40 ቢሊዬን ብር) በላይ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የዉጭ ምንዛሬ ገንዘብ ለማግኘት ተችሏል፡፡ 

• ባለፉት 12 ወራት ብቻ፣ 55 ሚ. ዶላር ገቢ አግኝቷል
• ለ117 ታላላቅ ሽልማቶች ታጭቶ፣ በ36 አሸንፏል
    በወቅቱ የአለማችን የሙዚቃ መድረክ ጎልቶ በመውጣት ከፍተኛ ስኬትን የተቀዳጀውና የበርካታ ታላላቅ አለማቀፍ ሽልማቶች ባለቤት ለመሆን የበቃው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ፤ ከአለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ዝነኞች ተርታ መሰለፉን ዘ ኢንኩዚተር ዘግቧል፡፡
አለማቀፍ ተወዳጅነትን ያፈራው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ፣ ፎርብስ መጽሄት ከሳምንት በፊት ይፋ ባደረገው የ2016 ከፍተኛ ተከፋይ 100 የዓለማችን ዝነኞች ዝርዝር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተካተቱት 15 ዝነኞች መካከል አንዱ መሆኑንና ከእነዚህ መካከልም ከፍተኛውን ገቢ ያገኘው እሱ እንደሆነ የጠቆመው ዘገባው፣ የ25 አመቱ ድምጻዊ አቤል ባለፉት 12 ወራት ብቻ 55 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጧል፡፡
“ዘ ዊክንድ” በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የግራሚ ተሸላሚው አቤል፤ ከዘንድሮ የአለማችን ከፍተኛ ተከፋይ 100 ዝነኞች መካከል የ30ኛ ደረጃን መያዙን የጠቆመው ዘገባው፣ “ቢዩቲ ቢሃይንድ ዘ ማድነስ” የተሰኘውና ከ2 ሚሊዮን ኮፒ በላይ የተቸበቸበው የሙዚቃ አልበሙ ለድምጻዊው ከፍተኛ ገቢ ማግኘትና በዝርዝሩ ውስጥ መካተት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጧል፡፡
ለ117 አለማቀፍ የሙዚቃ ሽልማቶች በመታጨት፣ ሁለት የግራሚና ስምንት የቢልቦርድ ሽልማቶችን ጨምሮ 36 አለማቀፍና ክልላዊ የሙዚቃ ሽልማቶችን ያገኘውና በወቅቱ የአለማችን የሙዚቃ መድረክ፣ አብሪ ኮከብ ሆኖ የወጣው አቤል፤ ባለፉት 12 ወራት ከአልበም ሽያጭ፣ ከሙዚቃ ኮንሰርቶች፣ ከኩባንያዎች ስምምነትና ከመሳሰሉት በድምሩ 55 ሚሊዮን ዶላር ሰብስቧል፡፡

Monday, 25 July 2016 09:35

የዘላለም ጥግ

(ስለ ታሪክ)

ታሪክ ሊወገዱ የሚችሉ ነገሮች ድምር ውጤት
ነው፡፡
ኮንራድ አድኖር
- ታሪክ ስምምነት ላይ የተደረሰበት ተረት
አይደለምን?
ናፖሊዎን ቦናፓርቴ
- በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የምርምርን ፋይዳ
ተገንዝበናል፡፡
አማር ቦሴ
- ትልቁ ጠላቴ ጊዜ ነው፡፡
ኢቪታ ፔሮን
- የሰው ልጅ ታሪክ የሃሳቦች ታሪክ ነው፡፡
ሉጂ ፒራንዴሎ
- የታሪክ ፀሐፊ፡- ያልተሳካለት የረዥም ልብወለድ
ፀሐፊ ነው፡፡
ኤች.ኤል.ሜን
- እግዚአብሔር ያለፈውን ለመለወጥ አይችልም፤
የታሪክ ፀሃፍት ግን ይችላሉ፡፡
ሳሙኤል በትለር
- ታሪክ፤ ማብቂያ የለሽ የተሳሳተ የአኗኗር ዘይቤ
ድግግሞሽ ነው፡፡
ሎውረንስ ዱሬል
- አብዮቶች የታሪክ አሽከርካሪ ሞተሮች ናቸው፡፡
ካርል ማርክስ
- የዘመናዊ መንግስታትን ማህበራዊና ፖለቲካዊ
ታሪክ ለማጥናት ከፈልግህ፣ ስለ ገሃነም አጥና፡፡
ቶማስ ሜርቶን
- የጥበብ ባለሙያ ስራ የዘመኑ ታሪክ እማኝ መሆን
ነው፡፡
ሮበርት ራውስሽንበርግ
- ታሪክ በአጠቃላይ መጥፎ መንግስት እንዴት ያለ
እንደሆነ ብቻ ነው የሚነግረን፡፡
ቶማስ ጄፈርሰን
- የነፃ ሰዎች ታሪክ የሚፃፈው በአጋጣሚ ሳይሆን
በምርጫ ነው፤ በራሳቸው ምርጫ!
ድዋይት ዲ. አይዘንአወር
- ቤተ-መፃህፍት የሃሳቦች ማዋለጃ ክፍል ነው -
ታሪክ ነፍስ የሚዘራበት ሥፍራ፡፡
ኖርማን ኮውሲንስ

