በመጪው ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ ላይ የሥልጣን ዘመናቸውን የሚያጠናቅቁት የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት የተከበሩ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የ89 ዓመት ልደትና የስልሳ ዓመት የስራ ዘመን አገልግሎት በዓል የፊታችን ማክሰኞ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም አምባሳደሮችና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በሸራተን አዲስ እንደሚከበር ተገለፀ፡፡ከአፄ ኃ/ሥላሴ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በሶስት መንግስታት በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ላይ እያገለገሉ የቆዩት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፤ ‹‹ለሃገር መስራትን የመሰለ ክብር ያለው ነገር የለም›› ይላሉ፡፡

Published in ዜና

ሃዊ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ የተባለው የቻይና ኩባንያ የገና በዓልን አስመልክቶ የፊታችን ሰኞ ለመቄዶኒያ የአዛውንቶች እንክብካቤ ማዕከል የምሳ ዝግጅትና ልዩ ስጦታ እንዳዘጋጀ ገለፀ፡፡ የሃዊ ቴክኖሎጂ ሰራተኞች የገና በዓልን ከማዕከሉ አዛውንቶች ጋር እንደሚያከብሩ የገለፀው ኩባንያው፤ ከምሳ ግብዣው በተጨማሪ ለአዛውንቱ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ጤፍና የአዋቂ ዳይፐር እንደሚበረከትላቸው ለማወቅ ተችላል፡፡ መቄዶኒያ የአዛውንቶች እንክብካቤ ማዕከል ጧሪ የሌላቸውንና ታመው በየመንገዱ የወደቁ አዛውንትን ሰብስቦ ድጋፍ የሚያደርግ የበጎ አድራጎት ተቋም ነው፡፡

Published in ዜና

“ሕዝቦች የስልጣን ባለቤቶች ናቸው፡፡ የምርጫው ውጤትም በእጃቸው ላይ ነው፡፡ እናም ሁላችንም የምርጫ ካርድ እንውሰድ፡፡ ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻና ፍትሐዊ እንዲሆን የበኩላችንን ጥረት እናድርግ፡፡ ምርጫ ዘጠና ሰባት ያሳየንን የሕዝብ ጉልበት በተግባር ላይ እናውለው፡፡ አሁንም ከተደራጀንና በነቂስ ለምርጫ ከወጣን----ማሸነፍ በእጃችን ያለ አማራጭ መሆኑን አንዘንጋ---”
ከሙሼ ሰሙ (የኢዴፓ ፕሬዚደንት)
በአንድ ወቅት ወደ ሰሜን ሸዋ ለቅስቀሳ ከተላከው የቅንጅት አመራር ቡድን ጋር ተመድቤ ቅስቀሳውን ካጠናቀቅን በኋላ፣ ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር የመወያየት እድል ገጥሞኝ ነበር፡፡ በቅስቀሳው እጅግ ደስተኛ የነበሩት አርሶ አደሮችን ማንን ትመርጣላችሁ ለሚለው ጥያቄ የሰጡኝ መልስ “ቅንጅትን” የሚል ነበር፡፡

ከፍተኛው ፍ/ቤት 14 አመት ፈርዶበት ነበር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የነበረችውን ሆስተስ አበራሽ ሀይላይን አይን አጥፍቷል ተብሎ ከፍተኛ ፍ/ቤት የ14 ዓመት እስር በይኖበት የነበረው የቀድሞ ባለቤቷ ፍስሃ ታደሰ፤ አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረበው ይግባኝ ትላንትና የ20 አመት እስር ተፈረደበት፡፡ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረበው ይግባኝ የስር ፍ/ቤት የህግ ስህተት አለበት ያለው አቃቤ ህግ፤ ተከሳሹ ጋብቻቸው 
በፍቺ ከተጠናቀቀ በኋላ ሆን ብሎ ሰው ለመግደል ማሰቡ፣ የእድሜ ታናሹንና የቀድሞ ባለቤቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ለመግደል መሞከሩ፣ ድርጊቱን መፈፀሜን አላስታውስም ብሎ በመካድ መከራከሩ እንዲሁም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቿ ላይ የፈፀመው ጉዳትና ድርጊት ሲታይ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ አነስተኛ መሆኑን ይጠቁማል ብሏል፡፡

