Administrator

Administrator

Saturday, 20 April 2024 12:41

ሥነ ቃላችን በጥቂቱ

እኛ ኢትዮጵያን እንደ ሌላ ሐብታችን ሁሉ ጥቂትም ቢሆን ያልተጠቀምንበት የሥነ ቃል ቅርሳችን ነው፡፡ ከ80 በላይ ብሔረሰብ እንዳለው አገር፤ የረዥም ዘመን ታሪክ ባለቤት ከመሆን አንፃር በርካታ ባህልና ትውፊት

እንዳለው አገር፣ ተዝቆ የማያልቀው የሥነ ቃል ሀብታችንን አልነካነውም፡፡ እንዲሁ ነገር ማጣፈጫ ከማድረግ ውጪ ብዙ አልሰራንበትም ፡፡
እንደ ሀገራችን ከፍታ፤ ውበትና ትንግርት፣ በሥነ ቃሉ ዘርፍ ብዙ አልገፋንም ፡፡ እያንዳንዱ ሐዘን ደስታችን ፤ዕድገት ውድቀታችን ፤ ማግኘት ማጣታችን ፤ እያንዳንዱ ክንውናችን የራሱ እሴትና መሠረት ያለው

መሆኑን፣ ለጥያቄ ለናሙና ያህል በማቅረባቸው ማሳያዎች ለማንበብ እሞክራለሁ፡፡
አንድ ማህበረሰብ የየዕለት ውሎውን፤የዘመናት ተግባሩን ፤ታሪካዊ እውነቱን በሥነ ቃል አማካኝነት ያስተላልፋል፡፡ ጥቃቅን ከሚመስሉ የዕለት ተዕለት ክስተቶች ተነስቶ ብዙ ማለት፤ ብዙ መፃፍ ይቻላል፡፡
ከ80 ብሔረሰብ በላይ ያላት አገር ማለት በሥነ ቃል ሐብቷ የበለጸገች ናት ማለት መሆኑን  አያጠራጥርም፡፡ ሥነ ቃሎች በበርካታ ሥፍራዎች በተመሳሳይነት ፤በቅርጽ ግን በልዩነት ልንመለከታቸው ወይም

ሊያጋጥሙን ይችላሉ፡፡ ማህበረሰባችን ለእያንዳንዱ ተግባር ሥነ ቃሉን ይጠቀማል፡፡ በአመጽ፤ በእርሻ፤ ፤በጦርነት፤ በሰላም፤ በሠርግ በለቅሶው….፡፡ በምሳሌ እያስደገፍን ለማቅረብ እንሞክር ፡፡ ሥነ ቃሎች

ከሚተላለፍባቸው መካከል ተረት፤አፈ ታሪክ ፤ሀተታ ተፈጥሮ፤ምሳሊያዊ አነጋገር፤ እንቆቅልሽ፤የሥራ ዘፈኖች፤ የክብረበዓል ዘፈኖች እና የልጆች ጨዋታዎች ይገኙበታል፡፡ ከእነዚህ የሥነ ቃል ምንጮች ምን ያህል ክፍሎችና

ዘርፎች፣ በአካባቢያችሁ  አስተዋውቃችኋል ብለን ብንጠይቅ፣ ገና ብዙ እንደሚቀረን መረዳት ይቻላል፡፡
የየክልልና የዞን ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች መሥራት የሚገባቸውን ትተው በሌላ እሴት በማይጨምሩ ተግባራት ተጠምደው ይውላሉ፡፡ ሥነ ቃሎቻችን አይደለም ለክልል ለሀገር፤ከሀገርም በላይ ለአህጉርና ለዓለም

አደባባይ ማዋል እንችላለን፡፡
በሥነ ቃሎቻችን መውደቅ መነሳታችን ፤ ማግኘት ማጣታችን ፤ደስታ ሀዘናችን፤ታሪክ ድርጊታችንን ማሳየት፤ ማስተማር እንችላለን፡፡ በመጸሐፍ ፤ በፊልም፤ በዘፈኖች አካትተን፣ በማቅረብ እንደ ማጣፈጫ መጠቀም

እንችላለን፡
እስኪ ዘወትር በንግግራችንና በጽሑፋችን ከምንጠቀምበት የሥነ ቃል ዘርፎች አንዱ በሆነው ምሳሌያዊ አነጋገር እንጀምር፡፡ ብዙም የማይዘወተሩትን ለማሳያት ያህል፡-
ተስካር ያየ ተማሪ ሸቀጥ ያየ አጣሪ
ዝንብ ቢጠራቀም
ጠጉራም ውሻ አለ ሲሉት በራብ ይሞታል
ፈላጻ በአየር ውስጥ አልፎ ፍለጋ አይተውም
ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው፤ ቀንዱ ይከለክለዋል
ለመከራ የጻፈው ቢነግድም አያተርፍም
በሰም የተጣበቀ ጥርስ ቢስቁበት አይደምቅ፤ቢበሉበት
ሰው ሆኖ የማይበላ፣ እንጨት ሆኖ የማይጨስ
ብረት ካልፈላ አይላላ
ደም ማልቀስ ድንጋይ መንከስ……..
ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አሰፋ፣ ነፍስን ይማርና፣ በጻፈው የሥነ ጽሑፍ መሰረታዊያን መጸሐፍ ገጽ 33 ላይ  ምሣሌያዊ አነጋገር ሲገልጽ፤ ሀ ምሳሌ አነጋገሮች በውስጣቸው አምቀው የያዟቸው ሃሳቦች፣ ከማህበረሰቡ

የዕለት ተዕለት ኑሮ ገጠመኝና  ምልከታ የተገኘ ሲሆኑ፤  ማህበረሰቡ የሚያምንባቸውና ታዋቂነታቸውን ያረጋገጠላቸው የሃሳብ መግለጫዎች ናቸው >> ይላል፡፡
የምሳሊያዊ አነጋገርን ሚስጥር ለመረዳት የተነገረበትን አውድ በውሉ ማወቅ አስፈላጊነው፡
ሚስጥሩ የሚታወቅ    ፍችው በመሆኑ ከተነገረበት ሁኔታውም ለብቻው ተነጥሎ የሚሰጠው ትርጉም አንዱን አቅጣጫ ብቻ የሚያመለክት ይሆንል፡፡
እንደ ምሳሊያዊ አነጋገር ሁሉ ሌሎችም የሥነ ቃል ዘርፎች በምሳሌ እያስደገፍን፣
ሁለተኛው ምልከታችን እንቆቅልሽ ላይ ማድረግ እንችላለን፡፡ እንቆቅልሽ በተለይ (ታዳጊና) የልጆች አእምሮን ንቁ ለማድረግ ፤ግንዛቤያቸው እንዲሰፋ ፤እንዲመራመር ፣ እንዲተጉ፣ እግረ መንገዳቸውንም ሥርዓትና ደንብ

እንዲያውቁ ማድረጊያ ቅርስ ነው፡፡ በእንቆቅልሽ በጥያቄ ከመፈተኑ በተጨማሪ ለማዝናናት፤ሳቅ ለመማርም ይሆናል፡፡ ለምሌ ያህል ፡-
ለማታምነው ፊቷ ፡ ምራቅ ነው ቅባቷ - ድመት
ቡቱቶ ለባሽ - ሰውን ለማኖር የተፈጠረ - እንሰት
አልቀረም ተቀጥቅጦ - አስተኛችው ፈርጦ ፈርጦ - ጌሾ
ሺህ አይን አለው፤አጥንት የለውም - እንጀራ
ዓይንዋን ተኩላ ገበያ የምትወጣ - ባቄላ
ወገበ ጎባጣ ሁሉ ቆምጣ ቆምጣ - ማጭድ
ከመሬት ወድቄ አንስቼ ብይዘው አለቀ - በረዶ
እንቆቅልሽ ፤ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን፣ በመጽሐፍ በተለያየ ክፍሎች መድቦ አሳይቶናል፡፡ በሰው የአካል ክፍሎች ፡ በእንስሳት በተክሎች ፤ በምግብ አይነቶች ፤ በእህል አይነቶች፣ .በቤት ውስጥ ቁሳቁሶች፤ በሥራ

መሣሪያዎች በተፈጥሮ ገጽታዎች ከፋፍሎ ለንባብ አብቅቶልናል፡፡ የምወደው መምህሬ ዘሪሁንን አመሰግናለሁ፤ መሬቱ ይቅለልህ ከማለት ውጪ ምን ማለት ይቻለኛል፡፡
ለማሳያ ያህል ይህን  ካልኩ፣ በየክልሉና ዞን የሚገኙ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ቢሮዎች፣ ሥነ ቃላቶችን ለማሳደግ ፤አደባባይ ላይ ለማውጣት መትጋት እንደሚኖርባቸው ለማሳሰብ እወዳለሁ፤ በበርካታ የስራ ዘርፍ፤

ባህላዊ ዘፋኞች፣ የክብር በዓል ዘፋኞች፤ የልጆች ጫዎታዎች፤ መጣጣጥፎች፤ አፈ ታሪኮች ተረቶች ተሰብስበው ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል፡፡ በዝባዝንኬ ጉዳይ ተጠምዶ ከመዋል ለሀገርም ለክልልም ሆነ ለዞን እሴት

የሚሆን  ሥራና  ባህል ላይ  ቢተኮር ተገቢ ይመስለኛል፡፡
(ጽሑፉን ለማደራጀት የተጠቀምኩት የመምህሬ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አሰፋው መጸሐፍ.፤ “1የሥነ ጽሑፍ መሠረታውያን“ መሆኑን እየገለጽኩ እሰናበታለሁ፡፡)

“ሁሉንም ሞክሩ የተሻለውን ያዙ” የሚለውን አባባል ቢያንስ እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲ (የዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ገብቶ የተማረ ተማሪ ያውቀዋል። በየዲግሪው ላይ የተፃፈ

 መሪ ቃልና ጥቅስ ነው። በህይወታችን ውስጥ በርካታ ውጣ ውረዶች ይገጥሙናልና በየፈርጅ በየፈርጃቸው እየሞከርን፣ እየወደቅን እየተነሳን፣ በጎና ሰናይ የሆኑትን እየለየንና እያጠናከርን፣ የሚበጀንን መያዝ አለብን፤

