ርዕሰ አንቀፅ

Rate this item
(20 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ከዳር አገር ወደ ዋናው ከተማ የመጡ አዛውንት ለንጉሱ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ከዙፋን ችሎቱ ዘንድ ተቀምጠው ተራቸውን ይጠብቃሉ፡፡ ባለሟሎች ስነ-ስርዓት እያስከበሩ ሁሉን በወግ በወግ ያስተናግዳሉ፡፡ አንዱ ሲጨርስ ሌላው ግባ ይባላል፡፡ በዚሁ ደንብ እኒያ የዳር-አገር መኳንንት ተራቸው ይደርስና ይቀርባሉ፡፡…
Rate this item
(13 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን መልኩ ወደ ቁራ የሚሄድ አንድ ጥቁርና ነጭ ዥጉርጉር ወፍ በአንድ ጫካ ውስጥ ይኖር ነበረ፡፡ በእርሻ ማሳው ውስጥ የሚያማምሩ ነጫጭ እርግቦች እየተመገቡ፣ ብር ትር እያሉ ሲጫወቱ አየ፡፡ ከወፋፍርነታቸው መልካም ተመግበው እንደኖሩ ያስታውቃሉ፡፡ የገላቸውና የላባቸው ንጣት ዐይን ይስባል፡፡ ያ…
Rate this item
(22 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሐኪም በሽተኛውን ሊጠይቅ ወደ በሽተኛው ክፍል ይሄዳል፡፡ ሐኪም፡ “እንደምናደርክ ወዳጄ?”በሽተኛ፡“ደህና ዶክተር፤ አንተስ ደህና አደርክ?”ሐኪም፤ “እኔ ደህና አድሬአለሁ፡፡ ለመሆኑ ህመምህ እንዴት ነው?”“በጣም ያልበኛል እንጂ ደህና ነኝ”ሐኪም፤ “ይሄ ጥሩ የመዳን ምልክት ነው፤ አይዞህ” አለውና ሄደ፡፡ በሶስተኛው ቀን ሐኪሙ…
Rate this item
(20 votes)
አንድ አርሶ አደር በአጥር ግቢው ውስጥ አንድ የፍሬ ዛፍ ነበረው፡፡ ሆኖም ይሄ ዛፍ ፍሬ አላፈራም፡፡ ስለዚህም አርሶ አደሩ፣“አንተ ዛፍ፤ስንት ዓመት ሙሉ ደጃፌ ቆመህ አንዲት ፍሬ እንኳን ሰጥተኸኝ አታውቅም፡፡ አሁን መቆረጫህ ሰዓት ደርሷል - ተዘጋጅ!” አለው፡፡በዛፉ ላይ በየቅርንጫፉ ውስጥ የሚኖሩና በጥላው…
Rate this item
(20 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አይጥና አንድ እንቁራሪት በቀጠሮ ይገናኛሉ፡፡ አይጥ፤ “እመት እንቁራሪት፤ አንዳንዴ ከውሃ ወጥተሽ መሬት ላይ ፀሐይ ስትሞቂ ሳይሽ ‘ምነው ከዚች ጋር ጓደኝነት ብንጀምር?’ እያልኩ ልቤ ስፍስፍ ይላል፡፡”እንቁራሪትም፤ “ሆድ ለሆድ የመነጋገር ነገር ጠፍቶን ነው እንጂ እኔም እኮ ባየሁሽ ቁጥር…
Rate this item
(23 votes)
ከኤዞፕ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡- ከዕለታት አንድ ቀን በአንድ ትልቅ በረት ውስጥ አንድ አውራ ዶሮና አህያ ይኖሩ ነበረ። አህያው ለአውራ ዶሮው፤ “ስማ አያ አውራዶሮ፤ መቼም እኔና አንተ የረዥም ጊዜ ወዳጆች ነን፡፡ ምንም ዓይነት ችግር ቢገጥመን እንዳንከዳዳ” አውራ ዶሮም፤ “ይሄንን ነገር…