ጨረቃ እንደ ፀሐይ
ጥልቅ የሆነ የንባብ ፍቅር ያደረበት ልጅ እያለ ነው። ቤተሰቦቹም ቀለም ቀመስ ስለሆኑና ኑሯቸውም የተደላደላ ስለነበር የንባብ ጥማቱን ለማርካት ችግር አልገጠመውም፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ለሚታተሙ ሳምንታዊ እና እለታዊ ጋዜጦች እንዲሁም መጽሔቶች አመታዊ ክፍያቸው ተከፍሎ ቤቱ ድረስ ይመጡለታል። መጽሐፍቶችማ ትልቁን የቤታቸውን መደርደሪያ ተርፈው በየቦታው ነው ተዝረክርከው የተቀመጡት፡፡
አነበበ፣ አነበበ፣ አነበበና … ጭንቅላቱ በእውቀት ተወጠረበት፡፡ እውነትም ጭንቅላቱ ይከብደው ነበር፡፡
አከራካሪው የፅንስ ማቋረጥ ተግባር!
“ፅንብ ማቋረጥ የወሊድ መከላከያ ተደርጐ ሊታሰብ አይገባም”
እንዲያው እግር ጥሎት አልያም ጉዳይ ኖሮት ፒያሳ ካቴድራል ትምህርት ቤት አካባቢ ወደሚገኘው ሠፈር ብቅ ያለ ይታዘበው፣ ይገረምበት ነገር አያጣም፡፡ በለጋ የወጣትነት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች በአካባቢው በብዛት ውር ውር ሲሉ መመልከቱም አይቀርም። ወጣቶቹ በሥፍራው በብዛት የሚታዩት ለአንድ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን ጉዳያቸውን የሚፈጽሙት ደግሞ በምስጢር ነው፡፡ በተለይ ከቤተሰቦቻቸው አባላት አንዱ ወይም አንዷ ምስጢራቸውን እንዲያውቁባቸው ስለማይፈልጉ፣ወደ ሥፍራው የሚመጡት ብቻቸውን አሊያም ከቅርብ ጓደኞቻቸው ጋ ነው፡፡
“የእኛ ሰዎች በየመን”
“ህይወት ውሳኔ ነው”
የሃፍቶም ልብ ሳኡዲን አልሟል - መንገዱን ማን ያሳየው?
ስመጥሩው ፀሀፌ ተውኔት ዊልያም ሼክስፒር “The Tempest” በተሠኘው ተውኔቱ “መከራና ችግር ሰዎች ጨርሰው ከማያውቋቸው ጋር እንዲጐዳኙ ያስገድዳቸዋል” ይላል፡፡ በእርግጥም የሠው ልጅ ቀን አዘንብሎበት አስቸጋሪና የመከራ ጊዜ ሲገጥመው፣ በመልካሙ ጊዜ አብሯቸው ሊውል ከማይፈልጋቸው ወይንም ጨርሶ ከማያውቃቸው እንግዳ ሰዎች ጋር ወዳጅነት ወይም አጋርነት ይመሰርታል፡፡ አበሻ “የጨነቀው እርጉዝ ያገባል” እንደሚለው መሆኑ ነው፡፡
ጠ/ሚኒስትሩ “ነፃ አገር ነው” ብለዋል - ማተሚያ ቤቶች እንዳትፈሩ!
