Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 10:11

ኖህልብወለድ ገፀ -ባህሪ ወይስ የገሃዱ ዓለም ሰው?

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ባለፈው ሰሞኑን በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የኖህ ዘመን ታሪክን በተመለከተ የሚወጡ መጣጥፎችን ስመለከት
እኔም በዚህ ሃሳብ ዙሪያ የምለው     ነገር ካለ ብዬ ማውጠንጠን ጀመርኩ፡፡ በተለይ የኖህ መርከብማረፊያዋ በአገራችን መሆኑን የሚገል የታሪክ መሐፍ መታተሙን ስሰማ፣ ነገሩ ግርም አለኝና ..ለመሆኑ የታሪኩ እውነታነት ባልተረጋገጠ ትረካ ላይ የባለቤነት ጥያቄ ማንሳቱ ፋይዳው ምንድን ነው?.. ብዬ አሰብኩ፡፡

ተረት የታሪክን ያህል ልቦናን በሚመስጥበት አገር እንዲህ ዓይነት መሐፍት ለደራሲያኑ  የገቢ መስክ ስለሚፈጥሩ ተመሳሳይ መሐፍት ወደፊትም እንደሚወጡ እንጠብቃለን፡፡
የዚህ ሑፌ አላማ መሐፉን ለመተቸት ሳይሆን (እውነቱን ለመናገር ባስብ እንኳን እውቀቱ የለኝም) ለመሐፉ መነሻ የሆነውን የኖህ ዘመን ትረካ እውነታነት በተመለከተ ከተለያዩ ወገኖች ከቀረቡት እጅግ በጣም ብዙ ጥያቄዎች ውስጥ በጣም ጥቂቱን አንስቶ ለመወያየት ነው፡፡
በዘፍጥረት ውስጥ የተተረከውን የኖህ ዘመን የጥፋት ውሃ የሚያነቡ ብዙ አማኞች ትረካውን እንደ እውነተኛ የታሪክ ዘገባ እንደሚቆጥሩት ይታወቃል፡፡ ይህ ትረካ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ መቶ በመቶ በተዓምራት የተሞላ ካልሆነ በቀር በገሃዱ ዓለም የተከናወነ ነው ብሎ ለማሰብ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች እንዳሉት የሚጠረጥሩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ መጠነኛ የጂኦሎጂ፣ የባዮሎጂ፣ የሃይድሮሎጂ፣ የቴክኖሎጂ የጥንቱ ዘመን ታሪክ እውቀት ያለው ሰው ይህን ትረካ እውነት ብሎ ለመቀበል ከፍተኛ የእምነት ናትና የነባራዊውን ዓለም ህግጋት መካድን ይጠይቃል፡፡ ላይ ላዩን ሲያገቡት ቀላልና ተራ የሚመስሉ በትረካው ውስጥ የተካተቱ ብዙ ድርጊቶች ጠለቅ ብለው ሲያዩአቸው በእውነት የተከናወኑ መሆናቸውን መቀበል ያዳግታል፡፡
ከዛሬ ሁለት መቶ ዓመት በፊት እንደ ባዮሎጂና ጂኦሎጂ ዓይነት የጥናት ዘርፎች ገና ዳዴ በሚሉበት ዘመን የኖህ ዓይነት ትረካዎች እንደ እውነት ቢቆጠሩ የሚያስገርም ነገር አይኖረው ይሆናል፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን በነዚህ የጥናት ዘርፎች በተደረሰበት የእውቀት መጠን የኖህ ትረካ ሲለካ ቀደምት ህዝቦች ከሚፏቸው ትረካዎች እንደ አንዱ አድርጐ ከመውሰድ ሌላ በእውነት የተከናወነ አድርጐ ማሰብ ከየዋህነት ያስቆጥራል፡፡
