Administrator
Monday, 01 June 2026 09:28
ጋዜጠኞች ምርጫውን ለመዘገብ ክልከላ እንደገጠማቸው ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የሰጣቸው መገናኛ ብዙኃንና ጋዜጠኞች በምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱና መረጃ እንዳይሰበስቡ ከተለያዩ የፓርቲ ታዛቢዎችና የፀጥታ ኃይሎች ክልከላ እየገጠማቸው መሆኑን አስታወቀ። በተለይም «ኢትዮጵያ ኢንሳይደር» የተባለው የዜና ምንጭ በልደታ፣ የካ፣ ቂርቆስ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ጋዜጠኞቹ ባጅ ይዘው እንኳ እንዳይቀርጹና መረጃ እንዳይሰበስቡ መከልከላቸውን ይፋ አድርጓል። ቦርዱ ይህንን ጋዜጠኞችን ከሥራ የማስቆም ድርጊት «የተሳሳተ» ሲል የኮነነ ሲሆን፣ ማንኛውም አካል ቦርዱ ሕጋዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ የመተባበር ግዴታ እንዳለበት በጥብቅ አሳስቧል።
ምርጫ ቦርድ ሂደቱን በነጻነት እንዲዘግቡ በአጠቃላይ 68 መገናኛ ብዙኃንን እና 1,815 ጋዜጠኞችን መዝግቦ መለያ ባጅ መስጠቱን ገልጿል። እነዚህ የጋዜጠኝነት ባጅ ያላቸው ባለሙያዎች በምርጫ ጣቢያዎች 200 ሜትር ንፍቀ ክበብ (ራዲየስ) ውስጥ ገብተው የመዘገብ ሙሉ ሕጋዊ መብት እንዳላቸው ቦርዱ አስታውቋል። በሌላ በኩል፣ ቢቢሲ ምርጫውን በአገር ውስጥ ለመዘገብ ፈቃድ እንዳልተሰጠው የተገለጸ ሲሆን፣ ምርጫ ቦርድ የመገናኛ ብዙኃንን ነጻነት የሚጋፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ከሕግ አሠራር ጋር እንዲሰለፉ ጥሪ አቅርቧል።
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 01 June 2026 07:15
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ አቶ ኢዮብ መሳፍንት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ተገኝተው ድምጽ ሰጥተዋል
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 01 June 2026 07:07
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 01 June 2026 07:02
"ምርጫው በሰላም እና በሥርዓት እየተካሄደ ነው” ኡሁሩ ኬንያታ
የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ መሪና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ መጀመሩን ገልጸዋል።
በምርጫ ጣቢያዎች የተመለከቱት ነገር መልካም እንደነበር የጠቀሱት ኬንያታ፤ ይህ በሰላምና በሥርዓት የመምረጥ ሂደት ቀኑን ሙሉ እንዲቀጥል ተመኝተዋል።
“ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋና ከተማ ናት፤ በዚህች ሀገር የሚመዘገብ ስኬት ለመላው አህጉር ብርሃን ነው” በማለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 01 June 2026 06:58
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድምጽ ሰጥተዋል
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 01 June 2026 06:55
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 01 June 2026 05:49
አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ድሉን በለንደን ጎዳናዎች ከሕዝብ ጋር እያከበረ ነው።
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ተፋላሚ የነበረው አርሰናል ባሁኑ ሰአት በእንግሊዝ ሰሜን ለንደን ከሁሉም ተጫዋቾቹና ደጋፊዎቹ ጋር በመሆን የፕሪምየር የሊጉ አሸናፊነታቸውን በጎዳና ላይ ትርዒት እያወጁ ይገኛል።
Published in
ስፖርት አድማስ
Tagged under
Sunday, 31 May 2026 08:11
ሰላም በዘፈቀደ አልራቀንም፤ ለፍተንበታል
1) እኛ ሰላም ያጣነው እንዲሁ በድንገት አይደለም፤ ሆን ብለን ሰርተንበት (ለፍተንበት) እንጂ። ዛሬም ለመሳሪያ ይዘፈናል። ዛሬም የገዳይ ልጅ ነኝ ይባላል። ፉከራ አለ። እኛ ከእንትና የበለጥን ጀግኖች ነን ይባላል። ዛሬም ልጆች በጦርነት ድምፅ መሃል ያድጋሉ።
ከዛ፣ ምን መዓት መጣብን?
2) በቅርብ ታሪካችን ውስጥ ሰዎች የሰሩት ትልቁ ስህተት መንግስትን እንደ ጓደኛ ማሰባቸው ነበር። መንግስት መቼም ቢሆን ያንተ ጓደኛ አይደለም። መንግስትን መግራት አትችልም። መንግስት የምትጠላቸውን ሰዎች ሲያጠቃ አንተም አብረኸው ልታጠቃ ትችላለህ፤ ነገር ግን መንግስት አድኖ በልቶ ሲጨርስ፣ ወደ እሱ በጣም ተቃርቦ የሚገኘው ማን እንደሆነ ገምት?
