Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 22 December 2012 09:59

“ምርጫ ቦርድ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የማይጨነቅ ተቋም ነው” - ተቃዋሚዎች “አንድም በማስረጃ የተደገፈ ቅሬታ የላቸውም” - ምርጫ ቦርድ

Written by 
Rate this item
(4 votes)

ከምርጫው በፊት ውይይት እንፈልጋለን በሚል በአንድ ላይ የተሰባሰቡ 33 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ምላሽ ተቃወሙ፡፡ ፓርቲዎቹ ከትላንት በስቲያ በሰጡት መግለጫ፤ “ምርጫ ቦርድ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የማይጨነቅ ተቋም ነው” ብለዋል። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ ፓርቲዎቹ ያቀረቡት ባለ 18 ነጥብ ቅሬታዎች በማስረጃ ያልተደገፉ ናቸው በማለት ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓቸዋል። “ተፈጠሩ የተባሉት ችግሮች መቼና የት ቦታ ላይ እንደተከሰቱ በማስረጃ ተደግፎ አልቀረበም” ያለው ቦርዱ፤ “ቅሬታዎቹ ወቅትን ያልጠበቁ፣ አግባብነትና የህግ ድጋፍም የሌላቸው ናቸው›› ሲል ቅሬታቸውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡

በ2002 ምርጫ የተወሰኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውና ታዛቢዎቻቸው እንደታሰሩና እንደተባረሩባቸው በመግለፅ ቅሬታ አቅርበው እንደነበር ያስታወሰው ምርጫ ቦርድ፤ በዚያው ጊዜ ጉዳዩን አጣርቶና የተባለው ችግር አለመፈጠሩን ተገንዝቦ ምላሽ እንደሰጠበት ገልጿል። 
“በከፍተኛ ማጭበርበር 99.6 ውጤት የተገኘበት ዓይነት ምርጫ እንዲደገም አንፈቅድም” ያሉት ፓርቲዎቹ፤ “በዘመነ ኢህአዴግ ከተደረጉ ምርጫዎች ሁሉ በዘረፋውና በኢ-ዲሞክራሲያዊነቱ የ2002 ምርጫን ተወዳዳሪ የለውም” ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል፡፡ የተሰራ ጥናት ጠቅሰው አስረድተዋል፡፡
ጥያቄያቸውን ከአንድ ወር በፊት ማቅረባቸውንና የቦርዱ ሃላፊዎች ባለፈው ዕሮብ በፅ/ቤታቸው ሲጠሯቸው ለውይይት መስሏቸው እንደነበር የጠቆሙት ፓርቲዎቹ፤ ሃላፊዎቹ ግን ‹‹ያነሳችኋቸው ጥያቄዎች አግባብ አይደሉም፤ ይህንኑ ለህዝብ ይፋ አድርጉት›› የሚል ምላሽ በቃል ሰጥተውናል፤ ይህም ፓርቲዎችንና የኢትዮጵያ ህዝብን መናቅ ነው ሲሉ ነቅፈዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ባለፈው ሳምንት ባለ 18 ነጥቦች ቅሬታ ለጠ/ሚ ጽ/ቤት ማስገባታቸውን ገልጸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የኢህአዴግ መንግስት 18ቱ ነጥቦች ትክክል መሆናቸውን ከምርጫ ቦርድ የበለጠ ያውቁታል፤ እንደ ምርጫ ቦርድ ሽምጥጥ አድርገው ይክዱታል ብለን አናስብም ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ ገዥውን ፓርቲም ሆነ እኛን እኩል ማስተዳደር ሲገባው ይሄን ሃላፊነቱን አልተወጣም ሲሉም ትችታቸውን ሰንዝረዋል - ተቃዋሚዎቹ፡፡
በሚያዝያ ወር በሚካሄደው የአዲስ አበባና የአካባቢ ምርጫ ላይ ይሳተፉ እንደሆነ የተጠየቁት ፓርቲዎቹ፤ ገና ውሳኔ ላይ አለመድረሳቸውን ገልፀዋል፡፡ “ህዝብንና ተቃዋሚን በናቀ ስሜት ወደ ምርጫ እንገባለን ብሎ ማሰብ ያስቸግራል፤ ግን ተስፋ አንቆርጥም፤ የመብት ጉዳይ ስለሆነ ከህዝብ ጋር ሆነን ህገ-መንግስቱ በሰጠን መብት እንጠቀማለን” ብለዋል፡፡
ፓርቲዎቹ መድረክን ይቀላቀሉ እንደሆነ ተጠይቀውም፤ “መድረክ ለዚህች አገር የሚጠቅም ከሆነ አባል እንሆናለን፤ እንቀላቀላለን” በማለት መልሰዋል፡፡

Read 3759 times

Latest from