ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
በኢትዮጵያ የብራዚል ኤምባሲ ያዘጋጀው የፊልም ፌስቲቫል የፊታችን ሰኞ እንደሚጀምር ኤምባሲው አስታወቀ፡፡ ቦሌ በሚገኘው የብራዚል ኤምባሲ ለሕዝብ ከሚቀርቡት የብራዚል ፊልሞች መካከል ሶስቱ አስቂኝ ሦስቱ ድራማ ናቸው፡፡ ፊልሞቹ በየእለቱ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ የሚታዩ ሲሆን ለአንድ ሳምንት እንደሚቆዩ ታውቋል፡፡ የመግቢያ ዋጋ በነፃ…
Rate this item
(0 votes)
የደቡብ አፍሪካውን አንጋፋ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ሽጉጥ አስመልክቶ እየተሰራ ያለው ፊቸር ዶክመንተሪ ፊልም በኢትዮጵያም ሊቀረጽ ነው፡፡ የእንግሊዝ “ቢር ኸርት ሊሚትድ” እና የደቡብ አፍሪካ DV8 ኩባንያዎች በአሜሪካ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በእንግሊዝ ቀረፃውን ያከናወኑ ሲሆን በኢትዮጵያ “ታይኩን ሪል ስቴት” በተባለ ኩባንያ አማካይነት…
Rate this item
(1 Vote)
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተቋቋመበት ሃምሳኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች እንደሚከበር የበዓሉ አዘጋጅ ብሔራዊ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤትና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዋቀረው ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት የዛሬ ሳምንት በአምቦ ከተማ በተዘጋጀ አውደ ጥናት ላይ እንደተገለፀው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት…
Rate this item
(0 votes)
በተለያዩ የኪነጥበባት ዘርፎች የተሰማሩ አርቲስቶች ለ “መቄደንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል” ገቢ ማሰባሰቢያ ነገ በዘጠኝ ሰዓት የእግር ጉዞ እንደሚያደርጉ ተገለፀ፡፡ በዝግጅቱ ላይ ከአርቲስቶች በተጨማሪ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አርበኞች እና ሰላሳ ሺህ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የእግር ጉዞው በሚጀመርበት የኤግዚብሽን ማዕከል…
Rate this item
(1 Vote)
ኩል ፊልም ፕሮዳክሽን “አምራን” የተሰኘ አስቂኝ የፍቅር ፊልም ነገ በአዲስ አበባ የግል ሲኒማ ቤቶች እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡ በፊልሙ ላይ ማህደር አሰፋ፣ ሳምሶን ታደሰ፣ ሠለሞን ሙሄ፣ ሰላም አሰፋ እና አሸናፊ ከበደ ተውነውበታል፡፡ የ103 ደቂቃ ርዝመት ያለውን ይሄን ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ ስምንት ወራት…
Rate this item
(0 votes)
ሚዩዚክ ሜይዴይ በገጣሚ አያልነህ ሙላቱ “ከድጡ ወደ ማጡ” የግጥም መፅሐፍ ላይ ነገ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ በብሄራዊ ቤተመዘክር ውይይት እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ “የመግቢያና የይዘት ተቃርኖ” በሚል ርእስ የሚደረገውን ውይይት የሚመሩት ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ናቸው፡፡