ለማለትም ነው። በእርግጥም በእያንዳንዱ ሙከራ ወቅት፣ እንቅፋት፣ ችግርና መከራ መኖሩ አይቀሬ ነውም ለማለት ነው። ለዚህ አብነት ይሆነን ዘንድ የሚከተለውን የአበው ወግ እንይ።
ሁለት ደገኛ ገበሬዎች፤ ኑሮ አልገፋ ብሎ ቁም ስቅላቸውን ያሳያቸዋል። አንዴ ዝናቡ እምቢ ይላል። አንዴ በሬዎቹ ይለግማሉ። አንዴ ደቦ ወጪዎች አይመቻቸወም። አንዴ ደሞ ሰብሉን ተባይ ይፈጀዋል። በእጅጉ

ይቸገራሉ። አዝመራውም አልሰምር ይላል።
አንደኛው ገበሬ አንድ ቀን መላ ዘየደ። ንግድ መጀመር አለብኝ ብሎ ወሰነና አዲስ ሙከራ ጀመረ። በሬዎቹን ሁሉ ሸጠ። የዘር እህሉንም ከሰቀለበት አውርዶ፣ ለቤት የሚፈልገውን ያህል አስቀረና አውጥቶ ሸጠ።

ከዚያም ባገኘው ገንዘብ ወደ ቆላ ወርዶ ለማረሻ ለዶማና ለማጭድ ወዘተ መሥሪያ የሚሆን ብረታ ብረት ገዛ። የገዛውንም ብረታ ብረት ወስዶ ለአገሬው ደገኛ ህዝብ ቸበቸበው። ቀስ በቀስ ኑሮው ተለወጠ።

አዱኛም አገኘ። ለውጡ በቀዬውም በአገሩም ተወራ፤ ተሰማ። ሀብቱ ጣራ ነካ። ይጭነው አጋሰስ ይለጉመው ፈረስ በደጅ በግቢው ሞላለት።
“አያ፤ እንዲህ ባንዴ የሆንከው ምን ዘዴ ከውነህ ነው ጃል?” ብሎ ይጠይቀዋል።
ምን የዱሮ ገበሬ የዛሬ ነጋዴ፤ የተሰማራበትን ሙያ ያስረዳዋል። ወደዚህ ስራ ቢገባ፣ በቀላሉ ካብታም እንደሚሆን ይገልጸለታል።
ሁለተኛው ገበሬም፤ ሳይውል ሳያድር ምክሩን ተቀብሎ በስራ ላይ አዋለና፣ ያለ የሌለ ንብረቱን ወደ ገንዘብ ለወጠ። ንግድ ጀመረ።
ቆላ ወረደ። ያገሩን ብረታ ብረት ገዛ። ተሸከመናም ሽቅብ ወደ ደጋ መንገድ ጀመረ። ሆኖም፤ ገና ዳገቱን አጋምሶ ሳያበቃ በተሸከመው ብረታብረት ክብደት ሳቢያ፣ ወገቡንም ጉልበቱንም ከዳውና ተዝለፍልፎ ወደቀ።

አወዳደቁም አጉል ነበርና አረፋ አስደፈቀው።
አንድ መንገደኛ የሰፈር ሰው ድንገት ሲያልፍ  አይት ኖሮ ወደሱ ቀርቦ፤ “አያ እገሌ፤ምን ሆነህ ነው?” ሲል ይጠይቀዋል።
ገበሬውም፤ “ወይ ወዳጄ፤ ያ ጎረቤቱ አያ እገሌ የሠራኝን ሥራ ለጠላት አይስጥ!” አለና መለሰለት።
“ምን አደረገህ? የልብ ወዳጁ እማይደለህ እንዴ? በሞቴ ንገረኝ፤ ምን አደረገህ?”
“ትርፉን ነግሮ መከራውን ሳይነግረኝ፤ ይሄው ለዚህ ዳረገኝ!!” አለው።
***
ሁሉም ስራ ችግሩ የሚታወቀው ሲሞከር ነው። ንግዱ፣ ትምህርቱ፣ ልማቱ፣ አስተዳደሩ፣ ፓርላማዊ ሥነ-ስርዓቱ፣ ምርጫው፣ ፍትሐዊ ባህሉ ወዘተ--ሁሉም ተሞክሮ፣ ተሰርቶ ታይቶ ነው። ካላዋጣ ደግሞ ካፈርኩ

አይመልሰኝ ሳይሉ፣ የማይሰራውን ፈጥኖ ጥሎ ሌላ መንገድ መፈለግ ግድ ነው። ስህተትንም በወቅቱ አርሞ፣ ሰናዩን አለምልሞ፣ ጠንካራውን አጎልብቶ፣ መያዝ ደግ ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ ከአምናው ምን

ተምረናል?  ለነገስ ምን ጨብጠናል? የማለት ድፍረትና ግልጽነት እንዲኖረን ያሻል።
አዲስ ፈር ለመቅደድ መስዋዕትነትን መክፈል፣ ያልተሞከረውን መሞከር፣ ያልታየውን ማየት ያስፈልጋል። ትላንት በሀሄድንበት መንገድ ዛሬም ብንመላለስበት ኮቴአችንን ከመጨረስ በቀር፣ ወደላቀ ግብ መድረስ እርም

ነው። ትላንት በተሟገትንበት፣ በተዛለፍንበት፣ ላንደማመጥ በተጯጯህንበት ሸንጎ ዛሬም ያንኑ እሪታና ጩኸት፣ ያንኑ ችኮላና ድንፋታ፣ ያንኑ እርግማንና ውግዘት ብናላዝን ብናስተጋባበት፣ ድምጻችን ከመዛሉ፣ ጉዟችን

ከመሰናከሉ በቀር ብዙ አንራመድም። ከመበቃቀል መተራረም፣ ቂም ከማርገዝ  የቂምን ሥነ-ነገር መርምሮ ለመንቀል መጣጣር፤ ዋና ጉዳይ የሚሆነውም ለዚህ ነው።
ከቶውንም ትላንት እጅግ ጨለማ የመሰለንን ንፍቀ ክበብ፣ ዛሬ በመጠኑ እንኳን ደብዛዛ ውጋጋን ካየንበት ውጋጋኑን ለማስፋት እንጂ “ይሄውላችሁ፣ ዛሬም በደምብ አላነጉትም!” እያልን ቡራ-ከረዩ ብንል፤ አንድም

የለውጥን አዝጋሚ ሂደት መካድ፣ አንድም ያ ውጋጋን ብሩኅ ፀዳል እንዳገኝ የእኛን አስተዋጽኦ መንፈግ ይሆናል። ባለፈው፣ ባልሞከርነው ነገር ሳቢያ ባጠፋነው ጊዜ ስንፀፀት፣ አዲስ ሙከራ የምናደርግበትን ሌላ ውድ

ጊዜአችንን እንዳናጨልም መጠንቀቅ ይበጃል። ሀገራችን አሁን ላለችበት ቦታ የበቃችውኮ በደጉም በክፉውም ሂደት ሳቢያ ነው። ማህበረሰባችንም እንደዚያው። ክፉውን አስወግዶ አንድ እርምጃ ለመራመድ ግን አዲስ

ሙከራ እንደሚያስፈልግ በመገንዘብ መንቀሳቀስን ይጠይቃል። የሌሎችን ድምፅ በትዕግስት መስማት፣ መንገዳቸውን በጥሞና ማየት፣ እኛ ያደረግንላቸወን ያህል እነሱም ያደርጉ ዘንድ ሁኔታዎችን ማመቻቸት። ለዚህ

ደግሞ ትርፉን ብቻ አውቀን መከራውን ሳናውቅ ከተጓዝን ህልማችን ሁሉ ከላይ እንደተጠቀሰው ገበሬ ጉልበት አጥቶ ይወድቃል። የራዕያችንም ክንፉ ከወዲሁ ይሰባበራል። ተስፋችን ሳይጫር ይከስማል። በዚህ መንገድ

የሄዱ ጳጳሱም፣ ሼኪውም፣ ሹሙም ዜጋውም፣ የፖለቲካ ቡድኖቹም፣ መንግስታዊ የሆኑና ያልሆኑ ድርጅቶቹም አበክረው ማስተዋል ያለባቸው ቁምነገር ይሄ ይመስለናል።
“ያለፈ ጥረታችንን ሳስታምመው ትዝ ሲለኝ
ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው እሚቆጨኝ”
ለማለት መቻል አለብን እንደ “ቴዎድሮስ”። ያልሞከርነውን ለመሞከር ዝግጁነት ወሳኝ ነው!! የመንፈስም የአካልም። ከዚያ በኋላ “ሁሉንም ሞክሩ፤የተሻለውን ያዙ”! ለመባባል እንችላለን።

ብልፅግና “የሚዲያ ሠራዊት” አደረጃጀት የለም ሲል አስተባበለ

በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹና በሚቃወሙ ግለሰቦች

ላይ ሐሰተኛ መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ ሥርጫትላይ መሳተፋቸውን   ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን አመለከተ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አመራሮችም በፓርቲው የወረዳ መዋቅሮች ትዕዛዝ በተለይም የመንግሥትን ገፅታ በሰው ሰራሽ መንገድ ለመገንባት ፌስቡክ ላይ በሚደረጉ አሳሳች ዘመቻዎች ላይ እንደሚሳተፉ

የቢቢሲ ምርመራ ያሳያል። ቢቢሲ ለዚህ ምርመራ በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳ አመራር፣ የፓርቲ አባል እንዲሁም በከተማዋና በፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎችና

ባለሙያዎች አነጋግሯል።
በተጨማሪም  በአዲስ አበባ ከተማ ሰባት ክፍለ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ የፓርቲው የወረዳ መዋቅሮች በዋትስአፕና ቴሌግራም ግሩፖች ውስጥ ለሶሻል ሚዲያ ዘመቻዎች የተለዋወጧቸውን መልዕክቶች ተመልክቷል።

