Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 11:49

በተቃዋሚ አመራሮች እስር... መንግሥትና ተቃዋሚዎች የተወዛገቡ ነዉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በተቃዋሚ አመራሮች እስር... መንግሥትና ተቃዋሚዎች የተወዛገቡ ነዉ
ባለፉት ሦስት ወራት መንግሥት በሽብርተኝነት ጠርጥሯቸው ከተያዙት ሠላሳ ሰዎች ውስጥ አስሩ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እንደሆኑ ታውቋል፡፡ መንግሥት በሰጠው መግለጫ፤ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የተያዙት እየፈፀሙ ያሉትን ተግባር ደርሼበት እንጂ በፖለቲካ ተሳትፎአቸው አይደለም ብሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት ተጠርጥረው የተያዙት አምስት የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው በማረሚያ ቤት ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ተጠርጣሪዎች አስመልክቶ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እና የፌደራል ማዕከላዊ መረጃ ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳሬክቶሬት ÄÊKtR! ረ/ኮሚሽነር ደመላሽ g/¸µx¤L" ለጋዜጠኞች የሰጡትን  መግለጫ እና ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ እንደሚከተለው አቅርበውናል፡፡   
ረ/ኮሚሽነር ደምመላሽ
በፌደራል ፖሊስና በመረጃና ደህንነት የሰው hYL" የተወሰነ ጊዜ ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች አገራችን ላይ በሽብር ወንጀል የሁከትና የብጥብጥ አጀንዳ YzW! ግንቦት ሰባት ከተባለው እና በአገራችን በፀረ ሽብር ህግ ከተሠየመው ድርጅት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተጠርጥረው ነው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ ከነሱ ጋር ተያይዞ የተለያዩ ማስረጃዎችና መረጃዎችን ፖሊስ አግኝቷል " ሂደቱ አሁን በምርመራ አስፈላጊው ማጣራት የተደረገበት ስለሆነ በጉዳዩ ላይ መግለጫዎች ተሰጥቷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ክህደትና ስለላ ሲፈጽሙ መያዛቸውን የሚጠቁም መግለጫ w_aL" እንደተባለውም ትክክል ነው" ግለሰቦቹ በዋናነት ተጠርጥረው በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሀገራችን የሽብር የሁከት እና የብጥብጥ አላማ ይዞ ከሚንቀሳቀሰው እና በሽብርተኝነት ከተሰየመው ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ለድርጅቱ እንደሚሰልሉ እና መረጃ እንደሚያቀብሉ በቂ ጥርጣሬ SlnbrN" በእዛ ጥርጣሬ ላይ ተመርኩዘን በቂ መረጃዎችን እና ማስረጃዎቻችንን በማሰባሰብ ነው በቁጥጥር ስር ያዋልናቸው፡፡ የአገራችን የሽብር ህግ ደግሞ ይሄንን በሚገባ የደነገገ ሲሆን በዚህ ተግባር ላይ የሚሠማራ ማንኛውም ግለሰብ በፀረ ሽብር ህጉ መሠረት በወንጀል እንደሚጠየቅ ተደንግጓል፡፡ ከዚህ አንፃር ነው ፖሊስ በቂ መረጃና ማስረጃ እጁ ካስገባ በኋላ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገው፡፡ ሌላው ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንዳለ ለሁላችንም ግልጽ ነው" በምርመራ ላይ ያለን ነገር ደግሞ  