በስልክ “ጋዜጣ አታትሙ” ብሎ ማዘዝ ቀረ! (የዲሞክራሲ አገር ነዋ)
ሰሞኑን ቴሌቪዥን ተመልክታችኋል ብዬ እገምታለሁ (ፓርላማ በኢቴቪ ማለቴ እኮ ነው!) አንዳንድ ወገኖች ምን እንደሚሉ ታውቃላችሁ? “ፓርላማም ኢቴቪም አያዝናኑም!” በእርግጥ ኢቴቪ አያዝናናም በሚለው እኔም እስማማለሁ (እንኳን እኔ ኢቴቪም ይስማማል!) እኔን ያልገባኝ ምን መሰላችሁ? ፓርላማው አያዝናናም የተባለው ጉዳይ ነው፡፡ እንዴ --- የት አገር ነው ፓርላማ የሚያዝናናው? የየትም አገር ፓርላማ እኮ (ሲንጋፖርና ታይዋንን ጨምሮ) ትላልቅ የአገር ጉዳዮች የሚታሹበትና የሚፈተጉበት እንዲሁም ህግ የሚወጣበት እንጂ ሰርከስ የሚቀርብበት የመዝናኛ ፕሮግራም አይደለም፡፡
“አቦ! እኛ ጋ ችግር የለም፤ ጣጣ የምታበዙት የመሃል አገር ሰዎች ናችሁ”
ገና እና መውሊድ በድሬዳዋና ሐረር
የበረሃዋ ገነት በሚል መጠሪያ የምትታወቀው የድሬዳዋ ከተማ ሰሞኑን በበዓላት ግርግር ተሟሙቃለች፡፡ ከአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተሰባሰቡ ምዕምናን የቁልቢ በዓልን በቅርቡ ያከበረችው ድሬዳዋ፤ አሁን ደግሞ የገና እና የመውሊድ በዓላትን ለማክበር ሽርጉዱን ተያይዛዋለች። አካባቢውን ከሌሎች አካባቢዎች ለየት የሚያደርገው ሁለቱንም በዓላት በእኩል ደረጃ ለማክበር የሚዘጋጁ ነዋሪዎች ያሉበት መሆኑ ነው፡፡ የድሬዳዋው ታይዋን ገበያ በገና ዛፎችና መብራቶች ገበያ ሞቋል፡፡ እየተዘዋወርኩ ገበያውን ስቃኝ በገና ዛፍ ገበያ ላይ የነበረች አንዲት ሴት ትኩረቴን ሳበችውና ተጠጋኋት፡፡ የለበሰችው ድርያና ኢጃቧ ወጣቷ የእስልምና እምነት ተከታይ እንደምትሆን ግምት አሳደረብኝና ጠየቅኋት፡፡
የ‘ፈረንጅ ረቡዕና ዓርብ’ አባዜ…
እንኳን ለብርሀነ ልደቱ አደረሳችሁማ!
እግረ መንገዳችንን እየከሰሙ ያሉና ‘ዳግም ልደት’ የሚያስፈልጋቸው ነገሮችን ዳግም ልደት ይስጥልንማ!
ሰውየው ለሚስቱ ሁልጊዜ የገና ስጦታ ይሰጣት ነበር፡፡ አንድ ዓመት በሆነ ምክንያት በሚስቱ ብሽቅ ይልባታል፡፡ እሷ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ “…የእኔ ወለላ፣ ዘንድሮ ለገና ምን ስጦታ ነው የምትሰጠኝ?” ትለዋለች፡፡ እሱም “ዓይኖችሽን ጨፍኚ…” ይላታል። እሷም ትጨፍናለች፡፡ “ምን ይታይሻል!” አላት፡፡ እሷም “ምንም!” ትለዋለች፡፡ ባል ሆዬ ምን ቢላት ጥሩ ነው…“የምሰጥሽ ስጦታ እሱን ነው፣ ምንም!” ዘንድሮ ብዙ ባሎች ለሚስቶቻቸው “ምንም!” የሚል መልስ ቢሰጡ አይገርምም፡፡ ብቻ ዓለም ባንኮች እንዳይሰሙኝ። ቂ…ቂ…ቂ…
የካናዬ መልካም አባትነት ጥርጣሬ ፈጥሯል
ኪም ካርዴሽያን ከራፐር ካናዬ ዌስት የመጀመርያ ልጇን መፀነሷ እያነጋገረ ነው፡፡ ለስምንት ወራት በፍቅረኝነት ለቆዩት ሁለቱ ዝነኞች ግንኙነት መቀጠል የ12 ሳምንት እድሜ እንዳለው የተነገረው ፅንስ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብላል፡፡ ኪም ካርዴሽያን ከእርግዝናዋ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ዝና ያገኘችበት የሪያሊቲ ሾው እና የፋሽን ንግስትነቷ አደጋ ላይ ይወድቃል የሚል ስጋት እንዳለ ኤምቲቪ ሲጠቁም፤ “ዘ ሃፊንግተን ፖስት” በበኩሉ በአወዛጋቢነቱ የሚታወቀው ካናዬ ዌስት መልካም አባትነት ጥርጣሬ እንደፈጠረ ዘግቧል፡፡ ፎርብስ መፅሄት በቲቪ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ ክፍያ በማግኘት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጣት ኪም ካርዴሽያን፤ በፋሽን እና በኮስሞቲክስ ንግዷ 65 ሚሊዮን ዶላር ሃብት ማካበት እንደቻለች ታውቋል፡፡