በግሩፖቹ ውስጥ ለወረዳ አመራሮችና ሚዲያ ሠራዊት አባላት የሚሰጡ ትዕዛዞችንና አፈጻጸማቸውን የተከታተለ ሲሆን የፌስቡክ ዳታዎችን በመውሰድም መተንተኑን ይጠቅሳል።
ሜታ (ፌስቡክ) ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ፤ “ሐሰተኛ አካውንቶችን” በመጠቀም “በኢትዮጵያ መንግሥት” የፌስቡክ ልጥፎች ላይ “ብዛት ያላቸው አዎንታዊ አስተያየቶች” መሰጠታቸውን በምርመራ እንደደረሰበት

አስታውቋል። ሜታ፤ በዚህ ድርጊት ላይ በተሳተፉ ሐሰተኛ አካውንት እና ገፆች ላይ እርምጃ መውሰዱን የገለጸ ሲሆን፣ ቢቢሲ ሲከታተላቸው የነበሩ አካውንቶችም እንዲወገዱ ተደርገዋል።
የብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ፤ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚባል አደረጃጀት “አለመኖሩን” በመግለፅ ለቢቢሲ በሰጠው የፅሁፍ ምላሽ፤ ጉዳዩን አስተባብሏል። የፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት፤ “በተለይ ‘ሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ

ንግግር ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ ጽሑፎችና ምስሎች ተሠራጭተዋል’ በሚል የተገለጸው ፍጹም ተቀባይነት የሌለው አገላለጽ ነው” ብሏል።
የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት ፌስቡክ ላይ የሚያርጓቸውን ዘመቻዎች በተመለከተ ለሦስት ወራት ያካሄደውን ምርመራ ውጤት በዝርዝር አስነብቧል።
ከሦስት ወራት በፊት ጥር 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ጀምሮ “አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ” የሚሉ ልጥፎች በበርካታ የኢትዮጵያውያን የፌስቡክ አካውንቶች እና ገጾች መሠራጨት ጀመሩ።
በፎቶና ጽሁፍ ከተቀናበረ ምስል ጋር የተሠራጩት እነዚህ ልጥፎች ፌስቡክ ላይ የወጡት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ አቡነ ጴጥሮስ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ መጓዛቸውን ተከትሎ

ነበር። የፌስቡክ አካውንትና ገጾች እንደተለጠፈ ቢቢሲ አረጋግጧል። ከግራፊክስ ምስሎች ጋር የተለጠፈው ይህ ጽሁፍ፤ ጥር ሁለት ቀን ብቻ  ቢያንስ 898 ጊዜ ፌስቡክ ላይ ተጋርቷል።
የምስሉ መግለጫ, አቡነ ጴጥሮስ “ኮብልለዋል” በሚል ፌስቡክ ላይ ከተሠራጩት ልጥፎች ውስጥ አብዛኛዎቹ “ፅንፈኝነት_ይውደም” እና “መከላከያ_የሀገር_ጋሻ” የሚል ሀሽታግ ተያይዞባቸዋል ይላል- የቢቢሲ

ምርመራ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን “የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተናፈሰ ያለው ወሬ እጅግ የተሳሳተ” መሆኑን በመጥቀስ፣ ጉዳዩን ያስተባበለችው በማግስቱ ነበር ያለው ቢቢሲ፤ ስለጉዳዩ ጥያቄ የቀረበላቸው

አቡነ ጴጥሮስ፤ አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ መግለፃቸውን አስታውሷል።
ይህ መረጃ ከተሰራጨ ከአንድ ወር ገደማ በኋላ “ኮብልለዋል” የተባሉት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ኢትዮጵያ ቢመለሱም፣ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጋቸውን

አስታውሷል።
በዕለቱ ስለ ሲኖዶሱ ዋና ፀሐፊ “መኮብለል” ፌስቡክ ላይ የተሠራጩት መረጃዎች፤ በመደበኛ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የተሰራጩ የተለመደው ዓይነት የሐሰተኛ መረጃ አልነበሩም። ቢቢሲ ባደረገው ክትትል፤ የመረጃዎቹ

ሥርጭት ካለፈው ዓመት ጥር ጀምሮ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር ቅራኔ ውስጥ የገባውን መንግሥት ከመሠረተው ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ጋር ግንኙት እንዳለው የሚያሳዩ ማስረጃዎችን አግኝቷል። የብልፅግና የሚዲያ

ሠራዊት አባላት በዚህ ዘመቻ እንዲሳተፉ ያደረገው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ የፓርቲ መዋቅር ብቻ አልነበረም። በቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ አባላትም የአቡኑን “መኮብለል” የሚገልጹ

ጽሁፎችና ምሥሎች እንደተላኩላቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ አመራር የሆኑ ግለሰብ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
በወረዳው የፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አመራር አባላት የዋትስአፕ ግሩፕ ላይ እነዚህ ምሥልና ጽሁፎች የተላኩት፤ “ዘመቻ አድርጉ” ከሚል ትዕዛዝ ጋር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
“ግሩፑ ላይ የተላከው ጽሁፍ የአቡነ ጴጥሮስን ዜግነት ይገልጽና ‘ከሀገር ወጡ፣ ኮበለሉ’ ይላል። ‘የውጭ ዜግነታቸውን ሽፋን አድርገው የተለያዩ የሐሰት ሰነዶችን በማዘጋጀት ከሀገር በሕገ ወጥ መንገድ ወጥተዋል’

ይላል” ሲሉ፣ በዋትስአፕ ግሩፑ ላይ የተለቀቀው ጽሁፍ በዕለቱ በፌስቡክ ላይ ከተሠራጨው ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
የአቡነ ጴጥሮስ ጉዳይ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፅህፈት ቤት የወረዳ መዋቅሮች አስተባባሪነት የተደረገ ብቸኛው የፌስቡክ ዘመቻ አይደለም ብሏል- በምርመራው ውጤት።
ሆኖም የብልፅግና ፓርቲ ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ፤ “የሚዲያ ሰራዊት” የሚባል አደረጃጀት የለም ሲል ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል።

