Administrator

Administrator


•  ተቋሙ በአፍሪካ የአይቲ ማዕከል ለመሆን እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል


በአፍሪካ የአይቲ ማዕከል ለመሆን ራዕይ ሰንቆ በአዲስ መልክ እየተዋቀረና እየተደራጀ መሆኑ የተነገረለት የአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽን፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ በይፋ  ሥራ እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡ በአይቲ ፓርኩ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ  የሆነው  የግል  የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጠት መጀመሩም ተጠቁሟል፡፡

ይህ ይፋ የተደረገው በዛሬው ዕለት ጠዋት በሸራተን አዲስ ሆቴል፣ “የዳታ ማዕከል አገልግሎት ሥነምህዳር ዕድሎችን ለፋይናንስ ዘርፉና ለቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪው ማመቻቸት” በሚል ርዕስ፣ ለግማሽ ቀን በተካሄደ ጉባኤ ላይ ሲሆን፤ ጉባኤውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽንና የዊንጉ አፍሪካ ዳታ ማዕከል  በትብብር እንዳዘጋጁት ታውቋል፡፡

የአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽኑን  የሚያስተዳድረው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፤የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር እውን በማድረግ ረገድ አይቲ ፓርኩ ጉልህ ሚና የሚጫወት ይሆናል፡፡ ከዚህ አንጻር ጉባኤው ወቅታዊና ተገቢ መሆኑን ሚኒስትሩ አስምረውበታል፡፡

የአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ አህመድ በበኩላቸው በሰጡት ማብራሪያ፣ የኮርፖሬሽኑ ትልቁ ዓላማው ቢዝነስ መሥራት የሚያስችል ሥነምህዳር መፍጠር መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህም ሁሉም በጋራ የሚጠቀምበት ሪሶርስ በአንድ ቦታ ያቀርባል ብለዋል፡፡

ራዕያችን የአፍሪካ የአይቲ ማዕከል መሆን ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ይህን ለማሳካትም  የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማምጣትና አቅምን በማሳደግ ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነትን ማጎልበት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ጉባኤ ላይ  በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የግል የዳታ ማዕከል፣ በአይቲ ፓርክ ገንብቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የጠቆመው ዊንጉ አፍሪካ የዳታ ማዕከል ኩባንያ፤ በምሥራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊላንድና ታንዛንያን  ጨምሮ በአራት አገራት በዘርፉ አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ  የሚገኝ ስመ-ጥር ኩባንያ ነው ተብሏል፡፡   

ኩባንያቸው በቀጣናው ተጠቃሽ  የዳታ ማዕከል አገልግሎት አቅራቢ መሆኑን የገለጹት የዊንጉ አፍሪካ ዳታ ማዕከል  ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ተሾመ፤ በኢትዮጵያም ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አስተማማኝ የዳታ ማዕከል መገንባቱን ጠቁመው፤ በዋናነት  የፋይናንስ ዘርፉና የቴክኖሎጂ ተቋማት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

ዊንጉ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ሥራ ከጀመረ 18 ወራት ማስቆጠሩን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ የዚህ ጉባኤ አንዱ ዓላማ እነዚህ የፋይናንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት ከፍተኛ ወጪ አውጥተው፣ የየራሳቸውን የዳታ ማዕከል ከመገንባት ይልቅ በኛ ማዕከል ቢጠቀሙ፣ የበለጠ እንደሚያዋጣቸው መረጃና ግንዛቤ ለመስጠት ነው ብለዋል፡፡ ጉባኤው አጋርነትና ትብብር የመፍጠሪያ መድረክ እንደሚሆንም ጨምረው አመልክተዋል፡፡
የዳታ ማዕከሉን ከሚመሩት ውስጥ 90 በመቶው ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የገለጹት የኩባንያው አመራሮች፤ ማዕከሉ ለወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ኢንጂነሮች ትልቅ የሥራ ዕድል መፍጠሩን አውስተዋል፡፡