Published in ዜና

በሠሜን ሸዋ ዞን መርሃቤቴ ወረዳ ልዩ ስሙ ጭራሮ ማርያም በተባለ ቦታ የቀድሞ ባለቤቱን ጨምሮ የባለቤቱን ወላጅ እናት፣ ወንድም እና የትዳር ጓደኛዋን በጥይት ደብድቦ የገደለው ተጠርጣሪ እስካሁን እንዳልተያዘ ተገለፀ፡፡ ተጠርጣሪው ታህሳስ 11 ቀን 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡30 ገደማ ነው ግድያውን የፈፀመው ተብሏል፡፡ በእለቱ በተፈፀመው ግድያ ወላጅ እናታቸውን ወ/ሮ ዘነበች አደፍርስን፣ ወንድማቸውን አቶ ችሮታው መኮንንን እንዲሁም እህታቸውን ወ/ሮ አበሬ መኮንን እና ባለቤቷን አቶ ተጫነን በአንዲት ጀንበር ያጡት አቶ አሻግሬ መኮንን፤ ይህን ሁሉ ሠው የገደለው ግለሠብ እስካሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር አለመዋሉ የፈጠረባቸውን ስጋት በመግለፅ ወደግድያ ላመራው ጠብ መነሻ የሆነው የንብረት ክፍፍል ጉዳይ መሆኑን ገልፀውልናል፡፡

Published in ዜና

የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ተሊላ፤ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፍትህ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ፡፡  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትያትር ጥበብ የመጀመርያ ድግሪያቸውን ያገኙት አቶ ሰለሞን፤ በጠ/ሚ ጽ/ቤት የተመደቡበት ሃላፊነት ከፍትህና ከአስተዳደር አካላት ለጠ/ሚኒስትሩ የሚመጡ ሪፖርቶችንና ሰነዶችን መመርመርና 
ሙሉ አጭር መግለጫ ማዘጋጀት፣ እንዲሁም የማጣራት ስራን ያካትታል፡፡ በመምህርነት የሰሩት አቶ ሰለሞን፤ በደቡብ ክልል ማስታወቂያ ቢሮ በኃላፊነት፣ በደቡብ ክልል መገናኛ ብዙሃን በስራ አስኪያጅነት ያገለገሉ ሲሆን በ1998 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሬዲዮ የሬዲዮ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ የነበሩ ሲሆን ኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሲዋሀዱ በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ተሾመው ሲያገለግሉ እንደቆዩ ታውቋል፡፡

Published in ዜና

የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችን የሚነቅፍ ፅሁፍ በግድግዳ ላይ ተፅፎ ተገኝቷል
ፖሊስ መንስኤውን እያጣራሁ ነው ብሏል
ባለፈው ረቡዕ በአራት ኪሎ ዩኒቨርስቲ የወንዶች ዶርም ግድግዳ ላይ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችን የሚነቅፍ ፅሁፍ ተፅፏል በሚል በተቀሰቀሰ ብጥብጥ፣ በበርካታ ተማሪዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ምንጮች ተናገሩ፡፡ ፖሊስ የብጥብጡን መንስኤ እያጣራሁ ነው ብሏል፡፡ ምንጮች እንደገለፁት፤ በወንዶች ዶርም ግድግዳ ላይ የተፃፈውን የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችን የሚነቅፍ ፅሁፍ ቀድሞ ያየው ተማሪ ለግቢው ፖሊስ ያመለከተ ሲሆን ፖሊሱም የተፃፈውን ፅሁፉ ወዲያው ያጠፋው ቢሆንም ፅሑፉ በሌላ ቦታ ላይም በመገኘቱ፣ ለብጥብጥ መነሻ ሆኗል ተብሏል፡፡

Published in ዜና

ለግብፅም ሆነ ለአውሮፓና ለኤሺያ ታህሳስ ልዩ ትርጉም አለው
ብርድ ወደ ሙቀት፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገሪያ ወር ነው
ታህሳስ 16 (ዲሰምበር 25)፡ “ፀሐይ የምትወለድበት ቀን” ነው
ዲሰምበር 25 ቀን የልደት ቀን የሚከበርላቸው አማልክት
ናዝራዊው ኢየሱስ፣ የፔርሻው ሚትራ፣ የግብፁ ሖረስ፣ የግሪኮቹ ዲየኒሰስ፣ የቱርክ አቲስ
ሁሉም የአምላክ ልጅ አምላክ ተብለው ይመለካሉ።
ሁሉም ከድንግል የተወለዱ እንደሆኑ ይታመንባቸዋል።
ሁሉም ሞተው ተነስተዋል - ብዙዎቹ በሶስተኛው ቀን።

Page 11 of 11