ብዙ የመሐፍ ቅዱስ እና የጥንቱ የመካከለኛው ምስራቅ ጥናት ጠበብት እንደ¸gL{ùT\ የኖህ ትረካ አፈ ታሪክ (myth) ሲሆን ምንጩም ከሜሶፖታሚያውያን የጐርፍ ትረካ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ከነዚህ ትረካዎች አንዱ የጊልጋሜሽ ትረካ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በዚሁ ጋዜጣ ላይ ብዙ የተባለ ነገር ስላለ ላለመደጋገም ብዙ ለማለት አልፈቀድኩም፡፡ ሌላው የኖህ ታሪክ መነሻ ሊሆን ይችላል፡፡ ተብሎ የሚገመተው የጥንት ግብፃውያን |Legend of the destruction of Mankind´ የተባለው ትረካ ነው፡፡ በዚህ ትረካ መሰረት ራ (Ra) የተባለው የግብፃውያን አምላክ በሰዎች ጥፋትና ድፍረት በመናደዱ ሀቶር የተባለች ሌላ አምላክ (godess) ልኮ ዓለምን በሙሉ ለማጥፋት ይወስናል፡፡ ሀቶር የሰው ልጆችን በመፍጀት ላይ ሳለች ራ መልሶ ስለራራ ሀቶርን x?bRBé ከጥፋቷ ያስቆማታል፡፡ የኖህንም ሆነ ሌሎቹን ታሪኮች የሚያስተሳስራቸው አንድ ነገር ሁሉም የሰው ልጆችን አጥፊነትና የአምላክን መሃሪነት ለመግለ የተፈጠሩ ስነ-መለኮታዊ ይዘት ያላቸው ትረካዎች መሆናቸው ነው፡፡
እስቲ ለጭውውት ይመቸን ዘንድ የኖህን ትረካ በትክክል የተከናወነ ታሪክ እንደሆነ አድርገን እንቁጠር፡፡ ከዚያም ከታሪኩ ውስጥ አንዳንድ ሃሳቦችን እያነሳን ምን ያህል እውነታነት ሊኖራቸው እንደሚችል እንመርምር፡፡
ቴክኖሎጂና የሎጂስቲክስ ችግር
በመጀመሪያ ደረጃ ፍጥረትን ሁሉ በውሃ ሙላት መፍጀት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ በጥፋት ውሃው ከወደሙት ውስጥ አብዛኞቹ ህፃናት ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የአማኞች መልስ በአብዛኛው ..ፈጣሪ የሚበጀውን ያውቃል፡፡ ሸክላ ሰሪው ሸክላውን እንዳሻ ቢያደርገው ማን ከልካይ አለበት፡፡.. ዓይነት ነው፡፡ (Might is right እንደሚባለው) የ ethics ጥያቄውን ትተን ወደ ክንውኑ ስናልፍ አንዱ የኖህ ችግር ሊሆን የሚችለው መርከቧን መገንባቱ ላይ ነው፡፡ መርከቧ የተገነባችው ከእንጨት እንደሆነ ተገልል፡፡ መርከብ መስራት እንጨትን በአንድ ሰብስቦ ከማሰር ባሻገር ?ነቶችን ሁሉ ተሸክሞ ከፍተኛ የማዕበል ጫናን እንዲቋቋም ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ኖህ የገጠመውን ዓይነት ክስተት ለመቋቋም ከእንጨት የተሰራ መርከብ x¥‰? እንደማይሆን የመርከብ ስራ ጥበብ በግል ያሳያል (የተጠራጠረ መረጃ አገላብጦ ያጣራ)፡፡ በአሁኑ ዘመን በጣም ትልቅ ሊባል የሚችለው ከእንጨት የተሰራ መርከብ ርዝመቱ ወደ 300 ጫማ ይጠጋል፡፡ በዚያ ላይ እነዚህ መርከቦች በብረት ቀበቶ (Straps) መጠናከር ሲኖርባቸው ውሃ ስለሚያስገቡ ያለማቋረጥ ውሃውን ማስወገድ (Pump ማድረግ) ያስፈልጋል፡፡ የኖህ መርከብን ብንመለከት በአሁኑ ዘመን አለካክ ርዝመቷ 450 ጫማ፣ ጥልቀቷ 45 ጫማ እና ጐኗ 70 ፊት እንደሆነ ተጠቅሷል (ዘፍጥረት 6፡15)፡፡ በዚህ ሁኔታ የመርከቧ መጠን በአሁኑ ዘመን በከፍተኛ ቴክኖሎጂ ከሚሰሩት የነዳጅ ጫኝ መርከብ (Oil tanker) ግማሽ ይሆናል፡፡ በመርከብ ስራው ላይ ከኖህ ቤተሰቦች በቀር የተሳተፈ ስለመኖሩ የተገለፀ ነገር የለም፡፡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ያሉት ስምንት አባላትን ያቀፈ ቤተሰብ መርከቧን ለመስራት ምን ያህል አስቸጋሪ ሁኔታ እንደሚገጥመው መገመት አዳጋች አይሆንም፡፡ በዚያ ላይ ዘመኑ ገና ብረት ስራ ላይ ያልዋለበት የነሃስ ዘመን መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ በመሆኑም ጠቅላላው ቤተሰብ ሌላውን ነገር እርግፍ አድርጐ ትቶ ሌት ተቀን በመርከብ ስራው ላይ ቢሰማራ እንኳን መርከቧን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚፈጀውን ጊዜ መገመት ያግዳግታል፡፡ ኖህና ቤተሰቦቹ ብዙ ዘመን ስለኖሩ የጊዜ ችግር አይገጥማቸውም ብለን ብናስብ እንኳን አንዱን ክፍል ሰርተው ወደ ሌላኛው ሲሻገሩ ከጊዜ ብዛት የቀደመው ሊበሰብስ ይችላል፡፡ በአጠቃላይ የመርከብ ስራው ፕሮጀክት የማያስኬድ (non-feasible) እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡
እንስሳትን ማሰባሰብና መጠበቅ
በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ የሚገኙ እንስሳት በሙሉ ከኖህ ጋር የተረፉ እንስሳት ቀጣይ ትውልዶች እንደሆኑ ከታሪኩ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ታሪኩ እውነት ከሆነ ኖህ እነዚህን ሁሉ የእንስሳት ዝርያ ከየመኖሪያ አካባቢያቸው ዞሮ መሰብሰብ ሊኖርበት ነው፡፡ (አለበለዚያ የተለመደውን የተዓምር ስራ ልንጠራ ነው)
የዋልታ ድቦችን ከሰሜን ዋልታ፣ ፔንግዊንስ ከአንታርክቲካ፣ የማርሱፒያል ዝርያዎችን ከአውስትራሊያ ማሰባሰብ አለበት፡፡ ሌሎችም እንዲሁ ከተወሰነ የዓለም ክፍል ውጭ ሊኖሩ የማይችሉ የእንስሳት ዝርያዎች አሉ፡፡ በዘመኑ የመጓጓዣ ዘዴ ውቅያኖስ ተሻግሮ ደን አቆራርጦ እንስሳቶችን ማሰባሰብ ምን ያህል ሊከብድ እንደሚችል አስቡት፡፡ እርስ በርስ የሚበላሉ እንስሳትን ለመከላከል እያንዳንዱ የራሱ ማስቀመጫ (Cage) ያስፈልገዋል፡፡ ከእንስሳቶች ዝርያ ብዛት አንፃር ሳይተፋፈጉ ከዓመት በላይ በመርከቧ ውስጥ ማቆየት የማይታሰብ ነው፡፡ በዚያ ላይ ለኖህ ቤተሰብና ለእንስሳቶቹ ሁሉ የሚመገቡት ምግብ ያስፈልጋል፡፡ የማገዶ እንጨትም ሳያስፈልጋቸው አይቀርም፡፡
