ልብ-ወለድ

Saturday, 10 August 2013 12:10

ሚሊየነሩ መቃብር ቆፋሪ

Written by
Rate this item
(25 votes)
የጉልማ መላኩ ሕይወትን የሚቀይር ተአምር የተፈጠረው እንደ ልማዱ በማለዳ ተነስቶ ወደ ሥራው እየሄደ ሳለ ነበር፡፡ ተአምሩ በተከሰተበት ዕለት ባለቤቱ ጐጄ፣ ከውድቅት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ በመነዝነዝ፣ እንቅልፍ በዓይኑ ሳይኳል እንዲያድር አድርጋው ነበር፡፡ ከንዝንዟ ለመሸሽ በጠዋት ተነስቶ ወደ ሥራው ሲሄድ ነው…
Saturday, 03 August 2013 10:51

ያልነገርኩሽ ነገር

Written by
Rate this item
(7 votes)
(ካለፈው የቀጠለ)ሀሌሉያ ሚናን እንዳፈቀረው አፍቅሮ አያውቅም፤ ኧረ እሱ ጭራሽ አፍቅሮ አያውቅም፤ አሁን ግን የሚያስበው ስለ ፍቅር፣ የሚያነበው ስለ ፍቅር፣ የሚያደምጠው የፍቅር ሙዚቃ ነው፡፡ በየቀኑ ከሚሰማቸው የፍቅር ዘፈኖች የወደዳቸውን ሀረጎች ስንኞች እየፃፈ ለሚና ስልኳ ላይ ይልክላታል። የትኛውም ሀረግ፣ የትኛውም ስንኝ ግን…
Saturday, 27 July 2013 14:19

ያልነገርኩሽ ነገር

Written by
Rate this item
(35 votes)
ሁለቱም ፍቅር ይይዛቸዋል ተብለው የሚጠረጠሩ አይነት አይደሉም፡፡ ‘እንዲህ የሚባል ነገር አለ እንዴ?’ ሊል ይችላል አንዳንድ ሰው፡፡ አዎ እንዲህ የሚባል ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ፡- “እከሌ እኮ ፍቅር ይዞታል፡፡” ሲባል” “ተዉት እባካችሁ እሱ ልማዱ ነው፡፡” የሚል መልስ ይሰማል፡፡ አንዳንዴም፡- “እከሊት እኮ ፍቅር…
Saturday, 20 July 2013 10:34

ዘቢብ

Written by
Rate this item
(3 votes)
(የሰባ መስዋዕት) ሐበሻ ሽፍታ ይወዳል፡፡በዝምታ የተኳለ መልከመልካምነት አይመስጠውም፡፡የቁጣ ዝናሬን ታጥቄ…ምንሽሬን ወልውዬ…ግስላ መሆን ነው፡፡ የገዛ ህሊናው ነበር እንዲህ እያለ ልቡ ውስጥ ነጋሪት እየጐሰመ ፋኖ ያደረገው፡፡ እንየው፤ ቀጠሮው ቀፎታል፡፡ የልጅነት ጊዜውን በዘርዛራ ወንፊት አንገዋሎ፣ አንገዋሎ፣ የትዝታውን ውጤት እንቅጥቃጭ አድርጐበታል፡፡ እጁ ላይ “ቴስቲ”…
Saturday, 13 July 2013 11:36

ክኒና

Written by
Rate this item
(4 votes)
አስር አለቃ ጠና ከካፊያው ለመሸሽ ወደ ፋርማሲው በረንዳ ጠጋ አሉ፡፡ «ተናግሬያለሁ ጌታው!... ሰሃት ታለፈ በኋላ ወደዚህ መጠጋት አይቻልም» አሉ የፋርማሲው ዘበኛ ኮስተር ብለው፡፡ «ምን ላርግ ብለህ ነው!?… ስንትና ስንት ብር ያፈሰስኩበት መዳኒት አጉል ሁኖ ሊቀርብኝ እኮ ነው!» ብለው ቆፈን ያደነዘዘው…
Saturday, 06 July 2013 13:36

ፍርሐት

Written by
Rate this item
(3 votes)
እያነበበ ነበር የቆየው እስከ ምሽቱ አራት ሰአት ድረስ፡፡ መፅሐፍ በህይወት ዘመኑ ከሶስት የበለጠ አንብቦ አያውቅም፡፡ ሶስተኛውን ሊጨርስ ትንሽ ነው የቀረው፡፡ ሦስት ሰአታት ማንበብ ቢቀጥል ይጨርሰዋል፡፡ ዝናቡ ድንገት ሲቆም ፀጥታ በቤቱ ውስጥ እና ዙሪያ ሰፈነ፡፡ ከጫጫታ ለመራቅ ብሎ ነው ከሳምንት በፊት…