አልነጋም፤ ካሳንቺስ ሰውዬው መኖሪያ ቤት በር ላይ ደርሰናል።
ደወልን፤ ስልክ አነሳ። አሁን ልቤ ዐረፈ። ብዙ ጊዜ መንገድ ስለመኼድ ስንመካከር ደስ ብሎት ይሰማል። ዐልፎ ዐልፎ ደግሞ ይሳተፋል። “እዚኽ ደርሰን እንዲኸ አድርገን” ዓይነት። ከዚያ ጠዋት እንቀጣጠራለን። በሰዓቱ ግን የእሱ ስልክ አይሰራም።
ሻንጣውን አንጠልጥሏት ወጣ።
መንገዳችንን ቀጠልን።
እንዲህ ሆነን ማፌድ ደርሰናል። ዛሬም ድረስ ዓሌክስ እግሩ ከቤት ይውጣ እንጂ፣ የሆነ ቦታ ሲደርስ ለቦታው ስርዓት እንደምን ተገዢ እንደሆነ ያየሁበት ጉዞ ሆነ።
መስቀል ልናሳልፍ የደጉ ሰው ነዳ ሽጉሞ ቢሎ እንግዶች ሆነናል። መስከረም እኩል ሲሆን እኖር፣ ማፌድ ባሩኝ የምትባለው ትንሽ መንደር ገባን።
ከዚያ በኋላ አምስት ቀናት ቆየን። ዝም ብዬ ሳስበው ይደንቀኛል። ዓለማየሁ ገላጋይ ጥቂት ሰአት ከሰው ጋር ሲያሳልፍ የዚያን ሰው ሁሉን ነገር የነጠቀ የሚመስለው፣ ሽቁጥቁጥ ነው። በእኔና የማፌድ ቀናት ግን መሰልቸት አልታየበትም። ያደምጣል፤ ደግሞ እግሩ አይድረስ እንጂ፣ ንባቡ የደረሰበት ቀዬ ብዙ ነውና፣ ከሚያውቀው እያነሳ ይጠይቃል።
የስነ-ሰብ ጥናት ባለሙያዎች እንደ እሱ ያሉትን ሰዎች Cultural Intelligence ያላቸው ይሏቸዋል። ዓሌክስ እንዲህ ያለ ሰው እንደሆነ አምናለሁ። ባህልን የሚረዳው በብልሃት ነው። በዚያ ላይ ትርጉም የሚሰጥበት ብቃት ያስቀናኛል።
ደመራ የለኮሰን ቀን ከቤቱ አባወራዎች ጋር ረዥሙን የችቦ ጫፍ እሳት አስነክሶ፣ በዚች የባሩኝ መንደር ጀፈሮ ላይ ሲራመድ፣ አንድ መስቀል ከቀዬው ያልተለየ ጉራጌ ይመስል ነበር።
ዓሌክስ ሌላ አካባቢ ሲቀላቀል ሰላማዊ ስለሆነ አይረብሽም። በአካባቢውም ላለመረበሽ ራሱን ከስፍራው ጋር በጣም ያቆራኛል። ከጉራጌ ምድር ስንመለስ፣ የጉዟችን ምክንያት ለሆነው ወንድማችን ሃይሉ ሰለሞን “ሰውዬው እሺ ብሎ ከቤቱ ይውጣ እንጅ ቆይታውን ማጣጣም የሚችል የጉዞ ሰው ነው” አልኩት። ተሳሳቅን።
አካባቢን የሚረዳበት መንገድ በስራዎቹ ላይ ፍንትው ብሎ ይታያል። ለምሳሌ “የሞጆ ቀትሮችን” በ”የብርሃን ፈለጎች” ላይ ሳነብ፤ የኢኮሎጂ ትዝብቱና የገለፃ ርቀቱ ደራሲው በእርግጥም መቼቱን ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን፣ ሳይንሳዊ በሆነ ሚዛን መረዳት ላይም የሚከበር ሰው ነው እላለሁ።
ከተፈጥሮ ያለውን ዝምድና በሥራዎቹ ተመልክቻለሁ። መራር ድምፆች በሰው በአካባቢና በተፈጥሮ ህልውና መስተጋብር ተጋምደው ይሰማሉ። “ታለ፤ በእውነት ስም” ላይ “ከተማ ሙቀት እና ጩኸት ነው.” ይላል። ይኼ አሁን የረቀቀው የተፈጥሮ ጥበቃ የሳይንስ ሊቃውንት ይዘውት ብቅ ያሉት የአካባቢ ፍልስፍና ነው። ዓለማየሁ በአጭሩ የGlobal Warming እና Sound  Pollution ችግር ከከተሜነት ቅጥ ማጣት ጋር የተሳሰሩበትን ቀውስ ትብታብ ያሳየናል። ወረድ ብሎም፤ “… ህይወት በከተማ ውስጥ ቅጥ አጥታለች፤ ተፈጥሮ ህብረ ዝማሬዎቿን ይዛ ተሰድዳለች። ወፎች- አይዘምሩም፣ ውሆች ፀናፅናቸውን አያንሿሹም፣ ዛፎች ከነፋሳት ጋር አይላፉም። ከዚህ በመነሳት፣ ዓለም አረንጓዴ ትችት ለሚለው ዘመነኛ አብዮት ዓለማየሁ Ecocriticismን በፈጠራ ሥራዎቹ በማሳየት ለአካባቢው የቀረበበትን ስሱ ልብ እንድናይ አድርጎናል።
ብዙ ጉዞዎችን አብረን ተጉዘናል። ለቀናት ቆይተናል። ምርጫው ያለበትን ቦታ በቅጡ መረዳት እንደሆነ አይቻለሁ። በእድሜ ጠና ካሉ ሰዎች ጋር መጨዋወት ይመርጣል። ብዙ ሰአት ወስዶ ራሱን እየነቀነቀ ያደምጣቸዋል።
ብዙዎች Bibliophile or Bookworm ስለሆነው ዓለማየሁ ያውቃሉ። እሱ ግን Empathetic የሚሉት ዓይነት ሰው ነው። ጥልቅ ብሎ ያደምጣል፤ ይረዳል። ከተረዳው ነገር ጋር አብሮ ይኖራል። ደጋግሞ “ለተፈጥሮ ግድ የለኝም። ፏፏቴ ለማየት ገደል ባልወርድ እመርጣለሁ” ይለኛል። ይሄንን እንዳልቀበል ያደረጉኝ ጉዞዎች ግን ነበሩን። ተራራው አጠገብ አብረን ስንቆም፣ ተራራውን የተመለከተበትን ስስት አልረሳውም።
ወደ አንኮበር አብረን ተጉዘናል። እመ ምህረት ተራራ አጠገብ ቆመን ለተፈጥሮው እጅ ሲሰጥ አይቻለሁ። ከዚያ የማያቆም ጥያቄ ቀጠለ፤ መኪናው እንዲቆም አሳሰበ።
“ቁንዲ የምትታይበት እንቆምና ፎቶ እንነሳለን፣” ይለናል። በእርግጥ ወደ ቁንዲ እንሂድ አይበል እንጂ ቁንዲ አጠገብ መድረስ ግን መሻቱ እንደሆነ ተረዳሁት። እንዲያ ባይሆን፣ ቅንብቢት በዚያ መልኩ መች ትገለጽ ነበር? ያለፈባቸውን ብቻ የሸኖ ጎዳናዎች በዚያ መልኩ ሊረዳቸው እንደምን ይችላል?
ተራራ ብቻ ሳይሆን፣ ውኃም ትንፋሹን ስትር አድርጎ ተፈጥሮን ያደምጥ ዘንድ ያደርገዋል። ወደ ጣና አብረን ተጉዘናል፤ በተደጋጋሚ። ጀልባ ላይ ከወጣ በኋላ ዐይኑን ባሕሩ ላይ ተክሎ ዝም ይላል። ያን ዓይነት ምሳጤውን የማስታውሰው፣ በሰዎች መካከል ሆኖ ዐልፎ ዐልፎ እጁን አፉ ላይ ያደርግና በሐሳብ ሩቅ ሲሄድ ነው። ይሄንን አይነት ስሜት በሀዋሳ የሀይቅ ዳርቻ አሞራ ገደል አረፍ ብለን ስንጫወት፣ እሱ ዐይኖቹን ሰድዶ ከፍቅር ሐይቁ ጋር ሲነጋገር አይቼበታለሁ። በጥልቅ ስለሚረዳው አካባቢ አንዳች ነገር ሲገልጽ ይነዝራል። ጎንደርን “የህልሜ ከተማ” ሲላት የቀናሁት ቅናት አሁንም አልለቀቀኝም። ወደ ጎንደር ስንሄድ ብዙ ጊዜ ሳይደርስ መመለስ የማይፈልግበት ቦታ ሞኝ መቆሚያ ነው። ለምን እንደሚወደው አላውቅም። ቦታው የጉልበት ሠራተኞች አሰሪ ጥበቃ የሚቆሙበት ሲሆን፣ ዓሌክስ በጎንደር ቆይታው አንዱን ቀን ሞኝ መቆሚያ ደርሰን እንምጣ ሳይለን አይቀርም።
ገና የፋሲል ከተማ ሲደርስ “ዋሴ ነጋሽ ሞኝ መቆሚያ ደርሰን አንመጣም?”ይጠይቃል። እንስቃለን። ወግ አጥባቂዎቹ አካባቢዎች አብረን ስንቆይ ወግ አክባሪው ዓለማየሁ ስፍራውን መስሎ የብዙ አባቶችን ልብ በልቶ ይመለሳል። ትዝታዎቹ ሆነው ይቀራሉ። ዓሌክስ ወደ ፀሐይ መውጫ ሲሄድ ደግሞ ቀላልና ተግባቢ ሰው ሆኖ ይገለጣል። የባሕር ዳር ልጆች የሚያውቁትን ዓሌክስ የድሬ ልጆች ኤውቁትም፤ ሁለቱንም የሚያውቀው ዓሌክስ ግን ቦታን፣ ሰውንና ባህልን የሚረዳበት መንፈሱ ድንቅ ነው።
በነገራች ላይ፣ ኣለማየሁ ገላጋይ ደርሼ ጥምድ ያደረኩት ሰው ነበር። በእልህ ሥራዎቹን አላነብም ብዬ ብዙ አመጽኩ። በጣም ብዙ ጊዜ። ለምን እንዲያ እንደሆንኩ  ሳስበው ብቻዬን ፈገግ እላለሁ። በሰዎች ጥያቄና ምልጃ አንድ መጽሐፉን ለማንበብ ተስማማሁ። “ወሪሳ”ን አነበብኩ። ከዚያ በኋላ በሆነው ተቃራኒ ስሜቴ በጣም እገረማለሁ።
ዓለማየሁ አምጰርጵርን ብቻ ሳይሆን፣ እኔንም አምጰረጰረኝ። ያለ ዕረፍት ሌሎቹንም ስራዎቹን አከታትዬ አነበብኩ። አንድ ቀን ሳገኘው ነገርኩት። አቀርቅሮ አድናቆቴን እንደ ሸክም ቆጥሮብኝ ዐለፈ። የጋራ ወዳጆች ነበሩን። አስደናቂው ነገር ግን  ትውውቃችን የጠነከረው በጉዞ ሆነ። ወደ ባሕር ዳርና ጎንደር አብረን ተጓዝን፤ ለወዳጅነታችን የማዶ ለማዶ በራፉን የገነጠልንበት ቆይታ ሆነ። እንዲህ እንደ ቀልድ አመት ዓመቱን እየወለደ፣ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን አብረን የምንውል ወዳጆች ሆንን።
“ወሪሳ” አስማት የሆነ ሥራው ነው፤ ብዙ ሰውም ይጋራኛል። “በፍቅር ስም”፣ “ታለ፤ በእውነት ስም” እና “ሐሰተኛው፤ በእምነት ስም” እጅግ የወደድኳቸው ስራዎች ናቸው። ከኢ- ልቦለዶቹ “ኢሕአዴግን እክሳለሁ” ያስገርመኛል፡፤ “ውልብታ” ሳትገባኝ የቀረች ስራ ናት።
በወዳጅነታችን የደረስኩበት ድምዳሜ ሰውዬው ዓለማየሁ፣ ከደራሲው ዓለማየሁ በላይ አስደናቂ ሰው ነው የሚል ነው። ስሱ ልብ አለው፤ ትልልቆቹን ያከብራል፤ ከነክብራቸው በደስታ ያልፉ ዘንድ ቁጭት መሰናክላቸውን የሚያነሳ መንገድ ጠራጊ ነው። ታዳጊዎችን አቅጣጫ ለመምራት መንገድ ቆሞ ይጠብቃል። ራሱን ዝቅ አድርጎ ከፍ የሚሉበትን ይመራል። ኣለምን ይንቃታል። ስስት አያውቅም፤ ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ፍቅሩን የማይሰስት ወዳጅ ነው።
ምንጭ፡ -“መልክአ ዓለማየሁ” ፤ቴዎድሮስ አጥላው (አርታኢ)

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የክብር ሽልማት ምርጥ 5 ዕጩዎች ታወቁ !


