Administrator

Administrator

  • የብልሹ አሠራርና ሙስናን ችግር በዐደባባይ የተናገሩ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ናቸው
  • ፓትርያርኩ ጽኑ አቋም ስለሌላቸው ለጣልቃ ገብነት የተመቹ ኾነዋል
  • ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር ይጠበቅባቸዋል
  • ፓትርያርኩ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው
  • ብቃት ያለው የአማካሪ መዋቅር  ያስፈልጋቸዋል

የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ፤ ለስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ከቀረቡት አምስት ዕጩዎች መካከል በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ በከፍተኛ ድምፅ መመረጣቸው ተነገረ። ሊቀ ጳጳሱ በቤተ ክርስቲያኒቱ የፓትርያርኮች ምርጫ ታሪክ ከፍተኛውን የመራጮች ድምፅ በማግኘት አሸናፊ መኾናቸው በተገለጸበት ወቅት የብዙዎችን ትኩረት በሳበ ኹኔታ በመስቀላቸው ሲያማትቡ ታዩ።
የወቅቱን ስሜታቸውን አስመልክቶ ‹‹ዜና ቤተ ክርስቲያን›› በተሰኘው መጽሔት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ÷ ‹‹ፓትርያርክ እኾናለሁ የሚል መንፈስ በውስጤ ስላልነበረ ውጤቱ ሲገለጽ እንዴት ነው ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ምንድን ነው ከሚል ደነገጥኩኝ፤ በዚያው ቅጽበት የተሰማኝ፣ እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› የሚል እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ከምርጫው ሦስት ቀናት በኋላ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው ሥርዐተ ሢመት÷ ለፓትርያርክነት መመረጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪ እንደኾነና ጥሪውን የተቀበሉት መኾኑን፣ መቀበላቸውም ለክብርና ለልዕልና ሳይኾን ለመሥዋዕት በመታዘዝ በመኾኑ የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት በመያዝ በጋራ እንደሚወጡት ያላቸውን እምነት ተናግረው ነበር፡፡
ፓትርያርኩ በዚያ ንግግራቸው ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በራሱ መተማመን አለበት›› ሲሉ በአጽንዖት የተናገሩ ሲኾን እንደ አንድ ልብ አሳቢ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾኖ በሥምረት ከሠራ፣ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱ ሊሠሩ ይገባል በሚል ካሳወቋቸው ተግባራት መካከልም ቤተ ክርስቲያኒቱ ፍትሕ ርትዕ እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ የእውነትና የሐቅ መገኛ እንድትኾን በመንፈሳዊነት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት የተደገፈ መጠነ ሰፊ የሥራ እንቅስቃሴ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ‹‹እምነትና ሐቅ በቤተ ክርስቲያን ካልተገኙ ከየት ይገኛሉ?›› ሲሉ የጠየቁት ፓትርያርኩ፤ ካህናትና ቤተ ክርስቲያኒቱን በሞያቸውና በልግሥናቸው አቅፈው ደግፈው የያዙ ምእመናንም የድርሻቸውን ለመወጣት ብርቱ ጥረት ማድረግ አለባቸው ማለታቸውም ይታወሳል፡፡
ከፕትርክና ሢመቱም በኋላ ለብዙኃን መገናኛዎች በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች÷ ሰው ሊመሰገንም ሊሾምም፣ ሊሻርም፣ ሊወቀስም የሚገባው በጠባዩ፣ በግብረ ገብነቱ፣ በትምህርቱ ብቻ እየተመዘነ እንጂ በዘሩ አንወደውም አንጠላውም በማለት በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ ሥር የሰደደ የመጠቃቀሚያ መንገድ ነው የሚባለውን በጎሰኝነት መሳሳብን ተቃውመዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቷ ታላቅ መኾኗንና ለታላቅነቷ የሚመጥኑ ሰዎች መገኘት እንዳለባቸው በአጽንዖት የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ‹‹የተሟላና የተቃና ሥራ ለመሥራት ከኹሉ አስቀድሞ ብቃትና ጥራት ያለው ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚኽ ደግሞ ሰው በሰው ላይ መደራረብ ሳይኾን ትምህርትና ችሎታ ያለው፣ ለተመደበበት የሥራ ደረጃ የሚመጥን ሰው መቀመጥ አለበት፤›› ብለዋል፡፡
የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ከላይ እስከ ታች ተስተካክሎ የመልካም ሥራ አብነት ይኾን ዘንድ ‹‹ሙስና ይጥፋ፤ ተጠያቂነትና ሐቀኝነት ይስፋፋ›› የሚለውን ዐዋጅ ደጋግመው በማሰማት እየታወቁ የመጡት ፓትርያርኩ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ለመጠበቅና ክብርዋን ለመመለስ ሊወስዳቸው ይገባል ያሏቸውን የለውጥ ርምጃዎች በመዘርዝር በምልዓተ ጉባኤው አጀንዳነት አስይዘው ለማስወሰን አስችለዋል፡፡
ፓትርያርኩ ሥር ነቀል ለውጥን የሚያመጡና ቆራጥ አቋምን የሚሹ ናቸው ያሏቸው እኒህ ርምጃዎች÷ ብልሹ አሠራር በፀረ-ሙስና እንቅስቃሴ የሚታረምበትና የሚወገድበት፣ የአስተዳደር መዋቅሩና የሚሠራባቸው ደንቦች ሕጎች፣ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖረው ተደርጎ የሚሻሻልበት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ራእይና ተልእኮ በግልጽ የሚታይበት ስትራተጅያዊ የአመራር ሥርዐት የሚነደፍበት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ላለው የገንዘብ አያያዝ አንድ ወጥ የኾነ ሥርዐት የሚዘረጋበት እንደኾነ አመልክተዋል፡፡
አቡነ ማትያስ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው ያሉት የአሠራር ብልሽት ሳይታረም ቢቀጥል ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሚገጥማት አስከፊ ችግር ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከተወቃሾች ተርታ በመቁጠር ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚታደግና ችግሮቿን የሚቀርፍ አጀንዳ በመያዝ ‹‹በእግዚአብሔር፣ በታሪክና በመጪው ትውልድ ፊት›› የሚመዘን፣ ችግር ፈቺ ውሳኔ እንዲወሰን የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት አነሣስተዋል፡፡
ፓትርያርኩ ከሹመታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርእሰ መንበርነት የመሩትና በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. የተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በይፋ ባስታወቁት በዚህ መግለጫቸው ላይ በመወያየት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሥራዎቿን በመሪ ዕቅድ በመምራት፣ ሙስናንና የመልካም አስተዳደር ዕጦትን ከሥሩ ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት የሚያቀርብ ከሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎችና ከምሁራን ምእመናን የተውጣጣ ዐቢይ ኮሚቴ ሠይሟል፡፡
ይኸው የቅ/ሲኖዶሱ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት የሁሉም አህጉረ ስብከት ማእከልና የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ በኾነው በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ ሀ/ስብከቱም በመዋቅርና አደረጃጀት፣ በሰው ሀብት አስተዳደር፣ በሒሳብ አሠራርና ቁጥጥር የሚታይበትን የገዘፈና የተመሰቃቀለ ችግሩን ለመፍታት የባለሞያ ቡድን አቋቁሞ በፍጥነት ወደ ተግባር ገብቷል፡፡
በመንበረ ፓትርያርክም በአዲስ አበባ ደረጃም የተቋቋሙት ሁለቱም አካላት የጥናት ውጤታቸውን በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ለተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርበው በማስገምገም የወሳኝ አካሉን ይኹንታ ከማግኘታቸውም በላይ ቀጣይ የአፈጻጸም አቅጣጫ ተሰጥቷቸዋል፤ የመሪ ዕቅድ ማህቀፉን ያስገመገመው ዐቢይ ኮሚቴ በቀጣይ ዕቅዱን በሥራ መተርጎም በሚያስችል ኹኔታ በዝርዝር አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ መመሪያም ተሰጥቶታል፡፡
የአዲስ አበባውን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ የሠራው የባለሞያ ቡድንም ጥናቱን ወደ ታች አውርዶ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በውይይት ካዳበረ በኋላ፣ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብና በቋሚ ሲኖዶሱ እንዲጸድቅ በምልዓተ ጉባኤው በተሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት ተግባሩን አከናውኖ የብዙኃን ካህናትና ምእመናን ተቀባይነት ያረጋገጠውን የጥናት ሰነድ በሀ/ስብከቱ አማካይነት ለቅ/ሲኖዶሱ አስረክቧል፡፡
ከነገ በስቲያ ሰኞ፣ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚከበረው አንደኛ ዓመት የበዓለ ሢመት ዋዜማቸው ላይ የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የተናገሯቸውንና ተጠንቶ የቀረበላቸውን በተግባር ለመተርጎም የሚንቀሳቀሱበት እንደሚኾን አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሓላፊዎች፣ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ተስፋቸውን ገልፀዋል።
ቤተ ክህነቱ ያለበትን መሠረታዊ ተልእኮውን የማያገለግል የተንዛዛ ቢሮክራሲ፣ ወገንተኝነትና ሙስና በፓትርያርክ ደረጃ አምነውና ተቀብለው በዐደባባይ ገልጠው ለመናገር አቡነ ማትያስ የመጀመሪያው እንደኾኑ የሚናገሩት አንድ አገልጋይ፤ የፓትርያርኩ መግለጫዎች በየአጥቢያቸው ችግሩን የሚጋፈጡ ወገኖችን በልዩ ልዩ መንገድ እንዳነሣሣ ይህም ቢያንስ ብልሹ አሠራሩን ለሕገ ወጥ ጥቅም ያዋሉ አማሳኞችን እንዳሸማቀቀ ይገልጻሉ፡፡
ለዓመታት የተከማቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘርፈ ብዙ ችግር በአንድ ዓመት ተጠንቶ ሊታወቅ ይችል እንደኾነ እንጂ መፍትሔ ያገኛል ተብሎ እንደማይጠበቅ የጠቀሱት አገልጋዩ፤ አንድ ዓመት የፓትርያርኩን ስኬት ለመገምገም በቂ አይደለም ይላሉ፡፡ ፓትርያርኩ በጵጵስና ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ በውጭ የነበሩ እንደመኾናቸው ቤተ ክህነቱን የመምራት ልምድ ሊያንሳቸው እንደሚችል ጠቁመው ይህን ክፍተት የሚጠቀሙ ከቀድሞም የነበሩና ዛሬም ያልታጠፉ የጥፋት እጆችን ተጽዕኖ በፓትርያርኩ ዙሪያ እንደሚያስተውሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ፓትርያርኩ የሚያስጠጓቸውን አማካሪዎች ማንነት በጥንቃቄ መለየት እንደሚኖርባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስለ ፓትርያርኩ የአንድ ዓመት ጉዞ የተጠየቁትና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ፣ ፓትርያርኩ ከተሾሙበት ዕለት አንሥቶ ያስተጋቧቸውን የተቋማዊ ለውጥ ዕሴቶችና መርሖዎች ተግባራዊ ለማድረግ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው የሚለውን አስተያየት ይጋራሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለው ኹኔታም ብቃት ያላቸውን እውነተኛ ባለሞያዎች ከፓትርያርኩ የሚያሸሽ እንጂ የሚያቀርብ አይደለም ብለዋል፡፡
የአስተዳደራዊ መዋቅር ማሻሻያ ሒደት የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የሚናገሩት የሥራ ሓላፊው፣ የአመራር ብቃትና ብስለት ተግዳሮቶቹን ለበጎ ለውጦ በመጠቀም እንደሚረጋገጥ ያስረዳሉ፡፡ ፓትርያርኩ ሥር ነቀልና ቆራጥ ተግባራዊ ርምጃ እወስዳለኹ ብለው በጀመሩት እንቅስቃሴ ተቃውሞ ሲገጥማቸው፣ ተቃውሞውን የማዳመጥ አባታዊ ሓላፊነት ቢኖርባቸውም ዋናውን የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ ሳይቀር እስከማመቻመች መድረሳቸው የፀረ ሙስና አቋማቸው ከሚዲያ ፍጆታና ከንግግር ያላለፈ፣ የሚናገሩትንም ያህል ጠንካራና ጽኑ አቋም የሚይዙና ውሳኔ ሰጭ ናቸው ብለው እንዳያምኑ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል፡፡ ይህም በውጤቱ የለውጥ ተቃዋሚዎቹን በማፈርጠምና የለውጥ ተስፋውን በማመንመን ሒደቱን አደጋ ውስጥ ሊከተውና የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር የበለጠ ሊያወሳስበው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
ለፓትርያርኩ የአቋም ጽናት፣የሊቃነ ጳጳሳቱ የአቋም አንድነት አስፈላጊ ነው የሚሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ፤ ከምንጊዜውም በላይ በቤተ ክህነቱ ላይ ተባብሶ የሚታየውን የተቋማዊ ለውጡን ሒደት የሚያደናቀፉ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡
ፓትርያርኩ በተመረጡበት ቀን “እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ›› ማለታቸው በርግጥም የሚገባ ነው ያሉት እኚሁ አስተያየት ሰጪ፤ ታላቋንና ጥንታዊቷን ቤተ ክርስትያን በአባትነት ለመምራት ተግዳሮቱ የበዛ ቢሆንም ወደ ዕድገትና ሥልጣኔ የሚያደርሰው ጎዳና በአቡነ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና መጠረግና መደልደል ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