በፖሊስ መኮንንነትና በመረጃ ባለሙያነት ሀገራቸውን ያገለገሉትሌተና ኮሎኔል ተፈራ ካሳ “ዘፍ
ያለው” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት መፅሃፍ ለገበያ ቀርቧል። ኮለኔሉ በ20 ዓመት አገልግሎታቸው የአይን እማኝ የሆኑበትን የኢትዮ ሶማሌ ጉዳይ እንዲሁም በወቅቱ የነበረውን የአገራችን አጠቃላይ ፖለቲካ ትኩሳት በመረጃ አስደግፈው በትረካ መልክ ያቀረቡበት ይሄው መፅሀፍ
የስለላና የአፈና ትንቅንቅን የሚያስቃኝ እውነተኛ ታሪክ ሲሆን በሁለተኛው ‹‹ለንባብ ለህይወት›› የመፅሀፍት አውደርዕይ መክፈቻ ላይ በድምቀት ተመርቋል፡፡ሌተናል ኮሎኔሉ መፅሐፉን ፅፈው ለህትመት ያዘጋጁት በ1985 ዓ.ም ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች የህትመት ብርሀን ሳያገኝ እንደቆየ የተገለፀ ሲሆን እርሳቸው ካለፉ በኋላ ልጃቸው ቴዎድሮስ ተፈራ መፅሐፉን የበለጠ በአርትኦት አበልፅጎ ለንባብ እንዳበቃው ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ ሌተናል ኮሎኔሉ 12 ዓመት በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ በአስተዳደር፣ በወንጀል ምርመራ በቴክኒክ ክፍል ስምንት ዓመት
ደግሞ በፀጥታ ጥበቃ መስሪያ ቤት የመረጃ ሀላፊዎች የቅርብ ረዳት ሆነው ባገለገሉበት ወቅት በአይናቸው ያዩዋቸው የተሳተፉባቸው እውነተኛ ክንውኖች በመፅሀፉ ተካተዋል መፅሀፉ በ341 ገፅ ተመጥኖ በ150 ብር እና በ25 የአሜሪካ ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

   ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት፣ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳትያ ናዴላ ማክሰኞ ዕለት ይፋ ማድረጋቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ፡፡
ኩባንያው በተጠናቀቀው ሩብ አመት 20.6 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ያስታወቁት ናዴላ፤ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ያገኘው ገቢ ግን 22.2 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ማይክሮሶፍት ኩባንያ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ያገኘዋል ተብሎ ከተገመተው በላይ ገቢ ማግኘቱ የተገለጸ ሲሆን ገቢው ሊያድግ የቻለውም የምርታማነትና በቢዝነስ ፕሮሰስ ክፍሉ ያከናወነው ስራ ውጤታማነት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ማይክሮሶፍት ባለፉት ሶስት ወራት ከጌሞች ሽያጭ ያገኘው ገቢ በ9 በመቶ ቢቀንስም፣ ከማስታወቂያ ያገኘው ገቢ በአንጻሩ በ54 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተነግሯል፡፡
ኩባንያው ባለፈው ሰኔ ወር በ26 ቢሊዮን ዶላር ሊንክዲን የተባለውን ማህበራዊ ድረገጽ መግዛቱን ያስታወሰው ዘገባው፤ ይህም በቀጣይ ገቢውን ያሳድግለታል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቋል፡፡





እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ ሰራተኞችን አባሯል

     ባለፈው ሳምንት የተቃጣበትን መፈንቅለ መንግስት ያከሸፈው የቱርክ መንግስት፤ በድጋሚ ተመሳሳይ ሙከራ ሊደረግ ይችላል የሚል ስጋት ውስጥ እንደገባ የተጠቆመ ሲሆን በርካታ ዜጎችን ከተለያዩ የመንግስትና የግል መስሪያ ቤቶች ማባረሩን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡
የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን መንግስት የተቃጣበትን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ማክሸፉን ተከትሎ በበርካታ የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና መምህራን ላይ የወሰደው የእስራትና ከስራ ገበታቸው የማባረር እርምጃ፣  በአገሪቱ ተመሳሳይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን ዘገባው ገልጧል፡፡
የኤርዶጋን መንግስት ባለፈው ማክሰኞ፣85 ያህል የአገሪቱን ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎችና መኮንኖች ማሰሩን የጠቆመው ዘገባው፤ አንዳንድ ምንጮች ግን የታሳሪዎቹ ቁጥር 125 እንደሚደርስ መናገራቸውን ጠቅሶ፣ይህም መንግስት በከሸፈው መፈንቅለ መንግስት የጦር ሰራዊቱ ሃላፊዎ እጃቸው አለበት ብሎ መጠርጠሩን ያመለክታል መባሉን አውስቷል። መንግስት የጦሩን እንቅስቃሴ ለመግታት በርካታ የጦር ሰፈሮችን በከባድ የጦር መሳሪያዎች ማስከበቡ የተነገረ ሲሆን የአውሮፓ የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት የኢስታምቡል ተወካይ አስሊ አይዲንታስባስም፤ መንግስት ይህንን እርምጃ መውሰዱ በድጋሚ የመፈንቅለ መንግስት ጥቃት ይፈጸምብኛል የሚል ስጋት ውስጥ መግባቱን ያሳያል ብለዋል፡፡ቢቢሲ በበኩሉ፤ የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን መንግስት ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ እየወሰደው ያለው እርምጃ ጥብቅ እየሆነ መምጣቱን በመግለጽ፣ ከስራ ገበታቸው ያገዳቸው ወይም ያባረራቸው ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ በላይ መድረሱን ዘግቧል፡፡ የአገሪቱ መንግስት እስካለፈው ረቡዕ ድረስ ከመፈንቅለ መንግስቱ ጠንሳሾች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል የጠረጠራቸውን 15 ሺህ 200 የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና መምህራን ከስራ ገበታቸው ማባረሩንና የሌሎች ተጨማሪ 21 ሺህ መምህራንን የስራ ፈቃድ መቀማቱን የጠቆመው ዘገባው፤ 1ሺህ 577 የዩኒቨርሲቲ ዲኖችም ስራቸውን እንዲለቁ መጠየቁን ገልጧል፡፡
የፖሊስ ባልደረቦች የነበሩ 8 ሺህ ሰዎች፣ 1 ሺህ 500 የገንዘብ ሚኒስቴር ሰራተኞች፣ 2 ሺህ 745 የፍርድ ቤት ዳኞች፣ 8 ሺህ 777 የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ሰራተኞች፣ ከ100 በላይ የብሄራዊ ደህንነት ተቋም ባልደረቦች፣ 257 የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ሰራተኞችና ሌሎች በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው መባረራቸውንም ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡
የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ፓርቲ የተላላካቸው 300 ሺህ ያህል የኢሜይል መልእክቶች አፈትልከው መውጣታቸውን ተከትሎ፣ የአገሪቱ መንግስት ዊኪሊክስ የተባለውንና መረጃዎቹን ዘርፎ ያሰራጨውን ተቋም ድረገጽ መዝጋቱን የዘገበው ደግሞ ዘ ጋርዲያን ነው፡፡
ስካይ ኒውስ በበኩሉ፤የቱርክ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ቦርድ ባለፈው ረቡዕ ባስተላለፈው ውሳኔ፣ ማንኛውም የአገሪቱ ምሁር ወይም ተመራማሪ ላልተወሰነ ጊዜ ከአገር መውጣት እንደማይችል ማስታወቁንና በውጭ አገራት የሚገኙትም በአፋጣኝ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማስተላለፉን ዘግቧል፡፡


በህንድ ጉጅራት አውራጃ የሚገኘው ሲንዱ የተባለ ሆስፒታል ሴት ልጆችን ለሚወልዱ ነፍሰጡር እናቶች ያለምንም ክፍያ የማዋለድና የህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ዘ ቴሌግራፍ ዘገበ፡፡
በአገሪቱ የሚገኙት አብዛኞቹ ነፍሰጡር እናቶች ወንድ ልጅ ለመውለድ እንደሚፈልጉና ሴት ሲወልዱ እንደሚበሳጩና እንደሚያዝኑ የጠቆመው ዘገባው፤ሆስፒታሉም ነፍሰጡሮች ሴት ልጆች ያላቸውን አመለካከት እንዲቀይሩ በማሰብ ነጻ የህክምና አገልግሎቱን እንደ ማበረታቻ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡
በህንድ ለሴት ልጅ ያለው አመለካከት የተዛባ በመሆኑ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሴት ልጅ ጽንሶች በውርጃ እንደሚቋረጡ ወይም እንደተወለዱ እንደሚገደሉ የጠቆመው ዘገባው፤ የአገሪቱ መንግስት ይህን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር እየሰራ እንደሚገኝና  የሆስፒታሉ ነጻ የህክምና አገልግሎትም የዚህ ጥረት አካል እንደሆነ ገልጧል። በሆስፒታሉ ሴት ልጆችን የሚገላገሉ ነፍሰ-ጡር እናቶች ለህክምና አግልግሎቱ መክፈል ከሚገባቸው 20 ሺህ የህንድ ሩፒ  ነጻ እንደሚደረጉ ተነግሯል፡፡
እናቶች የአገሪቱ መንግስት ከ1994 አንስቶ ተግባራዊ ባደረገው ህግ ነፍሰጡር ሴቶች ከወሊድ በፊት የጽንሱን ጾታ በምርመራ እንዳያውቁ መከልከሉን ያስታወሰው ዘገባው፤ይህም የተደረገው እናቶች ሴት ማርገዛቸውን ቀደም ብለው በማወቅ ጽንሱን ከማስወረድ ለመግታት እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ይህም ሆኖ በህንድ ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ብቻ 12 ሚሊዮን የሚደርሱ የሴት ጽንሶች በወላጆቻቸው የተዛባ የጾታ አመለካከት ሳቢያ በውርጃ እንዲቋረጡ መደረጋቸው በጥናት መረጋገጡን ዘገባው አመልክቷል፡፡