በቃል መልቲሚዲያ አማካይነት ‹‹ክብር ሽልማት›› በሚል ሀሳብ ለደራሲዎችና ለሚዲያ ባለሙያዎች ዕውቅና ለመስጠት ታላቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት የክብር ሽልማት አዘጋጆች ካለፈው ዓመት አንስቶ ባለሙያዎች፣ በድረገጽ እና በሌሎች የመገናኛ አውታሮች እንዲጠቁሙ ሲያደርግ ነበር፡፡

በዚህም መሰረት በሚዲያና በድርሰት ዘርፍ የተጠቆሙ ሰዎችን በድረገጽ ላይ በማውጣት ባለፉት 30 ቀናት ዳኞችና ህዝብ እንዲመርጡ ማድረጋችን ይታወሳል፡፡

አጠቃላይ በ16 ዘርፎች በባለሙያዎችና በሕዝብ ድምጽ ሲሰጥባቸው የቆየ ሲሆን፤ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ስርዓቱም ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 5 ቀን  2016 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ከእያንዳንዱ ዘርፍ ከተጠቆሙ ሥራዎችና  ሠራተኞች ውስጥ ምርጥ 5ቱን ለመምረጥ ከህዝብ የተገኘን 40 ከመቶ ድምጽ እንዲሁም በዳኞች የተሰጠን 60 ከመቶ አንድ ላይ በማድረግ፣ ክብር ሽልማት በ16 ዘርፎች ምርጥ አምስት ያላቸውን  ባለሙያዎች ዛሬ ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ያደርጋል፡፡  

ክብር ሽልማት የዳኝነት ስርዓቱን ሙያዊ ለማድረግ፣ ትክክለኛ የመዳኘት አካሄድን ተከትሏል፡፡ በተለይ  መስፈርቶችን ጊዜ ወስዶ በጥንቃቄ  በማዘጋጀትና መስፈርቶቹንም ደግሞ ደጋግሞ በመከለስ የተጣራ ማወዳደሪያ በመቅረጽ የዕውቅና ሥነ ስርዓቱ በጥብቅ የዳኝነት መስፈርት እንዲከናወን አድርጓል፡፡

ሁሉም ተወዳዳሪዎች በ2015 ባለው የሥራ ውጤታቸው እንዲዳኙ ተደርጓል፡፡ ይህንንም ዕውን ለማድረግ በክብር ሽልማት ስር የተዋቀረው የጥናትና ምርምር ማዕከል፣ የባለሙያዎችን የህይወት ታሪክ እንዲሁም ናሙና ስራዎችን በቋት ውስጥ በማጠራቀም ለዳኝነቱ ስራ ተገቢ መላ ዘይዶ የማወዳደሩን ስራ በተገቢው መልኩ አከናውኗል፡፡

የዳኝነት ሥራውም ፍጹም ምስጢራዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ባለሙያዎችን ከሥራቸው አንጻር ብቻ በማየት ወደ ውድድሩ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ዋናው የክብር ሽልማት ግብ የሰራ የልፋቱን ያህል እንዲመሰገን፣ እንዲታወቅና እንዲከበር ማድረግ ሲሆን ይህንንም ባህል በመላ አገሪቱ እንዲስፋፋ እንሻለን፡፡ ስለሆነም ትናንት በልዩ ልዩ መንገድ  ሥራቸውን በትጋትና በችሎታ የተወጡ ሰዎችን ዛሬ ደግሞ ዕውቅና አግኝተው ሊሸለሙ ይችላሉ፡፡

ዛሬ የዕውቅና ካባ የሚደርቡ ደግሞ ነገ ታሪካቸው እየተሰነደ ለትውልዱ ተምሳሌት ይሆናሉ፡፡ ክብር ሽልማት በቂ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎችና የቦርድ አባላት የሚመራ ሲሆን ለሥራችን መቃናት የረዱንን ሁሉ ከልብ ማመስገን እንወዳለን፡፡ በስተመጨረሻም ከዚህ በሁሉም ዘርፍ የተመረጡትን ባለሙያዎች ድምጽ እንድትሰጡ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን ፡፡  

በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ ምርጥ 5 የሚከተሉት ናቸው።
የዓመቱ ምርጥ ልብ ወለድ
፩ ቤባንያ (ዓለማየሁ ገላጋይ)
፪ ማሙሽ (ማይክል አዝመራው)
፫ ጠያይም መላዕክት (ቤተ ማርያም ተሾመ)
፬ ወድቆ የተገኘ ሀገር (ይፍቱሥራ ምትኩ)
፭ አሌፍ ቤት (ወንድሙ ገዳ)

የዓመቱ ምርጥ አጫጭር ልብወለድ
፩ አሳንቲ (ምርት ባቦ)
፪ አዎ እሱ ጋ ያመኛል (አድሃኖም ምትኩ)
፫ ናፍቆት (እስከዳር ግርማይ)
፬ አዝማሪው ልቤ (ጌታነህ ደጉ)
፭ እሰሩኝ (መሠረት ባህሩ)

የዓመቱ ምርጥ ግለታሪክ መጽሐፍ

፩ ኅብር ሕይወቴ (ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ)
፪ ተስፋዬን ፍለጋ (ማርቆስ ተግይበሉ)
፫ ሕይወቱ የአብራሪነት የአውሮፕላን ጠለፋ ትዝታዎቹ (ካፒቴን ልዑል አባተ)
፬ ዓለማየሁ እሸቴ (በወሰን ደበበ ማንደፍሮ)
፭ የህይወት ጎዳና (ሕይወት ጥላሁን)

የዓመቱ ምርጥ ተውኔት
፩ በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ (ውድነህ ክፍሌ)
፪ የሌሊት ሙሽሮች (ውድነህ ክፍሌ)
፫ የደፈረሱ ዓይኖች (ውድነህ ክፍሌ)
፬ ነገሩ አይቆምም (ድረስ ደሳለኝ)

የዓመቱ ምርጥ ግጥም
፩ እናርጅ እናውጋ (ጌራወርቅ ጥላዬ)
፪ ፍቅር ሰው ማኅሌት (ዮሐንስ ኃ/ማርያም)
፫ ፍለጋ (ፍቃዱ ጌታቸው)
፬ እንኳን መሃይም ሆንኩ (በለው ገበየሁ)
፭ ምርቃት (ዓለምነህ ረጋሳ)

የዓመቱ ምርጥ የፊልም ድርሰት
፩ ዶቃ (ቅድስት ይልማ እና ቤዛ ኃይሉ)
፪ ጋዜጠኛዋ (ሳሙኤል ተሻገር)
፫ ወዳጅ (ግዛቸው ገብሬ)
፬ ገምዛ (ሙሉቀን አረጋ)
፭ ቅኔ (ቅድስት ሳህለ)

የዓመቱ ምርጥ የወግና መጣጥፍ መጽሐፍ
፩ ችቦ (ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ)
፪ እያል ድሬ (ሚልኬሳ ሙሜ)
፫ ኦብሲቱ (ሐሊ ሙዘይን)

የዓመቱ ምርጥ የዘፈን ግጥም
፩ ላይለ ኩሉ (ዳን አድማሱ)
፪ አትከልክሉኝ (አብነት አጎናፍር)
፫ ገላጋይ (ዮሓና)
፬ እርፍ በይ (ዘሩባቤል ሞላ)
፭ ማንነቴ (ኤልያስ መልካ)

የክብር ሽልማት በሥነጽሑፍ ዘርፍ የሕይወት ዘመን እጩ
፩ ኃይለመለኮት መዋዕል
፪ ሳህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም
፫ ፀሐይ መላኩ
፬ ሲሳይ ንጉሱ
፭ አዳም ረታ

የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የመዝናኛ ዩቲዩብ
፩ ዶንኪ ቲዩብ
፪ ማያ ቲዩብ
፫ መሪ ፖድካስት
፬ ማራኪ ወግ
፭ ከናቲ ጋር

የዓመቱ ምርጥ የሚዲያ ሰው
፩ እሸቴ አሰፋ
፪ ግርማ ፍስሃ
፫ ምንይችል እንግዳ
፬ ወንድዬ ካሳ
፭ መንሱር አብዱልቀኒ

የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ዝግጅት አቅራቢ
፩ ኤደን ገብረሕይወት
፪ ሰይፉ ፋንታሁን
፫ አስካለ ተስፋዬ
፬ ዳናዊት መክብብ
፭ ዮናስ ከበደ

የዓመቱ በጋዜጠኝነት ዘርፍ የሕይወት  ዘመን ዕጩ
፩ ማዕረጉ በዛብህ
፪ ታምራት ገብረጊዮርጊስ
፫ ጸጋዬ ኃይሉ
፬ መርዕድ በቀለ
፭ አማረ አረጋዊ

የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት
፩ ጦቢያ
፪ ውሎ አዳር
፫ ትዝታችን በኢቢኤስ
፬ ፋና ቀለማት
፭ ጠያቂው ሲጠየቅ

የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት
፩ ሁሉ አዲስ
፪ የጥበብ መንገድ
፫ ታዛ
፬ መሰንበቻ
፭ ለዛ

የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት አቅራቢ
፩ ትዕግስት በጋሻው
፪ ወንድሙ ኃይሉ
፫ ብርሃኑ ድጋፌ
፬ ብስራት ከፈለኝ
፭ ሰለሞን ጫላ

ከአንድ እስከ አምስት የተጻፉት እንዲሁ ቅደም ተከተል እንጂ ደረጃቸውን አያሳይም፤ የአጻጻፍ ቅደም ተከተል እንጂ።
ከዛሬ ጀምሮ በዚህ ሊንክ እየገባችሁ የእናንተን አንደኛ ትመርጡ ዘንድ ተጋብዛችኋል።
????????????????????????
https://kibershilemat.com