              ዓለም በሁለት ተከፍላ በነበረ ዘመን ማለትም በካፒታሊስትና በሶሻሊስት ጐራ፤ ይወራ የነበረ አንድ ውጋውግ (witticism) አለ፡፡
ድሮ አንድ ጊዜ በፖላንድ አገር ከፍተኛ የሥጋ ዕጥረት ተፈጠረ፡፡ ህዝቡ አማረረ፡፡ ጋዜጦች፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ወሬው የሥጋ ዕጥረት ነገር ሆነ (ያው እንደኛው አገር)፡፡ ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደልማዳቸው ሰፋፊ ዘገባ ይሰጡበት ጀመር፡፡ (ያው በእኛ ላይ እንደሚያደርጉት)
ይህን የተገነዘበ አንድ ኩባንያ “ዓለም-አቀፍ የጥያቄና መልስ ውድድር” አዘጋጅቶ “በጣም ከባድ ከባድ ሽልማት ስለምሰጥ የቻለ ይወዳደር”፤ ብሎ አዋጅ አወጣ፡፡
በአዕምሮአችን እንተማመናለን ያሉ አዋቂዎች በሺዎች ተመዘገቡ፡፡ የማጣሪያ ውድድሮች ተካሄዱ፡፡ ጉዳዩ ስለ ፖላንድ የኢኮኖሚ ችግር ነው፡፡ ለመጨረሻ ፍልሚያ የደረሱት ፋይናሊስቶች ሶስት ናቸው፡፡ የአሜሪካ፣ የህንድና የሩሲያ ተፎካካሪዎች፡፡
ለመጀመሪያው ተረኛ የቀረበለት ጥያቄ
“Why is there a shortage of meat in Poland?” የሚል ነው፡፡ “በፖላንድ የሥጋ ዕጥረት ለምን መጣ?” ነው፡፡
በመጀመሪያ የአሜሪካዊው ተራ ነበረ፡፡ እሱም፤ አሰበ አሰበና፣ “What is Shortage?” አለ፡፡ ዕጥረት ማለት ምን ማለት ነው? (እንግዲህ “ዕጥረት” ማለት ቃሉም እራሱ በእኔ አገር አይታወቅም ማለቱ ነው፡፡)
ሁለተኛው የህንዱ ተራ ሆነ፡፡ ሌላ ጥያቄ ይጠይቁኛል ብሎ ሲጠብቅ ያው ጥያቄ ቀረበለት
“why is there a shortage of meat in poland” “በፖላንድ የሥጋ ዕጥረት ለምን መጣ? ህዳንዊውም፤ ትንሽ አሰበና፤ “what is meat?”
“ሥጋ ማለት ምን ማለት ነው?” አለ፡፡ (በህንድ አገር ሥጋ ከማይበሉት ወገን ነው ማለት ነው ህንዱ)
በመጨረሻ፤ ተራው የሩሲያዊው ሆነ፡፡ እሱም ሌላ ጥያቄ ይጠይቁኛል ብሎ ሲጠብቅ፤
“why is there a shortage of meat in Poland?” ሆነ ጥያቄው፡፡ “በፖላንድ ለምን የሥጋ ዕጥረት መጣ?”
ሩሲያዊውም አስቦ አስቦ፤ አስራሚ ጥያቄ አመጣ፡-
What is “why?” ሲል ጠየቀ፡፡
“ለምን?” ብሎ ጥያቄ ራሱ፤ ምን ማለት ነው ማለቱ ነው! (ያኔ በሩሲያ “ለምን?” ብሎ መጠየቅ የማይሞከር ነገር ነው፡፡)
*             *                    *
“ለምን?” ብሎ የማይጠይቅ ህብረተሰብ ተስፋ የለውም፡፡ “ለምን?” ተብሎ መጠየቅን የማይፈልግ መንግስትም ተስፋ የለውም፡፡ ሌሎች ብዙ ተጨማሪ ነገሮች ቢኖሩበትም የሩሲያ መንግስት መንኮታኮት ዕጣ-ፈንታው የሆነበት ምክንያት “ለምን?” መባል አለመፈለጉ፤ ኢ-ዲሞክራሲያዊነቱ፣ ሀሳባችሁን አትግለፁ ማለቱ፣ ህዝቡ ቃሉ እስኪጠፋው ድረስ “ለምን?” በማለት መገደቡ ነው፡፡ ለምን ብለን እንጠይቅ፡፡
ነዳጅ ይጠፋል! ለምን? መብራት ይጠፋል! ለምን?፤ ስልክ ይሰወራል! ለምን?፤ ውሃ ይደርቃል! ለምን … የባንክ ሲስተም የለም ይባላል-ለምን? ብዙ ለምኖች አሉ፡፡ ግን ጠያቂ የለም ተጠያቂም የለምም፡፡ ለምን? ለምን ብዙ? ነው፡፡... የሚታሸጉ ቤቶች አሉ፡፡ አንዳንድ ቤቶችን እየዘለሉ ይታሸጋሉ፡፡ ዝላዩ ለምን መጣ?... ዛሬ ለምን ብሎ መጠየቅ ያልቻለው ህዝብ ለምኖቹን ማጠራቀሙ አይቀርም፡፡ ከለምን ወደ ለምንም አልመለስም እንዳይሸጋር ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ እኛ ትልቅ ነገር እየሰራን ሊሆን ይችላል፡፡ ወደ ትላልቆቹ ተግባሮች የሚመጡትን ቀጫጭን ቧንቧዎች ቆሻሻ ከዘጋቸው ትልቁ ቧንቧ የት ይደርሳል?
በሀገራችን እንደሰንሰለታሙ ተራራ፤ ሰንሰለታማ ሙስና መኖሩን እየሰማን ነው (network of corruption መሆኑ ነው) እንደዋዛ የሚዘረጋ አይደለም-በአገራዊ መስክ ስናስበው፡፡ ይህ አይነኬ (insulated) ሰዎች መኖራቸውን ነው የሚናገረው:: ወይም ብረት-ለበስ ናቸው ማለት ነው:: ጥይት-ከላ (Bullet-proof) አካል የታደሉ፡፡ አንድ የፖለቲካ አቋሙን የቀየረ ፖለቲከኛን አንድ አድናቂው፤ “ብርሃኑን በማየትህ ተደስቻለሁ” አለው “አዬ ወዳጄ እኔ ብርሃኑን አላየሁም ይልቅስ ቃጠሎው፣ ቃጠሎው ነው የባሰብኝ!” አለ ይባላል፡፡ በሙስና ረገድ ቃጠሎው ገና የመጣ አይመስልም፡፡ በፓርቲ ቃጠሎ ገና ይፋ ያልሆነ ተቃጣይ ብዙ አለ፡፡ ሙስና የማያደርሰን ቦታ የለም! የናይጄሪያን ሙስና ጉድ ጉድ ስንል እኛው ሃዲድ እየሰራን ነው! “ጮሃ የማታውቅ ወፍ እለፉ እለፉ ትላለች!” ሆኗል! ኧረ ለምን እንበል!
ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የዓለም-አቀፍ ቀኖች ማክበር ወደ ፋሽንነት እየተቀየረ ይመስላል፡፡ የግሎባላይዜሽኑ በዓላዊ ገፅታ ካልሆነ በስተቀር ነው እንግዲህ፡፡ ቢቀናን “የጉዳይ-አስፈፃሚዎች ቀን” ብናከብር ለእኛ አግባብነት ሳይኖረው አይቀርም፡፡ ጉደኛ አገር ሆነናል እኮ፡፡ “ምን ትሰራለህ?” ሲባል ጉዳይ አስፈጽማለሁ ይላል አንድ ባለሙያ፡፡ የተማርከውስ አካውንቲንግ፣ ምህንድስና፣ ታሪክ፣ ማኔጅመንት ወዘተ ሲባል፤ “እሱን እንኳ በትርፍ ጊዜዬ እሰራዋለሁ” ይላል፡፡ ኢትዮጵያ ግን ይሄን ያህል የተማረ ዜጋ አለኝ ብላ ለዓለም ባንክ አስመዝግባለች፡፡ እሷም በትርፍ ጊዜዋ ካልሆነ!! ሰሞኑን “የአፍ መፍቻ ቀን” ተከብሯል፡፡ ለብዙ ዓመት የኢንፎርሜሽን ቀንም አክብረናል፡፡ ብዙ የነፃነት ቀኖችንም አክብረናል፡፡ የጀግንነት ቀናት ብዙ አሉን፡፡ የአድዋ ዋዜማ፣ የህውሃት ምስረታ ቀን አለ (የካቲት 11 እና የካቲት 23፤ የከተማ ልጆች ከአድዋ ወደ አድዋ እንዲሉ) ብዙ የፆም ቀኖችንም እናከብራለን፡፡  ዓለም-አቀፍ የጾም መያዣ ቀን ቢኖር ይገላግለን ይሆን? የኤች አይ ቪ ዓለም-አቀፍ ቀን አለ፡፡ የፍትህ ቀን አለ፡፡  የ ---- ቀን፣ የ ---- ቀን፣ የ----ቀን ብዙ ቀን አለን፡፡ (ተስፋዬ ካሳ የተባለው ኮሜዲያን .. “ኧረ ማታውን እንኳን ልቀቁልን” ብሎ ቀልዶ ነበር) እንደቀኖቹ ምክንያትና ብዛት .. ምነው ብዙ ደስታ በኖረን፣ ምነው ብዙ ተግባር በኖረን … ምነው ብዙ ፍቅር በኖረን! ግን የለንም፡፡ አንዳንዴ እንደኛ በኢኮኖሚ የደቀቁ አገሮች ቀኖቹን በውል ለማጣጣም ይችሉ ይሆን ያሰኛል? በባዶ ሆድ የእገሌ ቀን፣ የእንትን በዓል .. ምን ስሜት ይሰጣል? የሚል ብርቱ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ይሄንንም ለምን? ብለን እንጠይቅ፡፡ ትላንትም ዛሬም ምንም ዓይነት ስም እንስጣቸው፤
ሁኔታዎች በከፉ ቁጥር ትኩረት ሳንሰጣቸው ይገዝፉና አልነቃነቅ የሚሉ ይሆናሉ፡፡ ግምገማም፤ አዋጅም፣ ማስፈራራትም፣ ማፈራራትም፣ ካገር ማስወጣትም የማይበግራቸው ደረጃ፤ አይቀሬው ነገር ወደድንም ጠላንም ፈጦ ይመጣል - “መገነዣው ክር ከተራሰ፣ መቃብሩ ከተማሰ “እንደሚለው ነው አበሻ! ከወዲሁ አመጣጡን፣ ከወዲሁ አወጣጡን፣ ከወዲሁ ክፋቱን፣ ከወዲሁ ዐይነ-ውሃውን ስናየው ውጤቱ፤ አንድ የምናውቀው ፊልም እየመሰለን መጥቷል - አጨራረሱ የሚታወቅ!
“አለ አንዳንድ ነገር፣
አለ አንዳንድ ነገር
በዚህ ቢሉት በዚያ፣ ከመሆን የማይቀር”… ብለው ነበር ከበደ ሚካኤል፡፡
“መላጣ አናት ላይ ጠብ ያለች ውሃ እስካፍንጫ ለመውረድ ምን ያግዳታል?!” የሚለው የወላይታ ተረት መንፈሱ ይሄው ነው! ከዚህ ይሰውረን ጎበዝ!         

        የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ለፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ከ17 ዓመት በታች የታዳጊ ውድድር ከሳምንት በኋላ ይጀምራል፡፡ የታዳጊዎችን ውድድርን በጥራት ለመምራት ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በውድድሩ ተሳታፊ በሚሆኑ ክለቦች ላይ አስፈላጊውን  የእድሜ ማጣራት በማከናወን ከሞላ ጎደል ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ  ለማወቅ ተችሏል፡፡ በውድድሩ ከ17 ዓመት በታች ቡድናቸውን የሚያሳትፉ የፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ለተጨዋቾቻቸው የተዘጋጀውን የእድሜ ማረጋገጫ ምርመራ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የህክምና ኮሚቴ የግምባር ፍተሻ እና በቴክኒክ ኮሚቴው ተጨማሪ ማረጋገጫ መሰረት አከናውነዋል፡፡  ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድሩ የካቲት 22 እንደሚጀመር የገለፀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ተሳታፊ ክለቦች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ያስተላለፈ ሲሆን ዘንድሮ ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች ብዛት 9 እንደሆኑና ውድድድራቸውን በደቡብ እና በማዕከላዊ ዞኖች በመከፋፈል እንደሚያደርጉ አስታውቋል፡፡ በማዕከላዊ ዞን  ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ኢትዮጵያ ቡና፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ደደቢት፤ መብራት ሃይልና ሙገር ሲምንቶ ሲመደቡ፤ በደቡብ ዞን ደግሞ አርባምንጭ ፤ ሲዳማ ቡና እና ሃዋሳ ከነማ ይገኛሉ፡፡
ከ17 ዓመት በታች ውድድሩ የተዘጋጀው በታዳጊዎች ላይ በመስራት የአገሪቱን እግር ኳስ እድገት በጠንካራ መሰረት ላይ ለመጣል ያስችላል ተብሎ ነው የእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ለውድድሩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ተተኪ ተጨዋቾችን ለብሄራዊ ቡድን ለማፍራት እንደሚንቀሳቀስ  ስፖርት አድማስ ያነጋገራቸው የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የውድድር ዋና ስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ተድላ ዳኛቸው ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ  የታዳጊዎችን ውድድር ለማካሄድ በፌደሬሽን በኩል እንቅስቃሴው ከተጀመረ ቢቆይም ተግባራዊነቱ አልተሳካም ነበር፡፡ በቀድሞ የፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚ የሴቶች እግር ኳስ  ቡድኖችን ከማቋቋም ባሻገር የፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች የታዳጊ ቡድኖች እንዲኖራቸውና ውድድር እንዲያካሂዱ ከስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ተድላ ዳኛቸው፤ አሁን ያለው አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴም በወጣቶች ላይ መስራት ለእግር ኳሱ እድገት ወሳኝ አቅጣጫ ነው በማለት የታዳጊዎች ውድድሩን ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኑን ይገልፃሉ፡፡
የእድሜ ማረጋገጫ ምርመራዎች
አንድ ክለብ የሀ 17 ቡድን ሲመሰርት ማሟላት ያለበት መስፈርቶች በእግር ኳስ ፌደሬሽኑ በኩል ተቀምጠዋል፡፡ የመጀመርያው የተጨዋቾች የእድሜ ገደብን ማሟላትና ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ክለቦች በዘመናዊ የህክምና ምርመራ በማከናወን በሚያቀርቡት ማስረጃ ብቻ ሳይሆን በፌዴሬሽኑ የህክምና ኮሚቴ በኩል በግምባር የተጨዋቾችን ተክለሰውነት በተለያዩ ዘዴዎች በመፈተሽ በሚካሄድ  ምርመራ  መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ አቶ ተድላ ዳኛቸው እንደሚያስረዱት ክለቦች በየትኛውም ዘመናዊ የህክምና ተቋም የኤምአርአይ ምርመራቸውን ካከናወኑ በኋላ የፌደሬሽኑ  የቴክኒክ እና የህክምና ኮሚቴዎችን ተጨማሪ ማረጋገጫ ማድረግ ነበረባቸው፡፡ እንደ አቶ ተድላ ዳኛቸው ገለፃ ከኤምአርአይ ምርመራው ሌላ ኮሚቴዎቹ  በተለያዩ መንገዶች የተጨዋቾችን እድሜ ለማጣራት የሰሩት አንዳንድ የማጭበርበር ሁኔታዎችን ለማስቀረትነው፡፡ በዚህም መሰረት የህክምና ኮሚቴው የእያንዳንዱን ክለብ ተጨዋቾች  ወደ ስታድዬም ጠርቶ በአጠቃላይ ተክለሰውነታቸውን ገምግሟል፡፡ ማንኛውም ተጨዋች በሁሉም  ምርመራዎች የእድሜው ትክክለኛነት ካላረጋገጠ መጫወት አይችልም፡፡ ከ17 ዓመት በታች በተዘጋጀው የታዳጊዎች ውድድር ላይ የሚሳተፉ ክለቦች በስብስባቸው የሚይዟቸው ተጨዋቾች እድሜያቸው 15 እና 16 ዓመት  መሆን ሲገባው ይህን የእድሜ ገደብ በሟሟላት እስከ 25 ተጨዋቾች ያስመዘግባሉ፡፡  ክለቦች ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት የያዟቸውን ተጨዋቾች እድሜ በሁሉም ምርመራዎች እንዲያረጋግጡ በቂ ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ እስከ የካቲት 15  የተሰጠው ቀነ ገደብ ዛሬ ያልቃል፡፡ ከዛሬ በፊት ብዙዎቹ ክለቦች የምርመራ ሂደቱን እንዳጠናቀቁ የሚናገሩት አቶ ተድላ፤ አንዳንድ ክለቦች ቢዘገዩም  በአስቸኳይ አስፈላጊውን መመርያ ተከትለው እንዲሰሩ በማበረታት ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት የማጣራት ሂደቱን እንዲጨርሱ ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡ በማዕከላዊ ዞን ካሉት ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ደደቢት፤ መከላከያ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሉንም መስፈርቶች በሟሟላት እና በማረጋገጥ  የውድድሩን መጀመር በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ አርባምንጭ ከነማ እና ሃዋሳ ከነማ ግን ትንሽ ቢዘገዩም በቀጣይ ሳምንት የምርመራውን ሂደት እንደሚጨርሱ ተስፋ ተደርጓል፡፡
የእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ከምንጊዜውም በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ያለውን የእድሜ ማጭበርበር ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም መያዙን የገለፁት የውድድር ዋና የስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ተድላ ዳኛቸው፤ የተጨዋቾች መረጃ  በትክክለኛ መንገድ  ተሰርቶ በዘመናዊ የመረጃ ክምችት  መቀመጥ  ስላለበት የምርመራ ሂደቶችን በትኩረት መከናወናቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከታዳጊዎች ውድድሩ ጋር በተያያዘ የተጨዋቾች ምዝገባ የተከናወነው አለም አቀፍ መመርያን በመከተል ነው፡፡ በዚህ መሰረትም በእግር ኳስ ፌደሬሽኑ አሰራር በትክክለኛ ምርመራዎች እድሜው ተረጋግጦ የተመዘገበ ተጨዋች ወደፊት እድሜውን ሊጨምር ወይንም ሊቀንስ የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
የውድድሩ አካሄድ እና ጠቀሜታዎች