የአራፋት የሞት መንስኤ ከ8 ዓመት በኋላ አልታወቀም
የአሜሪካ ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (CIA) የኩባ ፕሬዚደንት የነበሩትን ፊደል ካስትሮን ለመግደል ከሁለት ደርዘን በላይ ሙከራዎች ማድረጉ ተደጋግሞ ተገልጧል፡፡ የእሥራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) በጥይትና በቦምብ ብቻ ሳይሆን በመርዝም ጭምር የአይሁዳዊቷን ሀገር ህልውና የሚፈታተኑ ጠላቶቿን የማስወገድ ልምድ እንዳለው የሚጠቁሙ ፍንጮች አሉ፡፡
ጠላትን፣ ተፎካካሪንና ተቀናቃኝን በመርዝ የመግደል ታሪክ ከሰው ልጅ የመግደል ታሪክ የማይተናነስ እድሜ አለው፡፡ መርዝ የማይታይ፣ ድምፅ የሌለውና አሻራም የማይተው ረቂቅ እንደመሆኑ በተለይ የስለላ ድርጅቶች ተመራጭ የመግደያ መሣሪያ በመሆን ዘመን የማይሽረው አገልግሎቱን ሲያበረክት ኖሯል፡፡
የዘንድሮ የገና ገበያ ዋጋ ከዓምናው የተሻለ ነው ተባለ
ሸማቾች በጤፍ ዋጋ መናር ተማርረዋል
የጤፍ ዋጋ ያልቀነሰው ምርቱ ከተመጋቢው ጋር ባለመመጣጠኑ ነው - መንግስት
በመዲናዋ የተለያዩ የገበያ ስፍራዎች ያገኘናቸው ሸማቾች የዘንድሮ የገና በዓል የገበያ ዋጋ ከዓምናው እንደሚሻል የገለፁ ሲሆን የጤፍ ዋጋ መናር ግን እንዳስመረራቸው ተናግረዋል፡፡ ለጤፍ ከ2ሺ ብር በላይ መናር ምክንያቱ በዋናነት የመንግስት ቸልተኝነት ነው ሲሉም ወቅሰዋል - ሸማቾች፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን በፓርላማ ለተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ አስተያየት በሰጡት ምላሽ፤ የጤፍ ምርት በ20 በመቶ መጨመሩን ጠቁመው፤ ዋጋው ሊቀንስ ያልቻለው ምርቱ ከጤፍ ተመጋቢው ጋር ባለመመጣጠኑ ነው ብለዋል፡፡
በአላትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በስፋት ማክበር እንደለመዱ የገለፁት አስር ቤተሰብ የሚያስተዳድሩት ወ/ሮ ዕፀገነትመንግስቴ፤ የዘንድሮ የገና ገበያ ዋጋ ከዓምናው መቀነሱን ይናገራሉ፡፡
የገና ዋዜማ እንግዶች 100 የዲላ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አዲስ አድማስን ጐበኙ
አንድ መቶ የሚሆኑ የዲላ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ከትላንት በስቲያ ካዛንቺስ የሚገኘውን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጎበኙ፡፡ የጉብኝቱ ዓላማ ተማሪዎቹ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ስለጋዜጠኝነት በንድፈ ሃሳብ ደረጃ የተማሩትን በተግባር ለማየትና እያንዳንዱን የስራ ሂደት ቦታው ድረስ ተገኝቶ ለመመልከት እንደሆነ የጉብኝት ቡድኑ ሃላፊዎች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ አዲስ አድማስን ከመጎብኘታቸው በፊት የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት፣ ፋና ብሮድካስቲንግ፣ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትንና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅትን (ኢዜአ) እንደጎበኙ የጠቆሙት ከቡድን ሃላፊዎቹ አንዱ የሆኑት መምህር ኃይለመስቀል ዘውዴ፤ በትላንትናው ዕለት ዋልታን እንደጎበኙና ዛሬ ወደ ዲላ ዩኒቨርስቲው እንደሚመለሱ አስታውቀዋል፡፡