በአመቱ 211 ጥቃቶች ተፈጽመው፣151 ሰዎች ሞተዋል

    ያለፈው የፈረንጆች አመት 2015፣አውሮፓ በታሪኳ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሽብር ጥቃት ማስተናገዷንና በአመቱ ከፍተኛው የሽብር ጥቃት የተመዘገበው በእንግሊዝ መሆኑን ዩሮፖል የተባለው የአህጉሪቱ ተቋም ማስታወቁ ተዘገበ፡፡
ዓመቱ በአውሮፓ አህጉር በርካታ ቁጥር ያላቸው የሽብር ጥቃቶች የታቀዱበት፣የከሸፉበትና የተፈጸሙበት ነው ያለው ተቋሙ፤በተለያዩ የአውሮፓ አገራት ውስጥ 211 ያህል የሽብር ጥቃቶች መፈጸማቸውን ጠቁሞ፣ 103 ጥቃቶችን ያስተናገደቺው እንግሊዝ ከአህጉሩ ቀዳሚውን ስፍራ መያዟን አስታውቋል፡፡ በአመቱ በፈረንሳይ 72፣ በስፔን ደግሞ 25 ያህል የሽብር ጥቃቶች መፈጸማቸውን ያስታወቀው የተቋሙ የአውሮፓ ህብረት የሽብርተኝነት ሁኔታና አዝማሚያ አመላካች ሪፖርት፤ በአመቱ የጂሃዲስት የሽብር ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ 687 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ከእነዚህም ውስጥ 94 በመቶው ጥፋተኛ መሆናቸው መረጋገጡን ገልጧል፡፡
በ2015 በአውሮፓ አገራት ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዙ ህገወጥ ድርጊቶች ተጠርጥረው የታሰሩ ግለሰቦች ከ1ሺህ በላይ እንደሆኑና ከእነዚህ መካከልም 424 የሚሆኑት በፈረንሳይ እንደታሰሩ የጠቆመው ሪፖርቱ፤151 ሰዎች በተሰነዘሩ ጥቃቶች መሞታቸውንና ከ360 በላይ መቁሰላቸውን አስታውቋል፡፡




እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ ሰራተኞችን አባሯል

     ባለፈው ሳምንት የተቃጣበትን መፈንቅለ መንግስት ያከሸፈው የቱርክ መንግስት፤ በድጋሚ ተመሳሳይ ሙከራ ሊደረግ ይችላል የሚል ስጋት ውስጥ እንደገባ የተጠቆመ ሲሆን በርካታ ዜጎችን ከተለያዩ የመንግስትና የግል መስሪያ ቤቶች ማባረሩን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡
የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን መንግስት የተቃጣበትን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ማክሸፉን ተከትሎ በበርካታ የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና መምህራን ላይ የወሰደው የእስራትና ከስራ ገበታቸው የማባረር እርምጃ፣  በአገሪቱ ተመሳሳይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን ዘገባው ገልጧል፡፡
የኤርዶጋን መንግስት ባለፈው ማክሰኞ፣85 ያህል የአገሪቱን ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎችና መኮንኖች ማሰሩን የጠቆመው ዘገባው፤ አንዳንድ ምንጮች ግን የታሳሪዎቹ ቁጥር 125 እንደሚደርስ መናገራቸውን ጠቅሶ፣ይህም መንግስት በከሸፈው መፈንቅለ መንግስት የጦር ሰራዊቱ ሃላፊዎ እጃቸው አለበት ብሎ መጠርጠሩን ያመለክታል መባሉን አውስቷል። መንግስት የጦሩን እንቅስቃሴ ለመግታት በርካታ የጦር ሰፈሮችን በከባድ የጦር መሳሪያዎች ማስከበቡ የተነገረ ሲሆን የአውሮፓ የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት የኢስታምቡል ተወካይ አስሊ አይዲንታስባስም፤ መንግስት ይህንን እርምጃ መውሰዱ በድጋሚ የመፈንቅለ መንግስት ጥቃት ይፈጸምብኛል የሚል ስጋት ውስጥ መግባቱን ያሳያል ብለዋል፡፡ቢቢሲ በበኩሉ፤ የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን መንግስት ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ እየወሰደው ያለው እርምጃ ጥብቅ እየሆነ መምጣቱን በመግለጽ፣ ከስራ ገበታቸው ያገዳቸው ወይም ያባረራቸው ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ በላይ መድረሱን ዘግቧል፡፡ የአገሪቱ መንግስት እስካለፈው ረቡዕ ድረስ ከመፈንቅለ መንግስቱ ጠንሳሾች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል የጠረጠራቸውን 15 ሺህ 200 የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና መምህራን ከስራ ገበታቸው ማባረሩንና የሌሎች ተጨማሪ 21 ሺህ መምህራንን የስራ ፈቃድ መቀማቱን የጠቆመው ዘገባው፤ 1ሺህ 577 የዩኒቨርሲቲ ዲኖችም ስራቸውን እንዲለቁ መጠየቁን ገልጧል፡፡
የፖሊስ ባልደረቦች የነበሩ 8 ሺህ ሰዎች፣ 1 ሺህ 500 የገንዘብ ሚኒስቴር ሰራተኞች፣ 2 ሺህ 745 የፍርድ ቤት ዳኞች፣ 8 ሺህ 777 የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ሰራተኞች፣ ከ100 በላይ የብሄራዊ ደህንነት ተቋም ባልደረቦች፣ 257 የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ሰራተኞችና ሌሎች በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው መባረራቸውንም ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡
የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ፓርቲ የተላላካቸው 300 ሺህ ያህል የኢሜይል መልእክቶች አፈትልከው መውጣታቸውን ተከትሎ፣ የአገሪቱ መንግስት ዊኪሊክስ የተባለውንና መረጃዎቹን ዘርፎ ያሰራጨውን ተቋም ድረገጽ መዝጋቱን የዘገበው ደግሞ ዘ ጋርዲያን ነው፡፡
ስካይ ኒውስ በበኩሉ፤የቱርክ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ቦርድ ባለፈው ረቡዕ ባስተላለፈው ውሳኔ፣ ማንኛውም የአገሪቱ ምሁር ወይም ተመራማሪ ላልተወሰነ ጊዜ ከአገር መውጣት እንደማይችል ማስታወቁንና በውጭ አገራት የሚገኙትም በአፋጣኝ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማስተላለፉን ዘግቧል፡፡


ማርቲን ሉተር ኪንግ
የነጻነት ታጋይ፡ የጥቁር ሕዝቦች ንቅናቄ መሪ እና የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ

‹‹ህልም አለኝ! አንድ ቀን አራቱ እምቦቃቅላ ልጆቼ በቆዳቸው ቀለም (በዘራቸው) ሳይሆን በውስጣዊ ስብእናቸው በሚመዘኑበት ማህበረሰብ ውስጥ እንደሚኖሩ፡፡ ዛሬ ላይ ሆኜ ይህን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››
በጣም አመሰግናለሁ ወዳጆቼ፡፡ የራልፍ አቤናዚን ቅንነት የመላበትና ልብ የሚነካ የማስተዋወቂያ ንግግር እያደመጥኩ ስለ ራሴ ሳስብ ነበር፤ ስለ ማነው እንዲህ የሚናገረው እያልኩ፡፡ መቸም ጓደኛችን በሆነ የኛ የምንለው ሰው አንደበት ስለ መልካምነታችን ሲነገር መስማት ደስ ይል አይደል፡፡ ራልፍ ማለት ለኔ በአለም ላይ በጣም የቅርብ ወዳጄ እምለው ሰው ነው፡፡
(ራልፍ፤ ከማርቲን ሉተርና ከሌሎች ጥቁሮች የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ጋር በመሆን ዘረኝነትንና ጭቆናን በሰላማዊ መንገድ የሚታገለውን ሳውዘርን ክርስቲያን ሊደርሺፕ ኮንፍረንስ  መስርቷል፡፡)
ያ ሁሉ የማስጠንቀቂያ ውርጅብኝ ሳያስበረግጋችሁ ከዚህ ስፍራ የተገኛችሁ ሁሉ፤ በዚህ ምሽት እናንተን በማየቴ ደስ ብሎኛል፡፡ እምቢ አሻፈረኝ! ማለታችሁ የሚያሳየውም እስከ ምንም ድረስ መስዋእትነት ለመክፈል ያላችሁን ቁርጠኝነት ነው፡፡ ይህ እዚህ በሜምፈስ እየሆነ ያለው በመላው አለም እኛን መሰል ሕዝቦች ውስጥ ሁሉ እየሆነ ያለ ነገር ነውና፡፡
እንበልና፤ አሁን የቆምኩት ገና በእምቅድመ ዓለም ጊዜ ላይ ቢሆንና የሰው ዘር ካለፈባቸው የታሪክ ምእራፎቹ ጋር መላው ዓለም ከአጽናፍ አጽናፍ እንደ ሰፊ ትእይንት ፊት ለፊቴ ተሰትሮ እንዳየው እድሉ ተሰጥቶኝ፤ ኃያሉ አምላክም ‹‹እነሆኝ ማርቲን ሉተር ኪንግ፤ እንኪያስ በየትኛው ዘመን ላይ ትኖር ዘንድ ትወድዳለህን@›› ቢለኝ ፤ ምናበ አክናፌን ዘርግቼ አድማሱን እያካለልኩ፤ በጥንቲቱ የግብጽ ምድር ወይም በቀይ ባህር በኩል ጠፍ በረኻውን አቋርጬ ወደ ተስፋዋ ምድር አቀናና ህልቆ መሳፍርት እጹብ ድንቅ ትእይንቶች ከሞሉባት ሀገር እደርሳለሁ። ግን እዚያም አልቆምም፡፡ እንደገና በኦሊምፐስ ተራራ አናት ለማረፍ በጥንቲቱ የግሪክ ሰማይ ላይ እከንፋለሁ፡፡ በዚያም ፕሌቶ፡ አሪስቶትል፡ ሶቅራጥስ፡ ዩሪፒደስ እና አሪስቶፋነስ ረቂቅ አርእስት ጉዳይ በሆነው በምድራዊውና ዘለዓለማዊው ህይወት ዙሪያ ለመወያየት ከሚሰየሙበት ከፓርሴኖን አምባ እታደማለሁ፡፡
(ፓርሴኖን Parthenon ከክ.ል.በ በ5ኛው ክፍለ ዘመን የተገነባና ዛሬም ድረስ በአቴና - ግሪክ ውስጥ ቆሞ የሚታይ ቤተ መቅደስ ነው፡፡ ስማቸው የተዘረዘረው አምስቱ ግሪካዊያን መምህራንና ጸሐፍት የኖሩበት ዘመን ደግሞ እስከ አሪስቶትል ሞት 322 ከክ.ል.በ ድረስ 160 አመታት የሚከነዳ ሲሆን፤ የልሂቃኑ አስተሳሰብና ፍልስፍናም ለምእራቡ አለም ዘመናዊ ስልጣኔ ታላቅ ተጽእኖ የፈጠረ ነው፡፡)
ግን እዚያም አልቆምም፡፡ ወደ ጥንታዊው ገናናው የሮማ ግዛት ዘንድ ተጉዤ በየትየለሌ ነገሥታትና ጎበዛዝት ገዢዎች የተከናወኑትን የእድገትና ስልጣኔ ፈለጎች አስተውላለሁ፡፡ ግን እዚያም አልቆምም፡፡ ደግሞ መለስ ብዬ እስከ ብርሃነ ህሊና (Renaissance) ዘመን እንሳፈፍና የሬኔይሳንስ ዘመንን ዳና፡ ለሰው ልጆች ያበረከተውን የባህልና ሥነ ውበት ብልጽግና በረከቶች እቃኛለሁ፡፡ ግን እዚያም አልቆምም፡፡ እንደገና መጠሪያ ስሜ በስሙ ከተሰየመው ሰውና ዘርማንዘሮቹ ቀዬ ድረስ እዘልቅና ማርቲን ሉተር በዊተንበርግ ቤተ ክርስቲያን መግቢያ በር ላይ የለጠፈውን ዘጠና ዘጠኝ  ፍሬ ነገሮች ዝርዝር ልቅም አድርጌ አነብባቸዋለሁ፡፡