ከ17 ዓመት በታች የሚካሄደው የታዳጊዎች ውድድር በአንድ ዙር እንደሚደረግ የተናገሩት የውድድር ዋና የስራ ሂደት ሃላፊው፤ የየክለቦቹ ተጨዋቾች ተማሪዎች እንደመሆናቸው ከውድድሩ በተያያዘ ትምህርታቸውን እንዳያስተጓጉልባቸው በሳምንት አንዴ ጨዋታዎችን ለማካሄድ እንደተወሰነና ታዳጊዎቹ በየስታድዬሞቹ በቂ ተመልካች እንዲያገኙ  ከተለያዩ የፕሪሚዬር ሊግና ሌሎች ውድድሮች ጋር ጎን ለጎን በማካሄድ  የፉክክር መንፈሱን ለማሟሟቅ መታሰቡን ገልፀዋል፡፡ በታዳጊዎች ውድድሩ ለሚያሸንፍ ክለብ ልዩ ዋንጫ መዘጋጀቱ እንደማይቀር የጠቀሱት የውድድር ዋና የስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ተድላ ዳኛቸው፤ በታዳጊ ደረጃ የሚደረግ ውድድርን በተለያየ የማበረታቻ ድጋፎች ማስኬድ መሰረታዊ ጥቅም ስለሚኖረው የእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ በዚህ ረገድ ትኩረት እንደሚሰጥ አስባለሁ ብለዋል፡፡
የፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች በታዳጊዎች ውድድር በመሳተፋቸው በርካታ ጥቅሞችን እንደሚያገኙ የውድድር ዋና የስራ ሂደት ሃላፊው ያስገነዝባሉ፡፡ የመጀመርያው  ጥቅም ውድድሩ ለዋና ቡድናቸው በቂ እና ብቁ ተተኪ ተጨዋቾችን የሚያሳድጉበት እድል ለክለቦች ይፈጠርላቸዋል፡፡ ዋና ቡድናቸውን ለማጠናከር ብቻ ሳይሆን ክለቦች በተጨዋቾች የዝውውር ገበያ ከፍተኛ ወጪ የሚያወጡበትንም ሁኔታ የሚያስቀርና ከራሳቸው አልፎ ለሌሎች ክለቦች ወጣት ተጨዋቾችን በዝውውር ገበያ በማቅረብ ገቢ ሊያገኙበት ይችላሉ፡፡ ከክለቦች ተጠቃሚነት ባሻገር ከፍተኛው ውጤት ክለቦች ለብሄራዊ ቡድን ወጣት እና ተተኪ ተጨዋቾችን በየጊዜው እንዲያፈሩ የሚያስችል መሆኑ ነው፡፡  በ2015 እኤአ ኒጀር ላይ በሚደረገው የአፍሪካ የሀ-17 ሻምፒዮና ኢትዮጵያ እንደምትሳተፍ አያይዘው ያነሱት አቶ ተድላ ዳኛቸው፤  በዚህ አህጉራዊ ሻምፒዮና ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ሀ 17 ብሄራዊ ቡድን የሚበቁ ተጨዋቾችን ለማግኘት ውድድሩ አመቺ መድረክ ይሆናል ብለዋል፡፡
በውድድሩ  ክለቦች በዋናነት በስልጠና ወጥ አሰራር እንዲኖራቸው ይደረጋል ያሉት  አቶ ተድላ ዳኛቸው፤  በየክለቡ ታዳጊዎችን የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ብቃታቸው እንደሚመዘን ወጥ የሆነ የስልጠና መመርያ ተከትለው እንዲሰሩ እና እንዲወዳደሩ ጥረት እንደሚደረግ አስገንዝበው፤ ለዚህም  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የቴክኒክ ዲፓርትመንት የስልጠና ማንዋል በመስራትና አሰልጣኞች ብቃታቸውን የሚያሳድጉባቸው ሴሚናሮች በማዘጋጀት እንደሚንቀሳቀስ በመግለፅም ታዳጊዎች  በወጥ  የስልጠና ሂደት በማለፍ ለብሄራዊ ቡድን ደረጃ ሲደርሱ በተመሳሳይ ብቃት እና አቋም እንዲኖራቸው ያስችላል ብለዋል፡፡
በክለቦች ህጋዊነት ሰርተፍኬት ያለው ወቅታዊ ሁኔታ
ከ17 ዓመት በታች በሚደረገው የታዳጊዎች ውድድር ላይ ክለቦች ቡድኖችን በማቋቋም መሳተፋቸው በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽንን የሚጠየቀውን የአንድ እግር ኳስ ክለብ መመዘኛ ለሟሟላት ወሳኝ መሆኑን የሚገልፁት የውድድር ዋና የስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ተድላ ዳኛቸው፤  የክለቦች ህጋዊነት ሰርተፍኬትን በየደረጃው በማግኘት በአህጉራዊ ውድድሮች ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን  ያስረዳሉ፡፡ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን በወጣ መመርያ መሰረት አንድ ክለብ በውድድር ሲሳተፍ ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች አሉ፡፡ እነዚህን መስፈርቶች የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያወጣው ያለምክንያት አይደለም፡፡ በሚያዘጋጃቸው አህጉራዊ ውድድሮች ለክለቦች የመሳተፍ ፍቃድ የሚሰጠው ተገቢውን መስፈርት አሟልተው የክለቦች ህጋዊነት ሰርተፍኬት ያገኙትን ብቻ  ነው፡፡  ክለቦች ይሄው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን መመርያ ተገልጾላቸው የተቀመጡትን መመዘኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ ከተነገራቸው ሶስተ ዓመታት አልፈዋል፡፡ ከመስፈርቶቹ መካከል በቅድሚያ ክለቦች በአደረጃጀታቸው በወጣቶች ላይ የተመሰረት መዋቅር  እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፤ ይህም የእግር ኳሱን ወጥ እድገት ለመቀጠል ወሳኝ ስለሆነ ነው፡፡
ክለቦች በታዳጊዎች እና በወጣቶች ስልጠና ሊያሰሯቸው የሚችሏቸው ብቁ አሰልጣኞች እንዲኖሯቸው ይጠየቃል፡፡ አንድ በፕሪሚዬር ሊግ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ክለብ ክለብ የተሟላ ዕህፈት ቤት፤ በቂ የፋይናንሻል አቅም ፤ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፤ የተሟላ የባለሙያዎች አደረጃጀት ሊኖረው ይገባል፡፡ በእነዚህ መስፈርቶች መሰረት ክለቦች  በሶስት  ደረጃዎች በኤ፤ ቢ እና ሲ በመመዘን የህጋዊነት ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል፡፡ የህጋዊነት ሰርተፍኬቱን ለመስጠት የእግር ኳስ ፌደሬሽኑ የክለቦች አደረጃጀት፤ አቅም አቅም በግንባር እንዲገመግም ሃላፊነት እንደተሰጠው አቶ ተድላ ዳኛቸው ሲናገሩ፤ ለዚህም ተብሎ ሁለት ኮሚቴዎች ተቋቁመው ከአዲሱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር በመተዋወቅ በቅርቡ ስራቸውን ይጀምራሉ ብለዋል፡፡ በክለቦች ህጋዊነት ሰርተፍኬት አሰጣጥ ላይ የሚሰሩት ኮሚቴዎች አንደኛው ቅደመ ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን ሌላኛው የይግባኝ ሰሚ  ነው፡፡ ቅድመ ውሳኔ የሚሰጠው ኮሚቴ በመጀመርያ ውሳኔ ሰጭነቱ ክለቡ ምን አሟልታል በሚል በቂ ግምገማ እና ክትትል በማድረግ የየክለቡን የፍቃድ ደረጃ የሚወስን ይሆናል፡፡ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ደግሞ ክለቦች በቅድመ ውሳኔ ሰጪ ኮሚቴው በተሰጣቸው  ደረጃ ላይ ቅሬታ ካላቸው ይግባኝ ብለው የተሰጣቸውን ምዘና ሊያስተካክሉ የሚችሉበት ነው፡፡
አንዳንድ ሁኔታዎችን በመገንዘብ ለመረዳት እንደሚቻለው በክለቦች ህጋዊነት ሰርተፍኬት መመዘኛ ብዙዎቹ  የኢትዮጵያ ክለቦች በሲ ደረጃ ሲሆኑ በቢ ደረጃ ያሉ ጥቂት ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ እግር ኳስ በኤ ደረጃ ሰርተፍኬት የሚያገኝ ክለብ የለም፡፡ በክለቦች ህጋዊነት ሰርተፍኬት እንዲሰጥ መመርያ ያስፈለገው አንድ ክለብ በአህጉራዊ ደረጃ በሚደረጉ ውድድሮች ለመሳተፍ ማሟሟላት  የሚገባው ደረጃዎች ስላሉ ነው፡፡ ክለቦች በዚህ መመርያ መሰረት ሊያሟሉ የሚገባቸውን መስፈርቶች እንዲያሟሉ በፊፋ በኩል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በተደጋጋሚ ቢሰጡም ብዙም እየተራመዱ አይደለም፡፡  የፐሪሚዬር ሊግ  ክለቦች አስቀድመው የሴቶች ቡድን በማቋቋም ተንቀሳቀሰው አሁን ውድድር እየተደረገ ውጤቱን በማየት ላይ ናቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የሀ 17 ቡድኖች መያዛቸው አንዱ ርምጃ ሲሆን አንዳንድ ክለቦች የቴክኒክ ዲያሬክተር መቅጠራቸው፤ በማርኬቲንግ ባለሙያ መስራትም መጀመራቸውም እንደለውጥ የሚታይ ቢሆንም ገና ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

