Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 December 2012 10:01

የአውሮፓ ፓርላማ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከእስር እንዲፈታ ጠየቀ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

አራት የተፈረደባቸው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ተሸለሙ
ከሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶበት የ18 ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከእስር እንዲፈታ የአውሮፓ ፓርላማ ጠየቀ፡፡ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ለጠ/ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ በፃፉት ግልፅ ደብዳቤ፤ ጋዜጠኛው በአፋጣኝ ከወህኒ ቤት እንዲለቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል።በሌላ በኩል አራት በፍ/ቤት እስር የተፈረደባቸው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ዝነኛውን የ2012 የሄልማን/ሃሜት ሽልማት ተሸለሙ፡፡ ተሸላሚዎቹ በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣ ርዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እንዲሁም በሌለበት የተፈረደበት የቀድሞው የ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ሲሆኑ ጋዜጠኞቹ ሽልማቱን ያገኙት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስጠበቅ ላደረጉት ጥረት ነው ተብሏል፡፡ 

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አንዷለም አራጌን ጨምሮ የ24 ተከሳሾችን ጉዳይ በቅርበት ሲከታተሉ መቆየታቸውን የጠቀሱት የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት፤ በተከሳሾቹ ላይ የተሰጠው ብያኔ ከሰብዓዊ መብት መርህ ጋር የሚጣጣም አይደለም ብለዋል፡፡ 
የፓርላማ አባላቱ በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሚመራው መንግስት ጋር ግንኙነት በሚፈጥሩበት ሁኔታ ላይ ተከፋፍለው የነበረ ቢሆንም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስን ለማስወገድ የአገሪቱ አፋኝ ህግ መከለስ አለበት በሚለው ላይ ለመስማማት ችለዋል ተብሏል፡፡
በ24ቱ የሽብርተኝነት ተከሳሾች ላይ ስለተሰጠው የፍርድ ብያኔ አስከፊነት የተናገሩት በአውሮፓ ህብረት ምክትል ፕሬዚዳንትና የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ካትሪን አሽተን፤ ለህጋዊ የፍርድ ሂደቱ እውቅና በመስጠትና እያንዳንዱ ሀገር ዜጐቹን ከሽብርተኝነት ለመከላከል ያለውን ሉአላዊ መብት በመገንዘብ፣ የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት በሰጡት መግለጫ “በፀረ - ሽብርተኝነት ህጉ ውስጥ የሽብርተኝነት ወንጀሎችን በተመለከተ የተቀመጠው ድንጋጌ ግልጽነት ስለሚጐድለው በኢትዮጵያ ህገመንግስት የተከበሩትን ሃሳብን የመግለጽና የመደራጀት መብትን ይጐዳል” ብለው እንደሚሰጉ ተናግረዋል፡፡

Read 4311 times