Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 01 December 2012 14:29

“መልሕቅ” እና “ለመድረስ” ፊልሞች ይመረቃሉ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በብስራት ገመቹ ተፅፎ የተዘጋጀውና በራሷ ፕሮዲዩስ የተደረገው “መልሕቅ” ፊልም ሰኞ እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር የሚመረቀው ፊልም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለሕዝብ መቅረብ ጀምሯል፡፡
በፊልሙ በ “ሰው ለሰው” የቴሌቪዥን ድራማ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ትተውን የነበረችው ብስራት በ “መልሕቅ” እየተወነች ሲሆን በዚሁ ድራማ የሚተውነው ዝናህብዙ ፀጋዬ፣ እንዲሁም ዳንኤል ገበየሁ፣ ኤርምያስ ሀብታሙ፣ አለባቸው መኮንን፣ መንገሻ ተሰማ፣ መክሊት ገብረየስ፣ እንድርያስ አስናቀው እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ የ110 ደቂቃ ፊልሙን ሠርቶ ለማጠናቀቅ 11 ወራት ፈጅቷል፡፡

ፊልሙን ያቀረበው ሉላ ፊልም ፕሮዳክሽን ነው፡፡ በሌላም በኩል ደቦል መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን በአንዱ አለም አባተ (ያፀደ ልጅ) እና ሰለሞን መኮንን ተጽፎ ሰሎሞን መኮንን ያዘጋጀው “ለመድረስ” የተሰኘ ፊልም እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በፊልሙ አድማሱ ከበደ፣ ስናፍቅሽ ተስፋዬ፣ ካሌብ ዋለልኝ፣ ካሳዬ ገበየሁ፣ ተስፉ ብርሃኔ፣ አልማዝ ኃይሌ፣ አስቴር አለማየሁ፣ ትእግስት ግርማ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል፡፡

Read 4545 times

Latest from