           በ2014 የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ የአምናው የፕሪሚዬር ሊግ ሻምፒዮን ደደቢት ወደ አንደኛ ዙር ማጣርያ ማለፉን አረጋገጠ፡፡ በሌላ በኩል በ2014 የአፍሪካ ክለቦች ኮንፌደሬሽን ካፕ  ቅድመ ማጣሪያ በሁለቱም ጨዋታ የተሸነፈው መከላከያ ከውድድሩ ውጭ ሆኗል። ባለፈው ሰሞን በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ  ደደቢት ከሜዳው ውጭ በዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም 2ለ0 ቢሸነፍም፤ በአጠቃላይ የደርሶ መልስ ውጤት 3ለ2 አሸንፏል።  በኮንፌደሬሽን ካፕ ቅድመ መጣርያ የመልስ ጨዋታ ሊዮፓርድስን በሜዳው ያስተናገደው የአምናው የጥሎ ማለፍ ሻምፒዮን መከላከያ 2ለ0 ተሸንፎ በአጠቃላይ ውጤት 4ለ0 ተረትቶ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡ በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ አንደኛ ዙር የማጣርያ ምእራፍ ኢትዮጵያን የወከለው ደደቢት የሚገናኘው  ከቱኒዚያው ክለብ ሲኤስ ሴፋክሲዬን ጋር ነው፡፡ ደደቢት ከቱኒዚያው ክለብ ጋር የደርሶ መልስ ትንቅንቁን ከሳምንት በኋላ በሜዳው ይጀምራል፡፡  
መከላከያ ትኩረቱን ወደ ሊጉ ይመልሳል
በ2014 የአፍሪካ ክለቦች ኮንፌደሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታዎች ወደ አንደኛ ዙር ለመግባት 11 ክለቦች እድል ነበራቸው፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን የጥሎ ማለፍ አሸናፊ የነበረው መከላከያ ከታላቁ የኬንያ ክለብ ጋር በመደልደሉ ቅድመ ማጣርያውን ማለፍ አልቻለም፡፡ መከላከያ ትኩረቱን ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ በመመለስ ለዋንጫ ተፎካካሪ እንደሚሆን ተገምቷል። መከላከያ ከዘንድሮ በፊት በአፍሪካ ደረጃ በሁለት የውድድር ዘመናት የተሳትፎ ልምድ ነበረው፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ ድሮ “ካፕዊነርስ ካፕ” ተብሎ በሚጠራው የጥሎ ማለፍ ዋንጫ በ1976 እኤአ ተሳትፏል፡፡ በወቅቱም እስከ ሩብ ፍፃሜ ለመጓዝ በቅቶ ነበር፡፡ በ2007 እኤአ ላይ ደግሞ በኮንፌደሬሽን ካፕ ሲሳተፍ ቅድመ ማጣርያውን አልፎ ነበር፡፡ ከዚያ በመጀመርያው ዙር ክለብ በሆነ የደርሶ መልስ ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ሆኗል፡፡
ደደቢት 3 ኬኤምኬኤም 2
በ2014 የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ከሳምንት በፊት በቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታዎች 14 ክለቦች ወደ አንደኛ ዙር ማጣርያ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ አምና የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሸነፈው ደደቢት በኢትዮጵያ የክለቦች ውድድር በአጭር ጊዜ ስኬታማ በመሆን ከመደነቁም በላይ ለዋናው ብሄራዊ ቡድን ባለው አስተዋፅኦም የተለየ ነው፡፡ በ2011 እና በ2012 እኤአ የጥሎ ማለፍ ሻምፒዮን ለመሆን የበቃው ደደቢት ለዚህ ውጤቱ በሁለት የውድድር ዘመን የአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ካፕን ለመሳተፍ ልምድ አለው፡፡ በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትየጵያን ሲወክል ግን ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
በሻምፒዮንስ ሊጉ የመጀመሪያ ዙር ማጣርያ የደደቢት ተጋጣሚ የሆነው የቱኒዚያው ክለብ ሴፋክስዬን በስኬት እና በምርጥነት ከአፍሪካ 5 ታላላቅ ክለቦች ተርታ የሚሰለፍ ነው፡፡ የቱኒዚያ ፕሪሚዬር ሊግን ለ8 ጊዜ ያሸነፈው ሴፋክስዬን በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለት ጊዜ በነበረው ተሳትፎ በ2006 ኤአ ላይ ሁለተኛ ደረጃ ያገኘበት ውጤት ከፍተኛው ነበር፡፡ በኮንፌደሬሽን ካፕ ደግሞ በ2007፤ በ2008 እና በ2013 እኤአ ለሶስት ጊዜያት ዋንጫውን በማንሳት እና በ2008 እና 20009 እኤአ በካፍ ሱፕር ካፕ ሁለተኛ ደረጃን አከታትሎ አስመዝግቧል፡፡
በቱኒዚያዊው አሰልጣኝ ሃመዲ ዳው የሚመራው ሴፋክሴዬን በተጨዋቾች ስብስቡ የካሜሮን፤ የጋና፤ የአይቬሪኮስት፤ የጋቦንና የሞሮኮ ተጨዋቾችን ያካተተ ሲሆን አጠቃላይ 26 ተጨዋቾች የሚገኙበት ስብስቡ በትራንስፈርማርኬት የዝውውር ገበያ ስሌት 8 ሚሊዮን 750ሺ ዩሮ የተተመነ ነው፡፡ 3152 የተመዘገቡ አባላት ያሉት ሴፋክሴዬን በሜዳነት የሚጠቀመወ 12ሺ ተመልካች የሚያስተናግደውን ስታዴ ታሌብ ማሃሪ ስታድዬምን    ነው፡፡

