ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
በገጣሚ ኤፍሬም ስዩም የተዘጋጀው “ተዋናይ ብሉይ የግዕዝ ቅኔያት ፍልስፍና ከቀደምት የኢትዮጵያ ነገስታትና ሊቃውንት” የተሰኘ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ከ11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በጣልያን የባህል ተቋም እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡ ውርስ ትርጉሙ በኤፍሬም ስዩም የተዘጋጀው መጽሐፉ፤ በሚመረቅበት ዕለት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋና መጋቢ ሃዲስ…
Rate this item
(0 votes)
በሚካኤል ልኡልሰገድ የተዘጋጀው “የፊልም ጽሑፍ አፃፃፍ” የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ከቀኑ 9፡30 በጣይቱ ሆቴል ጃዝ አምባ እንደሚመረቅ ፕሮግራሙን በትብብት ያዘጋጀው አላቲኖስ ፊልም ሰሪዎች ማህበር በላከው መግለጫ አስታወቀ፡፡ ሚካኤል ልኡልሰገድ “የማትበላ ወፍ” የተሰኘው ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር መሆኑ ይታወቃል፡፡
Rate this item
(2 votes)
በ1997 ዓ.ም ተጀምሮ በየአመቱ እየተካሄደ ያለው “የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል” ስምንተኛ ዝግጅት ባለፈው ሰኞ ምሽት በብሔራዊ ትያትር በሚደረግ የሽልማት ሥነሥርዓት እንደሚጠናቀቅ ሊንኬጅ አርት ሪሶርስ ሴንተር አስታወቀ፡፡ ዝግጅቱን የሚያቀርበው የሊንኬጅ አርት ዋና ሥራ አስኪያጅ አርቲስት ይርጋሸዋ ተሾመ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው፣ በፌስቲቫሉ…
Rate this item
(2 votes)
ሚዩዚክ ሜይዴይ “አመኛው ክልስ” በተሰኘው የዳንኤል ሁክ መጽሐፍ ላይ ነገ ውይይት እንደሚካሄድ ገለፀ፡፡ ከቀኑ 8 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመጻሕፍት የሚካሄደውን የሦስት ሰዓታት ውይይት፣ የመነሻ ሀሳብ በማቅረብ የሚመሩት የሥነ ጽሑፍ ባለሙያው አቶ አስቻለው ከበደ ናቸው፡፡
Rate this item
(1 Vote)
“አቦል፣ ቶና፣ በረካ” በሚል ርእስ ቡና ላይ ያተኮረ የሥዕል አውደርእይ እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በመጪው አርብ በአምስት ኪሎው ብሔራዊ ቤተመዘክር ተከፍቶ እስከ ታህሳስ 7 ለሕዝብ በሚቀርበው አውደርእይ የሚገኘው ገቢ፣ ቦንጋ ላይ ለሚገነባው የቡና ቤተመዘክር ሕንፃ ማሰሪያ እንደሚውል አዘጋጆቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
Rate this item
(1 Vote)
መሳይ ፕሮሞሽን ከመንሱር ጀማል ፕሮሞሽን ጋር በመሆን የፀረ “የፆታ ጥቃት” ዘመቻ ቀንን የተመለከተ ኪነጥባዊ ዝግጅት ትናንት ጠዋት በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት አዳራሽ አቀረበ፡፡ “እኔንም ይመለከተኛል” በሚል መሪ ቃል በቀረበው ዝግጅት ግጥሞች፣ ወግ፣ መነባንብ፣ ሙዚቃዊ ድራማ እና ሥነቃሎች ቀርበዋል፡፡