ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(4 votes)
የኮሜዲያን አስረስ በቀለ የሕፃናት መጽሐፍ ተመረቀ “በፍቅር ላይ ሾተላይ” እና “የተወጋ ልብ” የተሰኙ ሁለት መጻሕፍት ነገ ከጧቱ 2፡30 በብሔራዊ ትያትር እንደሚመረቁ ዳኒ ሮጐ የማስታወቂያና ፊልም ፕሮዳክሽን አስታወቀ፡፡ በደራሲ ትክክል ገና የተፃፉት ሁለት የረዥም ልቦለድ መጻሕፍት በ2004 እና በ2005 የታተሙ ናቸው።…
Rate this item
(0 votes)
የደራሲና ዳይሬክተር ሱራፌል ኪዳኔ “ፍቅሬን ያያችሁ” ፊልም የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት በብሔራዊ ትያትር እንደሚመረቅ ወርቅ ሚዲያ ፕሮዳክሽን አስታወቀ፡፡ ለመሥራት አንድ ዓመት በፈጀው ፊልም መሐመድ ሚፍታ፣ ሩት አርአያ፣ እንግዳሰው ሀብቴና ሌሎችም ተውነዋል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በሠዓሊ ኤልያስ ሥሜ የተዘጋጁ የሥዕል ሥራዎች የሚቀርቡበት “የተወጠረ ገመድ” የሥዕል ዐውደርእይ ዛሬ በብሪቲሽ ካውንስል የሚከፈት ሲሆን አውደርዕዩ በጎተ ኢንስቲቲዩት፣ በአሊያንስ ኢትዮፍራንሴና በጣሊያን የባሕል ተቋም እንደሚቀርብም ታውቋል። የስዕል አውደርዕዩ በመስከረም አሰግድ ኩሬተርነት የሚቀርብ ነው፡፡ ሰዓሊ ኤልያስ ሥሜ ካሁን ቀደም በግሉ ዘጠኝ…
Rate this item
(2 votes)
የሴቶችን አቅም ለማሳደግ ያለሙ ዝግጅቶች በሸገር ኤፍኤም እንዲሁም በአማራ ክልል ሦስት ኤፍኤሞች እያቀረበ ያለው “የኛ” የሬዲዮ ፕሮግራም፤ ዛሬ በባሕርዳር ስቴዲየም የሙዚቃ ድግስ ያቀርባል፡፡ ከቀኑ ሰባት ሰአት ጀምሮ በባሕርዳር ስቴዲየም ለሕዝብ በነፃ የሚቀርበው የሙዚቃ ድግስ በዋነኛነት በልጃገረዶቹ የሙዚቃ ቡድን ይደምቃል፡፡ የልጆገረዶቹ…
Rate this item
(1 Vote)
ሃያ ሰባተኛው ግጥም በጃዝ በመጪው ረቡዕ ምሽት እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ አስታወቁ። በራስ ሆቴል አዳራሽ በሚቀርበው ዝግጅት ገጣሚ ነቢይ መኮንንን ጨምሮ ምንተስኖት ማሞ፣ በረከት በላይነህ፣ ባየልኝ አያሌውና ምስራቅ ተረፈ ግጥሞቻቸውን ሲያነቡ፤ ሀብታሙ ስዩም ወግ፣ ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት ዲስኩር ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ 
Rate this item
(2 votes)
ቀደም ሲል ለንባብ የበቃው “በአራጣ የተያዘ ጭን” የተሰኘ የአጭር ልብወለድ መድበል፣ እንደገና ታትሞ ለገበያ ቀረበ፡፡ 19 አጫጭር ልብወለዶችን የያዘው መጽሐፍ የዮፍታሔ ካሳ ድርሰት ሲሆን፣ ተወዳጅነት በማግኘቱ ሁለተኛ ዙር 10ሺ ኮፒ እንደታተመ ተነግሯል፡፡ የመጀመሪያው እትም 5ሺ ኮፒ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በ233 ገጽ…