Saturday, 22 February 2014 13:21

ወንጀል

“ቨርጂኒያ “ጂንጀር” ላይትሌይ በቴክሳስ ምስራቃዊ ክፍል ኮሬይቪል ኮፊ ኬክስ በሚባል ስም የሚታወቀው በጣም ዝነኛ የኬክ መጋገሪያ ድርጅት ባለቤት ነች፡፡ የራሷ ፈጠራ ብቻ የሆነውን የኬክ ጣዕም ለመቅመስ ደንበኞቿ ከሩቅ ቦታ ወደ ትንሿ መደብር ይመጣሉ። አንድ ወጣት ልጅ ዝነኛ ኬኳን ከበላ በኋላ ከተማው ውስጥ ሞቶ ስለተገኘ ለመላው ማህበረሰብ እጅግ አስደንጋጭ ነገር ሆነ። በቅርቡ በኃላፊነት የተሾመው የፖሊስ አዛዥ ለጉዳዩ አስቸኳይ ዕልባት ለመስጠት ቃል ተብቷል፡፡ ጂንጀር ልትረዳው ብትፈልግም፣ እሱ ግን ድርጅቷ ውስጥ ተቀጣሪ የሆነን ሰው በግድያ ወንጀል ከሰሰ፡፡ እሷ ደግሞ ወጣቱ የፖሊስ አዛዥ ስለግድያ ወንጀሉ የደረሰበትን ድምዳሜ ስላለመነችበት ተቃወመችና ወንጀለኛውን ለማወቅ በምስጢር ራሷ ወንጀሉን መከታተል ጀመረች።”
ርዕስ- ጣፋጭ ጂንጀር መርዝ (Sweet Ginjer Poison)
ደራሲ - ሮበርት በርተን ሮቢንሰን
ተርጓሚ - አምሳሉ ጌታሁን ደርሰህ
ዋጋ 35 ብር
ህትመት - ላንጋኖ ማተሚያ ቤት

