በሚል የአልበም መጠርያ ዘንድሮ ለገበያ ያበቃውና 9 ምርጥ የሪሚክስ ዘፈኖች ያሉበት ስራው ተወዳጅ ሆኖለታል፡፡ ባለፈው ሳምንት በኦፊሴላዊ ድረገፁ በነፃ የተለቀቀው ..ዘ ዊከንድ.. የ9 ሪሚክስ ሙዚቃዎች አልበም በሁለት ቀናት ጊዜ ውስጥ በ180 ሰዎች ተገልብጧል፡፡..ሃይ ፎር ዚስ.. የተሰኘው የአቤል ዜማ ኢንትሩጅ የተባለ ፕሮግራም የመግቢያ ሙዚቃ ነው፡፡ ታዋቂ ከሆኑት የሰሜን አሜሪካ የአርኤንድቢ አርቲስቶች ድሬክ፤ ዶክ ማክኒና ኢላአንጀሎ ጋር በመስራት ላይ የሚገኘው አቤል፤ ከወር በፊት በቶሮንቶ ለመጀመርያ ጊዜ ሁለት ኮንሰርቶችን አቅርቧል፡፡ ከፍተኛ እገዛ እያደረገለት ያለው የአርኤንድቢ አቀንቃኙ ድሬክ አቤል ተስፋዬ ስኬታማ አቀንቃኝ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ ብሏል፡፡