የዘርፉ ዓለማቀፍ ተዋናዮች በአጋርነት አብረውን እንዲሰሩ መሳብ ችለናል ያሉት አመራሮቹ፤ የመንግሥት ደንብና መመሪያዎች ወጥተው እንደተጠናቀቁ እኒህ ተዋናዮች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡ ማይክሮሶፍት፣ ቲክቶክና ሜታ (የቀድሞው ፌስቡክ) የመሳሰሉ ግዙፍ ዓለማቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ወደዚህ አገር እንዲመጡም እየሰራን ነው ብለዋል - የዊንጉ አፍሪካ ዳታ ማዕከል ኩባንያ  አመራሮች፡፡

የዊንጉ አፍሪካ ዳታ ማዕከል፣ በ50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ መገንባቱ  ይታወቃል፡፡

በዚህ ለግማሽ ቀን በሸራተን አዲስ በተካሄደው ጉባኤ ላይ፣ የአይቲ ኢንዱስትሪው መሪዎች፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የፋይናንስ ተቋማት አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

የአምራች ኢንተርፕራይዞች አገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር ለ5 ቀናት ይካሄዳል


•  ኤግዚቢሽንና ባዛሩ ታህሳስ 3 በስካይ ላይት ሆቴል ይከፈታል


”ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ቃል፣ ”የኛ ምርት” የተሰኘ የአምራች ኢንተርፕራይዞች አገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር፣ ከታሕሳስ 3 እስከ ታሕሳስ 7 ቀን 2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራሮችና የፕራና ኢቨንትስ ዳይሬክቲንግ ማናጀር፣ ኤግዚቢሽንና ባዛሩን አስመልክቶ ዛሬ ጠዋት ረፋዱ ላይ በስካይ ላይት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

”የኛ ምርት” የተሰኘው ኤግዚቢሽንና ባዛር ዋና ዓላማ፣ አምራች ኢንተርፕራይዞች በምርት ትውውቅ፣ በምርት ሽያጭ፣ በገበያ ትስስር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በልምድና የመረጃ ልውውጥ የተሻለ አቅም መፍጠርና የዘርፉን ፋይዳ  ማሳየት የሚያስችላቸውን መድረክ መፍጠር ነው ተብሏል፡፡

በዚህ ኤግዚቢሽንና ባዛር፣ ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ ከ100 በላይ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ውጤት አምራቾች፣ የፕላስቲክ ውጤት አምራቾች፣ የቆዳና የቆዳ ውጤት አምራቾች፣ የአግሮ ፕሮሰሲንግ አምራቾች፣ የኬሚካል ውጤት አምራቾች፣ የማዕድንና ጌጣጌጥ ውጤት አምራቾች፣ የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤት አምራቾችና ሌሎች ዋና ድጋፍ ሰጪ ተቋማት የሚሳተፉበት ሲሆን፤ ከ50ሺ በላይ ገዢና ጎብኚዎች ይስተናገዱበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ፣ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ውጤታማ  የአገር ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች በአንድ ጣሪያ ሥር ተሰባስበው ከመላ አገራችን ከሚመጡ የህብረተሰብ ክፍሎችና ከአጋር ተቋማት ጋር የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል፣ ልምድና ተሞክሮ ለመጋራት ምቹ ዕድል የሚፈጥር እንዲሆን ለማስቻል ጥረት መደረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ በተጨማሪም፣ አምራቾች የደረሱበትን የቴክኖሎጂና የምርት የእድገት ስኬት ደረጃ፣ ልምድና ተሞክሮ የሚያካፍሉበት እንዲሁም በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፍ የሚያቀርቡበትና የፓናል ውይይት የሚካሄድበት መድረክ እንደሚሆንም ለማወቅ ተችሏል፡፡


”የኛ ምርት” ኤግዚቢሽንና ባዛር፣ ዘላቂ የንግድ ትስስርን ለመፍጠርና የምርት ዕድገትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በጥንቃቄ የታቀደ ነው የተባለ ሲሆን፤ ለተሳታፊዎች የንግድና የምርት ስኬት የሚተጋ ከመሆኑም በላይ የአምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶችን ማህበረሰቡ በአገር ምርት እንዲኮራና ትኩረት ሰጥቶ እንዲሸምት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ልዩ ኹነት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

”የኛ ምርት” የተሰኘውን አገር አቀፍ  ኤግዚቢሽንና ባዛር፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ፕራና ኤቨንትስ በትብብር እንደሚያዘጋጁት ታውቋል፡፡

Monday, 06 November 2023 19:09

1242.pdf addisadmassnews

https://online.fliphtml5.com/etocz/zlhw/

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከሚሰራቸዉ ዋና ዋና ተግባራት መካከል ከኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና በዘርፉ ውስጥ ካሉ አካላት ጋር ኪነ-ጥበብን በተለያዩ መንገዶች ማሳደግና በኪነ-ጥበብ የተገነባ ትውልድን ማፍራት ነዉ።
በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ ቴአትር ባለሞያዎች ማህበር ከቢሯችን፣ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንና ከቢ ኘላስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የቴአትር እና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና የቴአትር ተማሪዎች በተገኙበት ለአራተኛ ጊዜ እየተካሄደ ነዉ።
ፌስቲቫሉ ቦሌ በሚገኘው ፍሬንድሺፕ ሆቴል እና ሸጎሌ ባለው አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ውስጥ ይካሄዳል።
በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ (የኪነ-ጥበብ ሐብቶች ልማት፣ መድረኮችና ኩነቶች ዝግጅት ዳይሬክተር ) አቶ ሰለሞን ደኑ ቢሮው ከኢትዮጵያ ቴአትር ማህበርና ከሌሎች የኪነ-ጥበብ ባለድርሻዎች ጋር በትስስር በመስራት ኪነ-ጥበባዊ ጥናትና ዉይይቶች እየቀረቡ ለህዝብ መድረሳቸው ለዘርፉ የመረጃ ፍሰትን ያዳብራል ብለዋል።
በተጨማሪም ቢሮዉ ቀጣይ ይህን መሰል ፕሮግራም በማስተባበር እንደሚሰራ አሳዉቀዋል።
ዛሬ ጥቅምት 24 /2016 ዓ.ም የቴአትርና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል ላይ "የአዛውንቶች ክበብ" የተሰኘዉ ተዉኔት ታሪክ አወቃቀርና አጠቃላይ ገለፃ ተደርጎል።
ከዛሬ አርባ ዓመታት በፊት በፀኃፊ ተውኔት ነጋሽ ገ/ማርያም የተደረሰዉ "የአዛውንቶች ክበብ" ቴአትር በሀገራችን አንጋፋ በሆኑት በአውላቸዉ ደጀኔ፣ ወጋየሁ ንጋቱ እና በሌሎች ዕውቅ ተዋኒያን ተተዉኗል።
"የአዛዉንቶች ክበብ" ቴአትር በኢትዮጵያ የቴአትር ታሪክ ዉስጥ ትልቅ ሚና የጣለ እንደሆነ የቴአትር ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚደንት ቢኒያም ወርቁ አንስተዋል።
ድርሰት እና አጠቃላይ ታሪኩን የሚመለከት ጥናት በባለሙያ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል።
ቀጣይ በሚካሄደው የቴአትር ፌስቲቫል በገጣሚ ታረቀኝ በዳሳ የተደረሰዉ "የሁለት ክፍል ግብዣ" የተሰኘዉ ተውኔት ጥናትና ውይይት ሸጎሌ በሚገኘዉ በኢቲቪ አዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ይቀርባል ነዉ የተባለዉ።
ሌሎች የቀደምት ተውኔቶች በመድረክ ድጋሜ እየቀረቡ ለህዝብ ቢቀርቡ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል።
የኢትዮጵያ ቴአትር ባለሞያዎች ማህበር ጥያቄዉን በመዉሰድ እንደሚሰራ አሳዉቋል።
የአርካይቪንግ እና ዶክመንቴሽን ስራዎች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግባቸዉ እንደሚገባ ተነስቷል።
በተለይም ዲጂታል በሆነ መንገድ ቢቀመጡ በተፈለጉ ሰዓት መገኘት የሚችሉበት ሁኔታ ቀላል አማራጭ እንደሚሆን ኤርሚያስ ፍቅሬ/ጥናት አቅራቢ/ አንስተዋል።
የሁለቱ ተውኔቶች ጥናትና ውይይት በዋናነት የአርባኛ ዓመት መታሰቢያ ዘመናቸውን ምክንያት በማድረግ በትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ሌሎች የተውኔት ስራዎችን ለመዘከር ያግዛል ተብሏል።
(ባ/ኪ/ቱ ቢሮ)
አትሌት ታምራት ቶላ በኒው ዮርክ በተካሄደው የማራቶን ውድድር አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡
አትሌት ታምራት ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ58 ሰኮንድ የፈጀበት ሲሆን፤ የገባበት ሰዓትም በኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር ታሪክ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኗል፡፡
በውድድሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሹራ ቂጣታ ሶሰትኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል::
በሴቶቹ በኩል አትሌት ለተሰንበት ግደይ የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር ሁለተኛ በመሆን ስታጠናቅቅ፤ ኬኒያዊቷ አትሌት ሄለን ኦቢሪ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፋለች::