 “እኛ ት/ቤት እጆች ይናገራሉ፤ ዓይኖች ያዳምጣሉ” የሚል መፈክር መሰል ማስታወቂያ በየቦታው ተለጥፎ ይታያል፡፡ አንዳንድ ተቋም ስሙና መፈክሩ ሳይቀር ይለያል፡፡ ስሜትና ትኩረት ይስባል፡፡ የማወጋችሁ በመዲናዋ አንድ ለእናቱ ስለሆነው ት/ቤት ነው። “አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት”። ት/ቤቱ በ1956 ዓ.ም የዛሬ 60 ዓመት በውጭ ሚሽነሪዎች የተመሰረተ ነው፡፡ መጀመሪያ ላይዓላማው ለት/ቤት ሳይሆን ለመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደነበር ይነገራል።በኋላ ላይ ግን መስማት የተሳናቸው ተማሪዎችት/ቤት ሆነ፡፡ በአሁኑ ወቅት አምሳያ የሌለውብቸኛውመስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ብቻ ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት የመንግሥት ት/ቤት ነው ተብሏል። ሆኖም በ ሁሉ ነገሩ፡- በአስተዳደሩ፣ በአደረጃጀቱ፣ ተማሪዎቹን ለማገዝና ለውጤት ለማብቃት በሚያደርገው ጥረትና ተነሳሽነቱ እንዲሁም በችግር አፈታትዘዴው ፈጽሞ የመንግስት ት/ቤት አይመስልም።
ት/ቤቱ ከመንግሥት በዓመት 11 ሚሊዮን ብርበጀት እንደሚበጀትለት የሚናገሩት የት/ቤቱርዕሰ መምህር ወ/ሮ ከበቡሽ በቀለ፤ ይህም የሠራተኞችን ደሞዝ ጨምሮ አጠቃላይ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚውል ነው ይላሉ። አልፋ በአሁኑ ጊዜ 125 መስማት የተሳናቸውን ልጆች ከኬጂ እስከ 8ኛ ክፍል እንደሚያስተምር የገለፁት ርዕሰ መምህሯ፤ ከእነዚህ ልጆች ውስጥ የተወሰኑት መስማት የተሳናቸው ብቻሳይሆኑ የአዕምሮ ውስንነት ያለባቸው ጭምር
መሆናቸውን ጠቁመዋል። ተደራራቢ ችግሮች ያለበትና ትኩረት ያላገኘ ት/ቤት መሆኑን የሚናገሩት ወ/ሮከበቡሽ፤ ከአዲስ አበባ የተለያዩ አቅጣጫዎች
ለሚመጡ 37 ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪ ባንሸፍንላቸው ኖሮ ት/ቤት ላይመጡ ይችሉ ነበር ብለዋል። እንግዲህ የመንግስትት/ቤት ለተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪ እንደማይሸፍን ይታወቃል፡፡ አልፋ ከየት አምጥቶ ነው ለ37 ቤታቸው ሩቅ ለሆነተማሪዎች የዕለት የትራንስፖርት ወጪያቸውን
የሚሸፍነው? ለዚህ ነው ይለያል ያልኳችሁ፡፡ የት/ቤቱ አመራሮች የራሳቸውን ችግር በራሳቸውየመፍታትና ከተለያዩ ወገኖች ጋር በትብብር የመሥራት ባህልና ልምድ አዳብረዋል፡፡ የ37ቱ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፈነው ት/ቤቱ ያለበትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችበተረዱና እጃቸውን ለእገዛ በዘረጉ እጆች ነው ተብሏል፡፡ እጆች እንዲዘረጉ ግን ት/ቤቱ መጀመሪያ ችግሩን በሚያሳምን መልኩ መናገርና መቀስቀስ አለበት፤ አንድ ጊዜና ሁለቴ ብቻ ሳይሆን ደጋግሞ - ዓመቱን ሙሉ፡፡ በነገራችን ላይ እኔም ባለፈው ሐሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ት/ቤቱ ያቀናሁት፣አይ.ሲ.ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል የተለያዩ ድጋፎችን ለት/ቤቱ እንደሚያደርግ ጥቆማ ደርሶኝ ነው። በእርግጥም የሆስፒታሉ አመራሮችበዕለቱ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተው፣
ለእንስት ተማሪዎች ለ6 ወር የሚያገለግል የንፅህና መጠበቂያ፣ 60 ደርዘን ደብተር እንዲሁም የዕደ-ጥበባት ማዕከልን ለማጠናከርና ለተማሪዎች ትራንስፖርት ወጪ የሚውል 99ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
   ተማሪዎቹ የኢኮኖሚ ችግር እንጂ ትምህርት የመቀበል ችግር እንደሌለባቸው በልበሙሉነት የተናገሩት ርዕሰ መምህሯ፤ እስካሁን ት/ቤቱበ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 100 ፐርሰንት ነው ያሳለፈው ብለዋል፡፡ ይህ ብቻ ግን አይደለም፡፡ ተማሪዎቹ በዕደ-ጥበብና በፈጠራሥራዎችም አ ልተቻሉም ነ ው የ ተባለው፡፡ በየጊዜው ከሌሎች ት/ቤቶች ጋር እየተወዳደሩ በርካታ ዋንጫዎች ለት/ቤቱ ማስገኘት እንደቻሉ ርዕሰ መምህሯ በድል አድራጊነት ስሜት ተናግረዋል። በእርግጥም ይሄንን እውነት በት/ቤቱ ለዘገባ የተሰባሰብን የሚዲያ ባለሙያዎች በሙሉ በዓይናችን ማረጋገጥ ችለናል፡፡ አንድ
ቢሮ ውስጥ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት የሚበቃ የሚመስል ሥፍር ቁጥር የሌለው የዋንጫ ዓይነት ተደርድሯል፡፡ የአሸናፊነትና የስኬት አርማ ነው፡፡
የት/ቤቱን የዕደ-ጥበባትና የፈጠራ ማዕላት ተዟዙረን በጎበኘንበት ወቅት፣ ያ ሁሉ ዋንጫ በዘበት እንዳልተሰበሰበ ለመረዳት ችለናል።ተማሪዎች በልብስ ስፌት ማሽን ላይ ሥልጠና እየወሰዱ የሚሰሯቸው አልባሳት፣ መጋረጃዎች፣ ምንጣፎችና፣ የአልጋና ኮሞዲኖ ናሙናዎች ተዓምር የሚያሰኙ ናቸው። የዕደ-ጥበባትአሰልጣኞቹ እንደነገሩን፤ አንዳንዶቹ ተማሪዎች የልብስ ስፌት ማሽን የሚገዛላቸው ቢያገኙየራሳቸውን ሥራ ለመጀመር የሚያስችል
አቅምና ችሎታ አዳብረዋል፡፡አሁንም ለዚህ ሁሉ ውጤትና ስኬት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት ርዕሰ መምህሯንጨምሮ የአልፋ መምህራንና ሰራተኞች ናቸው፡፡
   ለዚህም ትልቅ ምስጋናና አድናቆት ይገባቸዋል። ከዚያም በ ላይ ግ ን ሁ ሉም ወ ገን የ አቅሙን ያህል ሊያግዛቸውና ሊደግፋቸው ይገባል።
አይ.ሲ.ኤም.ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል በዕለቱ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ርዕሰ መምህሯ፤ እነዚህን ህፃናት መርዳት ማለትአገርን መርዳት ነው፤ ብለዋል፡፡ በነገራችን ላይ በአልፋ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚታየው የተማሪዎቹ የተስፋ ብርሃንና የመምህራኑ የመነቃቃት ስሜት በራሱ ለለውጥና
ለተጨማሪ ስኬት መንደርደርያ እንደሚሆናቸው አያጠራጥርም፡፡ በእርግጥም ህፃናትን መርዳት አገርን መርዳት ነው!!


Russia's military death toll in Ukraine has now passed the 50,000 mark, the BBC can confirm.

In the second 12 months on the front line - as Moscow pushed its so-called meat grinder strategy - we found the body count was nearly 25% higher than in the first year.

BBC Russian, independent media group Mediazona and volunteers have been counting deaths since February 2022.

New graves in cemeteries helped provide the names of many soldiers.

Our teams also combed through open-source information from official reports, newspapers and social media.

More than 27,300 Russian soldiers died in the second year of combat - according to our findings - a reflection of how territorial gains have come at a huge human cost.

Russia has responded to the BBC's report saying only the defence ministry in Moscow can give this kind of information.

The term meat grinder has been used to describe the way Moscow sends waves of soldiers forward relentlessly to try to wear down Ukrainian forces and expose their locations to Russian artillery.

The overall death toll - of more than 50,000 - is eight times higher than the only official public acknowledgement of fatality numbers ever given by Moscow in September 2022.

The actual number of Russian deaths is likely to be much higher.

Two alleged spies suspected of planning to sabotage German military aid for Ukraine have been arrested in the southern German state of Bavaria.

The two men, described as dual German-Russian nationals, were detained in Bayreuth on suspicion of spying for Russia, prosecutors say.

Dieter S, 39, is suspected of a string of spying offences.

They include plotting an explosion, arson and maintaining contact with Russian intelligence.

He is also accused of fighting for a Russian proxy armed force in occupied eastern Ukraine.

The second suspect, identified as Alexander J, is accused of helping him since last month to identify potential targets for attack. He was due to appear in court on Thursday.

Germany is the second largest donor of military aid to Ukraine after the US, earmarking some €28bn (£24bn) since the start of Russia's full-scale invasion in February 2022.

According to prosecutors, the main suspect Dieter S is alleged to have discussed potential sabotage operations in Germany with his Russian contact since October last year, in an attempt to undermine its support for Ukraine.

They cite preparing explosive and arson attacks, especially on military and industrial infrastructure. Dieter S is said to have scouted potential targets including US military facilities, taking photos and videos and handing the information to the Russian contact.

German Justice Minister Marco Buschmann told German news agency DPA that the two arrests were "another significant investigative success" in the fight against Russian President Vladimir Putin's sabotage and spy networks.

Vice-Chancellor Robert Habeck, currently on an unannounced visit to Kyiv, said on Thursday that he was there "at a time when Ukraine needed all the support it can get in its fight for freedom".

The government in Berlin is spearheading a plan to help bolster Ukraine's air defences.

Chancellor Olaf Scholz said on Wednesday that EU countries should try to help Ukraine with additional air defence systems, especially Patriot systems. Germany has already sent Ukraine two Patriot air defences and has promised a third.

The United Arab Emirates witnessed its heaviest rainfall in 75 years this week, triggering massive flooding that swept away cars, caused flights to be canceled and left multiple people dead.

Some areas recorded more than 10 inches of rain in less than 24 hours, the state’s media office said in a statement Wednesday — the most since recordkeeping began in 1949.

At Dubai International Airport on Tuesday, nearly 4 inches of rain fell over the course of a 12-hour period on Tuesday, or roughly what Dubai usually records in an entire year.


Videos posted to social media showed planes moving through several feet of water on the tarmac. Others showed sinkholes swallowing up cars, water rushing through a mall and someone navigating the floodwaters using a jetski.

Photographers captured dramatic images of cars submerged in floodwaters.