ከአንድ ሚሊዮን በላይ የእንስሳት ዝርያዎችን (ያውም ጥንድ ጥንድ ሆነው፤ አንዳንዶቹ እንዲያውም ሰባት ሰባት ጥንዶች ናቸው) እለት ተእለት መመገቡና ቆሻሻን ማስወገዱ በስምንት ሰዎች ጨርሶ የሚቻል አይሆንም፡፡ በዚያ ላይ የእንስሳቶቹ ምግብ ሊበሰብስ ይችላል፡፡ ነገሩን የባሰ አስከፊ የሚያደርገው አንዳንድ ጥገኛ ተዋህስያን ከሚመርጧቸው እንስሳት ሰውነት W? መኖር አይችሉም (Host Specific Parasite)””
እነዚህ ተዋህስያን ከጥፋት ውሃው በኋላ መኖራቸው የሚያመለክተው በመርከቧ ላይ በተረፉት እንስሳት ውስጥ እንደነበሩ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ሰዎቹን ጨምሮ እያንዳንዱ እንስሳ በየዝርያው ውስጥ ብቻ የሚኖሩትን የተዋህስያን ዓይነት ተሸክሞ ነበር፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ መርከቧ የጫነችው የተስፋ ትውልድን ሳይሆን ለመዓት የተጠሩ የበሽተኞች ስብስብ ነው፡፡ ይህ ሁሉ በሽታና በሽተኛ በተሰበሰበበት ሁኔታ የመርከቧ ተሳፋሪዎች በወረርሽኝ አለማለቃቸው የሚገርም ነው፡፡ መቼስ የፈተናውን ብዛት ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም፡፡ ይህን እዚህ ላይ ገታ አድርገን ከሌላ አቅጣጫ ሌላ ጥያቄ እናንሳ፡፡
መሬትን ለመሸፈን የሚበቃ ውሃ ከየት መጣ? የስነ-ምድር ጥናት እንደሚያመለክተው፤ አብዛኛው የመሬት ገታ የተገነባው በብዙ ሚሊዮን ዓመታት በሚገመት ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የተፈጥሮ ክስተቶች ነው፡፡ አህጉራችን የተሸከመው የመሬት የላይኛው ክፍል እንቅስቃሴ (Plate tectonics)# የመሬት ቅርፊት (Crust) መታጠፍና መሰንጠቅ፣ እሳተ ገሞራ፣ የመሬት መሸርሸርና የደለል መከማቸት ጥቂቶቹ የመሬትን ገታ የሚቀይሩ የተፈጥሮ ክስተቶች ናቸው፡፡ ተራሮች መፈጠር የጀመሩት ከዛሬ 1.2 እስከ 2 ቢሊዮን ዓመታት መካከል እንደሆነ በስነምድር ጥናት ይገመታል፡፡ ለምሳሌ የሂማልያ ተራሮች መፈጠር የጀመሩት ከዛሬ 28 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ነው፡፡ የምድርን ገታ የሚቀይሩ የተፈጥሮ ክስተቶችና ሃይሎች አሁንም በስራ ላይ ናቸው፡፡ በቅርቡ በጃፓን ላይ የደረሰው የሱናሚ አደጋ መነሻ የምድር ቅርፊት (tectonic Plates) እንቅስቃሴ ውጤት ነው፡፡ አገራችንን አቋርጦ የሚያልፈው ታላቁ ስምጥ ሸለቆ መነሻው የመሬት ገ መሰንጠቅ (Faulting) እንደሆነ ይገለፃል፡፡
