Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 08 December 2012 14:24

“ዩሴ ዝግጅት” ሰኞ፤“ግጥምን በጃዝ” ረቡዕ - በራስ ሆቴል

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ወርሃዊ የሥነ ፅሁፍ ዝግጅቱን የፊታችን ሰኞ ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ በራስ ሆቴል እንደሚያቀርብ ዩሴ የማስታወቂያ ድርጅት አስታወቀ፡፡ በዝግጅቱ ላይ አርቲስት አዳነች ወልደገብርኤል፣ ገጣሚ ባየልኝ አያሌው፣ ገጣሚት ትዕግስት ማሞ፣ ተዋናይና ወግ ፀሐፊ ፍቃዱ ከበደ፣ ድምፃዊት ጠረፍ ጥላሁን (ኪያ)፣ ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ እና አርቲስት ሄኖክ በሪሁን የስነፅሁፍ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
በተመሳሳይ ዜና፣ ግጥም እና ሙዚቃ ተዋዝተው የሚቀርቡበት “ግጥምን በጃዝ” 17ኛ ምሽት ዝግጅቱን የፊታችን ረቡዕ ምሽት በራስ ሆቴል ትልቁ አዳራሽ ያቀርባል፡፡

በረቡዕ ዝግጅት መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ “ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቅኔና ፍልስፍና” በሚል ርእስ ንግግር እንደሚያደርጉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡ እውቋ አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ እና ታዋቂው አርቲስት ግሩም ዘነበ ቅንጭብ ተውኔት በሚያቀርቡበት በዚህ ዝግጅት፤ አበባው መላኩ፣ ደምሰው መርሻ፣ ቴዎድሮስ ፀጋዬ፣ ሐረገወይን አሰፋ እና አብርሃም አስቻለው ግጥሞቻቸውን ያነባሉ ተብሏል፡፡

Read 4060 times

Latest from