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚሰጠውን የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ተበረከተላት።

ሽልማቱ የተበረከተላት በኢትዮጵያና ጃፓን መካከል ያለው የስፖርት ዲፕሎማሲ እንዲጠናከር ላደረገችው አስተዋጽኦ መሆኑም ተገልጿል።

አትሌት ደራርቱ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሺንዞ አቤ በፈረንጆቹ 2014 ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር እንዲወያዩ እድርጋ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2019 ላይም ደራርቱ የጃፓን ስፖርት ኤጀንሲ ኮሚሽነር ከሆኑት ሱዙኪ ዳይቺን እና የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሃላፊ ሃሺሞቶ ሴይኮ ጋር በመምከር የልምድ ልውውጥ ማድረጓ ተገልጿል፡፡

ለረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የተሰጠው ይህ እውቅናና ሽልማት እኤአ ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሃገር ዜጎች በጃፓን መንግስት የሚሰጥ አንጋፋ የክብር ሽልማት መሆኑን በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።

ይህ ሽልማት የውጭ ሀገር ዜጎች በጃፓን እና በሌሎች ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማሳደግ ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሚሰጥ ሲሆን፤ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉም ይህን ከፍተኛ የክብር ሽልማት በማገኝት የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሆናለች።

አንጋፋው ደራሲ፣ ገጣሚ፣ ሀያሲ፣ ተዋናይ፣ ዳይሬክተር... ጋሽ ስዩም ተፈራ በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እና ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት በጋራ በመሆን በተዘጋጀው መድረክ ላይ የጥበብ አፍቃርያን ፣ አንጋፋ አርቲስቶች በተገኙበት የምስጋና መድረክ ዛሬ ጥቅምት 24/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ የባህል አምባሳደር ዮድ አቢሲኒያ ባህላዊ የምግብ አዳራሽ የምስጋና አዋርድና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተሸለሙትን ለአንጋፋ አርቲስቶች ያበረከቱት ኒሻን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶለታል።
በሀገራችን የትወና ሙያ የጎላ አሻራና ማህተም ያሳረፈ ታላቁ አርቲስት ጋሽ ስዩም ተፈራ በሀገራችን ኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ስራ
ዎች ለማሳደግ የተለያዩ የጥበብ ሰራዎች በመስራት አስተዋፅኦ ካደረጉ እውቅ አርቲስቶች አንዱና በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ሙያዎች 50 አመታትን ያገለገለና ለሀገራችን የኪነ-ጥበብ እድገት የታገለ የተመሰከረለት አርቲስት ነው።በዚህ የምስጋና መድረክም ጋሽ ስዩም የፃፋቸውን 3 መፅሓፎችን በይፋ አስመርቀዋል።
 