Saturday, 22 February 2014 13:19

ወግ

“አንድ ደራሲ በመግቢያው ስለ ጠቅላላ መፅሀፉ ይዘት ሲያብራራ ታላቅ ድግስ አዘጋጅቶ መግቢያ በሩ ላይ በመቆም ውስጥ ስለተዘጋጀው ምግብ ጣፋጭነት እየመሰከረ ወደ ብፌው አቅጣጫ እንደሚመራ ጋባዥ መሆኑ ነው፡፡
ደራሲውም ሆነ ጋባዡ መግቢያው ላይ ቆመው በአንድ አይነት ዜማ ታዳሚው ስለ ድግሱ በቂ ግንዛቤ ኖሮት እንዲገባ በማስረዳት ይደክማሉ፡፡ ይሄን ድግስ ለማዘጋጀት ስለ ተደከመው ድካም፣ በውጤቱም ስለተዘጋጁት አይነቶችም ያብራራሉ።
በውስጥ ስለተደገሰው ድግስ በራፍ ላይ ሆኖ የማብራራት አስፈላጊነት ወይም አላማ የታዳሚውን የመብላት ፍላጎት ማናር /አፒታይዘር/ ጭምር ሳይሆን አይቀርም፡፡ በእኔ እምነት ይህ ተግባር ተጋባዡን ጉጉ ያደርገዋል፡፡
በዚህ መፅሃፍ ውስጥ ስለተካተቱት ታሪኮች ይዘት ማውራት ካለብኝ ከአትኩሮታቸው በመነሳት እጀምራለሁ፡፡ በአንድ የማህበረሰብ ስብስብ ውስጥ (ሀገር ሊሆን ይችላል) ወሳኝ ሚና ስላላቸው፣ የየነዋሪውም ዋነኛ ግዱ ስለሆኑት ማለትም … ሀይማኖት፣ ፖለቲካና ማህበረ-ባህላዊ እሳቤ ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ፡፡”  
ርዕስ - ሕዝብ እና ነፃነት
ደራሲ - ሚካኤል ዲኖ
ዋጋ - 44 ብር

Saturday, 22 February 2014 13:17

ሰሞኑን የወጡ መፃህፍት

ግጥም
“የሰረቀ ሌባ
በካቴና ታስሮ
በፖሊስ ተይዞ
ሲሄድ ወደ ጣቢያ
መንገድ ላይ ያይሃል
ሊሰርቅ የሚሄደው
ዕልፍ-አዕላፍ
ሌባ፡፡”
ርዕስ -
ሲጠይቁ መኖር
(የግጥም ስብሰባ)   
ደራሲ - ደረጀ ምንላርግህ
ዋጋ - 34ብር
ህትመት - አንድነት ፕሪንተርስ

        ከተመሰረተ ስልሳ አምስት አመቱን ያስቆጠረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ አለምአቀፋዊ ተቋምነቱ እና የብዙዎችን ይሁንታ ያገኘበት ሀላፊነቱ በተግባር በሚያከናውነው ስራ አንፃር ሲመዘን ጥያቄ ላይ የወደቀ ድርጅት ነው፡፡ አሁን በሀላፊነት ላይ ያሉት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ ባን ኪ ሙን የመንግስታቱን ድርጅት የመለወጥ ሀሳብ በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡ ነገር ግን፣ ድርጅቱን በዋና ፀሀፊነት ካገለገሉ ስምንት ሰዎች ውስጥ አንዱ ብቻ ናቸው ስለ ለውጥ ምንም ተናግረው የማያውቁት፡፡ የተወሰኑ ለውጦች በተለያዩ ጊዜዎች የተደረጉ ቢሆንም፣ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ግን ምንም አይነት ለውጥ አለመደረጉ ጥያቄዎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲበረቱ አድርጓል፡፡
በድርጅቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች የአባል አገሮቹን ያህል የበዛ እና የተወሳሰበ ቢሆንም፣ በማሻሻያዎቹ ላይ ጥናት ያደረገው ዛክ ቱከር፣ ጥያቄዎቹን በሶስት ዋና ዋና ምድቦች ይከፍላቸዋል። አንደኛው ጥያቄ፡- በመንግስታቱ ድርጅት ውስጥ እንደ ባህል የተያዘውና እንደ አሰራር እየተከተለ ያለው መንገድ፣ ውሁዳን ሊሂቃንን ያካተተው የአባል አገሮች ቡድን የመንግስታቱን ድርጅትም ሆነ የአለም ፖለቲካ አድራጊ እና ፈጣሪ የሚያደርጋቸው ነው፡፡ ሁለተኛው ጥያቄ የሚያተኩረው ደግሞ፡- በመንግስታቱ ድርጅት እንደ አንድ ግብ የተቆጠረው ግሎባላይዜሽን በአባል አገሮች ሉኣላዊነት ላይ እየጋረጠ ያለው ስጋት ላይ ነው፡፡ ድርጅቱ ግጭቶችን በመከላከልም ሆነ ሰብአዊ ቀውስ በሚፈጠርበት ጊዜ ሰብአዊ አገልግሎቶችን በብቃት አይወጣም የሚለው ሶስተኛው ጥያቄ ነው፡፡
በለውጡ ላይ የድርጅቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ምክር ቤት ትልቅ ቦታ ሊሰጠው ይገባል። በድርጅቱ ቻርተር መሰረት የምክር ቤቱ ሚና ወደ ጥናት እና አማካሪነት ያተኮረ ነው፡፡ ነገር ግን፤ በሚሰራበት የምርምር፣ የባህል፣ የትምህርት፣ የጤና እና ተያያዥ ዘርፎች ላይ ልክ እንደ ፀጥታው ምክር ቤት  በድርጅቱ ስም ውሳኔ ማስተላለፍ የሚችልበት አቅም ሊሰጠውም ይገባል፡፡ ይህ መደረጉ ደግሞ በድርጅቱ ውሳኔ ላይ የብዙሃን ድምፅ እንዲካተት እና በተለይ በአሁኑ ወቅት ክፍተት ያለበት ከሰብአዊ ድጋፎች ጋር የተያያዙ ስራዎች ምላሽ እንዲያገኙ ያስችላል ይላል ዛክ፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ላይ ለውጥ ሲነሳ፣ የብዙዎችን ትኩረት የሚስበው የፀጥታው ምክር ቤት ነው፡፡ ምክር ቤቱ፤ አራቱን የሁለተኛው የአለም ጦርነት አሸናፊዎች ማለትም አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ እና ቻይና በቋሚ አባልነት  እና በየሁለት አመቱ የሚቀያየሩ አስር ተለዋጭ  አባላትን ይይዛል፡፡ ይህ ምክር ቤት ከሰላም እና ከደህንነት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከፍተኛው የድርጅቱ ክንፍ በመሆኑ ማዕቀቦችን ይጥላል፣ የሀይል እርምጃዎችን ያፀድቃል ወይንም ይሽራል፡፡ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የዘጠኝ አባላት ድምፅ ሲያስፈልግ የቋሚ አባላቱ ሙሉ የስምምነት ድምፅ ግን የግድ ያስፈልጋል፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ላይ በሚነሱ ጥያቄዎች እና ለማሻሻያ ይረዳሉ በሚል በተጠራ የከፍተኛ ባለሙያዎች ፓናል ሪፖርቱን ለድርጅቱ አቅርቧል፡፡ በፓናሉ ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት የተሰጠውን ሚና መወጣት እንዳቃተው ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ከሞላ ጎደል ሽባ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ የመነቃቃት አዝማሚያ ቢታይም፣ ከተወሰኑ ውጤታማ ስራዎች በስተቀር አንድን አሳሳቢ ጉዳይ ከመከሰቱ በፊት ለመከላከል ወይም ለተፈጠረ ቀውስ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ የሀይል መጠላለፍ እና መቆላለፉ በመጉላቱ፣ ቋሚ የምክር ቤቱ አባሎች ጥቅም ማስጠበቂያ ሆኗል፡፡ በተለያዩ ጊዜዎች ምክር ቤቱን ለማሻሻል የተደረጉ ሙከራዎች በተለይ የምክር ቤቱ አባልነት ላይ ይደረጉ በሚባሉ ማሻሻያዎች ስምምነት ላይ ባለመደረሱ ውድቅ ሲሆኑ ተስተውለዋል፡፡
በፓናሉ ላይ የምክርቤቱን አባላት ቁጥር ከአስራ አምስት ወደ ሀያ አራት በማሳደግ ሁለት ሞዴሎች ለውይይት ቀርበው ነበር፡፡ አንዱ ሞዴል፡- ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት የሌላቸው ስድስት አዲስ የቋሚ አባላትን ማካተት ሲሆን፣ ሁለተኛው ሞዴል ደግሞ አዲስ የቋሚ አባላትም ሳይኖሩ በየአራት አመቱ የሚለዋወጥ መቀመጫ ይኑር የሚሉ ናቸው፡፡
የፀጥታው ምክር ቤትን ጉዳይ አስመልክቶ የተሰጡ ብዙ አስተያየቶች አሰራሩ መሻሻል እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አምስቱ አገሮች በሞኖፖል ጠቅልለው የያዙት ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት በራሱ ከመሰረታዊዎቹ የህግ መርሆዎች ጋር ይጋጫል፡፡ አገሮቹ ውሳኔዎች እንዲያልፉ ወይም እንዲወድቁ ድምፅ የሚሰጡት ከሰብአዊ መብቶች ወይም ከአለም አቀፍ ህግ በመነሳት ሳይሆን፣ ከራሳቸው መንግስት ጥቅም እና ፍላጎት አንፃር ነው። የፀጥታው ምክር ቤት የተቋቋመው አለም አቀፍ ሰላም እና ደህንነትለ ለማስከበር ቢሆንም እያገለገለ ያለው ግን ለየአገሮቹ የኢኮኖሚ ጥቅም እና የጡንቻ ብቃት መለኪያነት ነው፡፡ ምእራባውያኑ በአለም ላይ ዲሞክራሲን የማስፈን እውነተኛ ፍላጎት ካላቸው ሥራው መጀመር ያለበት በመንግስታቱ ድርጅት፣ በተለይም በፀጥታው ምክር ቤት ነው፡፡ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቱ የተሰጠው ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ በመሆኑ ሰላም ማምጣት አልተቻለም፡፡ ይህ አሰራር፣ ክፍፍል እና ብዙ ተቃርኖ ያላቸው ቡድኖች እንዲፈጠሩ እድል ሰጥቷል፡፡ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት በመንግስታቱ ድርጅት ውስጥ ያለ የዲሞክራሲ መርሆችን የሚሸረሽር አሰራር ነው፡፡
በአለም ላይ ያሉ አገሮችና ህዝቦች እጣፈንታ በአምስት አገሮች ፍላጐት እንዲወሰን በመፈቀዱ ምክንያት አለማችን ይሆናሉ ተብለው የማይገመቱ እልቂቶችንና አሳዛኝ ክስተቶችን እንድታስተናግድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የሩዋንዳው እልቂት፣ የዳርፉር እና የሶሪያ ሰብአዊ ቀውሶች እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ። የመንግስታቱ ድርጅት ሩዋንዳ ውስጥ የተከሰተውን የዘር ማጥፋት እልቂት ቀድሞ መከላከል ያልቻለው ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ባላቸው አሜሪካን እና ፈረንሳይ ውሳኔ ነው፡፡ ሁለቱ አገሮች ከየጥቅሞቻቸው በመነሳት፡- አሜሪካ ከገንዘብ ጋር በተያያዘ፣ ፈረንሳይ ደግሞ አጋሮቿን ላለማጣት በሚል የግል ስሌት ውስጥ በመግባታቸው  ነው … ብዙሀን በአደባባይ እንደ በግ የታረዱት። የሲሪላንካው አማፂ ቡድን “ታሚል ታይገርስ” ላይ በመንግስት በኩል ይደርሱ የነበሩ ኢ-ሰብአዊ እርምጃዎችን ለመታደግ በሚል መንግስት ላይ ሊጣል የነበረ ማእቀብ ውድቅ የተደረገው በቻይና ሲሆን መነሻውም ቻይና ከሲሪላንካ መንግስት ጋር ያላትን ወዳጅነት ላለማሻከር ሲባል ነበር፡፡ ሶስተኛ አመቱን የያዘውና  በመንግስታቱ ድርጅት የዘመኑ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ የታየበት ነው የሚባለው የሶሪያ ጉዳይም ከዚህ ጨዋታ የዘለለ አይደለም። ለችግሩ መፍትሄ በሚል የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ፣ በቻይና እና በራሺያ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ውድቅ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ የበሽር አላሳድ መንግስትን የሚደግፉት ቻይና እና ራሺያ፣ የውሳኔ ሀሳቡ መንግስትን ብቻ በመኮነን ተቃዋሚ ሀይሎችን በዝምታ ያለፈው በዚሁ የውሳኔ ሀሳብ በመሆኑ ድምፃቸውን መንፈጋቸውን ይገልፃሉ፡፡ በመንግስታቱ ድርጅት የራሺያ አምባሳደር ቪታሊ ቸርኪን የአገራቸውን ውሳኔ አስመልክቶ ተጠይቀው በሰጡት አስተያየት፣ የውሳኔ ሀሳቡ ሁሉንም ወገኖች በእኩል የሚኮንን ሳይሆን የአላሳድን መንግስት በተናጠል የሚኮንን በመሆኑ አገራቸው ልትቀበለው እንደማትችል ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ፤ ጃፓን፤ ህንድ እና የብሪክስ አገሮች የፀጥታው ምክር ቤት አሰራር ላይ የማሻሻያ ለውጥ እንዲደረግ ከሚጎተጉቱ አገሮች እና አካባቢያዊ ድርጅቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ አሁን ባለው አሰራር የብዙሀንን ጥቅም ማስከበር እንደማይቻል በተለያዩ ማስረጃዎች አስደግፈው ያቀርባሉ። ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዳይሆን ቢደረግም ሆነ አገሮች እና አካባቢያዊ ድርጅቶች የመብቱ ተጠቃሚ መሆን ቢችሉ እንኳን፣ የራስን ጥቅም ማስላትን አያስቀርም፤ መጠላለፉን ከማወሳሰብ በስተቀር የሚሉም አሉ፡፡

