Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 September 2011 10:38

በአዲሱ የውድድር ዘመን

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ደሞዝ አድጓል፤ የተጨዋች 3ሺ የአሰልጣኝ 20ሺ ብር
-ክለቦች በፊፋ ደንብ መገደድ ይጀምራሉ
-የፊርማ ሂሳብ ለአሰልጣኝ እስከ 200ሺ ለተጨዋች እስከ  00ሺ ብር እየታሰበ ነው
-ፌደሬሽኑ የዳታ ቤዝ ማሽን ይገጥማል
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀጣይ የውድድር ዘመን በተጨዋቾች ዝውውር ገበያ በደሞዝ ክፍያ፤ በክለቦች አደረጃጀትና በፌደሬሽን አንዳንድ አሰራሮች ከፍተኛ ለውጦች እየታዩ መሆናቸው ተስተዋለ፡፡ የ

ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቦች ፈቃድ እንዲያወጡ ደንብና መመሪያ እያዘገጀ እንደሆነ ሲታወቅ በክለቦች የፕሮፌሽናል ደረጃ በፊፋ የወጣው ደንብ እንዲከበር እያሳሰበ ነው፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት የፕሪሚያር ሊግ ክለቦች ፊፋ ለአፍሪካ ሀገሮች ያወጣውን መመሪያ እናስፈፅማለን ብለው ቃል ገብተው ነበር፡፡  አንድ ፕሮፌሽናል ክለብ የታዳጊና ወጣቶች ፐሮጀክት መያዝ፤ የሴቶችን ቡድን መያዝ ፤ በአፍሪካ ደረጃ የሚመጥን የልምምድና የመጫወቻ ስታዲየም መገንባትና ለስፖርት ብቻ ተብሎ የተደራጀ ህፈት ቤት እንዲኖረው ፊፋ ሲደነግግ በኢትዮጵያ እግር ኳስ  ግን ተግባራዊነቱ ተጓትቷል፡፡ ፌዴሬሽኑ ክለቦች ቃል በገቡት መሰረት ክለብ ለመባል የሚያበቃቸው ነገር እንዲፈፅሙ ሲያስገድድ ላይሰንስ የሌለው ክለብ ደግሞ ለመወዳደር መብት የለውም በሚል ማስፈራርያ የልኡካን ቡድን አደራጅቶ በየክለቡ ፍተሻ እያደረገ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ በኢትዮጵያ እግር ኳስ  ደሞዝ  እያደገ ነው ፡፡  የአገር ውስጥ አሰልጣኞች ከፍተኛ ደሞዝ 20ሺ ሲደርስ የተጨዋች ከፍተኛ ደሞዝ 3ሺ ብር ማለፉን ሊብሮ በድረገፁ ዘግቦታል፡፡ ኢንሴቲቭ፣ የፊርማና ሽልማት የመሳሰሉት ሲጨመር አንድ ተጨዋች በዓመት ከ 200 እስከ 300ሺ ብር ያገኛል ያለው ዘገባው የዛሬ 20 ዓመት ፊርማ፣ ሽልማት፣ቦነስ ፣ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም ስለሌለ ደሞዝ ብቻ በመሆኑ ተጨዋቹ በዓመት የሚያገኘው ጥቅም ከ1200 ብር አይበልጥም ነበር ሲል አስታውቋል፡፡ የዛሬ 20 ዓመት 150 ብር የነበረው የአሰልጣኝ ደሞዝ ዛሬ 20ሺ መድረሱን የሚያትተው በሊብሮጂኬ.ኮም የቀረበ መረጃ አሰልጣኞች ለፊርማ ከ80-200ሺ ብር እየተቀበሉ መሆኑን አመልክቶ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ደሞዝ የሚያገኙት የደደቢቱ ገብረመድን ሃይሌና የሲዳማው ዳኛቸው አሰፋ መሆናቸውን ገልፆ ሁለቱም የወር ደሞዛቸው 20ሺ ብር መሆኑን አረጋግጧል፡፡ በአጣቃላይ የገነነ መኩርያ ሊብሮጂኬ  የተባለ ድረገ ይፋ ባደረገው የአሰልጣኞች የደሞዝ ደረጃ  በሁለተኛነት የቡናው ውበቱ አባተ፤ የአየር ሀይሉ ክፍሌ ቦልተና ከብሔራዊ ሊግ መድንን የያዘው አስራት ሃይሌ በ15ሺ ብር ወርሃዊ ደሞዝ የሚከተሉ  ሲሆን  ፣ የሀረር ቢራው ጸጋዬ  ኪዳነ ማርያም በ13ሺ ፤ ጥላሁንና አሸናፊ በ12ሺ፤ የሙገሩ ግርማ በ7ሺ ተከታታይ ደረጃ እንደሚይዙ ይፋ አድርጓል፡፡ የውጪ አገር አሰልጣኝ ካላቸው ሁለቱ ክለቦች ለቡልጋሪያዊው የመብራት ሃይል አሰልጣኝ ዮርዳን ስቶችኮቭ ምን ያህል እንደሚታሰብ ያልገለፀው የሊብሮ ድረገ ጊዮርጊስ ይፋ ባያደርግም ውስጥ ለውስጥ ግን ለአዲሱ ሰርቢያዊ አሰልጣኝ እስከ 14 ሺ ዶላር እንደሚከፈላቸው ገምቷል፡፡ የ2003 ዓ.