በፕሮግራሙም ጋሽ ስዩም ታምሞ በነበረበት ወቅት ድጋፍ ላደረገለት የኢትዮጵያ ህዝብና ግለሰቦች እንዲሁም የህክምና ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።
Saturday, 04 November 2023 00:00

አዲስ ዘመን ድሮ

ታሪክ ማንበብ  ያ ል ኖ ሩ በ ት ን ዘመን ያስኖራል››
ይባላል።ይህ ማለት እኛ ባልነበርንበት ዘመን የነበረውን ሁነት ይነግረናል ማለት ነው።አዲስ ዘመን ጋዜጣ የተለያዩ ዘመናት የየዕለት ሁነት ሰንዶ ያስቀመጠ የ82 ዓመታት ታሪክ ነው።ጋዜጣው በሰነዳቸው መረጃዎቹ ያልነበርንበትን ዘመን እንድንኖረው ያደርገናል።በዚያ ዘመን፤ የመንግስት አስተዳደር እና የማህበረሰቡ ሥነ ልቦና ምን ይመስል እንደነበር፣ ምን ነውር ምንስ አስገራሚ እንደሚሆን፣ በዘመኑ የነበሩ ህግና
ደንቦች፣ የኑሮ ሁኔታ እና የመሳሰሉትን ያሳየናል።በማስታወቂያዎች፤ በዘመኑ የነበረውን የገበያ፣ የቅጥር፣ የሚከለከሉና የሚፈቀዱ ነገሮችን ይጠቁመናል።በዜናዎች ደግሞ የዘመኑን ክስተቶች ያሳየናል።እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ እንበል።በዘመኑ ጋዜጣ ላይ ይወጡ የነበሩ ዘገባዎችን፣ ማስታወቂያዎችን፣ ወዘተ. ዛሬ ላይ ሆነን ስናነባቸውና ስንመለከታቸው ‹‹አሁን ይሄ ዜና ይሆን ነበር? ጋዜጣ ላይ መውጣት ነበረበት?›› የሚያሰኙ ነገሮችን እናገኛለን።ይህ ሲያጋጥመን ልብ ማለት ያለብን የዘመኑን ባህሪ ነው።ያኔ እንደዛሬው የማህበራዊ መገናኛ አውታሮች እንዲሁም ተፎካካሪ ጋዜጦችና መጽሔቶች አልነበሩም፡፡

እናም ከአፋልጉኝ ማስታወቂያ ጀምሮ የጠጅ ቤት እና የአረቄ ቤት ወሬዎች ሳይቀር በጋዜጣው ላይ ልናገኝ እንችላለን።ምክንያቱም በወቅቱ አስገራሚ ከነበሩ ከዚህ ጋዜጣ ውጭ ሌላ መታያ አማራጭ አልነበራቸውም። ለዛሬው በጥቅምት ወር በጋዜጣው ላይ የወጡትን
እናያለን ።ፋንቱ ያለሰፈሯ ሌሊት ስትዞር ተይዛ ታሰረች ጥቅምት 7 ቀን 1963 ዓ.ምወይዘሮ ፋንቱ ወንደማርያም የተባለች በንፋስ ስልክ አካባቢ የምትኖር ሴት ያለሰፈሯ ከሌሊቱ በ10 ሰዓት በየካቲት 12 አደባባይ ስትዘዋወር በመገኘቷ ተይዛ የሶስተኛ ወረዳ ፍርድ ቤት የአንድ ወር እስራት የቀጣት መሆኑን አስታውቋል።