ከአራት ሺህ ዓመታት በፊትና በአሁኑ ጊዜ ባለው የመሬት ገታ መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታሰብ ከፍተኛ የመልክዓምድር ልዩነት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ መጠነኛ አካባቢያዊ ለውጦች (Local Changes) ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ከአራት ሺህ ዓመታት በፊት የነበረውን የመሬት ገታ ከሞላ ጐደል ከአሁኑ ዘመን ጋር ማመሳሰል ይቻላል፡፡ በዘፍጥረት ትረካ ምዕራፎች ላይ የጥፋት ውሃው ሙላት ከዓለም ታላላቅ ተራሮች በላይ እስከ 22 ጫማ ከፍታ እንደነበረው ተጠቅሷል፡፡ በዚህ መሰረት ውሃው አሁን ካለበት የባህል ወለል በላይ እስከ 8.9 ኪ.ሜ ይደርሳል ማለት ነው፡፡ ይህ ሁሉ የውሃ ክምር በእያንዳንዱ ስኩየር ኢንች የመሬት ገ ላይ እስከ 800 ቶን የሚሆን ግፊት ወይም የውሃ ጫና ይፈጥራል፡፡ ይህን ሁሉ ጫና ተቋቁሞ ብርሃን በሌለበትና ጨዋማ በሆነ ውሃ ውስጥ የምድር እዋት ለአስር ወራት ቆይተው ዳግም ነፍስ ይዘራሉ ብሎ መገመት ጨርሶ ከስነ-ህይወት ጥናት (Biology) ጋር አለመተዋወቅ ነው፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ የመርከቧ ተሳፋሪዎች እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? እዋት በሌለበት ሁኔታ አጠቃላይ የህይወት መስተጋብር (ecosystem) መናጋት መከሰቱ አይቀርም፡፡ ከመጥለቅለቁ በኋላ ደረቁ መሬት ጨዋማ ይዘት ስለሚኖረው bx?R ጊዜ ለእዋት ህይወት ምቹ ይሆናል ማለት አይቻልም፡፡
እንደ አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ውጤት መሰረት 97.2% የሚሆነው የምድራችን ውሃ የሚገኘው በውቅያኖሶች ውስጥ ነው፡፡ የቀረው በሃይቆችና፣ በወንዞች፣ በግላሲየርስ፣ በዋልታዎች አካባቢ በበረዶ መልክ፣ በከርሰምድርና በትነት መልክ በአየር ውስጥ ይገኛል፡፡ የምድርን ገ ሙሉ ለሙሉ ለመሸፈን ቢያንስ አሁን በምድር ላይ ያለውን ውሃ 3.5 እጥፍ ተጨማሪ የውሃ መጠን ያስፈልጋል፡፡ በአየር ውስጥ ያለው የትነት መጠን በጠቅላላ ዝናብ ሆኖ ቢዘንብና በዋልታዎች ላይ የተከማቸው በረዶ በጠቅላላ ቢቀልጥ የውሃው ከፍታ ከ200 ጫማ በላይ ሊጨምር እንደማይችል ይገመታል፡፡ ውሃው ከየትም ይምጣ ብንል እንኳን መሬትን ለማጥለቅለቅ የሚበቃ የዝናብ ትነት መጠን የሚፈረው፡፡ የአየር ግፊት የኦክስጂንን እና የናይትሮጂንን Density ወደ መርዛማነት ደረጃ (toxic level) ከፍ ማድረጉ አይቀርም፡፡ በዚያ ላይ ያ ሁሉ የትነት መጠን ሊፈጥረው የሚችለው የብርሃን ግርዶሽ ከጥፋት ውሃው በፊት መሬትን በከፍተኛ መጠን እንድትቀዘቅዝ ሊያደርጋት ይችላል፡፡
