Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 December 2012 14:27

የቦሌመድሃኔአለም ቤተክርስትያን በቱሪስት መስሕብነቱ አስቦበታል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በቅርብ ዓመታት ካስገነባቻቸው ካቴድራሎች (ደብሮች) አንዱ የሆነው የቦሌ ደብረሳሌም መድሃኒዓለም፣ መጥምቁ ዮሐንስና አቡነ አረጋዊ ካቴድራል የቱሪስት መስሕብነቱን ያሰበበት መሆኑን አስታወቀ፡፡ ካቴድራሉ በአዲስ አበባ ካሉ አብያተክርስትያናት ትልቁ ነው፡፡ ውጭ ሀገራት በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች ዘወትር እየተጎበኘ ያለው ቤተክርስትያን የቱሪስት መስህብነቱን በማጠናከር ዘመናዊ ፏፏቴ (ፋውንቴን) አሰርቷል፡፡ የቀብር አገልግሎት የማይሰጠው ቤተክርስትያን ፏፏቴውን በመጪው ማክሰኞ ብፁአን ሊቃነጳጳስ እና ሌሎች እንግዶች በሚገኙበት እንደሚያስመርቅ የቤተክርስትያኑ ጽሕፈት ቤት ከላከልን መግለጫ መረዳት ተችሏል፡፡ በቦሌ መድሃኔዓለም ከሚጎበኙ ስፍራዎች መካከል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ በመሠራቱ አወዛጋቢ የነበረው ሐውልት ይገኝበታል፡፡

በሌላም በኩል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ማህበረ ቅዱሳን “የንባብ ባህልን በማሳደግ በመረጃና በእውቀት የበለፀገ ትውልድ እንፍጠር” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የውይይት መድረክ ዛሬ እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡ ዝግጅቱ በአንባቢነታቸው የሚታወቁ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሌሎች አባቶች፣ ደራስያን እና ሌሎች ግለሰቦች በሚገኙበት አምስት ኪሎ በሚገኘው የማህበሩ ሕንፃ ከሰዓት በኋላ ይካሄዳል፡፡ 
ይህ በዚህ እንዳለ ብሔራዊ ቤተመፃሕፍት እና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ የንባብ ባህልን ለማዳበር ያዘጋጀው ተመሳሳይ ውይይት “የንባብ ባህልና ወጣቱ” በሚል ርእስ ሐሙስ ከሰዓት በኋላ እንደሚቀርብ ኤጀንሲው አስታወቀ፡፡

Read 4893 times