ስትዘዋወር መገኘቷንና ተላላፊ መኪናዎችንም አድርሱኝ በማለት ማስቸገሯን ፖሊሶች
መመስከራቸውን አስታውቋል።ተከሳሿም ፍርድ ቤት ቀርባ በተጠየቀች ጊዜ በአድራጎቷ ጥፋተኛ መሆኗን ስላመነች ፍርዱ ተሻሽሎላት በ30 ብር መቀጫ ወይም በአንድ ወር እስራት እንድትቀጣ ተደርጎ መቀጫውን መክፈል ስላልቻለች አንድ ወር እንድትታሰር ወደ ወህኒ ወርዳለች ሲል ከአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘ ዜና ያስረዳል።ማስታወቂያጥቅምት 8 ቀን 1934 ዓ.ምበተፈሪ መኮንን ትምህርትቤት ገብተው
ለመማርለሚፈልጉ ልጆች ሁሉተማሪ ቤት ከመግባታቸው በፊት ጤናቸውን መመርመር ፈንጣጣ መከተብና ማናቸውንም የተማሪ ቤቱን ደንብፈጽመው በተማሪ ቤቱመዝገብ እንዲጻፉ የሚያስፈልጋቸውስለሆነ ይህንኑ ለመፈጸምከሚመጣው ማክሰኞ ጥቅምት11
ቀን ጀምሮ እስከጥቅምት 18 ቀንድረስ ጧት ከ3ሰዓት እስከ 7 ሰዓትእንዲሁም ከ9 ሰዓትእስከ 11 ሰዓትከተፈሪ መኮንን ተማሪቤት ድረስ እንዲሰበሰቡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግስት የትምህርትና የጥበብሚኒስቴር ያስታውቃል፡፡

የእስረኞች ሱቅ የሰረቀው በእስራት ተቀጣ ጥቅምት 10 ቀን 1972 ዓ.ምየግቢ አውራጃ ወህኒቤት ባልደረባ የነበረውተሾመ አያና የወህኒቤቱ የህግ እስረኞችዕቃ የሚሸጡበት ሱቅውስጥ ሌሊት ገብቶከሁለት ሺ 232 ብርበላይ መስረቁ ስለተረጋገጠበትበሰባት ዓመት ጽኑእስራት እንዲቀጣ የአውራጃውፍርድ
ቤት ባለፈውሳምንት ውስጥ በዋለው ችሎት በይኖበታል።በተያያዘም በጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር የጎፋ አውራጃ የርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ
ኮሚሽን ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ባልደረባ የሆነው አሰግድ አስፋው በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ዘላቂ መፍትሔ ማካሄጃ እንዲውል በኃላፊነት ከተሰጠው ገንዘብ ውስጥ ሶስት ሺ 147 ብር ከ45 ሳንቲም አጉድሎ ለግል ጥቅሙ አውሏል በመባል ተከሶ አድራጎቱ በማስረጃ ስለተረጋገጠበት ሰሞኑን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የጎፋ አውራጃ ፍርድ ቤት ወስኖበታል።
ሊሰርቅ የሄደው ሌባ ጠጅ አስክሮት ተያዘ ጥቅምት 10 ቀን 1959 ዓ.ምአባዲ ተስፋዬ መስከረም10 ቀን 1959 ዓ.ም ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ላይ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ የአቶ ካህሳይን ቤት ለመስረቅ ሄዶ ከዚያም ሲደርሱ በሩ ስለተዘጋባቸው በዕድሜና በሰውነት ያነሰው አባዲ በአጥር ተንጠልጥሎ ገባ።