#NoMore ብለህ ጮኸህ፣ ድምፅህ ሰልሎ ወደ ቤትህ ልትገባ ስትል፣ A little more ብሎ ለእራት ያውልሃል። መንግስት ውለታ አይቆጥርም። እነዚህ ደግሞ የባሱት ናቸው ስንል፣ አብረን ያጠናከርናትና በር የከፈትንላት (Enable ያደረግናት) ዓመፅ እንዳለችም ማስታወስ ደግ ነው። ለነገ ይጠቅም ይሆናል።
3) ወላጆቻቸው ሕይወታቸውን ኦርጋናይዝ ሊያደርጉ ሲሞክሩ የሚበሳጩ (ነፃነት የሚፈልጉ) ሰዎች፣ ለምን የጓደኞቻቸው ሕይወት ላይ 60 በመቶ አክሲዮን እንዳላቸው ይሰማቸዋል?
ተቃርኖ የዓለም ገፅ ስለሆነ ወይስ ኑሯችንን በተለየ መልኩ እየደገምን የምንኖር ሆነን?
4) "እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይኑር" (To each their own) ጥሩ አባባል ነው።
የሕይወት ትርጉም በእጃችን የለም። እንደ እቃ ሸመታ የተመቸንን ነው የምንመርጠው። በዛ ውስጥ የዳኝነት ወንበርን ተሻምተው የሚገዙ ብዙ አሉ። አትፍረድ የሚለውን ትዕዛዝ ለአማኞች ትተን፣ ስለሕይወት ውስብስብነት፣ ስለሰዎችም መልከ ብዙነት፣ እሱንም ስለመቀበል፣ "ራስህ ሁን፣ ሌሎችንም እንዲሆኑ ፍቀድ" (Be and let others be) ለሚለው ሐረግም አሜን ብንል!
5) ድል ለአርሰናል! እና ለሰፊው ሕዝብ ፡)
Agegeheu Asegid-
ከዝግጅት ክፍሉ፡- ከላይ የቀረበው ጽሁፍ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል፡፡ ኦሪጂናል ጽሁፉን እንደወረደ ከጸሃፊው ፌስቡክ ገጽ ላይ ታገኙታላችሁ፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ነፃ አስተያየት
Tagged under
Sunday, 31 May 2026 08:09
የአዲስ አበባ ፖሊስና የጣልያን ኤምባሲ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ደኔሮ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የጣልያን ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሚ/ር ሉካ ካርፔንትዬሪን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በሁለቱ አካላት መካከል በተደረገው የትውውቅና የውይይት መድረክ ላይ በቀጣይ ጊዜያት በጋራ ሊከናወኑ በሚችሉ የፖሊስና የፀጥታ ተግባራት ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።
በውይይቱ ወቅት ምክትል አምባሳደሩ ሚ/ር ሉካ ካርፔንትዬሪ፣ የኢትዮጵያና የጣልያንን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት በማንሳት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ በከተማዋ እያከናወነ ያለውን የፀጥታና የህግ ማስከበር ስራ አድንቀዋል። ኤምባሲያቸው ቀደም ሲል ለትራፊክ ሞተረኞች የሰጠውን ስልጠና ያስታወሱት ምክትል አምባሳደሩ፣ በቀጣይም ከፖሊስ ተቋሙ በሚቀርብ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍና ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሌተናል ጀነራል አስራት ደኔሮ በበኩላቸው፣ አዲስ አበባ የበርካታ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶችና የኤምባሲዎች መገኛ መሆኗን ጠቅሰው፣ የመዲናዋን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ ዋና ጠቅላይ መምሪያው ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ምክትል አምባሳደሩ ላደረጉት ጉብኝት በማመስገን፣ በቀጣይም ከኤምባሲው ጋር በተለይም በከተማ ፀጥታና ደህንነት ዙሪያ ይበልጥ በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
Published in
ዜና
Tagged under
Sunday, 31 May 2026 08:07
የአፍሪካ ሚሊየነሮች የት ነው የሚኖሩት?
በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ሚሊየነሮች እንዴት እንደተሰራጩ አስበው ያውቃሉ? የቅርብ ጊዜው የ"Henley & Partners" መረጃ እንደሚያመለክተው ደቡብ አፍሪካ ከአህጉሪቱ ባለጸጎች መካከል ሲሶ የሚሆነውን በመያዝ ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ፣ ግብፅና ሞሮኮ በደረጃው በቅርብ ርቀት ይከተላሉ።
የአፍሪካ አገራት በሚሊየነሮች ብዛት (በሺዎች) እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፦
ደቡብ አፍሪካ: 41.1ሺህ (33.6%)
ግብፅ: 14.8ሺህ (12.1%)
ሞሮኮ: 7.5ሺህ (6.1%)
ናይጄሪያ: 7.2ሺህ (5.9%)
ኬንያ: 6.8ሺህ (5.6%)
ሞሪሸስ: 4.8ሺህ (3.9%)
አልጄሪያ: 2.7ሺህ (2.2%)
ጋና: 2.6ሺህ (2.1%)
ናሚቢያ: 2.5ሺህ (2.0%)
ኢትዮጵያ: 2.4ሺህ (2.0%)
እነዚህ አኃዞች በበርካታ የአህጉሪቱ አገሮች ውስጥ እየታየ ያለውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና በአፍሪካ ያለውን ተለዋዋጭ የኢንቨስትመንት ገጽታ በግልጽ ያሳያሉ።
Great Africa-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ህብረተሰብ
Tagged under

