Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 December 2012 14:13

ዶ/ር ድሬ በከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ ሙዚቀኞችን ይመራል

Written by 
Rate this item
(2 votes)

የዓለማችንን 25 ከፍተኛ ተከፋይ ሙዚቀኞች ደረጃን የቀድሞው ራፕር፤ የሙዚቃ አሳታሚ ባለቤት እና ነጋዴ ዶ/ር ድሬ በአንደኛ ደረጃ እንደሚመራው ፎርብስ መፅሄት አስታወቀ፡፡ ዶ/ር ድሬ በ2012 በከፍተኛ ክፍያ አንደኛ ሊሆን የበቃው 100 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት ሲሆን “ቢትስባይድሬ” በተባለ የጆሮ ማዳመጫ ምርቱ ገበያው ስለተሟሟቀለት ነው ተብሏል፡፡ ዘንድሮ “ዘ ዎል ላይቭ” የተባለ የሙዚቃ ኮንሰርት በመላው ዓለም ተዘዋውሮ በማቅረብ የተሳካለት ፒንክ ፍሎይድ፤

በ88 ሚሊዮን ዶላር ሁለተኛ ደረጃን ሲወስድ በዓመቱ ከ100 በላይ የሙዚቃ ዝግጅቶች የሰራው እንግሊዛዊው ኤልተን ጆን በ80 ሚሊዮን ዶላር፣ ሶስተኛ ደረጃ ተሰጥቶታል፡፡ ዩ2 የሙዚቃ ቡድን በ60፤ ጆን ቦን ጆቪ በ60፤ ብሪትኒ ስፒርስ በ58፤ ፖል ማካርቲኒ እና ቴይለር ስዊፍት በእኩል 57፤ እንዲሁም ጀስቲን ቢበር እና ቶቢ ኬዝ በእኩል 55 ሚሊዮን ዶላር ገቢያቸው እሰከ 10 ያለውን ደረጃ አግኝተዋል፡፡ ሪሃና በ53፤ ሌዲ ጋጋ በ52፤ ኬቲ ፔሪ በ45 እንዲሁም አዴሌ በ35 ሚሊዮን ዶላር የዓመቱ ገቢያቸው ከአስሮቹ ደረጃ ውጭ መሆናቸው አስገርሟል፡፡

Read 3325 times