(ማርቲን ሉተር Martin Luther ከ1483 - 1546 የኖረ ጀርመናዊ የሥነ መለኮት ሊቅ theologian ሲሆን ፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን አንዳንድ አስተምህሮዎች የሞገተባቸው መከራከሪያ ሀሳቦቹ ለፕሮቴስታንት ጅማሮ ፈር ቀዳጅ ሆነዋል፡፡)
ግን እዚያም አልቆምም፡፡ ወዲህም እስከ 1863 መጥቼ፣ ይይዝ ይጨብጠው አጥቶ ቆይቶ በመጨረሻው የጥቁር ሕዝቦችን ነጻነትና ከመላው ዜጎች እኩልነት የሚያረጋግጠውን ሰነድ Emancipation Proclamation ግድ ለመፈረም የበቃውን አብርሀም ሊንከን ተብዬውን ‹እንግጭግጩ›ን vacilating president ፕሬዚዳንት አየዋለሁ፡፡ ግን እዚያም አልቆምም፡፡ ወደ ቅርቡ የአስራ ዘጠኝ ሰላሣዎቹ አመታት ጠጋ ብዬም ሌላውንና የሀገሩን ዜጎች የከፋ የኑሮ ማሽቆልቆል Bankruptcy ለመታደግ ከጊዜው ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ የተናነቀውን ሰው እያየሁ፡ አንደበተ ርቱእ ድምጹ ሲያስተጋባ እሰማዋለሁ፡... ‹‹የምንፈራው አንዳችም ነገር የለም፤ ራሱን ፍርሀትን ብቻ እንጂ!››
(ማርቲን ለማስታወስ የፈለገው በ1930ዎቹ የአሜሪካዊያኑ የመከራ አመታት “The Great Depression” ወቅት የሀገሪቱ መሪ የነበሩትን ፕሬዚዳንት ፍራንክሊን ሩዝቬልትን ነው፡፡)
አሁንም ግን እዚያም አልቆምም፡፡ ባልተጠበቀ ሁኔታ እጥፍ ዘርጋ ብዬ በርሬ፣ ኃያሉ አምላክ እግር ስር እገኝና እማጸነዋለሁ... ‹‹በሃያኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አጋማሽ ጥቂት አመታትን እኖር ዘንድ ምኞቴ ነው፤ ብትፈቅድልኝ ደስታዬ ወደር አይኖረውም!›› በማለት፡፡ እርግጥ ነው ይኼ ያልተለመደ ጥያቄ (‹የከፍታ በረራ›) ስለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ምክንያቱም አለም ቅጣምባሩ ጠፍቶባታልና፡፡ ሕዝቡ በደዌ ተቀስፏል፡፡ መከራ በምድሪቱ  ዙሪያ ተንሰራፍቷል፡፡ ግራ መጋባት ነግሷል፡፡ ለዚህም ነው እንዲህ ያለውን ምኞት ያልተለመደ የሚያደርገው፡፡ ሆኖም ግን አንድ ነገር እረዳለሁ፤ ይኸውም፡- ምንም ያህል አይን ይያዝ እንጂ። ድቅድቅ ጨለማው በወጉ ሲሰፍር ብቻ ነው ክዋክብቱን ጥርት አድርጎ ማየት የሚቻለው፡፡ የማስተውለውም ይህንኑ ነው፤ እግዚአብሔር በዚህ በሃያኛው ክፍለ ዘመን ለየነገሩ ምላሽ በሚሆን መልኩ ስራውን እየሰራ መሆኑን፡፡ የዚህም ማሳያው ሰዎች ለጥያቄዎች ተገቢ ያልሆነ የግርምቢጥ ምላሽ በሰጡ ቁጥር አጸፋውም የዚያኑ ያህል ሲከሰት በአለማችን ላይ ፍንትው ብሎ እየታየ ነው፡፡ ሳር ቅጠሉ ሕዝቡ ሁሉ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ተነስቷል፡፡ እናም ባሁኑ ጊዜ ሕዝቦች የትም ይሰብሰቡ ጆሀንስበርግ-ደቡብ አፍሪካም፡ ናይሮቢ-ኬንያ፡ አክራ-ጋና፡ ኒው ዮርክ ሲቲ፡ አትላንታ-ጆርጂያ፡ ጃክሰን-ሚሲሲፒ፡ ወይም እዚህ ሜምፈስ - ቴኔሲ የሁላችንም ጩኸት መቼም ቢሆን ያው አንድ ነው - ‹‹ነጻ መሆን እንሻለን›› የሚል። “ We want to be free.”
ሌላው በዚህ ዘመን በመኖሬ የምደሰትበት ነገር ቢኖር፤ እኛ ዛሬ ተገድደን ትግል የገጠምነውና ወደ መፍትኄው ጫፍ እየገፋነው ያለው ጉዳይ፡ የሰው ልጆች ባሳለፉዋቸው ዘመናት ሁሉ ሲላተሙት የኖሩት ችግርን በመሆኑ ነው፡፡ ያም ሆኖ ያለፉቱ ትውልድ የኛን ያህል እንዲጋፈጡት የሚያስችል አስገዳጅ ሁኔታ እና ለውጤት የሚያበቃ እድልና አቅምም አልገጠማቸውም ነበር፡፡ እንግዲህ ከእነርሱ የወረስናቸው ችግሮች አድገው ነው እኛ ዛሬ የተፋጠጥናቸው፡፡ የሰው ልጆች ለዘመናት ዛሬም ድረስ ስለ ጦርነትና ሰላም ያወራሉ፡፡ ከእንግዲህ ግን መወራቱ ማብቃት አለበት፡፡ ምክንያቱም አሁን የደረስንበት ጊዜ እንደስከዛሬው መብትን ለማስከበር ከሰላማዊ ትግል እና ከረብሻና የብጥብጥ ትግል የትኛውን እንምረጥ የምንልበት አይደለም፤ አማራጩ አንድና አንድ ሆኗልና፤ እርሱም ያው ሰላማዊ ትግሉን መቀጠል ወይም ደግሞ በቃ ከናካቴው ጨርሶ በህይወት አለመኖርን መምረጥ ብቻ ፡፡
