Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 09:42

አስቴር ፊልም ከአጫጭር ልቦለዶች ፊልም ሊሰራ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አስቴር ፊልም ፕሮዳክሽን አጫጭር የአማርኛ ልቦለድ ድርሰቶችን ወደ ፊልም ሊቀይር መሆኑን አስታወቀ፡፡ የፕሮዳክሽኑ ሥራ አስኪያጅ አርቲስት ይገረም ደጀኔ ..የትሮይ ፈረስ.. በአጭር ልቦለድ ላይ ተመሥርቶ የተሰራ ፊልም ሲመረቅ ሌሎች መሰል ፊልሞች ለመሥራት እየተንቀሳቀስን ነው፣ የሦስቱ ቀረፃ በመጪው ወር ይጀመራል ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የዳንኤል ወርቁ ..አቤት ዛሬ..፣ የሙልጌታ ጉደታ ..የሱራፌል እጣ.. እና የእንዳለጌታ ከበደ ..የእናትየው አይኖች.. አጫጭር ልቦለዶችን ወደ ፊልም ለመለወጥ ዝግጅት መደረጉን አርቲስት ይገረም ተናግሯል፡፡
ፕሮዳክሽኑ ሌሎች የአጫጭር ልቦለድ ፀሐፍትን ለተመሳሳይ ሥራ እያነጋገረ ነው፡፡

..አቻዬ.. እና ..ወንድ ከሆንክ.. ፊልሞች ለሕዝብ ቀረቡ
ቶፊቅ ሁሴን ስክሪን ፕለዩን ፎ ያዘጋጀውና ኤርምያስ ጌታሁን የፃፈው ..አቻዬ.. የ85 ደቂቃ የፍቅር ኮሜዲ ፊልም ከነገ ጀምሮ ለሕዝብ ሊቀርብ ነው፡፡ ከቀረፃ እስከ አርትኦት ስድስት ወራት የፈጀው ፊልም መስከረም 13 ቀን 2004 ዓመተ ምህረት በዋነኛነት በአዲስ አበባ ማዘጋጀ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በ..አቻዬ.. እነ ኤልሳቤጥ ጌታቸው (ቀጮ)፣ ሂሩት ኪሮስ፣ ኤርምያስ ጌታሁን፣ ልዑልሰገድ ካሳ፣ ፍቅሩ አብጤና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ እየወጡ ካሉት በርካታ ፊልሞች አንፃር ገበያ አያሰጋችሁም ወይ ተብሎ ከአዲስ አድማስ ጥያቄ የቀረበለት አዘጋጅ ቶፊቅ ሁሴን ..ጥሩ ከሰራህ ውድድሩ አያሰጋም.. ብሏል፡፡ ቶፊቅ ካሁን ቀደም የኢኒሽየቲቭ አፍሪካ የኢትዮጵያ ምርጥ ዶክመንታሪ ፊልም ብሎ በሸለመው ..ሻማዋ.. ፊልም እና ..ጋሬጣ.. በተባለው የአምስት ደቂቃ ፊልሙ ይበልጥ ይታወቃል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ አርቲስት ግሩም ኤርምያስ ያዘጋጀው ..ወንድ ከሆንክ.. ልብ አንጠልጣይ የቤተሰብ ፊልም ከነገወዲያ ምሽት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ይመረቃል፡፡ እንዳልካቸው ለበታ በፃፈው ፊልም ራሱ እንዳልካቸው፣ አዜብ ወንድወሠን፣ ትንቢት ገብረኪዳን፣ ወንድወሠን አለማየሁና ሌሎችም ተሣትፈዋል፡፡ የአንድ መቶ አምስት ደቂቃ ፊልሙ ተሠርቶ እስኪያልቅ አስራ ስምንት ወራት ፈጅቷል፡፡

 

Read 4060 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 09:45