ም የእግር ኳስ ውድድር ዘመን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከተጠቃለለ ከ2 ወር በሃላ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ተከፍቷል፡፡ በፌደሬሽን በይፋ የዝውውር መስኮቱ ሳይከፈት በፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች መካከል የአሰልጣኞችና የተጨዋቾች የዝውውር ገበያ  ለ2 ወር የደራበት ሁኔታም አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች የዝውውር መስኮቱ ከመከፈቱ በፊት እየተካሄዱ ያሉ የዝውውር ሂደቶች በፌዴሬሽኑ ህገደንብ መሠረት የተከናወኑ አለመሆኑን ሊገል ተገድዶ ነበር፡፡ ዘንድሮ በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተጨዋቾች ዝውውር አዳዲስ ለውጦች፤ አወዛጋቢ አጀንዳዎችና የክፍያ ክብረወሰኖች xU_mêL፡፡በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋችን ከክለብ ጋር የሚያገናኙ የእግር ኳስ ደላሎች ህጋዊ ሆነው እየሰሩ አልነበሩም፡፡ በዚህም በተጨዋቾች የዝውውር ገበያው የእግር ኳስ ደላሎችን ጨምሮ ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ተጠቃሚ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ በልምድ፣ ቀድሞ ተጨዋች የነበሩ፣ አንዳንድ ደጋፊዎችና አሰልጣኞች በእግር ኳስ ተጨዋቾች የዝውውር ገበያ ደላላ ሆነው ባልተደራጀ መንገድ እየሰሩ ቆይተዋል፡፡ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ለደላሎች ህጋዊ ፈቃድ ሰጥቶ በገቢው ተጠቃሚ የሚሆንበትን አሰራር ሳያበጅ በርካታ ዓመታት አልፈዋል፡፡ ከ2004 እ.ኤ.አ የውድድር ዘመን አንስቶ ግን ይህን አሰራር በህጋዊነት ለመተግበር እንደወሰነ ታውቋል፡፡ በዘልማድ በነበረው አሳራር ደላሎች ተጨዋችን አግባብተው በየክለቡ ካስቆጠሩ በኋላ ለስራቸው እስክ 2ሺ ብር ክፍያ ይጠይቁ ነበር፡፡ የፊርማ ክፍያ መሰጠት ከተጀመረ በኋላ ይሄው የገቢ ድርሻቸው ከ5በመቶ ጀምሮ በማድረግ ሲደልሉ ቆይተዋል፡፡ ህጋዊ የእግር ኳስ ደላሎች አለመኖራቸውና ፌዴሬሽኑ ይህን ትኩረት በመስጠት የፍቃድ ወረቀት ስላልሰጣቸው አንድም ገቢ ማጣቱን ሲያስከትልበት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ያሉ ተጨዋቾችን ለማዛወር ፈልገው ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡ ሰዎች ጋር በተደራጀ መንገድ መሰራት ለሚፈልጉ ሁሉ እንቅፋት ነበር፡፡ ፌዴሬሽኑ ከቀጣዩ የውድድር ዘመን ጀምሮ የእግር ኳስ ደላሎች ህጋዊ እውቅና ተሰጥቷቸው እንዲሠሩ ህገደንብ አርቅቆ አዘጋጅቷል፡፡ ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ደረጃ ያለው የእግር ኳስ ደላላ እንዲኖር ማድረግን ዋናው ትኩረቱ መሆኑን የሚገልፀው ፌደሬሽኑ በሁለት ዓይነት መንገድ የአገር ውስጥና የውጭ ደላሎች በሚል ፍቃድ ለመስጠትና የሙያ ብቃት ማሻሻያ ስልጠናዎችን ለማከናወን መወሰኑን አስታውቋል፡፡ ከገነነ መኩሪያ ድረገጽ ሊብሮጄኬ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በደራው የኢትዮጵያ እግር ኳስ የተጨዋቾች የዝውውር ገበያ ለፊርማ ከ100ሺ ብር እስከ 400ሺ ብር ክለቦች እየከፈሉ ናቸው፡፡በሌላ በኩል ፌዴሬሽኑ በአዲስ መመርያ ተጨዋቾች ላይሰንስ እንዲያወጡ ሊያስገድዳቸው እንደሆነም ይገለፃል፡፡ በአዲሱ አሰራር ተጨዋቹ ተጨዋች ነው ለመባል የሚያረጋግጥ መረጃ አቅርቦ ይህ ሲሟላ ላይሰንስ ይሰጠውና በፊዴሬሽኑ የታወቀ ህጋዊ አባል ይሆናል እየተባለ ነው፡፡ ተጨዋቹ ላይሰንስ ለማውጣት የተወለደበት ቀን የጤና ምርመራ የቀድሞ ክለብ በፊርማ ያገኛቸውን ገንዘቦች ሰፈሩ የሰፈር ጓደኞቹ የሚውልበት ቦታ የሚወዳቸው የምግብ ዓይነቶች ከ100 በለይ የሚሆኑ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥባቸውን ፎርም ይሞላል፡፡ እነዚህ መረጃዎች በሌላ ወገን ይጣራሉ፡፡ ተጫዋቹ በፎርም ላይ የሞላቸውን መጠይቆች ናርሰር በሚባል ማሽን ይቀመጣሉ፡፡ ማሽኑ በቅርቡ ከቱኒዚያ ይመጣል-ብሏል የሊብሮጂኬ ድረገ፡፡

 

Read 4012 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:45

Latest from