እዚህ በዝርዝር ማንሳቱ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ከተያዙ ገና ሁለተኛና ሦስተኛ ቀናቸው ነው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሲያዙ ከፍ/ቤት የመያዣና የመበርበሪያ ትዕዛዝ ወጥቶ ነው፡፡ በተጨማሪ ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ t«YöÆcW! እየተጣራ ያለ  ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ዝርዝር  መረጃና ማስረጃን መግለፁ አስፈላጊ አይደለም፡፡
አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ያሉትን መረጃዎችና ማስረጃዎች መግለ ይቻላል፡፡ ሌላው ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተያይዞ አንድ ነገር አለ፡፡ አገራችን በተለያዩ ጊዜ በሽብር ወንጀሎች ሲፈፀሙባት ቆይተዋል፡፡ ብዙ የሰው ህይወት xLÐL" ብዙ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አደጋዎች dRsêL" እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ንብረቶች ወድመዋል፡፡ ይሄንን ሁላችንም በደንብ እናውቃለን፡፡ ፖሊስም የፀረ ሽብር ግብረ ሃይሉ  አስቀድሞ አደጋውን ለመከላከል እንዲችል ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሱን እያደረጀና እያጠናከረ የሽብር ወንጀልን በመከላከል ላይ ይገኛል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በመሆናቸው xYdlM" ፖሊስ በሽብር ወንጀል በመጠርጠሩ እና ማስረጃና መረጃ አለኝ ብሎ ስላመነ ነው ፍርድ ቤት ቆሞ አስፈላጊውን የፍርድ ሂደት ስራዎችን የሚሰራው፡፡ እነዚህ ሰዎች ፍርድ ቤትም ሲቀርቡ በሰሩት ወንጀል እንጂ የፓርቲ አባል በመሆናቸው አይደለም፡፡ አሸባሪዎችን ይዘን ስንመረምርና ስናስቀጣ የመጀመሪያችን አይደለም፡፡ እከሌ ከዚህ ፓርቲ ነው YÃZ! እከሌ ከዚያ ፓርቲ ነው እንዳትነኩት የሚል ህግና ትእዛዝ እንደሌለ ነው መታወቅ ያለበት፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል
ሰሞኑን በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦችን ጉዳይ በተመለከተ መሠረተ ቢስ ወሬዎች ሲናፈሱ እየሠማንም ነው የከረምነው፡፡ ከነዚህም ነገሮች አንደኛው ግለሰቦቹ የተያዙት በሚያቀነቅኑት የተቃዋሚ የፖለቲካ አቋም የተነሳ ነው የሚለው መሠረተ ቢስ ስሞታ ነው፡፡ ሁላችሁም እንደምታውቁት አገራችን ህገመንግስታዊ የዲሞክራሲያዊ ስርአት የምትከተል ሀገር ÂT" በሀገራችን ውስጥ ከ90 በላይ የሚሆኑ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው እና እውቅና አግኝተው በነፃነት የሚንቀሳቀሱባት ሀገር ናት፡፡ በዚህ የተነሳም በይፋ የተመዘገቡበትን እና በህጋዊና በሠላማዊ መንገድ ለማራመድ የሚከተሉትን መስመር በመያዛቸውና በማቀንቀናቸው አንዳቸውም ለእንግልትና ለእስር የተዳረጉበት አንዳችም ሁኔታ የለም፡፡ ይሄ እንዲህ ሆኖ እያለ ግን በአንዳንድ ግለሰቦች በተለይ ግን በሽብር ስራ ውስጥ የተሠማሩ ሰዎች ህጋዊ እና ሠላማዊ የፖለቲካ አቅጣጫ ለመከተል እና ለመንቀሳቀስ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች አባልነትን እንደ ከለላና ሽፋን በመጠቀም አባላቶቻቸውን አስርገው የሚያስገቡበት ወይም ከነዚህ ድርጅቶች ውስጥ አባላት የሚሆኑትን በመመልመል ህገወጥ የሆነ የሽብር ስራቸውን በህቡዕ (በስውር) ለማካሄድ ጥረት የተወሰዱ የፀረ ሽብርተኝነት እርምጃዎች በፍርድ ቤት የተሰጡ ብያኔዎች በትክክል ያሳያሉ ስለሆነም ይሄንን ሁለት ጉዳዮች አምታቶ ግለሰቦቹ የሚከተሉትን የፖለቲካ አቋም የያዙትን የተቀናቃኝ የፖለቲካ አቋም ብቻ ስለያዙ በፀረ ሽብርተኝነት ሳቢያ ለእስር ተዳርገዋል የሚለው አመለካከት ውሃ የማይቋጥር መሠረተ ቢስ አሉባልታ እና ስሞታ ነው የፀረ ሽብር ህጉ በአገራችን ውስጥ ተግባራዊ ከሆነ ጀምሮ በበርካታ በሠላማዊ ነዋሪዎች ላይ ሊቀጡ ይችሉ ቢሆን ኖሮ ከፍተኛ ጉዳይት ሊያደርሱ የሚችሉ የሽብር እርምጃዎችን ከጅምራቸው እንዲቀጩ በማድረግ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ የአገራችን የፀረ ሽብርተኝነት ህግ እንዲወጣ በዋነኝነት ምክንያት የሆነው የነበሩ የወንጀለኛ መቀጫ ህግ ይሄንና እጅግ አደገኛ በአለም አቀፍ ደረጃ ትስስር ያለውን የከባድ የወንጀል ድርጊት ለመቋቋም እና አስቀድሞ መከላከል በሚያስችል መንገድ የተደራጀ " በጠቅላላው ማህበረሰቡ ዘንድ እጅግ ከፍተኛ አደጋን ከጊዜ ወደ ጊዜ ይዞ የመጣውን የሽብርተኝነት አደጋ በየሀገሩ ባሉ የህግ አስፈፃሚ ተቋማት ዘንድ የህግ መድበላቸውን እና አስተዳደራዊ የወንጀል መከላከልና ተቋማቶቻቸውን አቅም የመገንባት ስራዎች ውስጥ እንዲገቡ ያስገደደ በመሆኑ " ሀገራችንም የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አካል በመሆኗ እና በተደጋጋሚ ለሽብርተኝነት ብቃት ተጋልጣ የቆየች ሀገር በመሆኗ" በዚህ መሰረት በዚህ ልዩ የሆነው አደገኛ ወንጀል አስቀድሞ ከመከላከል እና ለመቆጣጠር ተጠያቂዎቹንም ለፍርድ በማቅረብ በመጨረሻም የህዝቡን ሰላማዊ እና ደህንነት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠበቅ የሚያስችል የህግ መድበል አውጥታለች፡፡  አዲሱን የፀረ ሽብርተኝነት ህግ ተቀናቃኞች እንደሚያወሩት ሳይሆን አለም አቀፍ መስፈርቶችን እና እስታንዳርዶችን y«bq! በርካታ ዲሞክራሲያዊ አገሮች የተከተሉትን የህግ አንቀ እና መርሆች መሰረት አድርጐ የተቀረፀ የህግ መድብል ነው፡፡ በህጉ ይዘቶች ላይ ሰብአዊ መብትን ያለ አግባብ ለመደፍጠጥ በተለይም በመናገር እና በሃሳብ ነፃነት ውስጥ ለፖሊስ ስራዎች መንገድ ለመክፈት ታስቦ የወጣ ድንጋጌ አይደለም፡፡ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ከፍተኛ ጥንቃቄ በሌላ በኩል ደግሞ ማህበራዊ ጥቅምን ሚዛን ላይ በማስቀመጥ ሁለቱን ተነፃፃሪ ጥቅሞችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሊጠብቅ በሚችልበት መንገድ ተቀርፆ የወጣ ህግ ነው፡፡ ይሄ ህግ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ እንደምታስታውሱት የተለያዩ የአሸባሪ ድርጅቶችን ህብረተሰቡ አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በሚያስችል መንገድ የሽብርተኛ ድርጅቶች ተለይተው እንዲወጡና እንዲሰየሙ b¥DrG" ከዚህም አልፎ አደገኛ የሽብርተኛነት ስራዎችን ከጅምራቸው በማጨናገፍ በህብረተሰቡ ሊቃጣ የነበረውን ከፍተኛ አደጋ በማስቀረት ረገድ ትልቅ አስተዋኦ እያደረገ ያለ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ይሄ ህግ ለስጋት ሊዳርጋቸው የሚችሉ ወገኖች ካሉ አቋማቸውን çStµklù! በሽብር ተግባር ውስጥ ለመግባት የሚቋምጡ ወይም የገቡ ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር በዜጐች መሰረታዊ ነፃነቶች ላይ የተሟላ ጥበቃ ለማድረግ የወጣው ህግ" የዜጐችን መሰረታዊ ዲሞክራሲያዊ ፖለቲካዊ መብቶች ያለ አግባብ ለመደፍጠጥ እና በህብረተሰቡ ላይ ሽብር ለመንዛት የሚቃጡ ወንጀሎችን አስቀድሞ መከላከል ብቻ አላማው ያደረገ በመሆኑ ነው ጥቅም አስገኝቷል ብለን የምናምነው፡፡