ከጥፋት ውሃው በኋላ ያ ሁሉ ውሃ የት ገባ? መቼስ ከአንድ ዓመት በኋላ በቅበት ተነነ ማለት አይቻልም፡፡ አንዳንድ ክርስቲያን ፀሐፍት፤ የመሬትና የውቅያኖስ አጠቃላይ ገታ በፍጥነት ተቀያይሮ ውቅያኖሶች ከጥፋት ውሃ በፊት ከነበራቸው ጥልቀት የበለጠ ጥልቅ፣ ተራሮች ደግሞ የበለጠ ከፍ እንዳሉ ያምናሉ፡፡ ሚሊዮን ዓመታት የሚፈጅን የተፈጥሮ ክስተት በአንድ ዓመት ውስጥ እንደተፈፀመ ማሰብ አስቸጋሪ ውጤቶችን ያስከትላል፡፡ ይህ በአንድ ዓመት ሊከናወን ይችላል ተብሎ የሚታመን የመሬት ገ ለውጥ፣ ከሚያመነጨው ሃይል (energy) አንፃር ጠቅላላ ምድርን ሊያግላት እንደሚችል ማስላት ይቻላል፡፡ በዚያ ላይ መጠነኛ የመሬት ቅርፊት መንሸራተት የሚፈጥረውን ሱናሚ ውጤት በቅርብ ጊዜ በጃፓን አይተናል፡፡ በዚህ ምክንያት የተነሳ ማዕበል ከፍታው እስከ አስር ሜትር እንደሚደርስ ተዘግቧል፡፡
ይህንኑ ክስተት በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ብናደርገው የኖህ መርከብ ሊገጥማት የሚችለው አበሳም በዚያው መጠን ሊጨምር እንደሚችል ማሰብ አያዳግትም፡፡ ምንም አጋጅ (Continental Speed brake) በሌለበት ሁኔታ የሚነሳው ማዕበል መርከቢቷን በቅበት ሊበታትናት ይችላል፡፡ የማዕበሉ ወዲያና ወዲህ እንደ ሮኬት የሚወናጨፉ የዛፍ ንቃዮች ወይም ሌሎች ግዑዝ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ብልህነት ነው፡፡ በእውነት ኖህ ከእንዲህ ዓይነት ማዕበል መትረፍ ይችላል? በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ኖህን ከመሆን አወጣን ከማለት በስተቀር ምን ማለት ይቻላል?
የጥፋት ውሃና የዓለም ህዝቦች ታሪክ
እንደ ጀምስ አሸር የመሐፍ ቅዱስ የዘመን ቀመር መሰረት፤ የጥፋት ውሃ የተከሰተው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2348 ዓ.ዓ ገደማ ነው፡፡ ዘመኑም በዓለም ታሪክ የነሃስ ዘመን ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህ የታሪክ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ3000 ዓ.ዓ እስከ 200 ዓ.ዓ ድረስ የዘለቀ ነው፡፡ ይህ የስልጣኔ እንቅስቃሴ በማንኛውም መንገድ ተቋርጦ እንደነበር የሚጠቁም ከመሐፍ ቅዱስ ውጪ (extra biblical)  መረጃ የለም፡፡ በተቃራኒው ከመሐፍ ቅዱስ ውጪ ያሉ የመረጃ ሑፎችና የአርኪኦሎጂ ቅሪቶች የሚጠቁሙት የተጀመረው የነሃስ ዘመን ስልጣኔ ሳይቋረጥ መቀጠሉን ነው፡፡ በቁፋሮ የተገኙ ከተሞች፣ መገልገያ መሳሪያዎች፣ የሸክላ ስራዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ቅሪተ ዓሞችና የተለያዩ ቁሳቁሶች ጠቋሚ መረጃዎች ናቸው፡፡ ምድር በውሃ ጠፍታ ቢሆን ኖሮ ተመሳሳይ የህዝቦች ስልጣኔ ሳይዛነፍ በተመሳሳይ ህዝቦችና በተመሳሳይ ቦታ መልሶ ያቆጠቁጣል ብሎ መገመት አዳጋች ነው፡፡