“...ሀገራችን ፀሐይ ወጥቶ! አሁንማ ፀሐይ ወጥቶልናል። ሆስፒታላችን ከተሰራልን ወዲህ ምን ችግር አለ... ሞትማ እንዲህ በቀላሉም አይደፍረን፡፡ መቼም ነብስ የእግዚሀር ናትና ሲያበቃላት መትረፊያ የላትም እንጂ... እንዲህ በምኑም በምኑም አልጋ መያዝማ ቀርቶአል፡፡ ይኼው አሁን እኔን ከበሽታ ነጻ አውጥቶኛል፡፡ እዚህ ጉያዬ ስር አንድ ሕመም ነበረብኝ... ፍልፍል አድርጎ አውጥቶ ወርውሮልኝ... ይኼው አሁን ነጻ አውጥቶኛል፡፡ ሐኪሙም አየለ የሚባለው ዶ/ር ነው...”
ከላይ ያነበባችሁት በመርሐቤቴ አለም ከተማ እናት ሆስፒታል ያገኘናቸው አባወራ እማኝነት ነው፡፡ መርሐቤቴ በአማራው ክልል የምትገኝ ስትሆን ከአዲስ አበባ በጎጃም መንገድ መካጡሪ ከተማ ሲደረስ ወደ ቀኝ በመታጠፍ ወደ /111/ አንድ መቶ አስራ አንድ ኪሎ ሜትር ጥርጊያ መንገድ ተገብቶ የምትገኝ ነች፡፡ መርሐቤቴ ተራራማ ስትሆን ዠማ የሚባል ወንዝ መሐል ለመሐል የሚጉዋዝባት እጅግ አስደናቂ ተፈጥሮአዊ ውበት ያላት ናት፡፡ በእርግጥ ከስድስት አመት በፊት መንገዱ እንዲህ በዋዛ የማይደፈር ሲሆን አሁን ግን ዳገት ቁልቁለቱ እንዳለ ቢሆንም ጥርጊያው በማማሩ በጥንቃቄ መንዳት እንጂ እንደቀድሞው ሰውን ማሰቃየቱ አብቅቶአል፡፡ እንደሀገሬው ተስፋም ብዙም ሳይቆይ ወደ አስፋልትነት ይቀየራል፡፡ ግራና ቀኙን እያዩ የተራራውን አቀማመጥ፣ ተፈጥሮአዊ ሀብቱን እያደነቁ ከአንዱ ተራራ ወደአንዱ እየተ ዙዋዙዋሩ ሲጉዋዙ ድካሙን ሳያስቡ ከመርሐቤቴ አለም ከተማ ይደርሳሉ፡፡ አለም ከተማ መሐል አደባባይ ላይ አንድ ልጅ የታቀፈ ሰው ሐውልት ያያሉ፡፡ ቀረብ ብለው ሲያጣሩ ምስሉ የሜንሽን ፎር ሜንሽን መስራች የዶ/ር ካርል ሄንዝ ቦም  ነው፡፡ ሜንሽን ፎር ሜንሽን በመርሐቤቴ ከሰራቸው የልማት ስራዎች መካከል እናት ሆስፒታል አንዱ ሲሆን በመሀል ከተማው አደባባይ ላይ የሚገኘው ሐውልት ለአስተዋጽኦው ማስታወሻ ሐገሬው ለመስራቹ ዶ/ር ካርል ያቆመለት ሐውልት ነው፡፡ እኛም ፈልገን የተጉዋዝነው እናት ሆስፒታልን ነውና በመጀመሪያ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ የሰጡትን ማብራሪያ ለንባብ እንላለን፡፡
“...እኔ አቶ ደነቀ አየለ እባላለሁ፡፡ በዚህ ሆስፒታል ቀደም ሲል የጤና መኮንን ሆኜ የሰራሁ ስሆን አሁን ደግሞ ስራ አስኪያጅ ነኝ፡፡ በአለም ከተማ እናት ሆስፒታል የተሰራው በሜንሽን ፎር ሜንሽን አማካኝት ሲሆን የመሰረት ድንጋዩ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1991 ዓ/ም ተጥሎ በ1996 ዓ/ም በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በሆስፒታሉ መስራች ዶ/ር ካርል ሄንዝ ቦብ ተመርቆ ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡
ጥ/ ሆስፒታሉ እናት ሆስፒታል የተባለበት ምክንያት ምንድነው?
መ/    የሆስፒታሉ መጠሪያ እናት እንዲሆን የተወሰነው በመስራቹ በዶ/ር ካርል ነው፡፡ ይኼውም የመሰረት ድንጋይ በሚጣልበት ወቅት ለሚሰራው ሆስፒታልም ስም እንዲወጣ ህብረተሰቡ ተነጋግሮ ሁሉም ለምርጫ የሚሆነውን ስም በልቡ ይዞ ነበር ወደስፍራው የተሰበሰበው፡፡ ከወጣው ህብረተሰብ መካከልም ህጻናትም ይገኙ ነበር፡፡ ከህጻናቱ መካከል አንዲት በዝቅተኛ ደረጃ ከሚኖሩ ቤተሰቦች የተወለደች ልጅ በጣም ቆሽሻ፣ በዝንብ ተወርራ በሚያሳዝን ሁኔታ ቆማ ነበር፡፡ ዶ/ር ካርልም ከልጆቹ መካከል ብድግ አድርገው አቅፈው እያዘኑ ከተመለከቱዋት በሁዋላ ስሙዋ ማን እንደሆነ ጠየቁ፡፡ ስሙዋ እናት መሆኑ ሲነገራቸው  ...በቃ ሆስፒታሉ እናት ተብሎአል ብለው ወሰኑ፡፡ በጊዜው ህብረተሰቡ በተለያዩ  ስሞች ላይ ውይይት አድርጎ የነበረ ስለሆነ ለምን በሚል ቅር ቢለውም ውሳኔው በመወሰኑ ሆስፒታሉ እናት ሆስፒታል ተብሎ ተሰይሞአል፡፡ ልጅቱም በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከነቤተሰቦችዋ እየተረዳች ትምህርቷን እንድትቀጥል ተደርጎአል፡፡
ጥ/    ሆስፒታሉ ደረጃው ምንድነው?
መ/    አለም ከተማ እናት ሆስፒታል ደረጃው በመጀመሪያ ደረጃ ወይንም በወረዳ ደረጃ ዲስትሪክት ሆስፒታል ሆኖ የሚሰራ ነው፡፡ ከአካባቢው አቀማመጥ ጋር ተያይዞ ሌላም ተመሳሳይ የጤና ተቋም ባለመኖሩ በአካባቢው የሚኖሩ ወደ 250‚000 /ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ/ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማገልገል ላይ ነው፡፡ ከሌሎች አጎራባች ክልሎች ወይንም ዞኖች ...ለምሳሌ ከኦሮሞ የሚመጡትንም ተገልጋዮች አካቶ በርካታ ሰዎችን እያገለገለ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት ወደ /158/ አንድ መቶ ሀምሳ ስምንት ሰራተኞችን የያዘ ሲሆን በተለይም ባለሙያዎችን በሚመለከት ከአምስት በላይ ዶክተሮች እና አንድ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት ስለሚገኝ ከደረጃው በላይ እየሰራ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ዶ/ር አየለ ተሸመ በአለም ከተማ እናት ሆስፒታል የማህጸንና ጽንስ ሐኪምና የሆስ ፒታሉ  ሜዲካል ዳይሬክተር ናቸው፡፡
ጥ/ ዶ/ር አየለ መርሐቤቴን ለስራ ከመመደብ ውጭ አስቀድሞ ያውቁዋታል?
መ/ እኔ ተወላጅነቴም እድገቴም በዚሁ በመርሐቤቴ ነው። አሁን የምኖርበት ቤት ቀደም ሲል ጤና ጣቢያ የነበረና እኔም የተወለድኩበት ማዋለጃ የነበረ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ከህክምና ትምህርት ቤት ተመርቄ እንደወጣሁ በጠቅላላ ሐኪምነትም የሰራሁት በዚሁ ሆስፒታል ነው፡፡ ከዚያም ለአራት አመት ያህል ከ2000-2004 እንደገና ስፔሻላይዜሽን ተምሬ በመመለስ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት በመሆን በማገልገል ላይ እገኛለሁ፡፡
ጥ/  ምደባው በአጋጣሚ ነው ወይንስ በምርጫ?
መ/ እኔ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ትምህርት ቤት በጥቁር አንበሳ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ስማር የማህጸን መፈንዳት ሪፖርት ሲደረግ ብዙዎች ከመርሐቤቴ የሚመጡ መሆናቸው የሚነገር ነበር፡፡ በጊዜው መንገዱ እጅግ አሳዛኝ እና አስቸጋሪ ስለነበር እንዲሁም የሚፈለገው ሕክምና በጊዜው በአካባቢው ካለው የጤና ጣቢያ አቅም በላይ የሆነ ችግር ስለሆነ ወላዶች በጣም ይሰቃዩ ነበር፡፡ በእርግጥ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት አምቡላንስ ይሰጥ ስለነበር ወደአዲስ አበባ እንዲደርሱ የሚደረግ ቢሆንም ከመዘግየት የተነሳ ረጅም ጊዜ በምጥ በመቆየት ሴቶቹ ይጎዱ ነበር፡፡ እናም አንዳንድ ጊዜ የጠዋት ሪፖርት ላይ የማህጸን መፈንዳት ደርሶአል ሲባል ከየት ከመርሐቤቴ ናት? እስከማለት ድረስ መነጋገሪያ መሆኑ በጣም ያሳዝነኝ ነበር፡፡ በእርግጥ ካለው ዘርፈ ብዙ የጤና ችግር ምክንያት አንባቢው በጤና ጣቢያ ደረጃ ባለበት ጊዜም ሶስት እና አራት ሐኪሞች ይመደቡ የነበረ ቢሆንም ሐኪሞቹም በዚህ የመቆየት ፍላጎት ስለሌላቸው እና ከጤና ጣብያው አቅምም ጋር በተያያዘ በተለይም ለወላዶች በቀላሉ የማይፈቱ የጤና ጠንቆች ይገጥሙዋቸው ነበር፡፡ ስለዚህ እኔም ትምህርቴን ልጨርስ እንጂ በዚያ ገጠራማ ቦታ ገብቼ ህብረተሰቡን ማገልገል አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡ መጀመሪያ ላይ ምንም እንኩዋን ጠቅላላ ሐኪም ብሆንም የእናቶችን ችግር ስለማውቅ ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት ጋር ተነጋግሬ ለሶስት ወር ለወላዶች የድንገተኛ ቀዶ ሕክምና ስልጠና አግኝቼ በማዋለድ ተግባር ላይ እንድሰማራ እራሴን አዘጋጀሁ፡፡ ከዚያም ከኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በተገኘው እድል እንደገና ለስድስት ወር ባለሙያዎችን አሰልጥኜ እኔም ስራዬን እዚሁ ቀጠልኩ፡፡
ጥ/ በገጠር ሆስፒታል ውስጥ እስፔሻሊስት ይመደባልን?
መ/ በጀት ስለሌለ የገጠር ሆስፒታል ውስጥ እስፔሻሊስት አይመደብም፡፡ እናም የጤና ቢሮው እምቢ ቢልም ከዚህ የስራ አመራር ቦርድና ሽማግሌዎች ሄደው በማስፈቀዳቸው እና የእኔም ፍላጎት ስለነበረበት እንድመደብ ተደርጎ በመስራት ላይ ነኝ፡፡
ዶ/ር አየለ ተሸመ በስራቸው ያጋጠማቸውን እንዲህ ሲሉ አውግተዋል፡፡
“...አንዲት ሴት በምጥ ተይዛ በቤቷ ትቆይና ልጇን ትገላገላለች፡፡ ነገር ግን እንግዴ ልጁ እምቢ ስላለ ወደሆስፒታል ያመጡአታል፡፡ ሴትየዋ በሞት እና በህይወት መካከል ነበረች። ስለዚህም እንግዴልጁን ለማውጣት መጀመሪያ የደም ልገሳ እንደሚያስፈልግ ስንነግራቸው እንዴት ተደርጎ የሚል ነገር ተነሳ፡፡ እኛም ምንም ችግር የለውም አልንና... ባለቤቷን...
አንተ ባለቤቷ አይደለህም? አልነው... ነኝ የእርሱ መልስ ነበር፡፡ ታድያ ሚስትህ ከምትሞት አንተ ደም ስጥ... ስንለው  ...አረግ …እኔማ ገበሬ ነኝ ከየት አምጥቼ ነው ለእሷ ደም የምስጥ? መልሱ ነበር፡፡
በመቀጠልም እናትየውን አነጋገርን፡፡
አረግ ...እኔማ ልጄ ብትሞት አልሻም፡፡ ነገር ግን ...እኔ አሮጊት ነኝ ደም ከወዴት አመጣለሁ? ለእኔም አልበቃኝ... መልሳቸው ነበር፡፡ አብረው የነበሩትም ይልቁንም ሳትሞት ይስጡን እና እንውሰድ፡፡ ከሞተች መውሰጃውም አይገኝ ወደሚል ውይይት ገቡ፡፡ እኛም አይናችን እያየ እንዳትሞት ተነጋገርንና ሰዎቹን አስወጥተን ...አንድ ሰራተኛና አንድ አስታማሚ ደም ሰጥተው ህይወቷን አተረፍናት፡፡
ከዚያም ያ ደም የለገሰ ሰውየ ተናደደና ወደሰዎቹ በመሄድ ...ሴትየይቱ  እኮ ሞታለች ...ለምን አስከሬኑን አትወስዱም ሲላቸው... ከተማይቱ እስክትናወጥ ድረስ ኡኡታቸውን አቀለጡት፡፡ በሁዋላም በሉ ዝም በሉ ...እሱዋ ድናለች ሲባል ተደሰቱ፡፡  ከዚያም ወደህብረተሰቡ ሄደው ምስክርነታቸውን ሲሰጡ ለካንስ ይኼም አለ በሚል አሁን ደም የሚለግሱ ሰዎች ማህበር ተቋቁሞአል፡፡ ወደ ሁለት መቶ የሚደርሱ ሰዎች የደም ልገሳ ማህበርተኞች ሆነው ተመዝግበዋል፡፡ ስለዚህም ሰዎቹ የደም አይነታቸው፣ የሚኖሩበት አካባቢ፣ የስልክ ቁጥራቸው ተመዝግቦ የሚገኝ ስለሆነ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ካሉበት ድረስ አምቡላንስ እየላክን እንጠራቸዋለን፡፡ ከሰራተኞቹም እኔን ጨምሮ ፈቃደኞች የሆንን በየሶስት ወሩ ደም እንሰጣለን። እናት ሆስፒታል የደም ባንክ ባይኖረውም አስፈላጊው የላቦራቶሪ ስራ እየተሰራ ለተጠቃሚዎች ደም ይሰጣል፡፡ በእርግጥ ከአዲስ አበባም ደም ባንክ የተቻለውን ያህል ደም ቢሰጠንም በቂ ስለማይሆን ከህብረተሰቡ የሚደረግልን እገዛ ችግሩን አስቀርቶልናል፡፡ ይህም ጥሩ ተሞክሮ ስለሆነ ለሌሎች እንደምሳሌ የሚነሳ ሆኖአል፡፡
ይቀጥላል፡፡