ረ/ኮሚሽነር ደመላሽ
እነዚህ አምስት ግለቦች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የሚገኙበት ምክንያት ግለሰቦቹ በአገራችን የፀረ ሽብር ህግ መሰረት በዚህ አመት አምስት የሽብር ድርጅቶች በህግ ተደንግገዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ አንዱ ግንቦት ሰባት ነው፡፡ ግንቦት ሰባት በአገራችን ላይ የተለያዩ ሁከቶች፣ ሽብሮችና ብጥብጦች እንደዚሁም ህገ መንግስታዊ ስርአቱን የመናድ አላማ ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው፡፡ ከዚህ ድርጅት ጋር እነዚህ ተጠርጥረው የተያዙ አምስት ግለሰቦች ከነዚህ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ፖሊስ ለብዙ ጊዜ ክትትል ሲያደርግ ስለነበር መረጃዎችን እና ማስረጃዎችንም በእጁ አስገብቷል፡፡ በተለይም በዚህ አዲስ አመት አገራችንን ወደ መበጥበጥ፣ ወደረብሻና  ሁከት ለማስገባት እና ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለመቀየር እንቅስቃሴ sþÃdRgù! ከዛም አስፈላጊ እቅድ አዘጋጅተው ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት በመፍጠር መረጃ በማቀበል እና የስለላ ስራዎችን በመስራት ስለተገኙና ስለተጠረጠሩ እንጂ ፖለቲካዊ በሆነ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በመቆየታቸው አይደለም፡፡ ፖሊስ እነዚህን ግለብ በቁጥጥር ስር ሊያውል የቻለው፡፡ ፖሊስ ይዞ ፍ/ቤት ቢያቀርብም በፍ/ቤት ተቀባይነት ሊሆን አይችልም፡፡ የሽብር ወንጀል ሲባልና በሀገራችን የፀረ ሽብር ህግ መሰረት ማሟላት የሚገባቸውን አሟልተው ከዛ ጥፋተኛ መሆናቸውን መገኘታቸውን ፖሊስ በማስረጃ ማቅረብ ሲችል ነው፡፡ እነዚህን ግለሰቦች ጥፋተኛ ብሎ ወደ ክስና ወደ እራሱ ጉዳይ ሊወስዳቸው የሚችለው ከዚህ አንፃር ስንይዝም ሆነ ሳንይዝም የብርበራና የመያዣ ትእዛዝ ስንጠይቅ አስፈላጊውን ማስረጃና መረጃ ፍርድ ቤት አቅርበን ነው ፖሊስ ከዚህ በኋላ ነው ወደ መበርበር እና ወደ መያዝ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ወደመፈለግ የሄደው፡፡ በዚህ መሰረት ተይዘው ፍ/ቤት ቀርበዋል ፍ/ቤቱም አምኖ ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በሽብርተኝነት ላይ ከዚህ ቀደም በወደሙ ንብረቶች እና የሰው ህይወት ላይ ከተቃዋሚ ፓርቲ አካላቶች ተጠያቂ የነበሩ ካሉ ከመንግስት ሠራተኛ ሆኖ መንግስትን እደግፋለሁ ብለው የነበሩ በተለያዩ የሽብር ተግባር ተመልምለው በህግ የተጠየቁበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ይሄ ነገር ዛሬ የሚቆምበት ሁኔታ አይደለም፡፡ ወንጀሉ በአለም አቀፍ ደረጃ የተስፋፋበትና አስጊ የሆነበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የአገራችን ፖሊሶች የመረጃና ደህንነት አካልም አስቀድሞ የመከላከል ስራን ለመስራት በህብረተሰብ ጋር ሆኖ እነዚህን ነገሮች በሚጠረጥርበትና በጥርጣሬ በሚያኝበት ቦታ ላይ ክትትል እያደረገ በዚህ ጉዳይ ሚሰማሩትን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እያዋለ መሄዱ የሚቆም ጉዳይ አይሆንም፡፡ ለዚህም እነዚህ ግለቦች በቁጥጥር ስር ሲውሉ የአገራችንን ህገ መንግስት የአገራችንን የፀረ ሽብርተኝነት ህግ ተከትለን ነው እነዚህን ሰዎች በቁጥጥር ስር ያዋልናቸው፡፡ ፍርድ ቤት እየቀረቡ ይሄዳሉ ፍ/ቤቱ ገለልተኛ ሆኖ ውሳኔ የሚሰጥበትን ሁኔታ እያመቻቸን እንሄዳለን ማለት ነው፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል
በዋነኛነት የዜጐችን መሰረታዊ መብቶች ለማስጠበቅ የወጣ ድንጋጌ ነው፡፡ ዜጐች ሽብርተኝነት ሰለባዎች የሚመርጥ ወንጀል አይደለም እራሳቸው ላይ አጥፍቶ ጠፊ አድርገው የሚሄዱ ሰለባዎቻቸውን አይመርጡም፡፡ ማንም ሰወ የጥቃቱ ሰለባ የሚሆንበት ነገር ነው ያለው፡፡ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በአመለካከት ወዘተ... ልዩነት አድርገው ሰለባዎቻቸውን የሚያጠቁ ወንጀለኞች አይደሉም፡፡ ሽብርተኞች ስለዚህ በመላው የህብረተሰብ ክፍለ እና የሰው ልጅ ላይ የተቃጣ ላይ በሰብአዊ ላይ የተቃጣ አደገኛ ወንጀል ነው፡፡ ሽብርተኝነት የሚባለው ዋነኛ ምክንያት ይሄ ነው፡፡ ስለሆነም ዜጐች ያልሆኑ ግለሰቦችንም ቢሆን መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶቻቸውን በህይወት ከመኖር ጀምሮ የመንቀሳቀስ መብታቸውን ወዘተ አጥፍቶ አጥፊዎች ማንኛቸውንም አላማቸውን በማሸበር በማስደንበርና ለማስፈራራት ለማስፈፀም ከሚቃጣቸው ሽብርተኞች ቅጣት ለመታደግ የወጣ ድንጋጌ ነው እርምጃውም ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በምንም አይነት መንገድ ከሰብአዊ መብቶች አፈፃፀም ጋር ቅራኔ ውስጥ እንደሚገባ ተደርጐ መታየት የለበትም፡፡ ስለሆነም አንዳንድ አገሮች ውስጥ ሽብርተኝነት ስር ሰዶ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ያስከተለባቸው አገሮችን ምሳሌ በመጥቀስ እንደዚህ አይነት አገሮች እውነት አገራችን ውስጥ ካልተከሰተ በስተቀር ሽብርተኝነት ለመጥላት ሽብርተኝነትን ከመቆጣጠር መንግስት እርምጃ መውሰድ የለበትም የሚለው አነጋገር እኔ ጤነኛ አመለካከት ካለው ፍጡር የሚመጣ ነው ብዬ አልገምትም፡፡ ሽብርተኝነት ለመከታተል እንዲህ አይነት ህግ ያወጡ አገሮች የሊባኖስ፣ የአፍጋኒስታን አይነቱ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ እስኪዘፈቁ ድረስ አልጠበቁም መጠበቁም አስፈላጊ አይደለም፡፡ እንደማንኛውም ወንጀል ልክ እንደ ህክምና ሁሉ በወንጀል መከላከል እና ጥበቃ ሂደት ውስጥ ትልቁ ቁምነገር በሽታ ከደረሰ በኋላ ለማከም ከመሮጥ ይልቅ በሽታ ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ነው ትልቁ ነገር፡፡ በአንድም ግለሰብ ላይ አደጋ ከመድረሱ በፊት አደጋውን ማስቆም ነው የማንኛውም የህግ አስፈፃሚ እና የወንጀል መከላከል ተቋም ውጤታማነት የሚፈተነው አስቀድሞ ወንጀል ከመድረሱ በፊት ለመከላከል ባለመብቃቱ በፓኪስታን ሁኔታ አልፈፀመም እና የፀረ ሽበርተኝነት ህግ አያስፈልገንም የሚለው አያስኬድም፡፡   
ረ/ኮሚሽነር ደመላሽ
ህዝቡ መረበሽ የለበትም፡፡ ፖሊስ ተጠንቅቆ እየሠራበት ያለው የአገራችን ሠላም የማስከበር" ህገመንግስቱን የማስጠበቅና የመጠበቅ"  ህብረተሰቡ አሁን የጀመረውን የልማት አቅጣጫ መቀጠል  ሲሆን ፖሊስ ብቻውን የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ ፖሊስ በጥርጣሬ የሚይዛቸውን በህገመንግስቱና ሕጉ በሚያዘው መሠረት ጉዳያቸው እንዲሄድ የማድረግ" ሁሉም ሰው ህገመንግስቱን የማስከበር እንጂ ፍራቻ መኖር የለበትም፡፡ ሁላችንም የምንመራው በህገመንግስት ነውፖሊስ ደግሞ ሠላም እንዲኖር ከሚያደርጉት ተቋማት አንዱነው" ስለዚህ ፍርሃት mF?R የለባቸውም፡፡  እነዚህ ሰዎች ፍ/ቤት እኮ የቀረበባቸው ጉዳይ በቂ አይደለም ብሎ ነፃ ሊለቃቸው YC§L" እንጂ ማንም ጉልበተኛ የሚኖርባት አገር አይደለችም፡፡    