(ከእስራኤል  ምክትል አምባሳደር ጋር የተደረገ ልዩ ቃለ መጠይቅ)

ኢራን ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ከ300 በላይ የድሮኖችና የሚሳኤሎች ጥቃት  በእስራኤል ላይ ያደረሰች  ሲሆን፤ እስራኤል አሜሪካና እንግሊዝን ጨምሮ ከአጋሮቿ ጋር በመተባበር ከተወነጨፉት ድሮኖችና ሚሳኤሎች ውስጥ 99 በመቶውን ከአየር ክልሏ ውጭ ማምከን መቻሏን አስታውቃለች፡፡ ኢራን የፈጸመችው ጥቃት የዛሬ 20 ቀን ገደማ በሶሪያ በሚገኝ ቆንስላዋ ውስጥ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት ለገደለቻቸው ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቿ አጸፋዊ ምላሽ መሆኑን ገልጻለች፡፡ የእስራኤል ጦር አዛዥ ጥቃቱን ተከትሎ ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ፤ በእስራኤል ግዛት ለተወነጨፉ ድሮኖችና ሚሳኤሎች ምላሽ መስጠታችን አይቀርም ብለዋል፡፡

የጆ ባይደን አስተዳደር፤ በኢራን ላይ በሚወሰድ የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ ተሳታፊ እንደማትሆን ግልጽ አድርጓል፡፡ ኢራን በበኩሏ፤ እስራኤል የአጸፋ እርምጃ ከወሰደች ፈጣንና ከአሁኑ የከፋ ምላሽ እንደምትሰጥ ዝታለች፡፡ አሜሪካ የእስራኤልን የአጸፋ እርምጃ የምትደግፍ ከሆነም፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት እንደምትሰነዝር ኢራን አስጠንቅቃለች፡፡ የእስራኤል አጋሮች የኢራንን ጥቃት አጥብቀው ቢያወግዙም፣ የጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ አስተዳደር አጸፋዊ ምላሽ ላይ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል፤ እዚህ አዲስ አበባ የሚገኘው በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ በጥቃቱ ማግስት እሁድ ሚያዝያ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ላይ ያስወነጨፈቻቸውን ድሮኖችና ሚሳይሎች አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ፣ ከእስራኤል ምክትል አምባሳደር ሚስተር ቶመር ባር-ላቪ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ  ተከታዩን ቃለ መጠይቅ አድርጓል፡፡
***

እስቲ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ኢራን በእስራኤል ላይ ስለፈጸመችው የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት ይንገሩን ?

ቅዳሜ ሌሊት፣ ኤፕሪል 13፣ የኢራን አገዛዝ፣ በእስራኤል ላይ ታይቶ የማይታወቅና ግዙፍ ጥቃት አድርሷል፤ከ300 በላይ የባላስቲክ ሚሳኤሎች፣ ክሩዝ ሚሳኤሎችና ድሮኖዎችን  በእስራኤል ኢላማዎች ላይ በማስወንጨፍ፣ ከፍተኛ እልቂትና ውድመት ለማድረስ ሞክሯል። ደግነቱ፣ በእስራኤል  የላቀ ወታደራዊ አቅምና በአጋሮቻችን ትብብርና  ድጋፍ ከተወነጨፉት ውስጥ  99 በመቶ የሚሆኑት ወደ እስራኤል የአየር ክልል ከመግባታቸው በፊት መትተን መጣል ችለናል።

በኢራን አብዮታዊ ጋርድ (IRGC) የተፈፀመው ይህ ጥቃት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን የሚጥስ ሲሆን፤ሌላ ቀይ መስመር ያለፈና  እስራኤል ለዓመታት ስትናገረው የኖረችውን የሚያረጋግጥ ነው፤ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚታየው አለመረጋጋትና ሽብርተኝነት ዋነኛ ምንጭ መሆኑን፣ እንዲሁም ለአካባቢያዊና ለዓለም ሰላም ስጋት መደቀኑን፡፡ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት እንድትሆን ፈጽሞ ሊፈቀድላት የማይገባው ለምን እንደሆነም የሚያጎላ ድርጊት ነው፤ ጥቃቱ፡፡


የእስራኤል የጦር አዛዥ፣ ለዚህ ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ እስራኤል   እንዴት ነው ምላሽ ልትሰጥ ያቀደችው?

ለዚህ ግዙፍ ጥቃት የሚሰጠው ምላሽ መከናወን ያለበት በብዙ ግንባሮች ነው፡- በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ጥቃት ያደረሰው የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) በአስቸኳይ በመንግስታትና በአለም አቀፍ አካላት በአሸባሪነት መፈረጅ አለበት።  የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC)፤ በጋዛ ሃማስና ኢስላሚክ ጂሃድን፣ በሊባኖስ ሂዝቦላን፣ በየመን ሁቲዎችንና በኢራቅ  የሺአ ሚሊሻዎችን ጨምሮ፣ በአካባቢው የኢራን አገዛዝ ተጨማሪ የሽብር ተላላኪዎችን በገንዘብ፣ በማሰልጠንና  በማስታጠቅ ይደግፋል፡፡  የኢራንን እኩይ ተጽእኖ ለማስፋፋትና የመካከለኛው ምስራቅን ለዘብተኛ  ኃይሎች ለማተራመስ በአካባቢው ምስቅልቅል ይፈጥራል፡፡

 በሁለተኛ ደረጃ ይህ ጥቃት፣ የኢራን የተራቀቁ ሚሳኤሎችንና ተዛማጅ ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ ስልታዊ አቅሞችን ማሳደድ፣ የአገዛዙን ወረራ ለማራመድና እስራኤልንና የአለምን ስርዓት ለአደጋ የሚያጋልጥ  መሆኑን አሳይቷል፡፡ የኢራን አገዛዝ ላይ በሚሳኤል መስክ ብቻ ሳይወሰኑ እንደዚህ አይነት ስትራቴጂካዊ አቅሞችን የማሳደድ እንቅስቃሴው  ላይ ጥብቅና አስጨናቂ  ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል።


በመጨረሻም፣ እንደማንኛውም እንዲህ አይነት መጠነ ሰፊ ጥቃት የተፈፀመባት ሀገርና የእስላማዊ  ሪፐብሊክ ባለስልጣናት ሀገራችንን ለማጥፋት በየእለቱ የሚሰነዝሩትን የዘር ማጥፋት ዛቻ ተከትሎ፣ እስራኤል ከዚህ ጥቃት ራሷን የመከላከል መብቷ የተጠበቀ ነው። ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው ወደፊትም ራሳችንን ከኢራን ጥቃቶች መከላከል እንቀጥላለን።


ኢራን ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰድን በተመለከተ የእስራኤል ጦር  ካቢኔ ለሁለት መከፈሉ ተነግሯል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሊሰጡን  ይችላሉ ?

ቀደም ሲል እንደገለጽኩት፣ እስራኤል ከዚህ የኢራን መንግስት ህገወጥ ጥቃት ራሷን የመከላከል መብቷ የተጠበቀ ሲሆን፤ እኛም ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው እናደርጋለን።

አሜሪካ፤ እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው የአጸፋ እርምጃ፣ እጄን አላስገባም  ማለቷን በተመለከተ እርስዎ  ምን ይላሉ?

አሜሪካና ሌሎች አጋሮች ከእኛ ጋር መቆማቸውን እስራኤል ታደንቃለች፤ ይህ ደግሞ የቅዳሜውን ጥቃት ለመከላከል በተደረገው ትብብር በግልፅ ታይቷል። በአሜሪካ የሚመራው ድጋፍና ትብብር በዋጋ የማይተመንና ወደር የለሽ ነው።

የትኛውም ሀገር በህልውናዋ ላይ የመጣ አደጋን ሊቀበል አይችልም ፤ እስራኤልም ከዚህ የተለየች  አይደለችም። እስራኤል ከኢራን የሚደቀንባትን ስጋት  አትታገስም፤ ጉዳት ለማድረስ ለሚደረገው ማንኛውም ሙከራ ሁሉ ጠንከር ያለ ምላሽ ትሰጣለች። እስራኤል፤ ኢራንም ሆነች ተላላኪ ድርጅቶቿ በዜጎቿ ላይ ስጋት አለመፍጠራቸውን ታረጋግጣለች።


የኢራን የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት፣ በተለይም፣ ከቀጠናዊው ውጥረት አንጻር ያለውን አሁናዊና የረዥም ጊዜ የደህንነት አንደምታ እስራኤል እንዴት ትገመግመዋለች?

ኢራን ሽብርተኝነትንና አለመረጋጋትን በማስፋፋት፣ ቀጣናዊ ወኪሎቿን በገንዘብ በመደገፍና  በማስታጠቅ ለዓመታት ዘልቃለች፡፡ ሃማስ በገንዘብ የሚደገፈው፣ የሚሰለጥነውና የሚታጠቀው በአብዛኛው በኢራን አገዛዝ ሲሆን፤ ለዚህ የዘር ማጥፋት አሸባሪ ቡድን የኢራን ድጋፍ ባይኖር ኖሮ፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2023 በእስራኤል ላይ የተፈፀመው ጥቃት አይከሰትም ነበር፡፡  ላለፉት ስድስት ወራት ኢራን በተላላኪዎቿ - ሃማስና ኢስላሚክ ጂሃድ በጋዛ፣ ሂዝቦላ በሊባኖስ፣ ሁቲዎች በየመንና  የሺዓ ሚሊሻዎች በኢራቅ፣ አማካኝነት በእስራኤል ላይ ጦርነት ስትከፍት ቆይታለች። በእስራኤል ሰሜናዊ ድንበር የሚሰነዘረው የሂዝቦላ ጥቃት ቀስ በቀስ እያደገና  ሙሉ ለሙሉ የባለብዙ ግንባር ጦርነት ስጋት እየሆነ መምጣቱን እንዲሁም  በቀይ ባህር ላይ በአለም አቀፍ መርከቦች ላይ በሁቲዎች የሚፈጸመው ጥቃት ዓለማቀፍ ንግድን እየጎዳውና የመላው ዓለም ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ማድረሱን  እናያለን።

 

የሰሞኑ ጥቃት የእስላማዊ  ሪፐብሊክ፣ እስራኤልን ከኢራን ግዛት በቀጥታ ሲያጠቃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሆኑ አንጻር፣ ግጭትን የማባባስ ተግባር  ተደርጎ የሚታይ ነው፡፡ ይህ መባባስ ክልሉን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወደ አለመረጋጋት እንዲመጣ በማድረግ፣ የከፋ ግጭት እንዳይፈጠር  ያሰጋል።  ክልላዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብር በእንደዚህ ዓይነት ምክንያታዊ ያልሆኑ ተዋናዮች ላይ ያለውንም ጠቀሜታ ያሳያል።

ከዚህ ጥቃት አንጻር፣ እስራኤል፣ የኢራን ወታደራዊ አቅም የጋረጠውን መጠነ ሰፊ ስጋት እንዴት ትመለከተዋለች?