አባዲ የቤቱን በር ከፍቶ እንደገባ እያማረጠ ለመስረቅ ጥሩ ጊዜ ሆነለት።በዚህ ሁኔታ የተሰረቀውን ዕቃ እያማረጠ እያጋዘ በማመላለስ እውጭ ካስቀመጠ በኋላ ጠጅ ጠጅ ሸተተው።ወደኋላው መለስ ቢል ጠጅ የሞላው በርሜል አየ።ጎንበስ ቢል የውሃ መቅጃ ቆርቆሮ አገኘ።ከዚህ በኋላ ምን ይጠየቃል ራሱን በራሱ ጋባዥ ሆነ።ከዚያ በኋላ ስካር ተጫጭኖት ስለተሸነፈ አባዲ ከወደቀበት ሥፍራ ሳይነሳ በዚያው ተኝቶ አደረ፡፡በማግስቱ ጠዋት ባለቤቶቹ ከእንቅልፋቸው ተነስተው ቤት ሊጠርጉ ሲሉ አባዲ ተጋድሞ አገኙት።ወዲያው በፖሊስ አስያዙት።ከዚያም ወደ ማረፊያ ቤት ተወስዶ በወታደር ደስታ በቃኸኝ አማካኝነት ቃሉን ሲሰጥ ‹‹ለመስረቅ
ሔጄ ጠጅ አስክሮኝ በዚያው ተኛሁ›› ሲል አረጋግጧል ብለው ሻለቃ ጌራ ወርቅ ገልጠዋል።
በትግሬ ግዛት የኢትዮጵያ የወሬ ምንጭ

ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም

በዛሬዋ_ዕለት

ከ 93 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ዋዜማ ፤ የታላቁ ንጉሠ ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለበዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ የተመረቀበት ዕለት ነበር።

የዳግማዊ አጤ ምኒልክ መታሰቢያ ሀውልት የቆመው/የተተከለው ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም ነበር፡፡

ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ የአባታቸውን የዳግማዊ አጤ ምኒልክን ስራና ውለታ ቀጣዩ ትውልድ ያስበውና ይዘክረው ዘንድ … ማስታወሻ የሚሆን የመታሰቢያ ሐውልት ለማሰራት አሰቡ፡፡

ሐውልቱንም በጀርመናዊው መሃንዲስ ሙሴ ሄንትል አማካኝነት አስጠንተው፤ ከጀርመን ተቀርፆ እንዲመጣ አዘዙ፡፡ ሀውልቱ የተመደበለት ቦታ ተደልድሎ ከተዘጋጀ በኋላ ገና ሳይተከል/ሳይቆም ንግሥቲቱ መጋቢት 22 ቀን 1922 ዓ.ም አረፉ፡፡

በመሆኑም የንግሥቲቱን እረፍት ተከትሎ ንጉሰ ነገሥት ለመሆን እየተዘጋጁ የነበሩት አልጋ ወራሽ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን፣ ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት (ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም) ሐውልቱ በታላቅ ክብረ በዓል እንዲተከል አደረጉ፡፡

በሐውልቱ ላይ አፄ ምኒልክ ካባ እንደለበሱ አንባር አጥልቀው በእጃቸው ጣምራ ጦር ይዘው በፈረሳቸው በ‹አባ ዳኘው› ላይ ተቀምጠው በግርማ ሞገስ ይታያሉ፡፡ የሐውልቱ ቁመት ከተፈጥሮ አካላዊ መጠን በላይ ሲሆን ‹አባ ዳኘው› ፊቱን ወደ ሰሜን መልሶ በኋላ እግሮቹ ቆሞ፣ የፊት እግሮቹን ወደላይ አንስቶ ይታያል፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በ 1929 ዓ.ም ወድቆ/ፈርሶ ነበር፡፡

የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት


ብርሃኑ ድንቄ የ 5ቱን የመከራ ዓመታት አጭር ታሪክ በሚለው መጽሐፋቸው ጣሊያኖች የአፄ ምኒልክን ሐውልት እንዴት እንዳፈረሱት እንደሚከተለው ገልፀውታል፡፡ …በቅድሚያ ሐውልቱ ያለበትን አካባቢ ረጅም እንጨት እየማገሩ በቆርቆሮ ሲያጥሩ ሰነበቱ….ይህንን ያየው የአዲስ አበባ ሕዝብ ሊያፈርሱት ነው ብሎ እርስ በእርሱ በሐዘን መነጋገሩን ቢሰሙ ‹‹ልናድስ›› ነው ብለው አስወሩ፡፡ ሁሉንም ነገር ካመቻቹ በኋላ ግን በየበሩ በታንክ ጭምር ጥበቃ አጠናክረው… ወደ ማታ የአራዳን አካባቢ በታንክ አጥረው በባውዛ ሌሊቱን ከተማውን እየተቆጣጠሩ በሌላ ኃይል ደግሞ ሐውልቱን ሲያፈርሱ አድረው ሲነጋጋ ወደ አልታወቀ ቦታ ወስደው ቀበሩት፡፡ ሕዝቡ እድሜና ፆታ ሳያግደው ሐዘኑን ይገልጽ እንደነበር አዛውንቶች ይመሰክራሉ።

በጊዜው የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበረው የሃንጋሪው ዶክተር ላዲ ስላስ ላቫ እንደፃፈው፣ ሐውልቱ ከፈረሰበት ቦታ ቆመው ያለቅሱ የነበሩትን ሰዎች የጣሊያን ወታደሮች በኃይል ይበትኑ እንደነበር ገልጿል፡፡

በሌላ ዘገባ ደግሞ አንድ ሕፃን ልጅ ሲያለቅስ ጣሊያኖች ደርሰው ለምን እንደሚያለቅስ ቢጠይቁት ‹‹የንጉሱን ምልክት ስላወረዳችሁ ነው›› ብሎ እንደመለሰላቸውና ጣሊያኖችም ከሙሶሊኒ ሌላ ንጉሥ እንደሌለው በመንገር ልጁን ገርፈው እንዳባረሩት ተገልጿል፡፡ ጣሊያኖች ሐውልቱን ካፈረሱ በኋላ ሰው ሳያይ ሸፍነው በመውሰድ በታላቁ ቤተ-መንግሥት አዳራሽ ጀርባ ቀበሩት…

የወራሪው ኃይል ከኢትዮጵያ ከተባረረ በኋላም ሐውልቱ ከተቀበረበት ቦታ ወጥቶ እንደገና ታድሶና ተጠግኖ ሚያዝያ 27/ 1934 ዓ.ም ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንዲቆም ተደረገ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ በ 1988 ዓ.ም የአድዋ ድል መቶኛ ዓመት ሲከበር ሐውልቱ ጥገና ተደርጎለት እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ታሪክን_ወደኋላ

????የእንጆሪ የጤና ጥቅሞች | Health Benefits Of Strawberries
????????????
????????የደም ግፊታችንን ያመጣጥናል፡፡
????????የቅድመ-ወሊድ ጤናን ይጨምራል፡፡
????????በሽታ የመከላከል ሥርዓትን ወይም አቅምን ይጨምራል፡፡
????????የአይናችንን ጤና ያሻሽላል፡፡
????????መጥፎ ኮሌስትሮልን ይዋጋል፡፡
????????ፀረ-ኢንፍላሜሽን ነው ወይም ኢንፍላሜሽንን ይካላከላል።
???????? ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪ አለው ወይም ባክቴሪያን ይከላከላል።
???????? ፀረ-ካንሰር ባህሪ አለው ወይም ካንሰርን ይከላከላል።
???????? ፀረ-ቫይረስ ባህሪ አለው ወይም ቫይረስን ይከላከላል።
???????? ፀረ-እርጅና ባህሪ አለው ወይም እርጅናን ይከላከላል።

Page 8 of 678