አቶ ሽመልስ ከማል
ማንም ጋዜጠኛ አትሞ ባወጣው ጽሑፍ የታሠረ የለም፡፡ ጋዜጠኛ ተብሎ የታሰረ የምናውቀው ውብሸት ታዬን ነው፡፡ እሱ ደግሞ በፃፈው ነገር xYdlM" እሱ የተያዘው የኢንፍራስትክቸሮችን ከአሸባሪ ጋር የማፍረስ አላማና ተግባር ላይ ተገኝቷል ተብሎ ነው! ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲህ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ የሚባለውን በጋዜትኝነት አያውቀውም፡፡ የት ተቀጥሮ እንደሚሠራ አናውቅም" ከዚህ በፊት አሳታሚ እንደነበር ነው የምናውቀው፡፡ በፊት ሲያሳትማቸው የነበሩ ጋዜጣዎች ወንጀል እየተፈፀመባቸው ነው ተብሎ በፍርድ ቤት ¬GdêL! ስለዚህ ግለሰቡ ጋዜጠኛ ስለመሆኑ አናውቀውም፡፡ ህብረተሰቡ ጋር ያለውን ብዥታ ለማጥራትም Uz¤?¾W ጥርት ያለ ነገር መስራት አለበት፡፡ በፃፈው ጽሁፍ ተከሰስኩ ያለም የለም፡፡ እኛም አናውቅም እነዚህ ሰዎች የተያዙት እንደውም በያዙት ተቋም ሽፋን በማድረግ የሽብር ወንጀል ሲፈጽሙ ተብለው ተጠርጥረው ነው" ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ xYwÈM" ሁለት እግር አለኝ ብሎ አንድ ዛፍ ላይ በመውጣት በሠላማዊ መንገድ እሄዳለሁ  የሚል የፖለቲካ ፓርቲ የሚደገፍ መሆኑን XÂMÂlN" ለምንሠራው ልማታዊና ሠላማዊ ዲሞክራሲያዊ ተግባር ማንኛውም አይነት እንቅፋት ሊያደናቅፈን አይችልም፡፡

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ የስራ አስፈፃሚ አባላት በትናንትናው ዕለት በ/ቤታቸው የአውሮፓ ህብረት፣ የጀርመን ኤምባሲና የእንግሊዝ ኤምባሲ ተወካዮች፤ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞችና አባሎቻቸው በተገኙበት በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በተያዙ አባላቶቻቸው ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የስራ አስፈፃሚ አባላቱ የሰጡትን መግለጫ በከፊል አቅርበነዋል፡፡  
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ  
ሽብርተኛም አይደለንም፤ የፀረ ሽብርተኛ አባልም አይደለንም፤ አባሎቻችንም ሽብርተኛ አይደሉም፡፡ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋርም ግንኙነት የላቸውም፡፡ የሰላማዊ ትግል ሃይማኖት ያደረግን ታጋዮች ነን፡፡ የሰላማዊ ትግልን እንደ ሃይማኖቱ የያዘው አባላችን አንዷለም አራጌ የሚጽፋቸው ጽሑፎች፤ ጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ በጥያቄና መልሶች የምታዩት ነው፡፡ በድርጅታችን ባለፈው ሳምንት ያወጣነው መግለጫ፤ በመድረክም በአንድነትም አመጽና የሽብር ተግባር የሚያነሳሳ ሁኔታ አልተፈጠረም፡፡ ይልቅ እኛ እንደዜጐች የፓርቲ አመራር አባላትም የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነፃነቱ እንዲታገል የምንሰራ ነን፤ ይህን አይደበቅም፡፡
ህዝብ መብቱን እንዲያስከብር መታገል አለብን፡፡ ይህንንም እንደግፋለን፤ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡ አንዷለምም ሆነ ሌሎች አባላት ይህንኑ ነው የሚገልፁት፡፡