በዓለም ላይ የረጅም ዘመን ቀጣይ ስልጣኔ ካስመዘገቡት ውስጥ ሜሶፖታሚያ፣ ግብ፣ ቻይና፣ ሚኖአን፣ የኢንዱ ሸለቆ እና ፊኖሺያን ይጠቀሳሉ፡፡ የሑፍ ታሪክ ከነበራቸው ቀደምት ስልጣኔዎች ውስጥ በሜሶፖታሚያ የነበረው የሱሜሪያን ስልጣኔ አንዱ ነበር፡፡ በሱሜሪያን የነገስታት ዝርዝር መሰረት የመጀመሪያው ስርወ-መንግስት የጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3350 ዓ.ዓ ገደማ ነው፡፡ በፕሮፌሰር ዋደል በተደረገ ጥልቅ ጥናት መሰረት፤ የሱሜሪያ ስልጣኔ ከተጠቀሰው ዘመን ጀምሮ እስከ ጥፋት ውሃ ዘመንና ከዚያም በኋላ ሳያቋርጥ ዘልቋል፡፡ በአብርሃም ዘመንም እንኳን ቢሆን (ከክ.ል.በፊት 1930 ዓ.ዓ አካባቢ) ስልጣኔው ተስፋፍቶ አካባቢው ከፍተኛ የባህል ማዕከል እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡
ከጥንት ስልጣኔዎች ውስጥ በይበልጥ የሚታወቀው የግብፁ ስልጣኔ ነው፡፡ የግብ ስልጣኔ የሚጀምረው ሜኒስ በተባለ ንጉስ በ3100 ዓ.ዓ በተመሰረተ ስርወ-መንግስት ነው፡፡ በግብ ታሪክ ውስጥ የአሮጌው ግዛት ዘመን (The old kingdom) ከ2800 ዓ.ዓ እስከ 2175 ዓ.ዓ ዘልቋል፡፡
በዚሁ የግዛት ዘመን የተገነቡት ባለደረጃ ፒራሚድ፣ ትልቁ ፒራሚድና ስፊኒክስ እንከን ሳያጋጥማቸው መዝለቃቸው የዓለም አቀፉን የውሃ መጥለቅለቅ ታሪክ ተዓማኒነት በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
የቻይናም ታሪክ ከላይ ካየናቸው ታሪኮች የተለየ አይደለም፤ ከሞላ ጐደል አስተማማኝ ሊባል የሚችል የቻይና ታሪክ የሚጀምረው በ3000 ዓ.ዓ አካባቢ ነው፡፡ ሹ ኪንግ የተባለው የቻይናውያን ቅዱስ መሐፍ ስለ ጥንት የቻይናውያን ባህል ብዙ መረጃዎች እንደያዘ ይታሰባል፡፡ እንደ መሐፉ ትረካና ደጋፊ የአርኪኦሎጂ ግኝት መሰረት፤ ከ2400 ዓ.ዓ እስከ 2200 ዓ.ዓ ባለው ዘመን ቻይና የተረጋጋችና በያኦ ስርወ-መንግስት የምትተዳደር ነበረች፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ስልጣኔውን ሊያስተጓጉል የሚችል ክስተት ስለመኖሩ የተዘገበ አንዳችም መረጃ የለም፡፡
እንዲህ እንዲህ እያልን ሌሎችንም ስልጣኔዎች መዘርዘር እንችላለን፡፡ ዋናው ቁም ነገር በነዚህ ሁሉ የህዝቦች ታሪክ ውስጥ ስልጣኔውን ያስተጓጐለ ዓለም አቀፍ የውሃ መጥለቅለቅ ስለማጋጠሙ መረጃ አለመገኘቱ ነው፡፡ ምናልባትም እውነታነት ቢኖረው እንኳን አንዳንዶች እንደሚያስቡት መጥለቅለቁ በአለም አቀፍ ደረጃ ሳይሆን አካባቢያዊ (Local flood) ሊሆን ይችላል፡፡ አልያም ተደጋግሞ እንደሚጠቀሰው ትረካው ከአጐራባች ህዝቦች የተወረሰ ሊሆን ይችላል፡፡

 

Read 3309 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:16