ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(1 Vote)
በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማና አካባቢዋ የሥነጽሑፍ አፍቃሪያን የተቋቋመው “ሆራቡላ ሥነጽሑፍ ማሕበር” 20ኛ የስነጽሑፍ ዝግጅቱን የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 7፡30 በከተማው ሕይወት ሲኒማ ትንሿ አዳራሽ እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡ “የብዕር አዝመራ” በሚል ርእስ በሚቀርበው ዝግጅት፤ የማሕበሩ አባላት የግጥም፣ መነባንብ፣ ጭውውት እና ሌሎች ኪነጥበባዊ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡…
Rate this item
(0 votes)
በ1940ዎቹ የተመሠረተው ጐንደር ዩኒቨርስቲ የተመሰረተበትን የ60ኛ አመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል ለአንድ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይ ይገኛል፡፡ ዩኒቨርስቲው ዘንድሮ ከሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በተጨማሪ በዓሉን ምክንያት በማድረግ 3ሺ የቀድሞ ተማሪዎችንም በድጋሚ ያስመርቃል ተብሏል፡፡ ዩኒቨርስቲው በማስገንባት ላይ ያለውን ሆስፒታልም በሰኔ ወር እንደሚያስመርቅ ታውቋል፡፡…
Rate this item
(2 votes)
The secret በተሰኘው የመጀመሪያ መጽሐፏ ከፍተኛ ዝናን የተቀዳጀችው አውስትራሊያዊ ደራሲ ርሆንዳ ባይርኔ The hero በሚል ያወጣችው ሦስተኛ መጽሐፏ “ጀግና” ተብሎ ወደ አማርኛ ተተረጐመ፡፡ መጽሐፉን የተረጐመው ብርሃኑ በላቸው ነው፡፡ “እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው በየራሳችን መንገድ ራሳችንንና ዓለምን የማበልጸግ ዓላማ ይዘን ነው”…
Rate this item
(25 votes)
በገጣሚ ሲሳይ ታደሰ /ዘ-ለገሐሬ/ የተፃፉ የግጥም ስብስቦችን የያዘው ‹‹ለፍቅራችሁ›› የተሰኘ የግጥም መድብል ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ 106 ግጥሞችን ያካተተው መድበሉ፤ “ለፍቅራችሁ” የሚል ርዕስ የተሰጠው መጽሐፉ ለህትመት እንዲበቃ ያገዙትን ሁሉ ለማመስገን እንደሆነ ገጣሚው ገልጿል፡፡ የግጥሙ መድበል ለአገር ውስጥ በ30 ብር፤ ለውጭ ደግሞ…
Rate this item
(65 votes)
በአስፋው መኮንን የተፃፈውና አስቂኝ፣ ቀልዶችና ቁምነገሮች የተካተቱበት መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡ በአገራችን በቃል የሚነገሩ በርካታ አዝናኝና ቁም ነገር አስተማሪ ቀልዶች ቢኖሩም ብዙዎቹ በመፃህፍት ተፅፈው ስለማይቀመጡ የሚረሱና የሚደበዝዙ ይሆናሉ፤ ስለዚህም መመዝገብ አለባቸው ብሏል አዘጋጁ፡፡ በ158 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ35 ብር ለገበያ…
Rate this item
(1 Vote)
በዕውቋ ድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ተፅፎ የተዘጋጀው “ቀሚስ የለበስኩለት” የተሰኘ ፊልም በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽና በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡ የድራማ ዘውግ ባለው የ1፡40 ደቂቃ ፊልም ላይ፤ ድምፃዊቷ ዘሪቱ ከበደ፣ የንግድ ም/ቤት ፕሬዚዳንቷ ሙሉ ሰለሞን፣ የጃኖ ባንዱ ድምፃዊ ዲበኩሉ…