የኢትዮጵያ ህገመንግስት የሚለው ህዝቡ የስልጣን ባለቤት ነው፤ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤት እስከሆነ ድረስ መብቱን እንዲያስከብር እንጥራለን፡፡ አንዷለምና ሁለቱ የአመራር አባላትም ከዚህ የተለየ ፍላጐት የላቸውም፤ ይሄንን በግልጽ ይናገራሉ፡፡ ድርጅታችን ወጣቶች ወደፊት እንዲመጡ አቅማቸውን አዳብሮ፤ የዛሬም ሆነ የወደፊት አመራር እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡
ከዚህ አኳያ አንዷለምና እነዚሁ ሁለቱ የታሰሩ ሰዎች በተለይ አንዷለም ከምርጫ ክርክር ጊዜ ጀምሮ የሚታወቅ ነው፡፡ ራዕይ ያለው፣ ቆራጥ፣ ወደፊት መሪ ለመሆን ተስፋ ያለው ጠንካራ አባል ነው፡፡  
ባለፉት ወራት የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ከሆነ በኋላ ድርጅታችን ገጽታውን እንዲለውጥ ብዙ አስተዋጽኦ እያደረገ ነበር፡፡ ሌሎችም ሁለቱም እንደዚሁ ይንቀሳቀሳሉ፡፡
በኦሮምኛ ሁለት ወይፈኖች በጋራ ለመንቀሳቀስ አይችሉም የሚባል ተረት አለ፡፡ አንዱ አንዱን ማሸነፍ አለበት እንጂ አይቻቻልም፡፡ ይህ መንግስትና መሪው ሌላ ተቀናቃኝ እንዲወጣ አይፈልግም፡፡ ብርቱካን ላይ የደረሰው ይኼው ነው፤ አሁንም እየደረሰ ያለው ይኸው አይነት ነው፡፡ በሌላ በኩል በህዝቡ ውስጥ ተጽእኖ የሚያሳድር ስራ እየሰራ ጠንካራ ድርጅት እንዲወጣ እንፈልጋለን፡፡ ከዚህ አኳያ ኢህአዴግ ሌላ ተቀናቃኝ ፓርቲ እንዲኖር አይፈልግም፡፡ በአንድ በኩል ኢህአዴግን የሚገዳደር ፓርቲ እንዳይኖር፣ ሁለተኛ ጠንካራ ግለሰቦች ወጥተው መሪያቸውን የሚገዳደር ሰው ለማየት አይፈልጉም፡፡ ከዚህ አኳያ በተለያዩ መንገዶች ስም እየጠለፉ ሰውን ማሰር ስራቸው ነው በእኔ አመለካከት፡፡
የንፁሀን ዜጐች አካል፣ ህይወት የሚያጠፉ ሰዎች፤ የህዝብን ንብረት የሚደመስሱ ሰዎች፤ በእንቅስቃሴያቸው ራሳቸውን በመግደልም ሆነ በተለያዩ ዘዴዎች ህዝብን ለማሸበር የሚሞክሩና የፖለቲካ ጠቀሜታ ለማግኘት የሚሞክሩ ናቸው፡፡ ይህንን እንደምንቃወም በግልጽ አስቀምጠናል፡፡
ኢህአዴግና መንግስት የሚፈልገው ድርጅቱ እንዳይኖር ነው፡፡ እንዲዳከም ነው፤ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን በፍርሃት ወደኋላ ገሸሽ እንዲሉ ነው የሚፈለገው፡፡ ይሄ እንዳይሆን ነው ዋናው ስራችን፡፡ ስራችንን ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡
አንዷለምና የአመራር አባሎቻችን እንዲፈቱ እንቅስቃሴ እናደርጋለን፤ የእነዚህ ሰዎች ጉዳይም ሆነ ሌሎች የታሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶች አባላትና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ እንታገላለን፡፡ በተጨማሪ የአገራችን የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ችግሮች እንዲፈቱ እንታገላለን፡፡ ብሎም ህዝባችን የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት እንዲሆን ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
S‰ አስፈፃሚና ምክር ቤት፣ ግብረ ሃይሎች አቋቁመን እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ ፕሮግራም አለን፤ በፕሮግራማችን የሚያምኑትን ሰዎች በአባልነት እንቀበላለን፡፡ አባል ስንመለምል በህገ ደንባችን መሠረት ነው፡፡ ከዛም በእንቅስቃሴያቸው እንከታተላቸዋለን፡፡ እኔ መብቴን አስከብራለሁ፤ ህዝብ መብቱን ያስከብራል ብሎ የሚነሳን ሰው መንግስት ሽብርተኛ ነው ይለዋል፡፡ ስለዚህ የአተረጓጐም ችግርም አለ፡፡ በፈለጉት መንገድ የመተርጐም ችግር ስላለ የእኛን አባላት በሽብርተኝነት ለመተርጐም ይፈልጋሉ፡፡ እኛ እናውቃለን የእኛን አባላት፡፡
