Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 08 December 2012 14:15

50 ሴንት በስራ ፈጠራው እየተደነቀ ነው

Written by 
Rate this item
(2 votes)

50 ሴንት “ስትሪት ኪንግ ዘ ኢሞርታል” የተባለ አዲስ አልበሙን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ኤምቲቪ ኒውስ ገለፀ፡፡ አልበሙ በ2003 ዓ.ም የወጣውን የመጀመርያ አልበሙን “ጌት ሪች ኦር ዳይ ትራይንግ” 10ኛ ዓመት ለማክበር ያዘጋጀው ነው፡፡ በዚህ አዲስ አልበም ስራው ላይ ራፐር ኤሚነም አስተያየት በመስጠት ከፍተኛ እገዛ እንዳደረገለት፣ ለኤምቲቪ ኒውስ የተናገረው 50 ሴንት፤ በሚሰጠኝ ሃሳብ ሁሌ የምደሰትበት ሰው እሱ ነው ብሏል፡፡ 50 ሴንት ከራፐር ኤሚኔም ጋር በመጣመር ልዩ አልበም ለመስራት የረጅም ጊዜ ፍላጎት እንዳለው መግለፁንም ዘገባው አመልክቷል፡፡ በሌላ በኩል በሙሉ ስሙ ከርቲስ ጃክሰን ተብሎ የሚጠራው ራፐር ፊፍቲ ሴንት እድሜያቸው ከ40 በታች ከሆኑ ዝነኛ ስራ ፈጣሪዎች አንዱ መሆኑን ሂፕሆፕ ኒውስ አስታውቋል፡፡

ቀድሞ ቦክሰኛ ለመሆን ጥረት አድርጎ የነበረው ፊፍቲ ሴንት፤ የቦክስ ግጥሚያዎችን በልዩ ሁኔታ በማዘጋጀት ከፍተኛ ገንዘብ እየሰራ መሆኑን አድንቆ የፃፈው ደግሞ ዩሮ ኒውስ ነው፡፡ በሎስአንጀለስ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን ከባባድ የቦክስ ግጥሚያዎች በማዘጋጀት እና እውቅናውን ተጠቅሞ በርካታ ተመልካች እንዲታደም በመቀስቀስ 50 ሴንት ምርጥ ፕሮሞተር ሆኗል እየተባለ ነው፡፡በምርጥ የራፕ ሙዚቀኛነት፤ በስራ ፈጣሪነት፤ በፊልም ተዋናይነት፤ ጂ ዩኒት በተባለ የሙዚቃ አሳታሚው፤ በተመሳሳይ ስም በሚጠራው የልብስ ኩባንያው እና በተለያዩ የፕሮሞሽን እና የንግድ እንቅስቃሴዎቹ ስኬታማ ለመሆን የበቃው 50 ሴንት፤ 250 ሚሊዮን ዶላር ሃብት ለማካበት መቻሉን ሴሌብሪቲኔትዎርዝ ድረገፅ ይገልፃል፡፡
በሚቀጥለው ዓመት በአሜሪካው የቴሌቭዥን ጣቢያ “ስታርዝ” ላይ 50 ሴንት የሚያዘጋጀውና ስለአንድ የምሽት ክለብ ባለቤት የሚተርክ ተከታታይ ፊልም መቅረብ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ በቅርቡ “ኪውቪሲ” በሚባል የገበያ ቻናል በስምንት ደቂቃ እስከ 177ሺ ዶላር የራሱን ኩባንያ የሄድፎን ምርቶች በመሸጥ የተደነቀው ፊፍቲ ሴንት፤ በቴሌቭዥን ስራዎቹ እንደሚሳካለት እየተነገረ ነው፡፡

Read 6311 times

Latest from