ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(12 votes)
በቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም የቤተመንግስትና የስራ ህይወት ዙሪያ የተፃፈው “የሌ/ኮ መንግስቱ ያልተነገሩ ሚስጥሮች” የተሰኘ መፅሀፍ ዛሬ ከማተሚያ ቤት ወጥቶ ለንባብ እንደሚበቃ አዘጋጁ አስታወቁ፡፡ የቀድሞው ልዩ ኃይል አባል እና የፕሬዝዳንት መንግስቱ አጃቢ በነበሩት እሸቱ ወንድሙ ወልደስላሴ የተፃፈው ባለ 120 ገፅ…
Rate this item
(0 votes)
የአዲስ አድማስ ፎቶ ጋዜጠኛ የሆነው አንተነህ አክሊሉ ያነሳቸው ከ30 በላይ ፎቶግራፎች የተካተቱበት “ላይት ኢን ሻዶው” የፎቶግራፍ አውደርእይ ካዛንቺስ በሚገኘው ኦዳ ታወር የፊታችን ሐሙስ ከምሽቱ 12 ሰዓት እንደሚከፈት አዘጋጁ አስታወቀ በኦዳታወር ሶስተኛ ፎቅ በቅርቡ በተከፈተው ኮክ ቺክን ባር እና ሬስቶራንት የሚከፈተው…
Rate this item
(1 Vote)
የግእዝ ቋንቋ እንዲያንሰራራ ያለመ ኪነጥበባዊ ዝግጅት ነገ ማምሻውን በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በኮሌጁ የምግብ አዳራሽ የሚቀርቡትን ድራማ፣የጥንታዊ ፅሁፎች ንባብ ፣ቅኔ፣ የግዕዝ ግሰሳ (ትንተና) ፣ጭውውትና ዜናን በግእዝ የኮሌጁ የግእዝ ቋንቋ ተማሪዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በህብረት እንደሚያዘጋጁት የጠቀሰው…
Rate this item
(0 votes)
ዓላማውን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ላይ ያደረገው “ሚስ ዩኒቨርስ” የቁንጅና ውድድር፤ በመጪው መስከረም ወር ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚካሄድ አዘጋጁ “ክሬቲቭ ኮሙኒኬሽን ኤንድ ኤቨንትስ” አስታወቀ፡፡ የውድድሩ ምዝገባና ፈተና ነሐሴ 11 እና 12 በፓኖራማ ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን መስከረም 10 በራዲሰን ሆቴል በሚካሄደው የ“ሚስ…
Rate this item
(2 votes)
በታተመበት ዘመን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቶ የነበረው “ጣምራ ጦር” ታሪካዊ ልቦለድ መጽሃፍ፤ ከ30 ዓመት በኋላ ዳግም ታትሞ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ የደራሲ ገበየሁ አየለ የበኩር ሥራ የሆነው ልቦለዱ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1975 ዓ.ም በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲታተም 30ሺህ ቅጂዎች እንደተሸጠለትና ለሦስት ጊዜ እንደታተመ…
Rate this item
(0 votes)
የደራሲ አዳም ረታ ረዥም ልቦለድ “ሕማማትና በገና” ነገ ውይይት እንደሚካሄድበት ሚዩዚክ ሜይዴይ አስታወቀ፡፡ ውይይቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አዳራሽ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ለሦስት ሰዓታት ይዘልቃል፡፡ የመነሻ ሃሳብ በማቅረብ ውይይቱን ከሚዩዚክ ሜይዴይ ባለሙያዎች ጋር የሚመሩት የሥነጽሑፍ ባለሙያው አቶ ቴዎድሮስ አጥላው…