ጥቃትም ይሁን የፖለቲካ መሳሪያ በእኛ አካሄድ ሽብርተኝነት ልክ አይደለም፡፡ ሌሎች ቡድኖች፣ ግለሰቦች አሉ፡፡ ሽብርተኝነትን በፖለቲካ መሳሪያነት የሚጠቀሙ አሉ፡፡ እኛ እንቃወማለን፤ ሰው ከዚህ እንዲጠነቀቅ እንጠይቃለን፡፡
በ2005 ዓ.ም ከ2 መቶ በላይ ንፁሃን ዜጐች በአዲስ አበባ ጐዳናዎች ላይ ተገለዋል፡፡ አሁን በቃለመጠይቁ ከተሳተፍነው መካከል ሶስት አባሎቻችን ለ3 ዓመት በእስር ቤት ቆይተዋል፡፡ ወ/ሪት ብርቱካንን አንዷ ነበረች፡፡
ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው
በ20 ዓመት ውስጥ ኢህአዴግ እራሱን እያየ አይደለም፡፡ ምርጫ 2002 99.6 በሙሉ አሸነፍኩ አለ፡፡ ይህን ህዝብ የሚያውቀው ነው፤ አሸንፏል አላሸነፈም የሚለውን ማየት ይቻላል፡፡ የመፈረጁ ነገር ለራሱ የፖለቲካ ጥቅም የሚያካሂደው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ጠንክሮ እንዲወጣ አይፈለግም፡፡ አንዱ ፓርቲ ገኖ እንዲያድግ ነው የሚደረገው፡፡ አንድነት ፓርቲ እንደተቋቋመ ወጣት ሴት ምሁር 6 ወር ሳይሞላት ነው እስር ቤት የገባችው፡፡
ለምንድነው የምትፈርጁት ተብሎ ኢህአዴግ ሊጠየቅ ይችላል? ሰላማዊ ትግል የምናካሂድ ሰዎች ለምን እንፈረጃለን የሚለው ሁኔታ መታየት አለበት፡፡
ፓርቲዎችን ግልጽ በሆነ ሁኔታ መንግስት አልፈረጀም፡፡ የአንድነት ፓርቲ ህልውና  ሰላማዊ ትግል ነው፡፡
አንዷለም አራጌ ከማንም የበለጠ የሰላማዊ ትግል መርህ ያለው ልጅ  ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል መርህ የሚከራከር፤ የሰላማዊ ትግልን እንደ ሃይማኖት የያዘ ልጅ ነው፡፡ የአንድነት አመራር አባላትም አመራሩም ጭምር ከሰላማዊ ትግል ውጭ ሊንቀሳቀሱ እንደማይችሉ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነን፡፡ የአንድ የሁለት ቀን አመራር አባላት አይደለም ያለን፡፡ ¬¶ክ ያለን አባላቶች ነን ያለነው፡፡ በህገመንግስቱ ተደራጅቶ የሰላማዊ ትግል ማካሄድ አንድነት የሚያምንበት መስመር ነው፡፡ አባላቶችን ግለሰቦች ብሎ መፈረጁ የዲሞክራሲ ሂደቱን ይጐዳዋል እንጂ አይጠቅመውም፡፡ በኢትዮጵያ ላለው የፖለቲካ የፍትህ የዲሞክራሲ ችግር አንድነት የሚያምነው ዋነኛው መንገዱ፣ የመጨረሻውም በሰላም መደራደር፣ መወያየት፣ መግባባትና ይሄንን ህዝብ ከአለበት ችግር ማውጣት ነው፡፡ የአንድነት አባላቶቹን ሲመረምር ሲመርጥ ስነስርዓት አለው፤ በትክክል በሰላማዊ ትግል እምነትና ሃይማኖት ያላቸውን ነው የሚመለምለው፡፡ ስለዚህ የመፈረጁ ሁኔታ በዚያ ነው የሚታየው፡፡  
ሽብርተኝነት አደጋ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አደጋ መሆኑ ቀርቶ የአለማቀፍ አደጋ ነው፡፡ በአፍጋኒስታን በፓኪስታን በሱማሌ የሚካሄደው አለማቀፋዊ ገጽታውን ነው የሚያወሳው፡፡ አንድነት ፓርቲ ሽብርተኝነትን በማንኛውም ሁኔታ ይቃወማል ያዋጋል፡፡ የፓርቲው መርህ ነው ይሄ፡፡ እንደ አንድነት ፓርቲ አመራርና አባላት፣ ተወካይ ሽብርተኝነት ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለአለም ህዝብ አደጋ፤ የጥፋት ሰራዊት ነው፡፡ ይኼን አንድነት ፓርቲ በከፍተኛ ጥንካሬ ነው የሚታገለው፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ቀርቶ በሰው ልጅና በአለም ላይ ሽብርተኝነት አደጋ ነው ብለን እናምናለን፡፡

 

Read 4911 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 11:58