እስራኤል ይህ ጥቃት እስላማዊ ሪፐብሊክ በኢራን አብዮታዊ ዘብ በኩል፣ አካባቢውን ለማተራመስና ሽብርተኝነትን ለማስፋፋት እንዲሁም ተጽእኖውን ለማስፋትና በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ትርምስ ለመፍጠር የሚያደርገውን ጥረት በተመለከተ ለብዙ አመታት ያስጠነቅቅነውን እንደ ማረጋገጫ አድርጋ ነው የምትመለከተው፡፡ በክልሉ ውስጥ ያሉ ብዙ ለዘብተኛና ኃላፊነት የሚሰማቸው ተዋናዮች፣ ይህን እውነታ ከረጅም ጊዜ በፊት ተገንዝበዋል።

የኢራን ተጽዕኖ ፈላጊነት ከመካከለኛው ምስራቅ ባሻገር  የተስፋፋ ሲሆን፣ በዓለም ላይ ያሉ ኃላፊነት የሚሰማቸው ተዋናዮች፣ የኢራን መንግስት ተፅእኖ ለመፍጠርና የአለምን ስርዓት ለማተራመስ የሚያደርገውን ጥረት ትኩረት ሰጥተው መቃወም አለባቸው። በቅርቡ የተፈፀመው ጥቃት፣ የኢራን አገዛዝ ስለ እስራኤል መጥፋትና ስለ ሽብርተኝነትን ማስፋፋት ጥሪ ሲያደርግ፣ ከምሩ ለመሆኑ ለሚጠራጠሩ ሁሉ እንደ ማንቂያ ደወል ማገልገል አለበት። የዚህ አገዛዝ ድርጊት እጅግ ጽንፈኛ የሆኑ መሪዎቹን ቃል የሚያረጋግጥ ነው፡፡

እስራኤል የኢራንን ጥቃት ለመግታት ምን ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን ትከተላለች?

የቅዳሜ ሌሊቱን ጥቃትን ተከትሎ፣ በተባበሩት መንግሥታት የእስራኤል አምባሳደር፣  የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደርግና በጉዳዩ ላይ እንዲወያይ ጠይቀዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ተጨማሪ አካላት እንዲሁም ሀገራት የኢራንን ጥቃት በማያሻማ መልኩ እንዲያወግዙና እስላማዊ ሪፐብሊክና ደጋፊዎቿ ጥቃታቸውን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ጥሪያችንን ማቀረባችንን እንቀጥላለን፡፡
እስራኤል፣ በዓለም ዙሪያ በርካታ ሀገራት፣ ኢራን በፈጸመችው ጥቃት ላይ ጠንከር ያለ ውግዘት ማሰማታቸውን በበጎነቱ  ተቀብላለች፣ ሌሎች ሀገራትም ይህን አስከፊ የአለም አቀፍ ህግ ጥሰት የሚያወግዙትን እንዲቀላቀሉ እናበረታታለን።
እደግመዋለሁ፣ በዲፕሎማሲው መስክ፣ ሁለት ፈጣን ተግባራዊ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው፣ እነዚህም፡-
1- የኢራን አብዮታዊ ዘብን (IRGC) በአሸባሪነት መፈረጅ።
2- ኢራን ለማሳካት እየሰራች ያለችውን  ባላስቲክ ሚሳኤሎች፣ ድሮኖች፣ በመካሄድ ላይ ያለውን የኒውክሌር መርሃ ግብርና የህዋ አቅሞችን ጨምሮ የኢራን ስትራቴጂካዊ  አቅሞች ላይ ያነጣጠረ ጉዳት የሚያስከትል ማዕቀብ መጣል። አለም ኢራንን  እንደዚህ አይነት ስትራቴጂካዊ አቅሞች እንዳታገኝና እንዳታዳብር ማገድና መከልከል አለበት፡፡
ጥቃቱ፤ እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2023 በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2231 ጊዜው ያለፈበትን  የማዕቀብ ስርዓት፣ በአማራጭና ሁሉን አቀፍ በሆነ  የማዕቀብ ሥርዓቶች በመተካት ማዕቀቡን የማስፋፋትና የመጣል አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥቶታል፡፡ ጥቃቱ በተጨማሪም የኢራን  የኒውክሌር መርሃ ግብር፣ ከመርፈዱ በፊት  በአስቸኳይ የማቆምና የመቀልበስ አስፈላጊነቱን አጉልቶታል፡፡

እስራኤል ተጨማሪ የግጭት መባባስን ለማስቀረትና በቀጣናው መረጋጋትን ለማስፈን ምን እርምጃዎችን ልትወስድ አስባለች?

እስከ ኦክቶበር 7, 2023 ድረስ መካከለኛው ምስራቅ ወደ ሁለንተናዊ ለውጥ እየገሰገሰ ነበር። ከ2020 ጀምሮ በአብርሃም ስምምነት፣ እስራኤል ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ባህሬንና ሞሮኮ ጋር የመደበኛ ግንኙነትና የሰላም ስምምነቶችን ተፈራርመናል፣ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ እየሰራንም ነበር። ሂደቱ ቀጠለና፣ ይህ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ባሉት ወራት ውስጥ ከሳውዲ አረቢያ ጋርም እንኳን ወደ መደበኛ ግንኙነት ለመግባት  እየተጓዝን ነበር። ይህ የመካከለኛው ምስራቅ የበለጠ ትስስርና ትብብር ያለው ራዕይ፣ቀጣዩ መንገድ ነበር፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ፣ የኢራን አገዛዝና በአካባቢው ያሉ ፅንፈኛ ተላላኪዎቹ፣ እንደዚህ አይነት አዎንታዊ ዲፕሎማሲያዊ እድገቶች ስጋት ውስጥ ጣላቸው፡፡ ይህ ለቀጣናው ህዝብ የተሻለ የወደፊት ተስፋ ቢፈነጥቅም፣ በመካከለኛው ምስራቅ የኢራን  ቀጣይ ተጽእኖና ሽብርተኝነት መስፋፋት ላይ እንቅፋት ፈጥሯል። በትንሹም ቢሆን፣ በጥቅምት 7 የተፈጸመው አሰቃቂ የሃማስ የሽብር ጥቃት ጽንፈኞች - በኢራን የሚመራው የኔትዎርክ አካል -- ባለፉት ጥቂት ዓመታት በእስራኤልና በአረቡ ዓለም መካከል የተደረጉትን አዎንታዊ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስኬቶች ለማስቆምና ወደ ኋላ ለመመለስ ያደረጉትን ሙከራ ይወክላል።

በዚህ የለዘብተኞች እና ጽንፈኞች ጦርነት፣ የቀጣናው ለዘብተኞች ያሸንፋሉ ብለን እናምናለን፤ እናም የእኛ ይበልጥ የተሳሰረና የተባበረ የመካከለኛው ምስራቅ የመፍጠር  የጋራ ራዕያችን፣ ይህ ጦርነት አብቅቶ፣ እስራኤል የድንበሯና ዜጎቿ ደህንነት ጉዳይ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ከተመለሰ በኋላ ዳግም መስመር ይይዛል፡፡  

እስራኤል የዓለማቀፍ አጋሮች፣ በተለይም የቀጣናው አጋሮች፣ የኢራንን የጥቃት እርምጃ በማውገዝና በመቃወም የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ  እንዴት ታየዋለች?

አሁንም ይህ የለዘብተኞችና የአክራሪዎች ጦርነት ነው -- ወደፊት የተሻለና ሰላማዊ ይሆናል ብለው  በሚያምኑ እና ግጭት፣ ሽብርተኝነትና ትርምስ ቀለባቸው በሆኑት መካከል  የሚደረግ ጦርነት ማለት ነው፡፡ በዚህ ጦርነት ደግሞ በአለም አቀፍም ሆነ በክልል ደረጃ አጋሮች አሉን፤ ባለፈው ቅዳሜ ለደረሰው ጥቃት ምላሽ በሰጡበት ወቅት ይህንን ለማየት የቻልን ይመስለኛል። እነዚህ አጋርነቶችና ትብብሮች  ጠቃሚ ናቸው፡፡ በአሜሪካ የሚመራው የእስራኤል አጋሮችና ተባባሪዎች  እኩይ ባላጋራ ሲገጥማቸው በጋራ መስራት ይችላሉ።

ከዚህ ክስተት ጋር በተገናኘ ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ምን መልዕክት ማስተላለፍ ይፈልጋሉ?

እስራኤል፤ አሜሪካና ሁሉም አጋሮቿ ከጎኗ መቆማቸውን ታደንቃለች፤ የኢራንን ጥቃት ለመከላከል ያደረጉትን እገዛም እናደንቃለን። የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ ጥቃት ላይ የሚያደርሰውን ውግዘት በበጎነቱ  ስንቀበል፣ ሌሎችም  ኃላፊነት የሚሰማቸው ተዋናዮች፣ የኢራንን ጥቃት በማውገዝ ከእስራኤል ጎን እንዲቆሙና የእስራኤልን እራሷን የመከላከል መብት እንዲደግፉ እናበረታታለን።

በተጨማሪም እስራኤል፣ የኢራንን ህዝብ እንደ ጠላት እንደማታየው ማጤን አስፈላጊ ነው፤ ይልቁንም ትኩረቷ የገዛ ህዝቡን በሚጨቁነውና ግቡ  እስራኤልን ማጥፋት በሆነው አክራሪ የኢራን አገዛዝ ላይ ነው፡፡ በእርግጥ ከቅዳሜው ጥቃት ወዲህ ባሉት ቀናት #IraniansStandWithIsrael የሚለው ሃሽታግ በማህበራዊ ትስስር X (የቀድሞው ትዊተር) ላይ እየታየ ነበር። የኢራን ህዝብ በዚህ አገዛዝ እየተሰቃየ መሆኑን እንረዳለን፤ እናም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉቱ  ድጋፋችንን እንገልፃለን።

Page 1 of 701