ርዕሰ አንቀፅ

Rate this item
(8 votes)
 ከዕለታት አንድ ቀን፣ አንድ አሮጌ ውሻ፤ ከጌታው ጋር የመጨረሻ የመለያያ ውይይት ያደርጋሉ፡፡ ጌታው - እንግዲህ ውሻ ሆይ! በህይወታችን በጣም ረዥም መንገድ ተጉዘናል፡፡ አያሌ ውጣ ውረዶችንም አልፈናል፡፡ የእናንተ የውሾች ሞቅ ያለው ኑሮ የጉልበታችሁ ዘመን ላይ ያለው፤ ወርቃማ ጊዜ ነው፡፡ ሰውም እንደ…
Rate this item
(7 votes)
ከዕታት አንድ ቀን፤ አንድ አንቱ የተባሉ፣ የደሩና የኮሩ የጥንት አርበኛ ፊታውራሪ፣ በአንድ የገጠር ከተማ ይኖሩ ነበር፡፡ እኒህ ሰው ጠላትን ባባረሩ ማግሥት የጀግንነት ተግባራቸው አልጠቅም ብሏቸው፤ ወደ ጫካ ወጣ ይሉና አደን ላይ ይሰማራሉ፡፡ ከርከሮ ካገኙ ከርከሮ፣ አውራሪስ ካገኙ አውራሪስ…ብቻ ያገኙትን የዱር…
Rate this item
(13 votes)
አንዲት የቆቅ ልጅ የስንዴ እሸት ትርክክ ብሎ በስሎ በሚገኝበት እርሻ አጠገብ ወጥመድ ተጠምዶ አይታ እናቷን፤ “እናቴ ሆይ፤ እሸት አምሮኝ ነበር፣ ከዚህ ማሣ ገብቼ እንዳልበላ ወጥመድ እንዳይዘኝ ሰጋሁ፣ ምን ይሻለኛል?” ስትል ጠየቀቻት፡፡እናቷም፤ “ተይ ልጄ ይቅርብሽ ትያዣለሽ አይሆንም” ብላ መከረቻት፡፡ ልጅቷ ግን…
Rate this item
(10 votes)
ሩሲያውያን አንድ ተረት አላቸው፡፡ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ንጉሥ በዋናው ከተማ ውስጥ እየተዘዋወረ ሳለ የጣት ቀለበቱ ይጠፋበታል፡፡ ወዲያው በጋዜጣ ላይ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ “የጣት ቀለበቴን አግኝቶ ላመጣልኝ ሰው ወሮታውን እከፍላለሁ” የሚል ነው ማስታወቂያው፡፡ አንድ ተራ ወታደር ዕድለኛ ሆነና ቀለበቱን አገኘ፡፡ “ምን ባደርግ…
Rate this item
(9 votes)
ጥንት ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ዐረብ ፍርድ ቤት ይቀርባል፡፡ የከሰሱት ሶስት ሴቶች ናቸው፡፡ ያለአግባብ ፈቶናል፣ በድሎናል፣ ብለው ነው አቤቱታ ያቀረቡት፡፡ ዐረቡ ቀርቦ እያንዳንዳቸውን፤ “ለምን እንዳባረርካቸው አስረዳ?” ተባለ፡፡ዐረቡም፤“የመጀመሪያዋ ሚስቴ ጠዋት ማታ ጭቅጭቅ አበዛችብኝ!” አለ፡፡ “ምን ብላ ጨቀጨቀችህ?” አሉ ዳኛው፡፡ “ነገ ትፈታኛለህ፤…
Rate this item
(6 votes)
ዴሞስቴን የተባለ የግሪክ ፈላስፋ ህዝብ በተሰበሰበበት ንግግር ለማድረግ እየተሳነው ስለተቸገረ፤ የንግግር ልምምድ ለማድረግ ወደ አንድ ወንዝ አጠገብ ይሄዳል፡፡ ወንዙ በከፍተኛ ፍጥነት እየተወረወረ ቋጥኝ ላይ ያርፍና ኃያል ድምፅ ይፈጥራል፡፡ ዴሞስቴን ደግሞ ይህንን ድምፅ ለማሸነፍ እጅግ ነጎድጓዳማ ድምፅ ያወጣል፡፡ ወንዙ በቀጣይ ጩኸቱን…