ያለንበት ጊዜ ይኼ ነው፡፡ ታዲያ ግን በዚህ የሰው ልጆችን ሰብአዊ መብቶች የማስከበር አብዮት ሂደት፡ ጥቁር ህዝቦችን ለረዥም ዘመናት ከተዘፈቁበት አስከፊ ረሀብና ጉስቁልና፡ ማብቂያ ያጣ መከራና እንግልት አላቅቆ ለእፎይታ እሚያበቃቸው አንድ የሆነ መፍትኄ ያውም ባስቸኳይ ማድረግ እስካልተቻለ፤ ምድርና ሞላዋ ሁሉ በአጉል የጥፋት አዘቅት መዋጣቸው አይቀሬ ነው፡፡ ለዚህም ነው እግዚአብሔር በዚህ ዘመን እንድኖር ስለፈቀደልኝ የምደሰተው፤ ቀጣዩን ውጤት ለማየት ስለታደልኩ። ዛሬም በዚህ በሜምፈስ እገኝ ዘንድ ስለተፈቀደልኝ የምደሰተውም ለዚህ ነው፡፡
አስታውሳለሁ እኔም፡ አዎን በደንብ አስታውሰዋለሁ፡ ቅድም ራልፍ እንዳለው፤ ኔግሮዎች ያለ እረፍት ከወዲያ ወዲህ በከንቱ እየባዘኑ፡ ያልበላቸውን እያከኩ፡ ሳይኮረኮሩ እየገለፈጡ የኖሩትን ህይወት፡፡ እነሆ ያ ዘመን አክትሟል፡፡ አሁን መብታችን መከበር አለበት፡፡ ለዚህም ደግሞ እኛም እግዚአብሔር በሰጠን ምድር ላይ ተገቢ ስፍራችንን እናገኝ ዘንድ ቆርጠን ተነስተናል፡፡
እዚህ ያሰባሰበንም ጉዳይ ይኸው ነው። ከየትኛውም አካል ጋር በምንም አይነት የጥፋት ‹አዝማሚያ› ወይም አሉታዊ ንትርክ አልተጠመድንም፡፡ የምንለው ነገር ቢኖር ‹ሰው ለመሆን ቆርጠን ተነስተናል፤ ሕዝብ ለመሆን ወስነናል፤ እኛም የእግዚአብሔር ፍጡሮች/ልጆች ነን፤ ስለዚህም ሌሎች እንድንኖር በሚቀይዱልን መንገድ ብቻ ተገድደን መኖር የለብንም፡፡› ነው፡፡  
እናም እንግዲህ ይህ ዘመን በታሪክ ውስጥ አይነተኛ ጊዜ ሆኖ የሚገኘው በምንድነው@ እኛ ሁላችንም አብረን በመሆናችን ነው፡፡ አብረን ሆነንም በጋራ አንድነታችንን በማስጠበቃችን፡፡ ሁላችሁም እንደምታውቁት፤ ፈርኦን በግብጽ ምድር የነበረውን የባርነት ዘመን ለማራዘም ይጠቀምበት የነበረው አንድ የተለመደ፣ በጣም የተለመደ ቀመር formula ነበረው፡፡ ያም ፎርሙላው ምንድን ነበር@ ባሮቹን እርስ በርሳቸው ማጋጨትና እንዳይግባቡ ማድረግ፡፡ ካልሆነማ መቼም ቢሆን ባሮች ባንድነት ከቆሙ በፈርኦኑ ህልውና ላይ አንድ የሆነ ነገር መከሰቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ እንዲያ ከሆነ ደግሞ ፈርኦኑ ባሮቹን በባርነት ቀንበሩ ስር ኮድኩዶ ለማቆየት አይቻለውም፡፡ ባሮች ባንድነት ሲቆሙ ከባርነት ነጻ የመውጣት ጅማሮ ይሆናል፡፡ ስለዬህ (ውድ የፈርኦን ባሮች አምሳያ ወገኖቼ ሆይ!) አሁን፤ በቅድሚያ ሳንከፋፈል አንድነታችንን በጽናት እንጠብቅና እንቁም!!!
(ማርቲን ሉተር ኪንግ ከመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች መኻከል ለምሳሌነት ያዋለው፤ እስራኤላዊያንን በባርነት ይገዛ የነበረውን ፈርኦን ነው፤ ነቢዩ ሙሴ ሕዝቡን ከግብጽ ወደ ‹የተስፋዋ ምድር› እስኪመራቸው - ማርና ወተት ወደምታፈልቀወ ከነዓን ... Canaan.)
ቀጣዩ ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ . . .
(ውድ አንባብን፡- ዘመኖቹ በሙሉ እ.ኤ.አ ናቸው)
 ምንጭ - GLENCOE
I have seen the Promised land
              by - Martin Luther King Jr.